Saturday, October 11, 2014

48 + 1 ደቂቃ ቢያልፍ ምን እንደሚከተል ግንዛቤ ነበር !! “ወያኔዎቹ የተሰራላቸው ውለታ አልገባቸውም”

time is up

ከስያሜው ጀምሮ እያነጋገረ ያለው የኢህአዴግ የአሜሪካ ጽ/ቤት የጥበቃ ሰራተኛ፣ በኢህአዴግ አባባል “ዲፕሎማት” አገር ለቆ እንዲወጣ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አንድ ደቂቃ ቢዘገይ ምን ሊከተል እንደሚችል አስቀድሞ ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበርተጠቆመ። በስምምነቱ መሰረት ወዲ ወይኒ መባረሩ ከህወሃት ደጋፊዎችና አመራሮች ቅሬታ ማስነሳቱን አስመልክቶ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት “ወያኔዎቹ የተሰራላቸው ውለታ አልገባቸውም ማለት ነው” ሲሉ መደመጣቸውን የጎልጉል ታማኝ ምንጭ ተናገሩ።
ለተቃውሞ ወደ ኢህአዴግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባመሩ ኢትዮጵያኖች ላይ ጥይት የተኮሰው የቀድሞው “ዲፕሎማት” ተመልሶ አሜሪካን መርገጥ እንዳይችል ተደርጎ የተባረረው በሁለቱም ወገኖች በተደረገ የውስጥ ስምምነት ነው። ለጉዳዩ እጅግ ቅርብ የሆኑእንደገለጹት በአሜሪካው የምስጢር አገልግሎት (Secret Service) እና የዋሽንግተን ከተማ ፖሊስ ወዲ ወይኒን ለማሰር ወስነው ነበር። ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት እነ አቶ ግርማ ብሩ “ጓዳቸውን” ፈቅደው ለማሰናበት ቅድሚያውን በመውሰዳቸው ተጠርጣሪው ወንጀለኛ ሳይያዝ ቀርቷል። ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት (State Department) የተሰጠው መግለጫም ቃል በቃልም ባይሆን ይህንኑ ያረጋገጠ ሆኗል።
የምስጢር አገልግሎቱም ሆነ የከተማው ፖሊስ ከ“ፖለቲካው ግንኙነት” ጋር በተያያዘ ስለሚፈጠረው የፖለቲካ ውዝግብ ቁብ እንደሌለው ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አቶ ግርማ ብሩ “በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ተነጋግረናል” ሲሉ ለአገዛዙ ተላላኪ ድረገጽ ባለቤት እንዳረጋገጡት የስቴት ዲፓርትመንት ሰዎች የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ያልተፈረደበትን ወንጀለኛ፣ ወዲ ወይኒን፣ ካገር የሚወጣበትን መንገድ እንዳመቻቹ ዲፕሎማቱ አልሸሸጉም።
“አሜሪካ በቂ ጥበቃ አላደረገችልንም” በማለት ተቃውሞ የሚሰነዝሩት አፍቃሪ ህወሃቶች የሚሰነዝሩትን ተቃውሞ አስመልክቶ “የተደረገላቸውን ውለታ ካለመረዳት ነውነው፤ አፋቸውን ቢዘጉ (ዝም ቢሉ) የተሻለ ነው” ሲሉ የተደመጡት ከፍተኛ ሃላፊ፣ ይህንን ሲናገሩ ክፉኛ ተበሳጭተውእንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የአሜሪካ መንግስት ተወንጃዩ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሚዲያ ቁርስና ምሳ ሲሆን፣ ከዚሁ በጋር ከኢህአዴግ ጋር የሚነሳው ውዝግብና በምስራቅ አፍሪቃ በኩል ስለሚከወነው የፖለቲካ ጨዋታ ሲባል ጉዳዩ አሁን በተከናወነበት መልኩ እንዲጠናቀቅ መወሰኗን ከጉዳዩ ብዙ ርቀት የሌላቸው ክፍሎች አመልክተዋል። አቶ ግርማም ቢሆኑ “በዲፕሎማሲያዊ” ሲሉ ቋንቋውን ቢያስውቡትም ስምምነቱ ስለመኖሩ ከማሳበቅ ወደኋላ አላሉም።
በገደብ፣ በስምምነት የተቆረጠው 48 ሰዓት ቢተላለፍ ምን ሊከተል እንደሚችል ግንዛቤ በመኖሩ እነ አቶ ግርማ ወዲ ወይኒን አፋፍሰው ኢህአዴግ አለገደብ ወደሚገዛት አገር ልከውታል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንድ ደቂቃ ቢዘገይ “ወዲ ወይኒ ወህኒ ወርደው ወዲ ወህኒ የሚል ስም ይሰጣቸው ነበር” ሲሉ ከዲሲ አካባቢ አንዳንዶች ተሳልቀዋል፡፡
ከኢህአዴግ ወገን አሁንም ዋሽንግተን ዲሲ ለተከራዩት ለጽህፈት ቤታቸው አሜሪካ ልዩ እንክብካቤ እንዲደረግ እየወተወቱ ነው። አሜሪካ ለዚህ ምንም ዓይነት የተለየ ጥበቃ የማታደርግ መሆኑ በተለያዩ መግለጫዎች የተነገረ ቢሆንም በህወሃት/የኢህአዴግ በኩል ጥያቄው እንዲነሳ ያደረገው መነሻ በድጋሚ ተመሳሳይ ውርደት እንዳይከሰትና ወደ ሌሎች አገራትም እንዳይዛመት ስጋት በመኖሩ ነው።
በተመሳሳይ ዜና ከአሜሪካ በሰዓታት ገደብ እንዲሰናበት የተደረገውና ተበደልን ባሉ ወገኖች ላይ ጥይት ሲተኩስ የነበረው ይኸው የትግራይ ተወላጅ ለሞራሉ በሚል ወደ ሌላ አገር ኤምባሲ ተዛውሮ እንዲሰራ አዲስ ምደባ እንደሚሰጠው የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ምንጮች አመልክተዋል። ከህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን ወጣ የተባለው ይኸው የአዲሱ ምደባ ጉዳይ ለወዲ ወይኒ “ተጋዳላይነት”፤ ለሌሎች ደግሞ “አለኝታነትን ለማሳየት” በሚል ታስቦ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
http://www.goolgule.com/what-would-have-happened-to-wedi-weyni-after-48-hours/

No comments:

Post a Comment