Thursday, October 30, 2014

የወያኔ የስለላ እጁ ረጅም ቢሆንም የፍትህና የእኩልነት የአንድነት ታጋዮች ከትግሉ ቅንጣት አናፈገፍግም

ዳዊትደመላሽ(ኖርዌይ)
ላለፉት 23 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀምጠውን ዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታ በጀመርነውና በተያያዝነው አዲስ አመት ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶቻችንን በማቻቻል በጋራ ልንታገል የሚገባና ለህዝባችንና ለሃገራችን ስር ነቀል ለውጥ ልናመጣ የሚያስችለንን ምዕራፍ የምንጀምርበት አመት መሆን አለበት። ባሳለፍናቸው በርካታ የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በእርስ መፈራረጅና መወነጃጀል የወያኔን እድሜ ከማራዘም ውጪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያተረፈው አንዳችም ነገር የለም። የአንድነት የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተቻቻለ የሃሳብ መግባባት ተቻችሎ እና ተግባብቶ ሁለገብ የትግል ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅብናል።

ኢትዮጵያ ሃገራችን ሀሳብን በነፃነት ያለፍርሀት መግለፅ የማይቻልባት፤ የዜጎች የኑሮ ደረጃ ከዕለት ዕለት እየተባባስ የሚሄድባት፤ ዘመናዊ የመረጃ መገናኛዎች ሆን ተብለው የታገዱባት፤ የህዝቦቿን ጥንታዊና ብርቅዬ የሆነውን መከባበርና አንድነት በዘር ጥላቻና በሀይማኖት ለመከፋፈል አገዛዙ የሚጥርበት፤ ዜጎች አለአግባብ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት፤ ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰደዱባት፤ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያልተካሄድባት፤ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉባት፤ ለሕግ ተገዢ ያልሆነ መንግሥት ያለባት፤ ዜጎች የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር በነፃነት ሠርተው መኖር የማይችሉባት፤ ነፃ ሚዲያ የሌለባት፤ ዜጎች ለሀብት ንብረታቸው ዋስትና የማያገኙባት፤ ህዝባዊ መንግሥት የሚናፍቅ ህዝብ ያለባት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ተቋማት የገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ መጠቀሚያ የሆኑባት፤ ቤቶች በቁመታቸው ማደጋቸው እንደዕድገት የሚቆጠርባት ሀገር ሆናለች።

የኢትዮጵያን አንድነት ከጥያቄ ውስጥ ያስገባውና የመበታተን አደጋ ላይ የጣለው፣ የዘር መርዝ በመርጨት ሌት ተቀን በመስራት ላይ የነበረው መለስ ዜናዊና በሱ ስር የሚመራውና ጥሎት የሞተው የኢሕአዴግ ጎሰኛ ስብስብ ነው። ይኸው ጎሰኛ ስብስብ ለመበታተን የሚረዳ አስተሳሰቡን ሕጋዊ ሽፋን በመስጠት በአንቀጽ 39 ደንግጎታል። የዛ ጥንስስ ነው አሁን በየቦታው ለሚካሄደው የጠባብ ጎሰኛ እንቅስቃሴ ማንሰራራት ምክንያት የሆነው። ለሕዝቡ የተሻለ ኑሮ፣ ለዲሞክራሲና ሰላም፣ ለአገር አንድነት እናስባለን የሚሉ ሁሉ ይህን አጥፊ ሂደት ሊቋቋሙት ይገባል። በተለይም የየማህበረሰቡ የተማረው ክፍል ከጎጥ ዋሻ ወጥቶ በሚያውቀው ከባቢና ቋንቋ የሚስተጋቡትን የጥፋት ቅስቀሳዎች መቃወም ይኖርበታል። አሁን ሁሉም የሚፈተንበት ወቅት ነው። ማን ለሰላም፣ ማን ለሰው ልጆች በጎ ነገር፣ ማን ለሰብአዊ መብት፣ ማን ለአንድነትና አገራዊ ነጻነት እንደቆመ የሚታይበት ጊዜ ነው። እነዚህን ፈተናዎች ለማለፍ የቤት ስራዎችን መስራት የግድ ይላል። ለዚህም ነው እኛ የአንድነት ሃይሎች ከትንሽነት ብዙነት፣ ከጠባብነትም ሰፊነት ይሻላል የምንለው።


በእድገት ተራምደዋል በሚባሉት ሃገራት የምንኖር ለዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ስርዓት ግንባታ የጋዜጠኝነት፣ የመፃፍና የሚዲያ ነፃነት ምን ያህል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያረግ እንዲሁም በዲሞክራሲ ላይ በተመሰረቱ የሃገራት ውስጥ የመፃፍ፣ የመናገርና የነፃ ሚዲያዎች መኖር ምን ያህል ታላቅና ጉልህ ሚና እንደሚጫወት እያየንና እያስተዋልን ነው። ነገር ግን እንደሃገራችን ኢትዮጵያ አይነት የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ስርዓት ይቅርና እጅግ መሰረታዊ የሚባሉት ሰብዓዊ መብቶች በእንጭጩ የተቀበሩባት ሃገር መናገርና መፃፍ እንደወንጀል እየተቆጠረ ነው። ከብዙ በጥቂቱ ሰሞኑን በዞን 9 ጦማርያን ላይ፣ ቀደም ብሎም በጋዜጠኞቹ በእስክንድር ነጋና በርዕዮት ዓለሙ ላይ የደረሰውን ማየቱ ብቻ በቂ ይሆናል። ሀገርንና ህዝብን አስተዳድራለሁ ብሎ ከዜጎች ይሁንታ ውጪ ስልጣኑን የተቆጣጠረው እንደ ወያኔ ያለ አምባገነናዊ ስብስብ 'እንዴት የአስተዳደር ችግሮቼ በጋዜጠኛና በብሎገሮች ፅሁፍ ይተቻል፣ እንደፈለገሁ አስራለሁ/ እገድላለሁ' ብሎ ለሃገርና ለህዝብ ኑሮ መሻሻል በጎ ሃሳብና መፍትሄ የጠቆሙና ያወያዩ፥ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባትና ለሃገር ማደግ በጨዋነት እይታቸውንና እውቀታቸውን ለማካፈል ብዕራቸውን ያነሱ ጦማርያንና ጋዜጠኞች ሁሉ እየሰበሰቡ የሌለባቸውን የ'ሽብርተኛነት' ስም እየሰጡ በየእስር ቤቱ ማጎር፣ ፍትህን ማጓደልና የፍርድ ሂደቱንም አሰልቺ እና ተስፋ አስቆራጭ እስኪሆን ድረስ በማራዘም ሌሎችንም በማስፈራራት መወያያና የመማማርያ መድረኮችን ማፈን ብሎም እንዲጠፉ ማድረግ ለጊዜው ከሆነ ነው እንጂ በዘላቂነት የትም አንደማያደርስ ወያኔ ከወዲሁ ሊያውቀው ይገባል።
ተደጋግሞ ከተለያዩ የህግ ባለሙያዎች እንደተገለጸው አለምዓቀፍ ህግን በተጻረረ መልኩ ኦኬሎ አኳይንና አንዳርጋቸው ጽጌን ከመንገድ ያውም ከሰው አገር በጉቦ አስጠልፈውና አፍነው በመውሰድ ያው የተለመደ ግፋቸውን እየፈጸሙ ይገኛሉ፣ ይህ የሚያሳየው ወያኔ እጁ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ ነው። እነዚህ ሁለት የፍትህና የእኩልነት ታጋዮች ኦኬሎ አኳይንና አንዳርጋቸው ጽጌ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንደ ሌሎች የተቃዋሚ መሪዎች የበኩላቸውን ለማበርከት ደፋ ቀና ሲሉ በወያኔ መረብ ውስጥ ቢገቡም ለፍትህና ለእኩልነት እንዲሁም ለሃገር ነጻነት የከፈሉት አስተዋጽኦ መቼም የማይረሳ ታላቅ መስዋእትነት ያበረከቱ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።
ስለዚህ ኢትዮጵያውያን የአንድነት ሃይሎች በመተባበር፣ በመጣመርና በመዋሃድ ሃይልን፣ እውቀትን፣ ህብረትን እንዲሁም ገንዘብን በማቀናጀት የወያኔን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብር ለአንዴና ለመጨረሻ አሸቀንጥሮ ወርውሮ ሃገርንና ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርዓቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬንና ህዝቤን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የበኩሌን ሃሳብ ለማቅረብ እወዳለሁ::
አንድነት ኃይል ነው !!

ድል ለሰፊው ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

Posted By.Dawit Demelash

1  .http://www.ethiomunich.com/component/k2/item/68-%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%8B%AB%E1%8A%94-%E1%8B%A8%E1%88%B5%E1%88%88%E1%88%8B-%E1%8A%A5%E1%8C%81-%E1%88%A8%E1%8C%85%E1%88%9D-%E1%89%A2%E1%88%86%E1%8A%95%E1%88%9D-%E1%8B%A8%E1%8D%8D%E1%89%B5%E1%88%85%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%8A%A9%E1%88%8D%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%89%B3%E1%8C%8B%E1%8B%AE%E1%89%BD-%E1%8A%A8%E1%89%B5%E1%8C%8D%E1%88%89-%E1%89%85%E1%8A%95%E1%8C%A3%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%8A%93%E1%8D%88%E1%8C%88%E1%8D%8D%E1%8C%8D%E1%88%9D











2.  http://quatero.net/pdf/dawit-demelash.pdf

3.http://www.ethiox.com/blog/?p=1022

Tuesday, October 28, 2014

ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !

ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ። 

ሃብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ወደ መጸዳጃ ቤት እንድዳይሄድ በመከልከሉ በፌስትታል ይጠቀም እንደነበረ፣ ለሶስት ሳምንታትም ቁጥር ስምንት በምትባል የጨለማ ቤት ዉስጥ ለብቻው እንዲቀመጥ መደረጉንም አረጋግጠናል።
“ወደ ፖለቲካው የማትመለስ ከሆነ ትወጣለህ። አለበለዚያ እዚሁ ነው የምትሞተው” በማለት አማራጭ ቢያቀርቡለትም፣ ሃብታሙ መሞትን እመርጣለሁ የሚል መልስ የሰጣቸው ሲሆን፣ እየደረሰበት ባለው ስቃይ በጣም እየታመመ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። “እስኪ ትግሉን እናስቀጥላለን የሚሉ ሰዎች ያድኑህ ? “ ሲሉ አሳሪዎቹ በስቃዩ የሚደሰቱ ሲሆን፣ ከባለቤቱ በስትቀር ጠበቃዉም ሁሉ ሳይቀር እንዳያየው ተደርጓል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ ፣ በታፈነና አየር በማያስወጣ ክፍል ዉስጥ እንዲታሰር በመደረጉ በተደጋጋሚ ለተቅማጥና ተያያዥ በሽታ መጋለጡን፣ እንዲሁም የመተንፈስ ችግር እንዳለበት ለማወቅ ችለናል። “የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው ? አንድነት ዉስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት እነማን ናቸው ? “ በሚል ጥያቄ የቀረበለት ዳንኤል ሺበሺ፣ ክብሩን በሚነካ መልኩ እንደሚሰደብም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ሃብታሙ አያሌው ፣ በእርሱ ላይ እይደረሰ ያለው ግፍ በማንም ዜጋ ላይ መድረስ እንደሌለበት በመግልጽ “የግፈኛው አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት አለበት” ሲልም ለህዝቡ የትግል ጥሪ አስተላልፏል።
የአንድነት ራዲዮ የዘገበዉን እንደሚከተለው ያድምጡ !



http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/16060#more-16060





Saturday, October 25, 2014

በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም

ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን: ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር 09/08/2014 ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳ አማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ አማራውን ህዝብ የለም ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል  ክደዋል።   የፕሮፌሰር መስፍን ክህደትእስላም ኦሮሞዎች ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ነበር የገደሉትለማለት ከሆነ፣ ሀቁና መረጃዎቹ ከፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ጋር እንደማይጠጣሙ በተከታታይ መረጃዎችን እየመዘዝን የአርባ ጉጉን እልቂት ለማቅረብ እንሞክራለን። ወይም ጉልበታቸው ለፈረጠመ ወንጀለኞች መውጫ ቀዳዳ በመፈብረክ የተለመደው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያምየወንድ በር እንስጥፍልስፍናም ከሆነ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያልተፈጸመና ያልተደረገ አያደርገውም ልንላቸው እንገደዳለን።

ከአባሎቻችንና ከደጋፊዎቻችን ጋር ለመወያየት የግብዣ ወረቀት ከላክን በሗላ፣ ከስብሰባው በፊት በአማራው ህዝብ ላይ በአርባ ጉጉ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፕሮፌሰሩ መካዳቸው ብዙዎችን እንዳስቆጣቸው መልክት ሲደርሰን፣ እኛም አንድን ሰው ከሀዲ ከማለታችን በፊት መረጃዎችን አቅርቦ ፍርዱን ለአንባቢ ለመተው፣ በጊዜው የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ለኢህአዴግ፣ ለውጭ መንግስታት ዲፕሎማቶችና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስ ያወጣውን የአቋም መግለጫ ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል።

የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አማካኝነት በአማራው ላይ የሚያካሂደውን የእልቂትና የሽብር ዘመቻ እያፋፋመው የአማራ ህዝብም ከፋሽስቶች ዘመን በባሰ ሁኔታ እያለቀ መሆኑን ባወጣው የአቋም መግለጫ አብራርቷል።
የመአህድ ፕሬዜዳንት ለሽግግር መንግስቱ ምክር ቤትና ለልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባቀረቡት መግለጫ ላይ እንዳብራሩት በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍና በደልሰብአዊ አእምሮ ሊሸከመው የማይችል ነውበተለይ ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓም ጀምሮ ጭፍጨፋው በከፋ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎ የጭፍጨፋው ሰለባ የሆነው አማራ ሬሳው በገደል ውስጥ እንዲጣልና በቤት ውስጥ እንዲቃጠል እየተደረገ ነውይላል::

ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓም ጀምሮ በአማራው ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የተካሄደው በአርሲ ክፍለ ሀገር በአንቦሳ ከተማና በአካባቢው ነው። ኢህአዴግ በዚህ ስፍራ የሚኖሩ ተወላጆችን ሰብስቦበነዚህ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙበማለት ትእዛዝ ሰጠ።

በማግስቱ ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓም አቡሌ የተባለውን መንደር በኦህዴድ (የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራቲክ ድርጅት) የታጠቀ ወታደር ተከቦ ተኩስ ከተከፈተ በሗላ መንደሩ በላውንቸር መደብደብና ማቃጠል ሲጀመር ህዝቡ ህይወቱን ለማዳን ህዝቡ በየአቅጧጫው መሸሽ ጀመረ። ከሚሸሹት መካከል 30 ህጻናት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ እንደተጠጉ ከቤተክርስቲያኑና ከካህናቱ ጋር ተቃጥለዋል። አከታትሎም 150 የአማራ ነዋሪ ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓል።

የአውራጃው የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ዲማ ጎርሜሳ ለወራሪው ሰራዊትአማራን መጨረስ ዛሬ ነውየሚል መፈክር በማሰማት አበሳ የሚባለው የአማሮች መንደር እንዲከበብ አስደርገው ህዝብ ከቤቱ ሳይወጣ መንደሩ እንዲቃጠል ተደርገ። በመንደሩ ከነህይወታቸው በቤት ውስጥ እንዳሉ የሞቱት ቁጥር የማይታወቅ ሲሆን የቤቶቹ ጠቅላላ ብዛት 150 ነው። ከቃጠሎው የተረፉት 50 ሰዎች ተይዘው በጥይት ተረሽነዋል።

በሌላም አሼ በተባለ መንደር በአማራ ተወላጆች በአካባቢው የሚፈጸመውን ሰቆቃ እየተመለከቱ የመንግስት ሃይል ያድነናል ብለው ሲጠብቁ 25 ሰዎች የኢህአዴግ ሰራዊት ፈጅቷቸዋል።

በጉና ወረዳ አዲስ አለም በተባለ ቦታም 150 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ ከማቃጠላቸውም ሌላ ሁለት የአገር ሽማግሌዎች እጅ እግራቸውን አስረው አቃጥለዋቸዋል።

ዋቄንትራ ከተባለው መንደር 100 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ አቃጥለዋቸዋል።

መሶ የተባለውን መንደር በጦር እንዲከበቡና 100 ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓ ከቃጠሎው የዳኑት 80 ሰዎች እጃቸው ታስሮ በኦህዴድ (የኢህአዴግ አንዱ ክፍል) ተረሽነው ሬሳቸው ቆሬ ከሚባል ገደል ውስጥ እንዲጣል ተደርጓል። አንድ ሰው በተአምር ከዚህ መአት ተርፏል።

እንደሴ ባዩ የሚባለው መንደር ነዋሪ የሆኑ አማሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ ሰራዊት እነዲከበቡ ከተደረገ በሗላ ከመንደሩ ነዋሪዎች መካከል 80 የሚሆኑት እጅ እግራቸውን ታስረው ተወስደዋል። ወደ ገደል እንደተወረወሩም ይወራል።

ስድስት ቤተ-ክርሲቲያናት በዚህ አካባቢ ተቃጥለዋል። ይህ ሁሉ የተፈጸመው ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓም በአንድ ቀን ነው ሲል የመአህድ መግለጫ አብራርቷል።

እንግዲህ ፕሮፌሰር መስፍን በሸገር ራዲዮ ጣቢያ የካዱት ይሄንን በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው።

(24/10/2014)

http://www.debteraw.com/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%88%AD%E1%89%A3-%E1%8C%89%E1%8C%89-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%8A%AB%E1%89%A3%E1%89%A2%E1%8B%8D-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB%E1%8B%8D-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A5/

Wednesday, October 22, 2014

በአፋር የፌደራል ፖሊሶች አንድ ሰው ገድለው ሌላ ሰው አቆሰሉ

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአሚባራ በአፋርና በኢሳ መካከል የተነሳውን ግጭት  ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው ገድለው ሌላ የአፋር ተወላጅን ደግሞ አቁስለዋል። በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከትናንት ጀምሮ ገዋኔና ቡድመዳ ወረዳዎች በጎርፍ መጥለቅለቃቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በቂ ድጋፍ እያደረገ አይደለም በማለት ወቅሰዋል።  በአዋሽ ቀበና ላይ የሚካሄደው የስኳር ፕሮጀክት እንዲሁም  የመተሃራ የበሰቃ ውሃ ለአዋሽ ውሃ መሙላት መንስኤ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በዚህም የተነሳ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው ብለዋል።

http://ethsat.com/amharic/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8D%8B%E1%88%AD-%E1%8B%A8%E1%8D%8C%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%88%8D-%E1%8D%96%E1%88%8A%E1%88%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5-%E1%88%B0%E1%8B%8D-%E1%8C%88%E1%8B%B5%E1%88%88/

Monday, October 20, 2014

በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ጫናው በርትቷል “ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› -የብአዴን አመራሮች

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሃፊ የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በእሱና በሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ ዛቻ እንደሚፈጸምባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ ‹‹ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም›› ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ጠበቃው ገልጾአል፡፡

በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል ተብሏል፡፡ ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ‹‹ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ›› በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ገልጾአል፡፡

ጠበቃው በ28/1 እናርጅ እናውጋ ለቀጠሮ ባቀናበት ወቅትም የእናርጅ እናውጋ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ስራው በረኩ እና የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ እና ሌሎችም ከፖሊስና ከጸጥታ የመጡ አመራሮች ‹‹ምን ልታደርግ ነው? ልትቀሰቅስ ነው?›› በሚል እንዳዋከቡትና አቶ ስራው በረኩ ‹‹አንጠልጥዬ ነው እስር ቤት የማስገባህ፡፡ ማንም ሊያድንህ አይችልም›› ብለው እንደዛቱበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነህ በፍትህ ስርዓቱ መገልገል አትችልም፣ ጥብቅናህን መልቀቅ አለብህ፣ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ ትጽፋለህ፣ የፍትህ መምሪያ ሃላፊውን (ጸጋየ መንግስቴ) ችግር እንደሚፈጽምብህ በነገረ ኢትዮጵያና በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ጽፈህበታል፣ እንዲህ እያደረክ መኖር አትችልም፣ አንተን ገሎ መጣል ቀላል ነው፣ ለነፍስህ የምታዝን ከሆነ አገር ልቅቅ›› ብለው እንደዛቱበት ገልጾአል፡፡

ሌሎች ጠበቃ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሄዱ ‹‹እሱ ማለት ሰማያዊ ነው፡፡ ሰማያዊ ደግሞ የአክራሪ ሙስሊም ፓርቲ ነው፡፡ እናንተ ለምን ከእሱ ጋር ትሄዳላችሁ?›› ብለው እንደሚያስፈራሯቸውና ደንበኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሰሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ጠበቃው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

ጠበቃውን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባል ሆነው ማደራጀት መብታቸው መሆኑን ሲገልጹ የብአዴን አመራሮች ‹‹እናንተ እኛን ስለማትረዱን ነው፡፡ እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም፡፡ ወንድ ከሆናችሁ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› በሚል ለህግ የማይገዙና ለሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት እንደሌላቸው አሳይተውናል ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲና አመራር የሆኑ ነጋዴዎች ከፓርቲው እንዲለቁ ለማድረግ የንግድ ድርጅታቸውን እንደሚዘጉ እያስፈራሩ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህልም አቶ ይኸይስ ቀጸላ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ‹‹ሻይ ቤት ከፍተው እያደራጁ ነው፡፡ የንግድ ድርጅቱን እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበታል፡፡ በመሆኑም ካላረፉ ሻይ ቤቱን እንዘጋዋለን›› እያሉ እንደሚያስፈራሩ ታውቋል፡፡

የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የገዥው ፓርቲ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እርምጃዎች እየተጠናከሩ ቢሆንም እርምጃው እነሱ ተጽዕኖ በመፍጠራቸው የመጣ በመሆኑ ይበልጡን እንደሚያበረታታቸውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


አቶ መኳንንት አበበን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችን የእጅ ስልካቸው ላይ በመወደል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

Sunday, October 19, 2014

በአፋር ክልል በተለያዩ ሞያዎች ሲሰሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ ታዘዘ

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአማራ ተወላጆች ላለፉት 20 አመታት በአፋር ክልል በተለያዩ ሞያዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል። አሁን ከአፋር ክልል ሾልከው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ እነዚህ የአማራ ተወላጆች በአስቸኳይ ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ በአማራ ክልላዊ መንግስት ታዘዋል። በጉዳዩ ላይ የአማራ ክልልና የአፋር ክልልን መንግስታት የተስማሙ ሲሆን «ይህ ውሳኔ በህወሓት ሆን ተብሎ በአፋር ክልል ለኢህአዴግ ታማኝ የሆኑ የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ተወላጆችን ለመተካት የተደረገ ነው» ሲሉም ምንጮቻች ያስረዳሉ።
(አፋር ክልል)

ወያኔ በተለይ በሶማሌ ክልልና በአፋር ክልል የሚሰሩ የአማራ ተወላጆችን «ከተቃዋሚዎች ጋር ይተባበራሉ» የሚል ስጋት እንዳለውና ከመጪው ምርጫ በፊት ከአፋር ክልል የአማራ ተወላጆችን አስወግደው በወያኔ ቤተሰብ እንዲተኩ አስቧል። በአፋር ክልል ብዙ በተለያዩ ሞያዎች በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ምሁራን ስራ የማያገኙበት ሁኔታ እያለ ክልላችን የህወሓት መጫወቻ መሆኑን የአፋር ወጣቶችን ሞራል የሚነካ ተግባር ነው ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ። በንግድም ቢሆን የአፋር ክልልን የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ተወላጆች ብቻ እንዲቆጣጠሩ እየተደረገ ሲሆን በአሁን ወቅት ይሄ ሁሉ ሴራ የሚያሴሩት በተንዳሆ ሱኳር ፋብረካ እያሰሩ የሚገኙት የቀድሞው የህወሓት ታጋይ አቶ ሚካኤል ናቸው።


አቶ ሚካኤል በየእሁድ በአፋር ክልል ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሎግያ ከተማ ስብሰባ የሚያደርጉ መሆኑንና የስብሰባ ቦታቸውም ናዝሬት ሆቴል ቁጥር 1 የሚባለው ሲሆን የናዝሬት ሆቴል ባለቤት በንግድ የአፋር ክልልን የወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ብቻ እንቆጣጠሩ የሚለፉ የትግራይ ሀብታም ናቸው። አሁን ለአቶ ሚካኤል ይህ የመንግስት ሰራተኞችን የማባረር ሴራ ከተሳካላቸው የአፋር ክልል መሉ በሙሉ በወያነ ቤተሰቦች ይያዛል ማለት ነው፣ የአፋር ህዝብም ቢሆን ከከተማ እያስወጡ ወደ ገጠር እየመለሷቸው ነው። ይህ ደግሞ ለወደፊት ከጀቡቲ ታኮሪ ወደ መቀሌ ለሚሰራው የባቡር ሀዲድ ዝርጋታና ወደ ፊትም የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ዞን የማድረግ አላማ ስላላቸው የአፋር ክልልን በቀላሉ ለመቆጣጠር ነው።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35538

የወያኔ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኖርዌይ ኦስሎ በኢትዬጵያኖች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው Okt 1...



Dawit Demelash

and other web site

http://www.debteraw.com/

ethiolion.com https://www.youtube.com/watch?v=eM5X5O-lIbY&feature=youtu.be

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35472

Thursday, October 16, 2014

በኢትዮጵያ ተከታታይ ፍንዳታዎች ይደርሳሉ የሚለው ስጋት አይሏል * ደህነቶች እና የኢምባሲ አታሼዎች(ተወካዬች) በስብሰባ ተወጥረዋል

በኤምባሲዎች የደህንነት አታቼዎች(ተወካዬች) እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት መካከል ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው
በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ ምእራባውያን ዲፕሎማቶች ዘንድ የሚደርሱ እናፈነዳለን መረጃዎች ከፍተኛ የሆነ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙ እና ለደህንነት አታቼዎች ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች እንደሚናገሩት መሃል አገርን እና ምስራቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪት ክልሎች ይደረጋሉ የተባሉ ፍንዳታዎች ከአልሸባብ የመጡ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው ቢባልም በአልሸባብ ውስጥ በተደረገ የመረጃ ማጣራት አልሸባብ ይህንን መረጃ እንዳልበተነ በአዲስ አበባ የአሜሪካን የደህንነት አታቼ ለማረጋገጥ ያደረጉት ሙከራ በከፊል ባይሳካም የሁኔታውን አሳሳቢነት አስመልክቶ በምእራባውያን የኤምባሲ ዲፕሎማቶች የደህንነት አታቼዎች እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል።


ከወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ይደርሳሉ የሚባሉ ፍንዳታዎች ምዕራባውያን ላይ ያነታጠሩ በመሆኑ የሰጉት የሃያላኑ ዲፕሎማቶች ሁኔታው ከመከሰቱ በፊት ለመቆጣጠር ሲሉ አስፈላጊውን የዲፕሎማቲክ ሩጫ እያደረጉ መሆኑ ሲታወቅ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ከሆነ ምርጫ እየደረሰ ስለሆነ ተቃዋሚዎችንና ያልያዛቸውን ጠንካራ ሰዎች ለማፈስ ወያኔ የሚጠቀምበት ስልት ነው። ህዝቡን እያስፈራራ የውጭ አገር መንግስታትንም እንዲሁ አሸባሪ ለመዋጋት እያለ እራሱ የቀበራቸውን ፈንጂዎች ያስጮህብናል። የፈለገውንም ይገድላል። ስለዚህ ህዝቡ ነቅቶ መጠበቅ የግድ ይለዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35459

Wednesday, October 15, 2014

የዞን9 ጦማርያኑ እና የወዳጅ ጋዜጠኞች የዛሬው ፍርድ ቤት ውሎ

ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ በነሶልያና ሽመልስ የሽብር ወንጀል የክስ መዝገብ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡት ስድስቱ የዞን9 ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ቀጠሮ ችሎቱ ከ20 ቀን በኃላ እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቀቀ።


ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ አይቶ ምላሽ እንዲሰጥበት የተቀጠረ ሲሆን በዚያም መሰረት ለተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥቷል ።

ፍርድ ቤቱም የጠበቆችን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በክሱ ሂደት ላይ ብይን ለመስጠት ለተጨማሪ ሃያ ቀን ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የሴት ተከሳሾችን በጓደኛና በቤተሰብ አለመጎብኘት ተከትሎ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዲያስረዳ የማረሚያ ቤቱ እንዲገኝ ጥሪ ቢደረግም አለመገኘቱን እና በፓሊስ በኩል ምላሽ ይዞ መቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ ሃላፌ እንዲገኙ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር።

 ነገር ግን ሴት ተከሳሾች በተለይ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ የመጎብኘት መብት መሰረታዊ መብታቸው በመሆኑ 20 መቆየት እንደማይገባ በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ የሴት ተከሳሾችን የጉብኝት መብት አስመልክቶ ለማየት ለጥቅምት 11 አጭር ቀጠሮ ሠጥቷል ።

በዛሬው እለት ነጭ በመልበስ የተገኙት ተከሳሾች በመልካም ፈገግታ እና በጠንካራ መንፈስ የነበሩ ሲሆን በፈገግታ ወዳጅ እና ጓደኞቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል።

በመጨረሻም የሚቀጥለው ቀጠሮ ለጥቅምት 25 የተወሰነ ሲሆን የሴት ታሳሪዎችን የጉብኝት መብት ጥያቄ አስመልክቶ በጥቅምት 11 ችሎቱ ቀድሞ ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።

የዞን9 ጦማርያን የክሱን ፈጠራነት፣ የጦማርያኑን እና ጋዜጠኞቹ በመአከላዊ ምርመራ ያለፉበትን የመብት ጥሰት እያስታወስን የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን የፓለቲካ መጠቀሚያነት ክስ ወዳጅ ጋዜጠኞችን እና ተከሳሽ ጦማርያንን በነፃ በማሰናበት ፍርድ ቤቱ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ተስፋ እናደርጋለን።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35427

Tuesday, October 14, 2014

ወገኖቻችን ዋጋ ለመከፈል ሲዘጋጁ እኛ ከጎን መቆም አለብን (የትግል ጥሪ)

አንድነት አዲስ ወጣት አመራር ይዞ ብቅ ብሏል። አቶ በላይ ፍቃዱ። ከዚህ በፊት በተከበሩ ዶር ነጋሶ ጊዳዳና እና የተከበሩ ኢንጂነር ግዛቸው አመራር ወቅት የተጀመሩ መልካም ስራዎችን በማጠናከር፣ በአዲስ አሰራና በአዲስ የትግል ግለት አዲስ ጉዞ ተጀምሯል።

የአንድነት ፓርቲ በአገሪቷ አራቱም ማእዘናት መረቡን የዘረጋ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ከተደረገ ኢሕአዴግን ማሸነፍ የሚችል፣ ብዙ አመራር አባላቱ እየታሰሩበትና ከፍተኛ ጫና እየደረሰበትም፣ የአምባገነኖችን ዱላ ተቋቁሞ የሕዝብን ጥያቄ ለማስከበር የሚተጋ ድርጅት ነው። ሕወሃት/ኢሕአዴግ፣ የአንድነት ፓርቲ፣ በፓርቲዎች ምክር ቤት እንደኮለኮላቸው፣ መድበለ ፓርቲ አለ ብሎ ለማስመሰል ለዲፕሎማሲ ፍጆታ እንደሚጠቀምባቸው፣ ፓርቲ ነን ባዮች ጀሌዎቹ፣ እንዲሆን ነው የሚፈልገው። ነገር ግን አንድነቶች፣ ትልቅ ዋጋ እየከፈሉም፣ ለአገዛዙ ራስ ምታት በመሆን፣ ትግሉን እየመሩት ነው።
ከሐምሌ 2005 እስከ ሰኔ 2006 ባሉት ጊዜያት፣ አንድነት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነትና የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርህ በሃያ ከተሞች ተንቀሳቅሷል። በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በደሴና በባህር ዳር ሁለት ጊዜ ፣ በአርባ ምንጭ፣ በጂንካ፣ በፍቼ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በጎንደር፣ በጊዶሌ፣ በወላይታ ሶዶ አንድ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፎችን ጠርቶ ሕዝቡን ያንቀሳቀሰ ሲሆን፣ በአዋሳ፣ በቁጫ፣ በመቀሌና በባሌ/ሮቢ ለቅስቀሳና ለመጓጓዣ ከፍተኛ ወጭ ከተደረገ በኋላ፣ በአገዛዙ አፈና ሰልፎቹ ቢስተጓጎሉም ፣ ቢያንስ በነዚህ ከተሞች ሕዝቡ የነጻነትን ድምጽ በቅስቀሳ ወቅት ለመስማት በቋቷል።
ኢሕአዴግ ከምእራቡ አለም የሚያገኘው እርዳታ፣ በግብር የሚሰበስበው በእጁ ነው። የአገሪቷ አበይት የመገናኛ ተቋማትን ይቆጣጠራል። ኢቲቪ፣ ፋና ፣ አዲስ ዘመን ….በመለስተኛነት ሪፖርተር የመሳሰሉ ሜዲያዎቹ ጠዋትና ማታ የአገዛዙን ፕሮፖጋንዳ ነው የሚረጩት።
አንድነት የሚተማመነው በሕዝቡ ድጋፍ ነው። የአንድነት ብቸኛ የኃይል ምንጭ እኛ ነን። እኛ ከመሪዎች ለዉጥ መጠበቅ የለብንም። እኛ መሪዎችን እየደገፍን የለውጡ አካል ነው መሆን ያለብን።
አንድነት የምርጫው ሜዳ እንዲሰፋና የፖለቲክ ምህዳሩ እንዲከፈት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን፣ ሰልፎችን ማካሄድ አለበት። በአገሪቷ ሁሉ ያሉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ለማደራጀት፣ አክቲቪስቶችን አስተባባሪዎችን፣ አደራጆችን በየክልሉ በብዛት ማሰማራት የግድ ነው። እንደ አቶ አንዱዋለም አራጌ፣ ሃብታሙ አያሌው አሁን ያሉትም አመራሮች፣ ነገ ሊታሰሩ እንደሚችሉ እያወቁ ትግሉን ለመምራት የቆረጡ፣ የፓርቲው አመራሮች፣ በራሳቸው ይሄን ትልቅ ሃላፊነት ሊወጡ አይችሉም። እንግዲህ እነርሱ ለመታሰር፣ ለመደብደብ፣ ለመገደል ሲዘጋጁ እኛ ትንሿን የድርሻችንን መወጣት ሊያቅተን አይገባም። አንድነትን ባለን አቅምና ጉልበት ሁሉ ለመደገፍ መዘጋጀት ይኖርብናል።
በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ለመከታተል የሚከተለውን የፌስ ቡክ ገጽ ላይክ ያደርጉ
https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj
በዉጭ አገር ያላችሁ፣ ፓርቲዉን በጽሁፍ፣ ጠቃሚና ፕሮፌሽናል አስተያየቶች በመስጠት ሆነ በማንኛዉም ገንዝበ ነክ ባልሆኑ ጉዳዮች ለመርዳት ፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል ወይንም የአንድነት ድጋፍ ድርጅት አካል ሆናችሁ መስራት ለምትፈልጉ በሚከተለው አድራሻ ኢሜል ይላኩልን።
millionsforethiopia@gmail.com
በገንዘብ ለመርዳት http://www.andinet.org/ በመሄድ በስተቀኝ በኩል ከላይ «Donate» የሚለውን ይጫኑ !
ነጻነትን ስለተመኘናት አናገኛትም። ነጻነት ርካሽ አይደለችም። ዋጋ ታስከፍላለች። እያንዳንዳችን የነጻነትን ጉዞ፣ የነጻነትን ትግል እንቀላቀል። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን:: እስካሁን ብዙ የአገዛዙን ግፍ አውርተናል። እስከአሁን ነጻነታችንን ሌሎች እንዲሰጡን ጠብቀናል። እስካሁን ሌሎችን ተችተናል። አሁን ጣታችንን ወደኛ የምናዞርበትና፣ እያንዳንዳችን የምንነሳበት ጊዜ ነው። አሁን ካልተነሳን ፣ አሁን ትግሉን ካልተቀላቀልን መቼ ? እኛ ካልተነሳን ማን ?  
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15984