Wednesday, December 30, 2015

ወያኔ ሀገራችንን ቆርሶ ለሱዳን ሊሰጥ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተነሥ!!!

የወያኔ ባለሥልጣናት በሰነድ ደረጃ ከዓመታት በፊት ለሱዳን ስለሰጡት በተግባር መሬት ላይ ደግሞ ሰሞኑን ሊያስረክቡት ሽር ጉድ እያሉበት ስላለው ጉዳይ በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች ሲጠየቁ “ይሄንን ፈጥረው የሚያወሩት ግርግር ፈጥረው የራሳቸውን ጥቅም ማስጠበቅ የፈለጉ ቡድኖች ናቸው፤ ከእኛ ጋ ጭራሽም በአጀንዳ ደረጃም እንኳን የለም!” ሲሉ መሰንበታቸው ይታወቃል፡፡

እንዲህ ብለው እየተናገሩ ግን የሱዳን መንግሥትና የወያኔ ባለሥልጣናት ይሄንን ሰሞን ርክክቡን መሬት ላይ ተፈጻሚ ለማድረግ ሽርጉዱን አጧጡፈውታል፡፡ ለሱዳን ሊሰጡት ባሰቡት መሬት ላይ ያለውን አርሶአደርም እያፈናቀሉና እየጠረጉ መሬቱን ነጻ ሲያደርጉ ከራርመዋል፡፡ የተፈናቀሉ ገበሬዎች በጎንደር ከተማና በሌሎችን ስፍራዎች ሜዳላይ ፈሰው ይሄንን ሰሞን ጨምሮ በተለያየ ጊዜ ተመልክተናል፡፡ ለምን? ተብሎ ሲጠየቅ የወያኔ ባለሥልጣናት ከሰባት ዓመታት በፊት ይሰጡት የነበረው መልስ በሬቱን የሱዳን ባለሀብቶች እንዲያለሙት በሊዝ ተሰጥቷቸዋል” የሚል ነበር፡፡

በአሁኑ ሰዓት የወያኔ ሠራዊት ለሱዳን የሚሰጠውን መሬት ርክክብ ኮሽታ በማይሰማበት ሁኔታ ለማስፈጸም በቦታው ሰፍሮ እየተጠባበቀና እንቅፋት ይፈጥራሉ ተብለው የተጠረጠሩትን ያካባቢውን አርሶ አደሮች ለመፍጀት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ይንን የመሬት ርክክብ በመቃወም ሊነሣ የሚችለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቀነስ ከተቻለም ለማስቀረት ሲባልም ቅማንትንና አማራን የማተላለቅ የማባላት ሴራ ተጠንስሶ ተፈጻሚ በማድረግ የሕዝቡን ትኩረት ከድንበር መሬቱ ላይ አስነሥተው የእርስ በእርስ ፍጅት ላይ እንዲጠመድ በማድረግ መሬቱን ለማስረከብ የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር ቻልን ብለው አስበዋል፡፡

ከአቶ መለስ በኋላ ሁለተኛው የሱዳን ጠ/ሚ በኢትዮጵያ አቶ ኃይለማርያም ለወያኔ “የሕዝብ” ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር “ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠና የሚሰጥም መሬት የለም! በመሬት ጉዳይ ላይም ከሱዳን መንግሥት ጋር ተደራድረን አናውቅም!” በማለት ወያኔ እንዲናገሩ የሰጣቸውን መልእክት ተላላኪው ሰውየ አድርሰውናል፡፡ አቶ ኃይለማርያም ለሱዳን ተቆርሶ ስለሚሰጠው መሬት የተናገሩት ንግግር ስለዚህ ጉዳይ አቶ መለስ አንድ ወቅት ላይ ከተናገሩት ንግግር ምንም የጨመሩት የቀነሱትም አንዲት ነገር ሳይኖር ነበር ያችኑ ሸምድደው መጥተው የተፉት፡፡

“በደናቁርት ቤት ሀን ማወቅ ሊቅነት ነው” እንዲሉ ወያኔም ብልጥ ሆነና ሊያቄለን በማሰብ ይሄንን ቃል ተናገረ፡፡ “ታዲያ እየተፈናቀለ ያለው ገበሬስ በምን ሒሳብና ለምንስ ነው ከቀየው እየተፈናቀለ እንዲለቅ እየተደረገ ያለው?” ተብለው ሲጠየቁ ደናቁርቱ፣ አሕዮቹ፣ የእንግዴ ልጆቹ፣ ጉግማንጉጎቹ፣ በክህደት ተፀንሰው በክህደት የተወለዱቱ፣ ክህደት አሳድጎ ክህደት ያስረጃቸው ጭንጋፎቹ ወያኔዎች ቅንጣት ታክል እንኳን ሐፍረት ሳይሰማቸው በዚያ እርጉም አንደበታቸው “የሱዳን ባለሀብቶች እንዲያለሙት በሊዝ ተሰጥቷቸዋል” ሲሉ የነበረውን የበፊት ሐሰተኛ ምክንያት ትተው ምን ብለው ይመልሳሉ “አይ እሱማ መሬቱ የሱዳን ነው! ሱዳኖቹ መሬታቸውን ለአማራ ገበሬዎች እያረሱ እንዲጠቀሙበት ለረጅም ዓመታት ፈቅደውላቸው ስለነበረ ነው የአማራ ገበሬዎች እዚያ መሬት ላይ ሊገኙ የቻሉት እንጅ መሬቱ የሱዳን ነው!” ብለው በአደባባይ በብዙኃን መገናኛ እንቅጩን ነግረውን አረፉት፡፡

ይንን የሚሉበት ምክንያት እንግዲህ ብልጥ ተሁኖ ተሙቶ “እነዚህ እርጉሞች መሬት እኮ ቆርሰው ሰጡ! ኧረ! እነዚህ ምን ጉዶች ናቸው! እንዴት ዓይነት ከሀዲዎች ቢሆኑ ነው? እንዴት ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ እሠራለሁ እታገላለሁ የኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ ከሚል አካል በገዛ ሀገሩና ሕዝቡ ላይ በየትኛውም የዓለማችን መንግሥታት ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በገዛ ሀገሩና ሕዝቡ ዘንድ ክህደት ፈጽሞ ለባዕድ ሀገር መሬትን ያህል ያውም 1600 ኪሎ ሜትር (ግዝፈ ጉዝ) እርዝመት በ20 እና 40 አንዳንድ ቦታ ላይም በ60 ኪ.ሜ. (ግ.ጉ.) ስፋት የሚያህል አገር የሚያክል መሬትን ይሰጣል? የፈለገውን ያህል ከሀዲና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባይ እራስ ወዳድ ቢሆኑ እንዴት በዚህን ያህል የክህደት አረንቋ ውስጥ እራሳቸውን ያሰጥማሉ?” ተብሎ ጉድ እንዳይባልና ሕዝቡም መሬቱን ላለማስነጠቅ እንዳይቆም፣ አይሆንም! አይደረግም! ብሎ እንዳይቆጣ በለመዱት ክህደት እብለት በተሞላ ሐሰተኛ ነውረኛ ስድ አንደበታቸው “ተቆርሶ ለሱዳን የሰጠነውም የምንሰጠውም መሬት የለም! መሬትን በተመለከተ ከሱዳን ጋር ያደረግነው ምንም ዓይነት ድርድር የለም!፣ አይ እሱማ መሬቱ የሱዳን ነው! ሱዳኖቹ መሬታቸውን ለአማራ ገበሬዎች እያረሱ እንዲጠቀሙበት ለረጅም ዓመታት ፈቅደውላቸው ስለነበረ ነው የአማራ ገበሬዎች እዚያ መሬት ላይ ሊገኙ የቻሉት እንጅ መሬቱ የሱዳን ነው!” ብለው ካዱ፡፡

እንዲህ ብለው ክደው ሲያበቁ ግን ከላይ በገለጽኩላቹህ መልኩ አርሶ አደሩን እያፈናቀሉም እየገደሉም ነጻ ሲያደርጉ ቆይተው መሬታችንን ለሱዳን ለማስረከብ ተጠናቀው ተቀምጠዋል፡፡ መቸ ያፍሩና! ሰው ቢሆኑም አልነበር ሊያፍሩ ሊሸማቀቁ ስቅጥጥ ሊላቸው ይችል የነበረው? መቸ ሰዎች ናቸውና? ሕዝቡ እንደራሱ ዓይን አፍንጫ እጅ እግር ይዘው ሲያያቸው ሰው እየመሰላቸው በሚያደርጉት ዕብለት ክህደት ጥፋት “እንዴት! ግን?” እያለ በመደነቅ እጅግ ይገረማል ግራ ይጋባል፡፡ እነሱ የሰው አካል ይዘው ይታዩ እንጅ እንደ ሰው ይናገሩ እንጅ አሁን የወያኔ ግሪሳ ምናቸው ነው ሰው የሚያሰኛቸው በሞቴ?

ጥሩ እንግዲያውስ ያገሬ ገበሬ ቀየ ሱዳኖች እያረሰ እንዲጠቀምበት ለረጅም ዓመታት ፈቅደውለት ሲያርሰው የኖረ መሬት ከሆነ ሕዝቡ “የለም! አይደለም ደማችንን ስናፈስለት አጥንታችን ስንከሰክስለት የኖርነው የኢትዮጵያ መሬት ነው! እንኳንና ይሄንን ያህል መሬት አንዲት ሳንቲ ሜትር (ቅንጠ ጉዝ) እንኳን አንሠጥም!” እያለ ነውና እየቀጠቀጣቹህ እየጨፈጨፋቹህ ከገዛ መሬቱ አጽድታቹህ አፈናቀላቹህ ለሱዳን ከማስረከባቹህ በፊት የምትሉት መሬት የሱዳን ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በብዙኃን መገናኛ ማስረጃ አቅርቡልና!!!

እውነቱ ግን አይደለምና ይሄ የአሀሬ ገበሬ ከአያት ቅድመ አያት ቅምቅማቱ እየወረሰው እየተረከበው የመጣው፣ እየተጨፈጨፈ እንዲነሣ እንዲለቀው እየተደረገበት ያለው መሬት ይቅርና ስናር ድረስ ያለው መሬት የኢትዮጵያ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ሞልተዋል፡፡ ቱርኮች በበርካታ መድፎች ታግዘው ድንበር አልፈው ስናርን በያዙ ጊዜ ዐፄ ቴዎድሮስ ለንግሥት ቪክቶሪያ በጻፏቸው ደብዳቤዎች ልቀቁ ቢሉ እምቢ በማለታቸው ሊገጥሙ እንደሆነ በጻፏቸው ደብዳቤዎች በተደጋጋሚ መግለጻቸውን ማንም የሚያውቀው ታሪክ ዘግቦ የያዘው ሀቅ ነው፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ገና በሽፍትነታቸው እያሉ ጀምረው ወራሪዎቹ ድንበር እየተሸገሩ ስናር በገቡ ቁጥር ሔደው በመውጋት ድል እያደረጉ እያባረሩ ጠብቀው ያቆዩት መሬት ነበር፡፡

እነሱ ግን ሳይታክቱ ሳይሰለቹ በየጊዜው ድንበር እየዘለሉ እየመጡ ዛሬ ሊወስዱት አቆብቁበው ካሉበት ድረስ ደረሱ፡፡ እጅግ የሚገርመኝ ነገር የሱዳን መሬት ከኛን ሀገር ከእጥፍ በላይ 2,505,813 ስኩዌር ኪሎ ሜትር (አራት ማዕዘናዊ ግዝፈ ጉዝ) ሆኖ እያለ የሕዝባቸው ቁጥር ደግሞ ከእኛ ሕዝብ ከግማሽ በታች አርባ ሚሊዮን (አእላፋት) ሆነው እያለ የዚህን ያህል መስበድበዳቸው ነው፡፡ “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” ነው የሚባለው?

ወያኔዎች እውነት በሀገርና በሕዝብ ላይ ጸያፍና አስነዋሪ ክህደት የፈጸማቹህ ካሆናቹህና በድርጊታቹህ የማታፍሩ ከሆነ መሬቱ የኢትዮጵያ ለመሆኑ ጠንቅቀው የሚያውቁ ማስረጃና መረጃ የያዙ ተቆርቋሪ ወገኖች አሉና ከእነሱ ጋፍ ፊት ለፊት በመገናኘት የያዙት ማስረጃና መረጃ የተሳሳተ የውሸት መሆኑን እንድንረዳ እንድናውቅ አድርጋቹህ አሳፍራቹህ ስትሰዷቸው እንያቹሃ? እስኪ ወንድ ከሆናቹህ ከሀዲ፣ ነውረኛ፣ ወራዳ ወንበዴ ካልሆናቹህ ይሄንን አድርጉና በሉ እንያቹሃ?

መንጋ ጭንጋፍ የእንግዴ ልጅ ሁላ!!! እኔ አይደለም እናንተን ሆኘ መኖርን ላስብ ልመኝ ይቅርና እናንተን በማየቴ በእናንተ ዘመን በመኖሬ ራሱ እንዴት ዓይነት ልገልጸው ከባድ ሐፍረት መሸማቀቅ ውርደት እንደሚሰማኝ እንዴት አድርጌ በነገርኳቹህ!!! እንዴትስ አድርጌ ብነግራቹህ እናንተን ይገባቹሀል እንዴ?

የነውረኛነታቹህ ነውረኛነት ጭራሽ “ሀገሬ ተቆርሳ ባዕድ አይወስዳትም ይሄንን በዓይኔ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ!” እያለ ከሱዳን ወታደር ጋር ጉርቦ ለጉርቦ የሚተናነቀውን ጀግና ቆፍጣና ያገሬን ገበሬ “እንደ አማራ ክልል ሽፍቶች ጠብ ጫሪነት ቢሆን ኖሮ የሱዳንና የኢትዮጵያ ግንኙነት ይሻክር ነበር። ሱዳኖች ታግሰውናል!” ብላቹህ ጀግኖቹን ቆራጦችን የቁርጥ ቀን ብርቅና ድንቅ ዕንቁ ወገኖቻችንን “ሽፍታ” ብላቹህ አዋርዳቹህ ስትጠሩ እንዲያው ጥቂት እንኳን አታፍሩም? ለነገሩ ሀገር ማለት ድንበር ማለት ምን ማለት እንደሆነ የት ታውቁትና ምድረ ምናምንቴ የእርግማን ልጅ ቆሻሻ ሁላ!

እንግዲህ ልዩነታችን ይሄንን ያህል ነው፡፡ ምንም እንኳን እናንተ ያልተማራቹህ የደናቁርት ጥርቅም ብትሆኑም ቅሉ “ያልተማረ” እያላቹህ የምትገልጹት ያገሬ ገበሬ ለአንድያ ለፍሱ ሳይሳሳ ለውድ ሀገሩ ለክቡር ድንበሩ መሥዋዕትነትን ሲከፍል “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” የሚለውን የአሕያ አስተሳሰብ የሁለንተናቹህ መርሕ ያደረጋቹህት እናንተ የጉግ ማንጉግ ጥርቅሞች ግን “የእኛ (ወያኔ) ህልውና አደጋ ላይ ከሚወድቅ የምናባቱ ሀገር፣ የምናባቱ ሉዓላዊነት፣ የምናባቱ ብሔራዊ ጥቅም” እያላቹህ ከሀገር መሬት እስከ ሕፃናት ሴቶች ልጆቻችን ድረስ ለባዕዳንና ለጠላት አሳልፋቹህ በመስጠጥ የጠላት መጫዎቻ መቀለጃ በማድረግ ይህች ሀገርና ይሄ ሕዝብ አይቶት ሰምቶት ለማያውቀው ውርደት ዳረጋቹህት፡፡ የኢትዮጵያዊነት የሰውነት ልዩነታችንን ርቀት ልብ አላቹህት? ይሄንን ያህል ናቹህ ምድረ ወራዳ! እንዴት ብላቹህ ልብ ትሉታላቹህ? መቸ የሰውነት መገለጫ አላቹህና!
እንዲያው በሞቴ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹህ፡- ስንት ዓመት ለመኖር ነው በዚህ ደረጃ ዘቅጣቹህ አድፋቹህ ጎድፋቹህ እረክሳቹህ የገዛ ሀገራቹህን የገዛ ሕዝባቹህን ጥቅም አሳልፋቹህ በመስጠት እራሳቹህን ለማኖር የምትጥሩት? ሰው እንዴት በዛ ቢባል ከ80 ዓመት በላይ ለማይኖረው ዕድሜ የዚህን ያህል እራሱን ያዋርዳል? ሽህ ዓመት ትኖራላቹህ እንዴ? እንዲህ እያደረጋቹህ “ኢትዮጵያዊያን ነን” ስትሉ እንዲያው ትንሽም አታፍሩም? ሰው ብትሆኑ ነበራ! በነውረኛ ድርጊታቹህ በክህደታቹህ ልታፍሩ ልትሸማቀቁ ትችሉ የነበረው፤ እናንተ ምናቹህ ሰው ነው?

ወገናዊ ጥሪ ሀገሩን እያገለገለ ለሚመስለው የወያኔ ሠራዊት፡-

በገዛ ሀገራቹህና ሕዝባቹህ ላይ ታሪካዊ ክህደት በመፈጸም ወደ ሱዳን ተቆርሶ የሚሰጠውንና ተቆርሶ የሚከለለውን መሬት ለማስረከብ የሀገራቸውን መሬት አሳልፈው ላለማሰጠት ሲዋደቁ ለቆዩትና ለመዋደቅ የተዘጋጁትን ያገሬን ገበሬዎች “በአፈጻጸሙ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ችግር ፈጣሪዎች!” ብሎ በመፈረጅ በእነሱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ አቆብቁበህ ያለህ የወያኔ ሠራዊት ሆይ! እባካቹህ የዚህ ምስኪን ሕስብና ምስኪን ሀገር አካ መሆናቹህን አስቡ! መገመት እንደሚቻለው ማሰብ ማሰላሰል የምትችሉ ይመስለኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ነን ብላቹህ እንደምታስቡም ያታወቃል፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ እንደወታደርነታቹህ የሀገርን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ከባዱ ግዴታና ኃላፊነት ያለው በእናንተ ላይ ሆኖ ሳለ ወያኔ እናንተን በመጠቀም የሀገርን ሰፊ መሬት አሳልፎ ለባዕድ ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት እንደምን በጸጋ ተቀብላቹህ አስፈጻሚዎች ትሆናላቹህን???
እስኪ ልብ ብላቹህ አጢኑት? እውን ሀገር ለማስገኝጠል ሉዓላዊነቷን ለማስደፈር ነው ወይ ወደ ውትድርናው የተቀላቀላቹህ? “የገዛ ሀገሩን ያፈራረሰው ብቸኛውና የመጀመሪያው ከሀዲ ሠራዊት” ሠራዊት ተብለህ በታሪክ ተወቃሽ ተከሳሽ መሆን ትፈልጋለህ ወይ? ካልሆነ በወገንህ ላይ ልታርከፈክፈው ያዘጋጀኸውን አረር ከውስጥህ ለሀገር ሳይሆን የሀገርን ጥቅም አሳልፎ በመስጠት ለወያኔ ህልውና ታማኝ ሆነው ታጥቀው እየሠሩ ባሉት ከሀዲዎችና በሱዳን ወራሪ ወታደሮች ላይ አርከፍክፈውና ታሪክ ሠርተህ የዜግነት ግዴታህን ተወጣ! ስምህን ከባንዶች ሳይሆን ከጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ተርታ አሰልፍ! አስቀምጥ! ይሄንን ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ የተጣለብህን ታሪካዊ አደራ ተወጣ! አደራ በሀገሩ ፍቅር ተለክፎ ሰክሮ ነሁልሎ የሀገሩ መሬት በከሀዲያን በባንዶች ለባዕድ መሰጠቱ ኅሊናውን ባሳተው ባንገበገበው ባሳበደው ወገንህ ላይ እንዳታዘንበው በሰማይና በምድር ንጉሥ በመድኃኔዓለም ክርስቶስ፣ በአጋእዝተ ሥላሴ ስም የተገዘትክ የታሠርክ ያድርግህ!

ወገናዊ ጥሪ የወያኔን የውንብድናና የጠላትነት ተግባር እንዲህ እየተመለከትክ ለወያኔ በመሥራት ወያኔን እያገለገልክ ሀገርን የምታገለግል ለሚመስልህ የመንግሥት ሠራተኛ የወያኔ ደጋፊ ሁሉ፡-

እንደምታዩት ወያኔ ከራሱ በላይ ቅንጣትም እንኳን ብትሆን ለሀገርና ለሕዝብ የማያስብ የነውረኞች የጉዶች ቡድን ነው፡፡ ይሄ የጉዶች ቡድን ከራሱ በላይ ለማንም እንደማያስብ ለራሱ ጥቅም ከሆነ ግን አላደርገውም የሚለው ምንም ነገር የሌለው ከሀዲ እርጉም የባንዳ ጥርቅም መሆኑን እያያቹህ “እኛን እስከጠቀመ ድረስ፣ በልተን እስካደርን ድረስ” በሚል ይሄንን ግዙፍ ጸያፍ የክህደት ተግባሩን በቸልታ ብትመለከቱ አስተሳሰቡ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንደመሆኑ ይሄ በሀገር ላይ የጨከተ የአውሬና የደናቁርት መንጋ ነገ ለእያንዳንዳቹህም የማይመለስ መሆኑን ጠንቅቃቹህ በመረዳት “በቃኝ! ከዚህ በኋላ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የወያኔ የጥፋትና የክህደት ሥራ ተባባሪ አልሆንም!” ብላቹህ በአንድነት በመነሣት ከራሱ በስተቀር “ኧረ እንዲያው ድንቁርናቸው ነው እንጅ ለራሳቸውም እኮ አይጠቅምም ነበር!” ለማንኛውም ከራሱ በስተቀር ለማንም በማያስበው ከሀዲ መንጋ ላይ በመነሣት እራስህን ሀገርህን እንድታድን በልዑል እግዚአብሔር ስም ትጠየቃለህ፡፡ ይሄንን ባታደርግ ግን ብዙ ሳትቆይ የሚቆጭህ መሆኑን አበክሬ ላስገነዝብህ እወዳለሁ “ወይኔ! ምነው ያኔ ተነሥቸ በነበርኩ!” የምትልበት መራራ ጊዜ ከፊትህ መጥቶ አፈር ድሜህን ያስግጥሀል፡፡ ልብ አድርግ፡፡

ወገናዊ ጥሪ ለትግሬ ሕዝብ፡-

የትግሬ ሕዝብ ሆይ! ወያኔ የህልውናው መሠረቱና አለኝታው የባዕዳን ሀገራት መንግሥታና ሆዳም አሕያ የየብሔረሰቡ አድር ባይ ሹማምንት አገልጋዮቹ መሆናቸው ቢታወቅም የአንተ አቅም ለእሱ ህልውና የሚያበረክተው ኢምንት እንደሆነ ቢታወቅም አንተን መሠረቴ አለኝታየ እያለ ህልውናው መሆንህን እየተናገረ በስምህ በመነገድ እንደኖረና እንዳለ አሳምረህ ታውቀዋለህ፡፡ 

እስከአሁንም ወያኔ በዚህች ነገርና ሕዝብ ላይ በተደጋጋሚ ክህደት ሲፈጽም “በስማችን እየገዛህማ እንዲህ ልታደርግ አትችልም!” ስትል ታይተህ ተሰምተህ አታውቅም፡፡ ይልቁንም የሚመካበትን ሙሉ ድጋፍ ስትሰጥ ነው የኖርከው፡፡ እንኳንና እዚህ ሀገር ውስጥ ያለኸው ይቅርና በውጪ ሀገራት በነጻነት መቃወም በሚያስችላቸው ሀገራት ያሉ ልጆችህ እንኳን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገን ጋር ሆነው የወያኔን የክህደት ተግባር ሲያወግዙ ሲቃወሙ ታይተው ተሰምተው አይታወቁም፡፡

ወያኔ የህልውናው መሠረትና አለኝታው አንተ እንደሆንክ እንድትታሰብ ማድረጉና ያደረገውን ቢያደርግ ዝም ማለትህ ወያኔ በፈጸመው ክህደትና ወንጀሎች ነገ ተጠያቂው አንተ መሆንህን ልብ ብለኸዋል ወይ? ከዚህ በላይ መቸና ምንስ ቢያደርግ ነው “አይ! በስማችን እየተጠቀምክማ እንዲህ ልታደርግ አትችልም! አንተ ነገ አላፊ ነህ እኔ ግን እንደ ሕዝብ ኗሪ ነኝ ነገ አንተ በፈጸምከው ግፍ ወንጀልና ክህደት ሁሉ እኔ ተጠያቂ ዕዳ ከፋይ መሆኔ ስለማይቀር እንዲህ እንኳን ልታደርግ አትችልም!” የምትለው መቸና ምንስ ቢያደርግ ነው? የወያኔ ነውረኛ ቆሻሻ ወራዳ ማንነት እንደ ሕዝብ አያሸማቅቅህም ወይ? አያሳፍርህም ወይ? እባክህ ይሄ የወያኔ አሳፋሪና አዋራጅ ክህደት መንቂያህ ይሁንና “ዞር በል ወራዳ አዋራጅ አላውቅህም! አልይህ!” በማለት ከሌሎቹ ወገኖችህ ጋር ቁም ተሰለፍ! “አንተን የሚበላ ጅብ እኔንም ይብላኝ” ከሚለው አስተሳሰብህ ተላቀቅ!!!

ወገናዊ ጥሪ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፡-

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ዝምታህ እስከመቸ ነው? ከቶ ምን ቀረህ? ይሄ የወያኔ ክህደት ምንም ቢሆን ልትታገሳቸው ከማትችላቸው ጉዳዮች እንዳልሆነ እያወክ የዝምታህ ምሥጢር ምንድን ነው? ምን ዓይነት አዚም ነው አፍዝዞ አደንዝዞ እያስበላህ ያለው? ኧረ እባክህ ንቃ! ኧረ እባክህ ጨርሰህ ሳትጠፋ በቃ! በል?

አንድ ላይ ሆ! ብለህ ይሄንን ግፈኛ ነውረኛ ወራዳ አገዛዝ እንዳትገላገል ያደረጉህን እንደወትሮህ ሀገር ስትነካ ቀፎው እንደተነካበት ንብ አንድ ላይ ሆ! ብለህ በመነሣት የሀገርህን ድንበር ብሔራዊ ጥቅምህን እንዳታስጠብቅና እንዳታስከብር ወያኔ ኦነግና ሌሎቹ የጥፋት ኃይሎች በዘር በሃይማኖት ከፋፍለው የጥንካሬህን ምንጭ አንድነትህን አፈራረሱት የአንደኛህ ሕመም ለሌላኛህ የማይሰማህ የጎጥህ እንጅ የሀገርህ ጥፋትና ጉዳት የማይገድህ የማትተባበር አድርገው የግፍ አገዛዙ በአፍ ጢምህ እስኪደፋህ በሰብእናህ እስኪጫወትብህ ሀገር አልባ አድርጎ እንደባሪያ እንደመጻተኛ በሀገርህ ጉዳይ የማያገባህ ባዕድ እስኪያደርግህ አገርህን ሲያፈራርሳት ድረስ ተሸክመኸዋል፡፡

በፊት ከነበረህ የላቀና የሠለጠነ አስተሳሰብህ ማለትም ጠባብ ጎጠኝነት ጠባብ ብሔርተኝነት ጎጅ እንጅ ጠቃሚ አለመሆኑን፣ ጠባብ ብሔርተኞች ሥልጣን ይዘው ሆነው እንደምናያቸው ፀረ ዲሞክራሲያዊና (መስፍነ ሕዝባዊና) ፀረ ሰብአዊ አስተሳሰብ መሆኑን፣ የሰው ልጆችን ዕኩል ያለማየት ለማየትም ያለመፈለግ አድልኦ የሞላበት ኢፍትሐዊ አስተሳሰብ የተጣባው የተቆራኘው መሆኑን፣ ሀገር የሚያፈርስ ነቀርሳ አስተሳሰብ መሆኑን ጠንቅቀህ ተረድተህ አንድነትን የነገሮችህ ሁሉ መሠረት በማድረግ በምንም ነገር ብትፈተን ምንም ዓይነት ችግር ቢደርስብህ ጨቋኞችና ሀገር የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን በመገንዘብ አንድነትህን ለድርድር ሳታቀርብ በሀገርህና በህልውናህ ላይ የሚመጣብህን ፈተና ስትመክት፣ ስታከሽፍ፣ ስታሸንፍ ከኖርክበት የሐሳብ ልቀትህና የሠለጠነ ሥነልቡናዊ ልዕልናህ ከፍታህ አውርደው የድንቁርና አስተሳሰብ በሆነው፣ ጠንቅ፣ ችግር፣ ሞት በሞላበት ጠባብ የጎጠኝነት ነቀርሳ የመረዙህንና በጠንቅ በምስቅልቅል ማጥ ውስጥ ላትወጣ እያሰመጡህ ያሉትን ወያኔን ኦነግንና ሌሎች የጥፋት ኃይሎችን ከነደንቆሮ አስተሳሰባቸው ከጫንቃህ ላይ አሽቀንጥረህ ወርውረህ በአንድነት መድኃኒትህ እራስህንና ሀገርህን ከሞት ከጥፋት ከመፈራረስ ታድን ትታደግ ዘንድ የእነ አርበኛው አቡነ ጴጥሮስን ግዝት የሰማችው ምድር ለአንተ ደግሞ አፍ አውጥታ “የኔ ሞት ያንተ ሞት ነው! የኔ መፈራረስ ያንተ መፈራረስ ነው! የኔ መጥፋት ያንተ መጥፋት ነው! ልብ አድርግ ስማ! ስማ! ስማ!” እያለች ትማጸናለች ለራስህ ብትል ስማ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!


ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49582

Sunday, December 27, 2015

እነ ሀብታሙ አያሌው በጠቅላይ ፍ/ቤት የቃል ክርክር አደረጉ | አብርሃ ደስታ “ጭቆናን ካላጋለጥኩ ምኑን ተቃዋሚ ሆንኩት?” አብርሃ ደስታ

‹‹እኔ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እንደመሆኔ መጠን የኢህአዴግን ጭቆና ማጋለጥ ግዴታዬም መብቴም ጭምር ነው! ይህን ካላደረጉ ምኑን ተቃዋሚ ሆንኩ?›› አብርሃ ደስታ ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም! የታሰርኩት በኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራ ነው! እኔ የፖለቲካ እስረኛ ነኝ!›› ዳንኤል ሺበሺ


በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በነፃ የተሰናበቱት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋና በተመሳሳይ የክስ መዝገብ ውስጥ ከአመራሮቹ ጋር የተከሰሰው አቶ አብርሃም ሰለሞን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም በመቅረብ የቃል ክርክር አድርገዋል፡፡

በችሎቱ የተሰየሙት ግራ ዳኛ መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው ታህሳስ 8 ቀን 2008 ዓ.ም ተከሳሾቹ የፍ/ቤቱ ሰብሳቢ ዳኛ የሆኑት አቶ ዳኜ መላኩ ከሰብሳቢነታቸው እንዲነሱ ባቀረቡት የፅሁፍ አቤቱታ ላይ መልስ ለመስጠት፤ የተከሳሾቹንና የአቃቤ ሕግን የቃል ክርክር ለማድመጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተከሳሾቹ ‹‹ሰብሳቢው ዳኛ ይነሱልን!›› ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ፍ/ቤቱ ስላላመነበት ውድቅ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

አቃቤ ሕግ በችሎቱ ባቀረበው የይግባኝ አቤቱታው ተከሳሾቹ ከግንቦት ሰባት አመራር አባላት ጋር በተለያየ ጊዜ መገናኘታቸውን፤ ይህንንም የሚያስረዳ ማስረጃ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ማቅረባቸውን ነገር ግን የስር ፍ/ቤቱ እነዚህን ማስረጃዎች ሳይመዝን ‹‹በደፈናው ውሳኔ ስለሰጠ›› ይግባኝ መጠየቃቸውንና የስር ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሲሰጥ ከጭብጥ መውጣቱን ገልጿል፡፡ ‹‹ፍ/ቤቱ ከፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀፅ 23 መሰረት የቀረበውን የሰነድ ማስረጃዎች በመመልከት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ፍ/ቤቱ ይወስንልን ዘንድ እንጠይቃለን›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

1ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌውና 5ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ሰለሞን በጠበቃቸው አምሃ መኮንን በኩል የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ አቶ አምሃ መኮንን የስር ፍ/ቤቱ ደምበኞቻቸውን በነፃ ሲያሰናብታቸው የቀረቡትን ማስረጃዎች መዝኖ መሆኑን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ አቃቤ ሕግ በክሱ ላይ ያቀረባቸው ነገሮች እንደመረጃ እንጂ እንደማስረጃ ሊያዙ እንደማይገባ የተከሳሾቹ የቀድሞ ጠበቃ በስር ፍ/ቤት ክርክር አድርገው የስር ፍ/ቤቱ ሐምሌ 2 ቀን 2007 ዓ.ም ‹‹በማስረጃ ሊያዙ ይገባል!›› ብሎ ብይን ማስተላለፉን አቶ አምሃ አውስተዋል፡፡ ጠበቃው ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ በኩል የሚቀርቡ ማስረጃዎችም ፍ/ቤት ሊመረምራቸው እንደሚገባ ሲያስረዱ፡- ‹‹የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ በኩል የሚቀርቡ መረጃዎችን ፍ/ቤቱ ሙሉ ለሙሉ የሚቀበል ከሆነ የፍ/ቤቱ ሚና ምን ሊሆን ነው? ፍ/ቤቱ ከተቋሙ በኩል የሚቀርቡለትን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ የሚቀበል ከሆነም ፈራጁ ፍ/ቤት ሳይሆን ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ነው›› በማለት አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ደምበኛቸው አቶ ሀብታሙ አያሌውም በክሱ ላይ ‹‹ዘመነ ካሴ›› ከተባለው የግንቦት ሰባት አባል ጋር በመነጋገር አብረው ለመስራት ተስማሙ ተብሎ ቢገለፅም ይህን የሚያስረዳ ማስረጃ አለመቅረቡን ገልፀዋል፡፡ ደምበኛቸው ከግለሰቡ ጋር ባደረጉት የስልክ ልውውጥ አንድም ቦታ ላይ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን እንዳልገለፁ ጠበቃው ጠቁመዋል፡፡ በክሱ ላይ የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ የሆነው አቶ ሀብታሙ አያሌው ከዘመነ ካሴ ጋር ግንኙነት አደረጉ ተብሎ የተገለፀው ከእውነታ የራቀ መሆኑን ጠበቃው ገልፀዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ አቶ ሀብታሙ አይደለም የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሊሆኑ ቀርተው፤ የፓርቲው አባል እንዳልነበሩም አቶ አምሃ አስረድተዋል፡፡ አቶ ሀብታሙ በበኩላቸው በክሱ ላይ ተከሳሽ በዚህ የሞባይል ቁጥር ግንኙነት አድርጓል ተብሎ አለመገለፁን የስልክ ልውውጡም ምን እንደሆነ የሚያስረዳ አንዳች ነገር አለመቅረቡን ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡

አቶ አምሃ ደምበኛቸው በሆነው 5ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ሰለሞን ላይ ምንም አይነት የሰነድ ማስረጃ አለመቅረቡን የግንቦት ሰባት አባል ነው ሲባልም፤ በግንቦት ሰባት መዋቅር ውስጥ እንዳለ የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረቡን ደምበኛው በምንም አይነት የሽብርተኝነት ተግባር ላይ እንደተሰማራ የሚገልፅ ምንም አይነት ማስረጃ አለመቅረቡን ገልፀዋል፡፡ አቶ አብርሃም ሰለሞን በበኩሉ ያለአንዳች ማስረጃ መታሰሩን ሲያስረዳ፡- ‹‹ከታሰርኩ በኋላ ነው ማስረጃ ሲፈለገብኝ የነበረው፤ ከታሰርኩ በኋላም ቤቴ እንኳ አልተፈተሸም፡፡ መንግስት አሰረኝ ብዬ አላምንም ያሰረኝ አንድ ግለሰብ ነው›› ሲል ተደምጧል፡፡

2ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ 3ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃ ደስታና 4ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ ያለጠበቃ በመቆም በግል ክርክራቸውን ያካሄዱ ሲሆን፤ ሶስቱም ተከሳሾች የአቃቤ ሕግ የይግባኝ ማመልከቻ ላይ እነሱን የሚመለከት ቅሬታ አለመቅረቡን ለፍ/ቤቱ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም! የታሰርኩት በኢህአዴግ የፖለቲካ ሴራ ነው! እኔ የፖለቲካ እስረኛ ነኝ!›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የቃል ክርክር ለማድረግ ያዘጋጁት ወረቀትም በማረሚያ ቤቱ እንደተቀደደባቸው ለፍ/ቤቱ አሳይተዋል፡፡ ወረቀቱ ማህተም የተደረገበት ቦታ ተቀዶ መውጣቱን በችሎቱ ለነበሩ ታዳሚያን በግልፅ ታይቷል፡፡

3ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃ ደስታም ከታሰሩ በኋላ ማስረጃ ሲፈልግባቸው እንደነበርና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ የሚቀርብ መረጃ በፍ/ቤት ሳይመዘን ሙሉ ለመሉ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ ተቋሙ ከሳሽም፣ መስካሪም፣ ዳኛም ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ዘንድ ደግሞ ፍ/ቤት መምጣትም አያስፈልግም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በክሱ ላይ ለኢሳት ቴሌቪዥን ቃለምልልሰ ሰጠ ተብሎ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ሲያስረዱ፡- ‹‹እኔ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እንደመሆኔ መጠን የኢህአዴግን ጭቆና ማጋለጥ ግዴታዬም መብቴም ጭምር ነው! ይህን ካላደረጉ ምኑን ተቃዋሚ ሆንኩ?›› በማለት ለፍ/ቤቱ የገለፁ ሲሆን፤ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ ሃሳባቸውን ሲገልፁ የነበሩትም የኢህአዴግን ጭቆናን ማጋለጥ መብታቸው በመሆኑ እንደሆነ ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡

4ኛ ተከሳሽ አቶ የሺዋስ አሰፋ በእሳቸው ላይ የቀረበ አንድም የሰው ምስክር እንደሌለ ገልፀው፤ ማዕከላዊ በነበሩበት ወቅትም በምርመራ ላይ አንድም ቀን ስለግንቦት ሰባት ተጠይቀው እንደማያውቁ ምርመራ ላይ ሲጠየቁ የነበሩትም ስለ ሰማያዊ ፓርቲ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ የሺዋስ የሰማያዊ ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ አያሌ መከራዎችን እየተጋፈጡ እንደሚገኙ ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡ ያለፉትን 6 ወራት በማንም አለመጎብኘታቸውን ለፍ/ቤቱ ገልፀዋል፡፡

ፍ/ቤቱ የቃል ክርክሩ በፅሁፍ ተገልብጦ ከቀጣይ ቀጠሮ በፊት ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ እንዲቀርብ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌው የሚገኙበት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም መልስ እንዲሰጥ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የማረሚያ ቤት ተወካዩ በተጠቀሰው ቀን አቶ ሀብታሙን ይዞ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መዝኖ ውሳኔ ለመስጠት ለታህሳስ 29 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ እነ ሀብታሙ አያሌው ነሐሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49442




Thursday, December 24, 2015

ግፍ ሲፈጸም ዝምታን ከመረጥን እንደ አገር እንጠፋለን -ሃብታሙ አያሌው | ከቂሊንጦ እሥር ቤት

ለነጻነታቸው በሚያደርጉት ትግል፣ ኢትዮጵያ እንደ እናት ሆና የረዳቻቸዉ ፣ እንደ ጋና፣ ታንዛኒያና ሴኔጋል ያሉ የአፍሪካ አገሮች እንኩዋን ሳይቀሩ የትናየት በደረሱበት ዘመን፣ እንደ ደርግ ዘመን አሁንም በኢትዮጵያ፣ ረሃብና ችጋር የሚገድለን አልበቃ ብሎ፣ ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያዉያን እጅ እየተገደሉ ነው። 

በቅርቡ በጎንደር እና በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎቸ እንዳየነው፣ በዜጎች ላይ የደረሰው ግድያ፣ ድብደባና ግፍ እጅግ በጣም ልቤን እንዳደማው መግለጽ እወዳለሁ። ለሞቶት ነፍስ ይማር፣ ለቤተሰቦቻቸዉም መጽናናቱን ያብዛላቸው እላለሁ።

በወገኖቻችን ላይ የደረሰን ጭካኔ አጥብቄ እያወገዝኩ ፣ የአገዛዙ ታጣቂዎች ተቃዉሞ ከሚሰማባቸው ቦታዎች በአስቸኩዋይ እንዲወጡ እጠይቃለህ። መንግስት ገዳዮችን፣ ትእዛዝ የሰጡትን ለፍርድ እንዲያቀርብና ጉዳት ለደረሰባቸው አስፈላጊውን ካሳ እንዲሰጥ እጠይቃለሁ። ገዢዎች የሕዝብን መሰረታዊ ጥያቄ በማናናቅ፣ በሚቆጣጠሩት ሜዲያ በሕዝብ ላይ የሚያሰሙት ዛቻ፣ ማስፈራራት ፣ ስድብ አቁመው፣ ለሕዝብ መሰረታዊ የመብት፣ የነጻነት የፍትህና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እጠይቃለሁ።

እኔን ጨመሮ በርካታ ዜጎች በሰላም ሐሳባችንን በመግለጻችን ሽብርተኞች ተብለን፣ ፍትህ ተነፍገን በግፍ ታስረናል። ነጻ ጋዜጦች ተዘግተዋል። በሌሎች አገሮች የእንስሳት መብቶች ሲከበሩ፣ በኛ አገር ግን ለሰብእና ክብር አይሰጥም። ዜጎች በአገራቸው ፈርተዉና ተሸማቀው ነው የሚኖሩት። ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ስደትን መርጠዋል። በልማት ስም ጥቂቶችን ለመጥቀም፣ ገበሬዎች ከእርሻቸው ይፈናቀላሉ። “ከዚህ ብሄረሰብ ናችሁ፣ የናንተ መሬት አይደለም” ተብለው ብዙዎች የዘር ማጽዳት ወንጀል ይፈጸምባቸዋል። በጎንደር ለምለም የአገራችን መሬት፣ ሕዝብ ፓርላማው ሳያውቀው ሊሰጥ እንደሆነ እየሰማን ነው። አገር በ 11% አድጋለች እየተባለ፣ አሥር ሚሊዮኖች ለረሃብ ተጋልጠዋል። ይሄ ሁሉ መቆምና መስተካከል አለበት። “ኢሕአዴግ ልብ ይበል ፤ 
የጥፋት እጆቹን ይሰብሰብ ፣ ሕዝብን ያክብር፣መሰረታዊ የፖለቲካ ሪፎርም ያድርግ፣ ለብሄራዊ መግባባት ራሱን ያዘጋጅ” እላለሁ።


ነጻነትን ለተጠሙ፣ ፍትህን ለተራቡ ኢትዮጵያዊያን መልእክት አለኝ። ነጻነት፣ ፍትህ ከሌሎች በስጦታ የሚሰጠን አይደለም። ነጻነትና ፍትህ እኛው ራሳችን ታግለን የምናገኘው ነው። በመሆኑም የአገሪቱዋ ሕገ መንግስት እና አለም አቀፍ ሕጎች በሚፈቅዱት መሰረት፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻችንን እንድናሰማና ትግሉን እንድንቀላቀል ጥሪ አቀርባለሁ። ግፍ ሲፈጸም ዝምታን ከመረጥን እንደ አገር እንጠፋለን። የአንዱ ሕመም እኛንም ሊያመን ይገባል። እንተባበር፣ እንደራጅ፣ በጋራ፣ በማያዳግም ሁኔታ፣ “በኢትዮጵያችን ከዚህ በሁዋላ በግፍ ደም መፈሰስ የለበትም” እንበል። አሁንስ በቃን !!!!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49378

Saturday, December 19, 2015

‹‹ኃብታሙ አያሌው ላይ በጤንነቱ የተነሳ ለሚደርስ ችግር›› ሐኪሞቹ ‹‹ኃላፊነት አንወስድም›› አሉ

                        ኃብታሙ አያሌው


የቀድሞው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ሐብታሙ አያሌው ከማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ቆይታ አንስቶ እያሰቃየው የሚገኘውን የኩላሊት ህመሙን ከብዙ ንትርክ በኋላ በዘውዲቱ ሆስፒታል እንዲታከም የተደረገ ቢሆንም የሐብታሙን ህክምና በመከታተል ላይ የሚገኙ ሐኪሞች ኩላሊቶቹ ከፍተኛ ክትትል የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ሐብታሙ በሆስፒታሉ አልጋ በመያዝ አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባው ያዛሉ፡፡

እንደ ሆስፒታሉ የመረጃ ምንጮች ከሆነም ሐብታሙን ታህሳስ 5 ቀን 2008 በዘውዲቱ ሆስፒታል የመረመሩት ዶክተሮች የምርመራቸውን ውጤት ከተመለከቱ በኋላ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ከሌሎች ሶስት የኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስቶች ጋር በመመካከር ቢሆንም የህሊና እስረኛውን ለህክምና ምርመራ ያመጡት የወህኒ ቤቱ ፖሊሶች ሐብታሙን ‹‹አሳይታችሁ አምጡት››ተብለናል በማለት መልሰው ወስደውታል፡፡


በሆስፒታሎች አልጋ ይዘው እንዲታከሙ በዶክተሮች የሚታዘዙ እስረኞች በፖሊስ እንዲጠበቁ ተደርገው አልጋ የሚይዙ ቢሆንም ሐብታሙ ጤንነቱ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገራቸው ህክምናውን አቋርጦ እንዲሄድ አድርገውታል፡፡


በዚህ ወቅት በፖሊሶቹ ውሳኔ የተበሳጩ ዶክተሮች ‹‹በጤንነቱ የተነሳ አንዳች ችግር ቢፈጠርበት እኛ ኃላፊነት አንወስድም፡፡እናንተም የባለሞያ ምክራችንን ትታችሁ ህመምተኛውን መውሰዳችሁን ፈርሙልን››በማለት ጥያቄ ቢያቀርቡላቸው ለመፈረም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለጽ ወስደውታል፡፡


ሐብታሙ፣አብርሃ፣የሺዋስና ዳንኤል ዛሬ በቀረቡበት ፍርድ ቤት የተሰየሙት የመሐል ዳኛ ጉዳያቸውን የመመልከት ሞያዊም ሆነ ስነ ምግባራዊ ብቃት እንደሌላቸው በመጥቀስ እንዲነሱላቸው መጠየቃቸው ተነግሯል፡፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49259

Tuesday, December 15, 2015

የህወሓቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጎንደር ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰባቸው


ከአዲስ አበባ ጎንደር የገቡት የአገዛዙ ባለስልጣናት የህወሓቱ አባይ ፀሀዬ፣ የህወሓት ተላላኪ የሆነው ብአዴን ቁንጮዎች በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ናቸው፡፡ የክልሉ ሹም ገዱ አንዳርጋቸውም በአጃቢነት ተገኝቷል፡፡

አባይ፣ በረከትና አዲሱ በትናንትናው ዕለት የዞኑን ካቢኔ አባላትና ጥቂት የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎችን በጎሃ ሆቴል ሰብስበው በጎንደር ስለሰፈነው አለመረጋጋት፣ አመፅና ጦርነት ለማነጋገር ሞክረው “ይህ ሁሉ ችግር ከደረሰና ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ በኋላ ምትመጡ እስከ ዛሬ የት ነበራችሁ? የህዝብ ቁጣ ጫፍ ደርሷል አሁን እናንተ መጣችሁ አልመጣችሁ የምትፈይዱት ቅንጣት ታክል ነገር የለም…” የሚል ምላሽ ያለበት ከወትሮው ለየት ያለና ጠንካራ ተቃውሞ ከተሰብሳቢው ተሰንዝሮባቸዋል፡፡ በተለይም በባለስልጣናቱና በካቢኔው መካከል የተፈጠረው እሰጣገባና ንትርክ ወደ ከረረ ያለመግባባት ውስጥ እንደከተታቸው ታውቋል፡፡


እነበረከትና አባይ የጎንደርን ነዋሪዎች በየክፍለ ከተማው ሰብስበው ለማነጋገር መድረክ እንዲያመቻቹላቸው የዞኑን ካቢኔ አባላት ጠይቀው የካቢኔ አባላቱ በአሁኑ የትኩሳት ወቅት ህዝብ መሰብሰብ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ እና ባለስልጣናቱ ራሳቸው ወርደው ያሻቸውን ማድረግ እንደሚችሉ ቁርጥ ያለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


በመሆኑም እነ በረከትና አባይ ፀሀዬ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ወድቀው የሚያደርጉት ጭንቅ ጥብብ ብሏቸው አሁንም በጎንደር ከተማ ጎሃ ሆቴል ውስጥ ይገኛሉ፡፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49153

መድረክ ባለ 6 ነጥብ መግለጫ አወጣ | “ሕዝቡ በጉልበትና በማጭበርበር የተቀማውን መብት ለማስመለስ በሰላማዊ መንገድ ይታገል”

የሕዝቦችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ የሚከናወኑ የኢህአዴግ ሕገወጥ እርምጃዎች ሕዝባችንን ለከፍተኛ ችግር፣ ሀገራችንንም ለአሳሳቢ ሁኔታ እየዳረጉ ስለሆነ በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!!
(ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ)
የኢህአዴግ አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በተግባር ሊያውላቸው ያልተዘጋጀባቸውን ድንጋጌዎች ከሀገሪቱ ሕገመንግሥት ጀምሮ ሲያውጅ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ያወጃቸውን ድንጋጌዎች በማፍረስና በተግባር እንዳይውሉ በማድረግ የዜጎችንና የሕዝቡን መብቶች የሚጥሱ ተግባራትን እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ ከአንድ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት በጉልበትና በማጭበርበር ቀምቶ መንግሥት ነኝ ከሚል አምባገነን ቡድን የሚጠበቅ ቢሆንም፣ መዘዙ የሀገራችንን ደህንነትና የሕዝቦቻችንን እኩልነትና አንድነት ለማይሹ ኃይሎች አፍራሽ እንቅስቃሴ ቀዳዳ እየሰጣቸው መሆኑ መድረክን በእጅጉ ያሳስበዋል፡፡
ከእነዚህ ሕገመንገሥታዊ ድንጋጌዎች ጥሰት መነሻነት ከተፈጠሩት ውስብስብ ችግሮች ውስጥ አንዱ የአዲስ አበባ ከተማንና የኦሮሚያን ክልላዊ መንግሥት ግንኙነት በሚመለከት፣ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 “የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል” የሚለውን በማንአለብኝነት ከመጣስ የመነጨ ችግር ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኢህአዴግ ሥርዓተ-አልበኝነት መገለጫ ሆኖ የቆየው በሕገመንግሥቱ የሰፈረው ዝርዝር የአፈጻጸም ሕግ ሳይወጣ ከ21 ዓመታት በላይ መቆየቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ እንዲሁም በአዲስ አበባ አከበቢ የሚሠሩ የልማት ሥራዎችንም በሚመለከት ሕዝቡን በአግባቡ ሳያወያዩ ጥቂት እበላ ባይ ካድሬዎችን በአስፈጻሚነት በማሰማራት የእርሻ መሬታቸውን እየነጠቁ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የማካለል እንቅስቃሴ ላይ መሠማራቱ በተከታታይ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችንና ውዝግቦችን ከማስነሳቱም በላይ ለብዙ ዜጎች ሕይወት በኢህአዴግ መንግሥት አርመኔአዊ እርምጃ መቀጠፍ ምክንያት ሆኖአል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዲስ አበባ ከተማን ከሕግ አግባብ ውጪ ማማስፋት ጋር በተያያዘ በሕዝቡ ዘንድ ካደረው ስጋት በመነሳት የተቀሰቀሰውን ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞን በኃይል ለማስቆም የኢህአዴግ መንግሥት በወሰደው እርምጃም በርካታ ተማሪዎችና ሌሎች ዜጎች መገደላቸውን መድረክ በእጀጉ ይኮንነዋል፡፡


የተገደሉት ዜጎችም

1ኛ፡- ተማሪ ካረሳ ጫላ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣
2ኛ፡- ተማሪ ጉቱ አበራ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣ 3ኛ፡- ተማሪ ሚፍታህ ጁንዲ በምዕራብ ሐረርጌ በደኖ ወረዳ፣
4ኛ፡- ተማሪ ገዘሃኝ ኦልሂቃ የሀራማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪ፣
5ኛ፡- ተማሪ ደጀኔ ሰርቤሳ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ቶሌ ወረዳ፣
6ኛ፡- ተማሪ በቀለ ሰቦቃ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣
7ኛ፡- ተማሪ በቀለ ሰይፉ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣
8ኛ፡- ተማሪ ሙራዲ አብዱ የሀራማያ 2ኛ ደረጃ ተማሪ፣
9ኛ፡- አቶ ጫላ ተሾሜ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ባቢቻ ከተማ፣
10ኛ፡- ተማሪ አብደታ ባይሳ ምዕራብ ሸዋ ጫለያ ወረዳ ባብቻ ከተማ፣
11ኛ፡- ተማሪ ዱሌ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣
12ኛ፡- አቶ ታመነ ጸጋዬ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣
13ኛ፡-ተማሪ ደረጀ ጋዲሰ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣
14ኛ፡- ተማሪ ፈቃዱ ግርማ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣
15ኛ፡-ተማሪ ሉጫ ገማቹ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣
16ኛ ተማሪ አያና ባንቲ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣
17ኛ፡- ተማሪ አላዛር ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ ነዋሪ
18ኛ አቶ ኤብሰ ቱጆ ሆሮ ጉዱሩ ፍንጫ፣
19ኛ፡- አቶ ደበላ ጣፋ ጫንጮ ላይ ተገድሎ ተጥሎ የተገኘ፣
20ኛ ወ/ሮ ዲሶ ሚሊኬሳ ሕልፈታ ወረዳ
21ኛ፡- አቶ አበበ ቡሎ ወሊሶ ከተማ፣
22ኛ፡- አቶ ታዴ ሰፈራ አመያ ከተማ፣
23ኛ፡- አቶ ሌንጮ ሁንዴራ ወሊሶ ከተማ፣
24ኛ፡- አቶ ሰለሞን ሞገስ አማያ ከተማ፣
25ኛ፡- አቶ ታዴ አንዲሳ ወንጪ ከተማ፣
26ኛ፡- አቶ እናውጋው ኃይሉ ግንደበረት ወረዳ፣
27ኛ፡- ተማሪ አብደታ ለታ ግንደበረት ወረዳ
28ኛ፡-አቶ ባይኢሳ ገደፋ አቡና ግንደበረት
ወረዳ 29ኛ፡- ተማሪ አስቻለው ወርቁ ግንጪ ወረዳ፣
30ኛ፡- ተማሪ ሰይፉ ቱራ ግንጪ ወረዳ፣
31ኛ፡- ተማሪ አሸናፊ ግንጪ ወረዳ፣
32ኛ፡- አቶ ገላና ባቃና ጪቱ ከተማ ነዋሪ የነበሩ ስለመሆናቸው የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከዚህም ሌላ ከመቶ ባለይ ዜጎች ቆስለዋል፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእስራት ተዳርገዋል፡፡ ሰላማዊና ሕጋዊ ተቃውሞን ለማፈን በመንግሥት እየተወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ እስከ አሁንም እንደቀጠለ በመሆኑ፣ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት መድረክን በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል፡፡ እንደዚሁም በቅርቡ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ወሕኒ ቤት በእስረኞች ላይ የተፈጸመው ግዲያ መድረክን አሳስቦታል፡፡
ከዚህም ሌላ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ “የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው” የሚለውንና በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነፃ የማግኘት፣ የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው” ተብሎ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በከተሞችና በእንቨስትመንት ማስፋፋት ስም የአርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን መሬት እየቀሙ በማፈናቀል ለከፍተኛ የኑሮ ችግሮች እየዳረጉዋቸው ይገኛሉ፡፡ መድረክ ይህንን የኢህአዴግ መንግሥት የመሬት ቅሚያ እርምጃ ደጋግሞ ሲያጋልጥ የቆየ ሲሆን በእርምጃው ምክንያት በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው የጉዳት መጠን ከጊዜ ወደጊዜ በአሁኑ ወቅት እየሰፋ ስለመገኘቱ መረጃዎች ያሳያሉ፡፤
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገዛዙ በርካታ የሀገሪቱን ከተሞች ለማስፋፋትና መሬቱንም በፌዴራል መንግሥት ቁጥጥር ሥር በመሬት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ለማስተዳደር፣ የማስተር ፕላንና የሪፎርም ከተሞች ብሎ በመሰየም፣ በየከተሞቹ አከባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች ይዞታዎች አርሶ አደሩን ሳያማክሩና ተገቢውን ካሳ ሳይከፍሉ ወደ ከተማ ለማካለል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ነዋሪውን ሕዝብ ለከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ ስለሆነም የኢህአዴግ አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በማንአለብኝነት አምባገነናዊ ስሜት እየተመራ ፌዴራላዊ ሥርዓቱንና የዜጎችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ እየፈጸመ ከሚገኘው ሕገወጥ ተግባር እንዲቆጠብ እንጠይቃለን፡፡ በተለይም፡-


1ኛ፡- ከአዲስ አበባ ከተማና ከኦሮሚያ ክልል ግንኙነት ጋር በተያያዘ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮች ሕገመንግሥቱን ተግባራዊ ባለማድረግ ምክንያት እየተከሰቱ ስለሆኑ የሕገመንግሥቱን አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 ተግባራዊ የሚያድርግ ሕግ በአስቸኳይ ወጥቶ ተግባራዊ እንዲደረግና ለችግሩ ዘላቂ እልባት እንዲሰጥ፣ ለከተማዋ ልማት የሚወጡ እቅዶችም የሕገመንገሥቱን ድንጋጌ የሚያከብሩ ሆነው የአከባቢውን አርሶ አደሮች መብትና ጥቅም በሚገባ የሚያስጠብቅ እንዲሆኑ፣


2ኛ፡- በቅርቡም መንግሥት ሕገወጥ እርምጃ ለመውሰድ በተንቀሳቀሰበት ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ባደረጉና በሌሎችም ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም፣


3ኛ፡- እስከአሁን የዜጎችን ሕይወት በሕገወጥነት ያጠፉና ሌሎች ጉዳቶችን ያደረሱ የመንግሥት አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡና ለሟቾቹ ቤተሰቦችም ተገቢው ካሳ እነዲከፈላቸው እንዲደረግ፣


4ኛ፡- በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ሕገመንግሥቱ ያረጋገጠላቸው ከመሬታቸው የያለመፈናቀል መብታቸው ተከብሮ፣ በየአከባቢያቸው በልማት ሥራዎች ሰበብ ኑሮአቸው እየተናጋ ለችግር የሚዳረጉበት ሁኔታ በአስቸኳይ ተወግዶ፣ የሚከናወኑት የልማት ሥራዎችም ቢሆኑ የአከባቢውን ሕዝብ ይሁንታ ያገኘና መብታቸውን የጠበቀ እንዲሆን እንዲደረግ፤

5ኛ፡- በተለይም በአሁኑ ወቅት ከተሞችን በማስፋፋት ስም የአርሶ አደሩን መሬቶች ወደ ከተማ ለማካለልና በከፍተኛ ዋጋ በሊዝ ለመሸጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ፣ አርሶ አደሩን በስጋት ውስጥ እየከተተው ስለሚገኝ፣ ኑሮአቸውን ለማሻሻል የሚበቃ በቂ ካሳ ሳይከፈል ይዞታቸውን ለመንጠቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቆም እንዲደረግ፣


6ኛ፡- በቅርቡ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ወሕኒ ቤት የተገደሉ በርካታ ዜጎች ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ የሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት ያጠፉና ጉዳት ያደረሱ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡና ለሟቾቹ ቤተሰቦችም ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም መድረክ በንጽሐን ዜጎቻችን ላይ በኢህአዴግ መንግሥት የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን ኢሰብአዊ ግዲያ በጥበቅ እያወገዘ ለሟቾቹ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡ መላው ሕዝባችንም በኢህአዴግ በጉልበትና በማጭበርበር በተካሄዱት ምርጫዎች የተቀማውን ሕገመንግሥታዊ መብቶቹን ለማስከበር ሰላማዊ ትግሉን እንዲያጠናክር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ጥሪ ያቀርባል፡፡


ድል ለሕዝባዊ ትግላችን !!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
ታህሳስ 5 ቀን 2008 ዓ ም
አዲስ አበባ


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49137

Monday, December 14, 2015

ሕዝብን ለመጨፍጨፍ እየዘመተ ያለው ጦር


በነሶሞራ የሚመራው እዝ፣ ህዝብን ለመጨረስና በሃይል አንገትን ለማስደፋት ሁለት ዲቪዝን ጦር ወደ ምራብ ሸዋና ወለጋ እየወሰደ ነው። ይህ አይነቱ እንቅስቃሴ አገዛዙ ሊወስደው የሚችለው የመጨረሻ ተግባር ነው። ጎንደር ላይ ከሰፈረው ጦር በተጨማሪ ወደ ኦሮሚያ እየተሰማራ ያለው ሲደመርበት በሌሎች ከተሞች የሚኖረው ጦር በጣም የተመናመነ ነው።

በመሆኑም በአዲስ አበባ. በጎጃም፣ በወለኦ፣ በሰሜን ሸዋ፣ እና በደቡብ ክልል ሕዝቡ ለነጻነትና ለመብት ድምጹን ማሰማት ቢጀመር ይሄ ስርዓትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመገርሰስ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።
በመሆኑም ሌላው ማሀበረሰብ ድምጹን ያሰማ ዘንድና በኦሮሚያና በጎንደር ለመብታቸው ከቆሙ እየተገደሉ ካሉ ወገኖቻችን ጎን እንዲቆም ያስፈልጋል።

እስከ አሁን በጎንደር ከ150 በላይ ዜጎንች የተገደሉ ሲሆን በኦሮሚያ የዛሬን ቀን ሳይጨመር ከሰባ በላይ ሕይወታቸው አልፏል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49101

Thursday, December 10, 2015

የኖርዌይ ኢምባሲ ዜጎቹ ወደ ጎንደርና ኦሮሚያ የተጠቀሱ ከተሞች እንዳይሄዱ መከረ


(ዘ-ሐበሻ) አዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኢምባሲ በጎንደር እና በኦሮሚያ ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ዜጎቹ በሁለቱ ክልሎች በተመረጡ አካባቢዎች እንዳይሄዱ አስታወቀ::

ከኖርዌይ ኢምባሲ የአዲስ አበባ ድረገጽ ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ እንደሚጠቁመው በጎንደር ባለፈው ሳምንት በ እስር ቤት ላይ የደረሰው ቃጠሎን ጉዳይ አንስቶ በአሁኑ ወቅት በታች አርማጭሆ; በም ዕራብ አርማጮና ጭልጋ አካባቢ ጦር የታጠቁ ኃይሎች እንቅስቃሴ እያደረጉ በመሆኑ ወደዚያ አካባቢ ለመሄድ ለደህነነት አስጊ በመሆኑ ዜጎቹ እንዳይሄዱና ከነዚህ አካባቢዎች እንዲርቁ መክሯል::

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ አደባባይ ከወጣ እና ፖሊስ እና ተማሪዎችም ከተፋጠጡ በኋላ በተለይ በአምቦ እና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞው እጅጉን በማየሉ የኖርዌይ ዜጎች ወደዚያ አካባቢ እንዳሄዱ አስጠንቅቋል::


በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ የተረጋጋና ያልታሰበ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ያስታወቀው ኢምባሲው ዜጎቹ ወደዚያው እንዳይሄዱ ከሄዱና አንድ ችግር ካጋጠማቸውም ቶሎ ለኢምባሲው ሪፖርት እንዲያደርጉ አስጠንቅቋል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48924


Saturday, December 5, 2015

ትግሬው ድርጅት ብአዴን ተጨማሪ 5ሚሊዮን አማሮችን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዕቅዱን ይፋ አደረገ

ተጨማሪ መሬቶችንን ለትግሬና ለሱዳን መስጠትና የሚፈናቀለው ህብረተሰብ በርሀብ እንዲያልቅ ማድረግ በዕቅዱ ተካትዋል!!

በ35ኛው የሙት አመት ዝክር ላይ የተወያየው የጠላት ትግሬ ቡድን ብአዴን የእስካሁኑ የ5ሚሊዮን አማሮች ከምድረ ገጽ መጥፋት አንጸባራቂ ድል ብሎታል።የተጨማሪ የ5ሚሊዮን አማሮች እልቂት የሚፈጸምበትን የማስፈጸሚያል ስልት በዝርዝር ያስቀመጠው ጠላት ድርጅት ብአዴን ለተግባራዊነቱ እንረባረባለን ሲል መግለጫ አውጥትዋል።የዘር ማጥፋቱ የማስፈጸሚያ ስልት እንደሚከተለው ቀርብዋል።
1.የሚያመክኑ መድሀኔቶችን በወሊድ መቆጣጠርና ክትባት ሽፋን በብዛት ማሰራጨትና እንዲጠቀሙ ማድረግ።
2.ህዝቡን በመከፋፈል በሚፈጠረው ግጭት የአማሮች እልቂት እንዲከሰት ማድረግ
3.በኢንቨስትመንት ሽፋን ትግሬዎችን በማስፈር አማሮችን በማፈናቀል በርሀብ እንዲያልቁ ማድረግ።
4.የበሽታ ወረርሽኝ እንዲከሰት በማድረግ የህክምና አገልግሎት እንዲዘገይ በማድረግ እልቂት እንዲፈጸም ማስቻል።
5.የአማራ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ የግብር ጫና በመጣል ከውድድር ውጪ እንዲሆኑና ጠላት ትግሬ እንዲቄጣጠር ማድረግ ፣እንዲሁም በአብቁተ አማካኝነት አርሶ አደሩ እዳ ውስጥ እንዲዘፈቅ ማድረግ።
6.የውሸት ክሶችን በመፍጠር አማሮች እንዲታሰሩና እንዲገደሉ ማድረግ።
7.ከዚህ በፋት በማብቃትና በቢ.ፒ.አር .እንደተደረገው በአማራው መንግስት ሰራተኛ ላይ የሚያሸማቅቁና ሞራልን የሚሰብሩ አስጨንቀው ለበሽታ የሚዳርጉ ግምገማዎችንን በማካሄድ የህብረተሰቡ ሞራል እንዲላሽቅ ማድረግ ይህ በጥላቻና ሞራል በሚነኩ ዘለፋዎች የታጀበ ነው።
8.ተጨማሪ መሬቶችንን ለትግሬና ለሱዳን መስጠትና የሚፈናቀለው ህብረተሰብ በርሀብ እንዲያልቅ ማድረግ።
9.ተምሮ የሚመረቀው የአማራ ወጣት ተመሮ ስራ እንዳያገኝና በራሱ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ።
10.ተካታታ የጥላቻ ዘመቻዎችን በማድረግ ሌሎች ህብረተሰቦች እንዲያገሉት ማድረግ ።እነዚህ በዝርዝር የቀረቡት ዋና ዋና የማስፈጸሚያ ስልቶች ናቸው ተፈጻሚነታቸውም በሚስጥር እንደሚሆን ከጠላት ትግሬ ድርጅት ብአዴን ተገልጽዋል በተጨማሪም ዕቅዱ የትግሬን የበላይነት በአተማማኝ ሁኔታ ለማስቀጠል እንደሚረዳ ተገልጽዋል።

http://www.satenaw.com/amharic/archives/11021

Monday, November 30, 2015

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የሕዝብ ተቃውሞ በአደባባይ ቀጥሏል * ፌደራል ፖሊስ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ 3 ተማሪዎችን ገደለ

የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ አድማሱን እያሰፋ መሆኑ ተሰማ:: የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳሉት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የተጀመረውና ጎማ ጭምር በአደባባይ በማቃጠል የተስፋፋው የሕዝብ ቁጣ ትናንት እና ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል::

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በሰላማዊ መንገድ ቁጣቸውን ለመግለጽ የተሰበሰቡ ተማሪዎች ከፌደራል ፖሊስ በቆመጥና በጠመንጃ ሰደፍ የተደበደቡ መሆኑን በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸው በተፈጠረው ብጥብጥ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል::

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ተማሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ምንም ዓይነት ንብረት ሳያወድሙ ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም ፖሊስ እርምጃ ሊወስድ ችሏል:: አሁንም በዩኒቨርሲቲው አካባቢ አለመረጋጋት እንዳለ ዘገባዎች ጠቁመዋል::
የኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ በአምቦ እንዲሁም በነቀምቴ ከተሞችም ቀጥሎ ተማሪዎቹ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ውለዋል:: የአይን ዕማኞች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት በአምቦ ፌደራል ፖሊስ መንገድ በመዝጋት የተማሪዎቹን ቁጣ ለማብረድ ጥረት ቢያደርግም ከከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መለስተኛ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎቹ ተቃውሞ ገንፍሎ ወጥቷል::

አዲሱን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃውም በሃገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የሚደረገው ቁጣ አሁንም እየተስፋፋ ሲሆን ሕዝቡ ይህ ማስተር ፕላን እንዳይተገበር የሕይወት መስ ዋዕትነት ሳይቀር እንደሚከፍል በመዛት ላይ ይገኛል::


በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማስፋፋት ስም በሰበታ ከተማ ለመለስ ዜናዊ መንደር ግንባታ በከተማው ለባለሃብት የተሰጠ የመሬት ፈቃድን የሚያሳይ ምስጢራዊ ደብዳቤ ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት ለሕዝብ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48607

Saturday, November 28, 2015

የሕወሓት አስተዳደር አዲስ አበባን “እናሰፋለን” በሚል ሰበብ የሚሰራው ሸፍጥ ተጋለጠ (ምስጢራዊውን ደብዳቤው ይዘናል)

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ሕዝቡ ሕወሓት የሚመራው መንግስት ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም አደባባይ በመውጣቱ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት እና ለበርካቶች መቁሰል ምክንያት እንደነበር ይታወሳል:: እነዚህ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ የሃገራችን ፍሬዎች ምክንያታቸው በአዲስ አበባን የማስፋፋት ምክንያት ምስኪን ገበሬዎችን በማፈናቀል መሬታቸውን ለባለሃብቶች ለመሸጥ ነው የሚል ነው:: ሕወሓት የሚመራው መንግስት “በልማት” ስም የተለያዩ የሃገራችንን መሬቶች ገበሬዎቹን በማሰናበት ለውጭ ባለሃብቶች በመሸጥ ይታወቃልና ወትሮም እነዚሁ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ሕዝቦች አደባባይ ወጥተው ይህን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ገበሬዎችን ያፈናቅላል ያሉትን አዲሱን ማስተር ፕላን ቢቃወሙ አይገርምም::

ዛሬ የተለቀቀው ምስጢራዊ ደብዳቤ በአዲስ አበባን የማስፋፋት ስም በሕወሓት መንግስት የሚደረገውን ጥልቅ ሴራ ያጋለጠ ነው:: ምስጢራዊው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ‘ሆዜ ሂማንተሪያን ፋውንዴሽን” የተሰኘ ድርጅት የመለስ ዜናዊን መንደር በሰበታ አዋስ ወረዳ ያቀረበውን ጥያቄ ወረዳው መቀበሉን ያረጋገጠበት ነው:: ደብዳቤው እንደሚለው ለመለስ ዜናዊ መንደር ግንባታ ለሆዜ ፋውንዴሽን አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሄክታር ወረዳው እንዲያዘጋጅ መጠየቁን እና ይህንንም ማዘጋጀቱን ነው::

እንግዲህ አዲስ አበባን እናስፋፋለን የሚሉት ምስኪን ገበሬዎቹን አፈናቅሎ ምን ለመፍጠር እንደሆነ ከዚህ በታች ከቀረበው ደብዳቤ ይረዱና አስተያይትዎን ያስቀምጡ::


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48562


Tuesday, November 24, 2015

“በአዛዙ የአፈና መዋቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነትና የእኩልነት ትግል አይቀለበስም” – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ


ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱና በሌሎች ራሱ ባወጣቸው ህጎች በርካታ መብቶችን ለይስሙላ ቢደነግግብ ቅሉ፤ በተግባር ግን እነዚህን መብቶች ሆነ ብሎ ባደራጀው የአፈና መዋቅሩ እየደፈቃቸው ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን አገዛዙ የመደራጀት መብትን በወረቀት ቢያሰፍርም ‹‹እግር እስኪያወጡ እንጠብቃለን፤ እግር ሲያወጡ ግን እንቆርጣለን›› በሚል መርህ ፓርቲዎችን በዚሁ የአፈና መዋቅሩ በገሃድ እያፈረሰ ቀጥሏል፡፡ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ፈቅጃለሁ ቢልም ጋዜጠኞችን በማሰር፣ በማሳደድና ሚዲያዎችን በመዝጋት አማራጭ ሀሳብ እንዳይራመድ አድርጓል፡፡ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ወረቀት ላይ ቢደነግግም በአስተዳደራዊ መዋቅሩ መሰረት ክርችም አድርጎ ዘግቶታል፡፡ የዜጎችን የመዘዋወር መብት ቢደነግግም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፓስፖርት በመንጠቅ ጉዟቸውን በማተጓጎል ላይ ይገኛል፡፡ የመንግስት አሰራር ግልፅና ተጠያቂነት አለበት ተብሎ ተደንግጓል፤ ነገር ግን በየ መስርያ ቤቱ ያለ እጅ-መንሻ ዜጎች አገልግሎት ማግኘት አይቻልም፡፡ ይህ ሁሉ አፈና ሆነ ተብሎ ታስቦበት፣ የአገዛዙን ስልጣን ለማራዘም የሚደረግ መዋቅራዊ ጫና መሆኑን ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡

ዛሬ በሀገራችን ከፍተኛ ርሃብ፣ ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስራ አጥነት፤ ስደት እና ሌሎችም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶች በሰፊው ተንሰራፍተው ይገኛሉ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ወቅታዊ ጉዳዮች ከህዝብ ጋር ተወያይቶ አቋም ለመውሰድና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለመሰንዘር ህዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የእውቅና ደብዳቤ ለማስገባት በተደጋጋሚ ጥረት ያደረግን ቢሆንም የአፈና መዋቅሩ የእውቅና ደብዳቤውን መቀበል ባለ መፈለጉ ለ5 ጊዜ ተጉላልተን በ6ኛው በሪኮመንዴ(በፖስታ) ለመላክ ተገደናል፡፡


የእውቅና ደብዳቤው በሪኮመንዴ የደረሰው አስተዳደሩ ህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም ላይ ሆኖ ‹‹ህዳር 18/2008 ዓ.ም አልፏል›› በሚል ለተጨማሪ ጊዜ ደብዳቤውን ሳያስተናግድ ቀርቷል፡፡ ህዳር 18 ያላለፈ መሆኑን ካስረዳን በኋላ ለሶስት ቀናት በተደጋጋሚ ብንመላለስም ‹‹ከደህንነትና ፖሊስ ጋር ካልተመካከርኩ እውቅና አልሰጥም›› ሲል እምቢታውን ገልጾአል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአባላትና ደጋፊዎቻችን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ልናደርገው የነበረው ውይይት ሊደናቀፍ ችሏል፡፡


ከዓለም የነጻነት የትግል ታሪክ እንደምንገነዘበው በአገዛዝ አፈና የተገታ የህዝብ ጥያቄ ኖሮ አያውቅም፡፡ አፈናው የነጻነትን ጊዜ ቢያዘገይ እንጅ ፈጽሞ ሊያስቀርም አይችልም፡፡ ስለሆነም ጭቆናው ወደ ነፃነት የሚያስኬደውን ጉዞ እልህ አስጨራሽ ከማድረግ በቀር ዘላቂነት ኖሯቸው የነጻነት ጥያቄውን ፈጽሞ ማዳፈን እንደማይችሉ አገዛዙ ሊረዳ ይገባል፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ለማይቀረው የነፃነት ትግል ቆርጦ እንዲነሳና ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ህዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም
አዲስ አበባ


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48484

Monday, November 16, 2015

መንግስት ረሃቡን ለመደበቅ ከፍተኛ መመሪያ አስተላለፈ ጋዜጠኞችና የረድኤት ድርጅቶች ረሃቡ ወደ ተከሰተበት ቦታ እንዳይሄዱ ተከለከለ

ሕወሓት የሚመራው የኢትዮጵያ ገዢ በኢትዮጵያ የተከሰተውን እና 15 ሚሊዮን ሕዝብን ለረሃብ ያጋለጠውን አደጋ ለመሸፋፈን ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋዳ ሥራዎችን ከመስራት በተጨማሪ መረጃዎች እንዳይወጡ እስከማፈን ደረጃ መድረሱን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል::

የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት; የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስተርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በአንድ ላይ ተቀናጅተው እየሰሩት የሚገኘው የመረጃዎችን የማፈን ሥራ ታች ድረስ ወርዶ እስከ ፓርቲ አባላትና “ደጋፊ” የተባሉ ሰዎች ጭምር እንዲሰራበት እየተደረገ ነው:: “ረሃቡን አስታከው ለውጭ መንግስታት ሊያሳጡን የሚሞክሩትን መታገል አለብን” በሚል እነዚህ ሶስት መስሪያ ቤቶች ባወጡት መመሪያ መሠረት የውጭ ጋዜጠኞችም ሆነ የረድኤት ድርጅቶች ረሃቡ ወዳለበት ቦታ ሄደው ፎቶ እንዳያነሱ; ቭዲዮ እንዳይቀርጹ; ማንኛውንም ቃለምልልስ እንዳያደረጉ ተከልክሏል:: በተለይ ቢቢሲ በቅርቡ በኢትዮጵያ በአንድ ትንሽ ክልል ስፍራ ብቻ በቀን 2 ህፃናት በረሃቡ እየሞቱ እንደሆነ መዘገቡን ተከትሎ አለም አቀፍ ሚዲያዎች እና የአፍቃሬ ሕወሓት መንግስት ደጋፊ የሆኑ ሃገራት ሳይቀር ከዚህ ቀደም “ልማታዊ መንግስት” እያሉ ሲያሞካሹ የነበረውን አፋቸውን በመጠራረግ ረሃቡን እና መንግስት የሚከተለውን ፖሊሲ እንደገና እየመረመሩ እንደሚገኙ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ይናገራሉ::

እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ በቅርቡ በቢቢሲ የቀረበችውን እናት የአማራ ክልል ጋዜጠኞች አስገድደው ቃለምልልስ ያደረጓት ሲሆን በቅርቡም በመንግስት ሚዲያዎች ላይ “አልራበኝም” ዓይነት ንግግር በማስደረግ የቢቢሲን ዘገባ ለማስተባበል ሥራ እየተሰራ ይገኛል::

ከሥስቱ መስሪያ ቤቶች በተላለፈው መመሪያ መሠረት የመንግስት ሃላፊዎች ከላይ እስከታች በየሶሻል ሚዲያው በመውጣት ችግሩን መንግስት ተቆጣጥሮታል እያሉ መጻፍ እና መናገር አለባቸው:: “ተቃዋሚዎች የመንግስታችንን መልካም ገጽታ ለማጠልሸት ሆን ብለው የሚያደርጉት ሤራ ነው” እያሉም በውጭ ያሉ ኤምባሲዎችና ተላላኪዎች እንዲያነገሩ ትዕዛዝ ከመተላለፉም በላይ መንግስትን ይደግፋሉ ለተባሉ የውጭ ጋዜጠኞች ወደ ሃገር ቤት እንዲገቡና መልካሙን ነገር ብቻ እንዲዘግቡ ኢምባሲዎች መሥራት እንዳለባቸውም የወጣው መመሪያ ሲያመለክት ስለመንግስት መጥፎ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ የተባሉ ጋዜጠኞች ግን ረሃቡ ወዳለበት ቦታ እንዳይሄዱ/ ምስል መቅረጽና ቃለምልልስ ማድረግ እንዳይችሉ የኮምዩኒኬሽን መስሪያ ቤት ፈቃድ እንዳይሰጥ ት ዕዛዝ ወርዷል::


በስልጣን ላይ ያለው መንግስት 15 ሚሊዮን ሕዝብ በመራቡ የተነሳ በወዳጅ ሃገሮቹ ሳይቀር በመጥፎ አይን እየታየመምጣቱ በስርዓቱ ውስጥ “ገጽታችን ተበላሸ” በሚል ራሱን የቻለ ሽብር ፈጥሯል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48271

Thursday, November 12, 2015

ፕሮፓጋንዳው ሰብዓዊነት ይኑረው !!! ሰው እየሞተ ነው !! ቁጥሩን ቤቱ ይቁጠረው !!!

በሀገራችን ያለው ድርቅ ክብደት ከ1977ጋር የሚመሳሰል እንደሆነ የመንግሰት ሹም ከሸገር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ምልልስ አረጋግጠዋል፡፡ ልዩነቱ ግን አሁን መንግሰት ይህን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አለን የሚልው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አቅም ግን መሬት ላይ ወርዶ ስናየ ወኔ ብቻ ይመስላል፡፡ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ የፈረንጆቹን ደጅ እንዳይጠኑ የሚያደርጋቸው አይደለም፡፡

“ደርግ” በ1977 የነበረፈውን ድርቅ ለዓለም ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን የዚያን ጊዜ በነበረው ቀዝቃዛ ጦርነት መነሻ በሁለቱ ጎራ በሚደረገው ፍልሚያ ግዳይ የሚጣልብት ወቅት ነበር፡፡ ደርግ ለዓለም ህብረተሰብ ጥሪ ባቀረበበት ወቅት የሶሻሊስቱ ተከታይ በመሆኑ ይህ ጎራ ይህን ድጋፍ የሚያደርግበት አቅም የሌለው ሲሆን ይህን ለማድረግ አቅም ያላቸው ምዕራባዊያን ግን ውጤቱን በደንብ ሳናየው ድጋፍ ላለመስጠት መቁረጣቸው ለችግሩ ክብደት አንዱ እንደ ነበር ለመረዳት ሊቅ መሆን አያስፈልግም፡፡ 

በተጨማሪ ለ1997 ድርቅ ተገቢው ምላሽ በምዕራባዊያን እንዳይሰጥ በወቅቱ በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩት በተለይ ህወሃት እና ሻቢያ የተጫወቱት ሚና ቀላል የማይባል ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ሆነን ስናየው ሰብዓዊነትን ለፖለቲካ ጥቅም እንዳዋሉት ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡


አሁን ባለው ሁኔታ የኢህአዴግ መንግሰት ከምዕራባዊያኑ ጋር ያለው ቅርበት ከደርግ እንደሚሻል ስለሚታመን በተጨማሪ ህውሃትና ሻቢያ በዛን ጊዜ የሰሩትን ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለመስራት የሚችል ታጣቂ ሀይል ባለመኖሩ ችግሩን ለመቋቋም በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ መንግሰት አቅሙ የከብቶቹን ህይወት ለመታደግ ለምን አልተጠቀመበትም? ካልቻለ ደግሞ ምዕራባዊያኑ ድጋፍ ለማድረግ ከፈለጉ አሁንስ ቢሆን ከብቶቹ ሳይሞቱ እንዲደርሱልን ለምን አልተደረገም? የሚለው ጥያቄ ለማንሳት አርብቶ አድር መሆን አይጠበቅብንም፡፡

ሁሉም የሚረዳው አንድ ሀገር በድርቅ መቼም ቢሆን ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ይህ በዓለም ላይ ተደጋጋሚ ክስተት እንደሆነ ማንም ያውቃል፡፡ ድርቅ ሲኖር ግን ይህን ድርቅ የሌላ ሶሰተኛ ሀገር ድጋፍ ሳይጠየቅ ለመፍታት አቅም መፍጠር መቻል ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ባላት ስነ ምህዳር ከዚህ የተሻለ ማድረግ እና ለሌሎች መትረፍ ይገባት ነበር፡፡ ይህ ደግሞ አሰማት ሳይሆን ሊተገበር የሚችል የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ ነው ብሎ የሚያምን መንግሰት ያስፈልጋል፡፡ ኤክስፖርት የሚደረግ ታንክ ሰራን በፍፁም በዚህ ወቅት ሊያኮራን የሚችል ስ አይደለም፡፡ አሁን የምንረዳው መንግሰት ችግሩን ሪፖርት አድርጊያለሁ ማለትን እንደመውጫ ቀዳዳ እየተጠቀመበት መሆኑን ነው፡፡

አሁን በመሬት ላይ ያለው ሀቅ በምግብ እና ውሃ እጥረት ከብቶች በብዛት እየሞቱ ሲሆን፤ መቼም እንደ እንሰሳቱ በብዛት ሰው እየሞተ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን አሁን በተፈጠረው ሁኔታ ከምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ ቀደም ሲል የነበረባቸው የጤና ችግር አግርሽቶም ይሁን አዲስ ጤና መቃወስ ተፈጥሮ ህፃናት ብቻ ሳይሆን አረጋዊያንም ሆኑ ባለጡንቻው ጎልማሳ የሚሞቱበት ሁኔታ እንዳለ ግን መካድ አይቻልም፡፡ ከዚህ ስንነሳ በምግብ እጥረት ምክንያት ሞት የለም ብሎ ፈሊጥ፤ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሁለት ህፃናት በቀን ይሞታሉ ያለው ለሌላ ዓላማ እና የሀገር ገፅታ ለማበላሸት ነው የተባለውን የመንግሰት ሹም መግለጫ ስንሰማ ከማፈር ውጭ ምን ልንል እንችላለን፡፡ የመንግሰት ሹሞቸ ፕሮፓጋንዳውን ጋብ አድርገው ሰብዓዊነት በመላበስ እየሞተ ያለውን ሰው መታደግ የግድ ነው፡፡ ስንት ሰው ሞተ ቤቱ ይቁጠረው፡፡

አንድም ሰው በድርቅ አልሞተም የሚል መግለጫ የሰጡትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ከላይ እንደገለፅኩት ቀደም ሲል በአካባቢዎቹ የኖረው ችግር ላይ ሲታከል ሰዎች እንደሚሞቱ መገንዘብ አቅቷቸው ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የተደረገ መሆኑን ማውቅ ግድ ይለናል፡፡ በዚህ ፕሮፓጋንዳ ማፈራችን እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡ የምናፍረው ደግሞ ከ30 ዓመት በኋላ ድርቅን ለመቋቋም የሚችል ህብረተሰብ ሊገነባ የሚችል ስርዓት መመስረት ያለመቻላችን ነው፡፡ ይህን መንግሰት ዛሬም ስህተቱን “በኤሊኖ” ክስተት አሳቦ በስልጣን እንዲቆይ የፈቀድነው እኛው ነን፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን በምንም መመዘኛ አምስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በፈለገ የተራዘመ የተፈጥሮ ችግር ጊዜ ቢሆን እንኳን ምግብ ለመለመን የማትችል ሀገር ለማድረግ የሚያስችል ፖሊሲና ሰትራቴጂ የሌለው መንግሰት እንዳይኖር ማድረግ ካልቻልን ምርጫው የራሳቸን ነው፡፡ ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ እኛ ከላፈቀድን መሬትን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ፤ ሴፍቲኔት በሚባል የመንግሰት ድጎማ ስር ህዝቡን በተራዘመ ሰንፍና እንዲኖር በማድረግ በአምስት ዓመት በሚመጣ የይስሙላ ምርጫ ካርድ አግኝቶ አገዛዙን ለማራዘም የሚፈልግ መንግሰት ይህን ዓይነት ሰርዓት ሊዘረጋ አይችልም፡፡ እንዲህ ሲያደርገን እንቢ ብለን መከላከል ምርጫው የእራሳችን ይሆናል ማለት ነው፡፡

በተለጠጠ ዕቅድ ተሰፋ ውስጥ (የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ልብ ይሏል) የከተማ ነዋሪውን ሸምቶ ለማብላት የውጭ ሀገር የሰንዴ ገበያን አማራጭ ያደረገ መንግሰት፤ በሀገር ውስጥ በእርሻ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ዘመናዊ ገበሬዎች እርሻ መሰሪያና ሌሎች ግብዓቶች ድጎማ አድርግ ሲባል ነፃ ኢኮኖሚ ነው ይለናል፡፡ አንድ በዘመናዊ እርሻ ለመሰማራት የሚፈልጉ ዘመናዊ ገበሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰበሰቡት ስብሰባ ላይ ከጎኔ ቁጭ ብለው የነገሩኝ አስደማሚ ነገር “መንግሰት ሰንዴ ለመግዛት በጨረታ የሚያባክነው ጊዜ እና ገንዘብ ለእኛ ድጋፍ ቢያደርግ ለጨረታ ከሚባክነው ጊዜ ባነሰ በሀገር ውስጥ ሰንዴ ለማምረት እንችላለን” የሚል ነው፡፡ ይህን ሀቅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ለግብርና ሚኒሰትሩ የኪራይ ስብሰቢዎች ወሬ ነው የሚሆነው፡፡ ግብርና መር ስትራቴጂና ፖሊሲ ብለው ምግብ በሀገር ውስጥ ማሟላት ሳይችሉ ለዘላለም ሊገዙን ሲፈልጉ እሺ ብለን አለን፡፡



ለማነኛው ኢትዮጵያ ሀገራችንን ምድሯ “በኤሊኖ” ክስተት ይሁን በሌላ “ድርቅ” ጎብኝቷታል፡፡ ይህ ድርቅ አድጎ ደግሞ ዜጎችን ህይወት ቀሰ በቀስ እየወሰደ ነው፡፡ ይህን “ችጋር” ለመቋቋም ዜጎች በጋራ መነሳት ይኖርብናል፡፡ ፈረንጆቹ ይህ ውጤት እንዲቀለበስ ከልብ ከፈለጉ አንድም ሰው ሳይሞት ሊደርሱ የሚያስችል ሰርዓት አላቸው ነገር ግን የሰጡት ድጋፍ ህይወት አድን መሆኑ እንዲታወቅ ችግሩ እስኪሰማን ብዙ ሀይወት መጥፋቱ በሚዲያ ታይቶ ቅሰቀሳ እስኪደረግ ሊዘገዩ ይችላሉ፡፡ በዚህ መሃል ምትክ የሌለው የሰው ልጅ ህይወት ያልፋል፡፡ ይህ እንዳይሆን መንግሰት አሁን ከጀመረው ተራ ፕሮፓጋንዳ ወጥቶ ወደ ቀጥተኛ ህዝቡን ያሳተፈ ምላሽ እንዲሰጥ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48191

Saturday, November 7, 2015

ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ የምትወዳትን ሀገሯን ጥላ አሜሪካ ገባች


በቅርቡ ከሕወሓት መንግስት እስር ቤት የተለቀቀችው ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ዛሬ አሜሪካ ገባች::
ዛሬ ኖቬምበር 7, 2015 ዋሽንግተን ዲሲ ዱልስ ኤርፖርት የደረሰችው ርዕዮት በዲሲና አካባቢዋ በሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደማቅ የሆነ የ እንኳን ደህና መጣሽ አቀባበል አድርገውላታል::

በሕወሓት መንግስት እስር ቤት ውስጥ ስቃይ ሲደርስባት የቆየችው ጠንካራ ሴት በበቀል ተነሳስተው ህክምና ሁሉ ሳይቀር ከልክለዋት ሲበቀሏት እንደነበር በተደጋጋሚ ሲዘገብ ቆይቷል:: ዓለም አቀፍ ተቋማት በታሰረችበት ጊዜ ሲሸልሟት የቆየችው ር ዕዮት ለበርካታ ሴቶች ተምሳሌት በመሆን ትጠቀሳለች::


ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ምናልባትም በሰሜን አሜሪካ ቆይታዋ ትምህርቷን ልትቀጥል እንደምትችል ይገመታል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48066

Friday, November 6, 2015

የሕወሓት መንግስት በመደለያዎች እና በግዳጅ ጭምር የመከላከያ ሠራዊት አባላትን በየሥፍራው እየመለመለ መሆኑ ተሰማ

የሕወሓት መንግስት ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ልኮ ሬሳቸውን በአደባባይ ሲያስጎትት

የህወሓት አገዛዝ ልዩ ልዩ ማማለያዎችንና መደለያዎችን በመጠቀም በግዳጅም ጭምር ወጣቶችን ለእግረኛ ተዋጊ ጦር ሰራዊትነት ለመመልመል በመላ አገሪቱ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ ለተንሰራፋው የህዝቡ የከፋ ድህነትና ስራ አጥነት መንስኤ የሆነው የህወሓት አምባገነናዊ አገዛዝ ድህነታቸውን ተጠቅሞ ዕልፍ አዕላፍ ወጣቶችን በአገር መከላከያ ስም በመመልመል በየጠረፉ በሚደረጉ የሽምቅ ውጊያዎች ውስጥ በመጨመር ያለቀባሪ በየበረሃው ወዳድቀው እንዲቀሩ በማድረግ በደምና አጥንታቸው የስልጣን ዘመኑን ለመቀጠል ሲፍጨረጨር መቆየቱ በግልፅ የሚታወቅ እውነታ ነው፡፡


በስልጣንና የንዋይ ፍቅር የነሆለለው ዘረኛው የህወሓት ቡድን ምስኪን ኢትዮጵያዊ እናቶች ኩበትና እንጨት ለቅመው ሽጠው፣ ለባለፀጋ ተገርደው በችጋር አለንጋ እየተገረፉ ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን ወደ ሶማሊያ ምድር በማስገባት በጥይት እያስጨፈጨፈ ሬሳቸው ሳይቀር በሞቃዲሹና በሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ ልክ እንደውሻ በድን በገመድ ታስሮ እንዲጎተት እያደረገ በምስኪኖች ሞት እሱ ረብጣ ዶላር እያፈሰ ይገኛል፡፡

       በሶማሊያ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች

የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ ጦር መልምሎ የማሰልጠን ህልሙን ዕውን ለማድረግ ወጣቱን ያማልላሉ ብሎ ያወጣቸው ሦስቱ የማስመሰያ ቅጥር የሙያ መስኮች ለመከላከያ ኢንጅነርኢንግ ኮሌጅ ትምህርት፣ ለአየር ኃይል አብራሪነት እና ለልዩ ኮማንዶና አየር ወለድ የሚሉ ናቸው፡፡

በመሆኑም ለመከላከያ ኢንጅነርኢንግ ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርት በሚል ሰበብ ቴክኒክና ሞያ ት/ቤት ተመርቀው ስራ ማግኘት ያልቻሉትን በእግረኛ ተዋጊ ሰራዊትነት ለመመልመል ከፍተኛ ጉትጎታ ላይ ነው፡፡ 


ለአየር ኃይል አብራሪነት ደግሞ ከከዚህ ቀደሙ የመመልመያ መስፈርት በተለየ ሁኔታ በፊዚክስ፣ ሂሳብ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ “C” በቂ ነው የሚል አዲስ የቅጥር መስፈርት አውጥቷል፡፡ 


በየመንደሩ የተሰገሰጉት መልማይ ዲስኩራም ካድሬዎችም “ዳርፉር ሄዳችሁ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ብር ዝቃችሁ ትመለሳላችሁ…” በማለት ወጣቱን የእርጎ ባህር እያሳዩ ወላጆችን ደግሞ “ልጆቻችሁ በመንግስት ተምረው ኢንጅነርና ፓይለት እንዲሆኑላችሁ እና ከችጋር እንዲያወጧችሁ መምከርና በገሰፅ አለባችሁ…” እያሉ የድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ደም በከንቱ እንደ ጅረት መፍሰሱን እንዲቀጥልና በአገራችን ላይ የተጫነው የባርነት አገዛዝ ዘመን እንዲራዘም ቀን ከሌሊት እየተጉ ነው፡፡


ህወሓት ከዚህ ቀደምም በ1980ዎቹ ዓ.ም መጨረሻ በመላ አገሪቱ የሚገኙ 12ኛ ክፍልን አጠናቀው ዩኒቨርሲቲ መግባት ያልቻሉ ወጣቶችን ለኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርት ስልጠና በሚል አታሎ በገፍ መልምሎ በሙያ ዘርፉ ከተመረቁ በኋላ የሚያገለግሉት “በአገር መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ እንደሆነና በመጀመሪያ ወታደራዊ ስልጠና መውሰድ ግዴታቸው እንደሆነ አሳምኖ ወደየ የእግረኛ ተዋጊ ማሰልጠኛ ማዕከሎች ካስገባና አሰልጥኖ ካወጣቸው በኋላ ቆይቶ በፈነዳው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ማግዶ ሁሉንም አስጨርሷቸዋል፡፡ 


የሀወሓት አገዛዝ ከማማለያው ጎን ለጎን የድሃው ህዝብ ልጅ የሆኑ ወጣቶችን አስገድዶ የመመልመል ሙከራም እያደረገ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ “በደቡብ ክልል” በጎፋ ሳውላና በቁጫ የሚኖር እያንዳንዱ ወላጅ ቢያንስ አንድ አንድ ልጅ እንዲያዋጣ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ 



ሆኖም የህወሓት አገዛዝ የቱንም ያክል ማማለያና መደለያ ቢያቀርብ እንዲሁም በጉልበት ቢያስገድድ እስካሁን ድረስ ተታሎ አንድም የተመዘገበ ወጣት እንደሌለ እንዴውም በተቃራኒው ወጣቱ የሚደርስበት ጭቆና አንገሽግሾት እየተደራጀ ጫካ በመግባት ላይ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48032

Thursday, October 29, 2015

በአማራው ስም የሕወሓት ተላላኪ የሆኑ ሆዳም የብአዴን አመራሮች በአማሮች ላይ የሠሯቸው 14 እርጉም ግፎች

ተላላኪው ም/ል ጠቅላይ ሚ/ር እና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ም/ል ደመቀ መኮንን; ሕወሓት የሚሳደበው አንሶ የአማራውን ሕዝብ                ከተሳደቡት አቶ አለምነህ መኮንንና ከተላላኪ የአማራ የጦር መኮንኖች ጋር::

በትናንትናው እለት የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቃለምልልስ ሲያደርጉ ተከታተልሁ:: ርእሰ መስተዳድሩ ባንድ ወቅት “አማራ የራሱን የጦር ጀኔራል መርጦ ህዝቡን እያስታጠቀ ነው” በሚል በትግራዩ ገዥ አቶ አባይ ወልዱ ለቀረበባቸው ክስ “አዎ ለክልሌ ጀኔራል ነኝ” ብለው መልስ ሰጡ የሚል ጽሁፍ አንብቤ ስለነበር ልቤ በኩራት እብጥ ብሎ ክብር ሰጥቻቸው ነበር:: በአማራው ላይ የሚደርሰው ዘርፈ ብዙ ጥቃት ያበቃ ዘንድ በብአዴን ውስጥ ያሉት አማሮች በቁጭት “በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በቃ!”ብለው ተነስተዋል ማለት ነው ብየ ገምቸ ነበር:: ምንም ቢሆን ልጅ የወላጆቹን ባህሪ መውረሱ አይቀርም: ይኸው የብአዴን አማሮች ያባቶቻቸውን ወኔ ተላበሱ ብየ በደስታ የምሆነውን አጥቸ ነበር:: ይሁንና ሰውየው በሰሞኑ ያደረጉት ቃለመጠይቅ ላይ ብአዴን የአማራ ህዝብ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ከሌሎቹ ወገኖቹ ጋር በእኩልነት እንዲኖር ከትምክህተኞችና ከጠባቦች ጋር ብዙ ትግል እንዳደረገና ውጤት እንዳስገኘ ሲገልጹ ሰማሁና ከልብ አዘንሁ:: አቶ ገዱ እናንተ የምታወሩትን ወይስ ምድር ላይ የሚታየውን እንመን? እንደእኔ እምነት የአማራ ህዝብ መቸም ቢሆን ያላገጠመውን ፈተና በናንተ ጊዜ እየተፈተነ ነው:: አማራ ተኮር የሆነ ጭፍጨፋ የተፈጸመውና ህዝባችን አጎንብሶ እንዲኖር የተደረገው በናንተ ጊዜ ነው:: ይህ ሁሉ መከራ በአማራው ላይ ሲፈጸም “ለምን እንዲህ ይሆናል” ብላችሁ ለመሟገት የሚያስችል እንጥፍጣፊ ወኔ የላችሁም:: እንዲያውም ድርጅታችሁ በተላላኪነት ተግባር ተሰማርቶ ግፍ አንገፈገፈን ብለው ተቃውሞ ያሰሙትን ወገኖች አሳዶ በመምታት የወያኔ አፋኝ ስኳድ ሆኖ እየሰራ ያለ ድርጅት እንደሆነ ህዝባችን አሳምሮ ያውቃል:: “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ” ነውና እስቲ በኢህአዴግ ጊዜ በአማሮች ላይ የተፈጸመውን ግፍና የናንተን አቋም በጥቂቱ እናስታውሳችሁ:-

1. በደርግ የመጨረሻ ዘመን አሶሳ ላይ አማሮች ብቻ ተለይተው ሲታረዱና በእሳት ሲቃጠሉ ድርጅታችሁ አንድም ተቃውሞ አላሰማም::

2. የናንተን ድርጅት ያካተተው ኢህአዴግ መላ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ አማሮች እየተለቀሙ ከነነፍሳቸው በገደል ሲጣሉ:በገጀራ ሲታረዱ: በእሳት ሲቃጠሉ ድርጅታችሁ የወገንተኝነት ስሜት ተሰምቶት “ለምን ምንም ያላጠፉ ሰዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ እንዲህ አይነት ግፍ ይፈጸምባቸዋል?” ብሎ በመቆርቆር እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ መብት ለማስከበር ሲንቀሳቀስ አልታየም:: እንዲያውም ያሁኑ ፓስተር የያኔው የድርጅታችሁ ሊቀመንበር ታምራት ላይኔ በጅጅጋ ተገኝቶ በሶማሊያ ክልል በሚኖሩት አማሮች ላይ የሶማሌ መንግስትና ህዝብ እርምጃ እንዲወስዱባቸው በመቀስቀስ ድርጅታችሁ ጸረ አማራ መሆኑን እናንተም የጠላት ሀይል አንድ ክንፍ መሆናችሁን አስመስክሯል::

3. ከንጉስ ኃይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ ለብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር: ለሰው ልጅ እኩልነትና ነጻነት እልህ አስጨራሽ ትግል ሲያደርጉ ከነበሩትና መስዋእትነት ክከፈሉት ሰወች መሀል የአማሮች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም:: ይሁንና በነገስታቱና በደርግ ጊዜ በኤርትራ ላይ ተፈጽሟል ለተባለው ወንጀል አማሮችን ቀጥተኛ ተጠያቂ በማድረግ አስመራ ድረስ ሄደው “ማሩን” ብለው ከሻእቢያ እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ እንዲለምኑ ሲደረግ “ለምን እንዲህ ይሆናል? ባለፉት ስርአቶች በገዥነት የተቀመጡ አማሮች ብቻ አልነበሩም: ታዲያ እንዴት አማራው ብቻ ይቅርታ ጠይቅ ይባላል?” ብላችሁ ለህዝባችሁ መብትና ክብር ያሰማችሁት ተቃውሞ አልነበረም::

4. አማራ ከየክልሉ ሀብት ንብረቱን ጥሎ የሞተው ሞቶ ማምለጥ የቻለው እግሩ ወዳመራው ሲሰደድ “አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ ሀገር ውስጥ የሚኖር አማራ ካላግባብ ሀብት ንብረቱን ሊነጠቅ: ህይወቱን ሊያጣ አይገባም” ብላችሁ ስትከራከሩ አልተሰማችሁም:: ይባስ ብሎ የድርጅታችሁ የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሰ ከኦሮሚያ የተባረሩትን አማሮች በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ የተባረሩት ሰዎች አጭበርባሪወችና ዘራፊወች ናቸው ነበር ያሉት:: የአማራ ሰዎች እንደዚያ በጅምላ ከየክልሎች አላግባብ እንዲፈናቀሉ ሲደረግ በአማራ ክልል ግን የሌሎች ክልሎች ተወላጆች በድርጅታችሁ ታቅፈውና ሹመኛ ሆነው በአማሮች ላይ እየፈረዱና ሀብቱን እየመዘበሩ በማናለብኝነት ቀጥለዋል:: ለዚህስ የምትሰጡት መልስ ምንድን ነው? የሚገርመው ደግሞ የአማራን ህዝብ ጥንብ እርኩሱን አውጥቶ ያዋረደው የክልሉ ተወላጅ አቶ አለምነው መኮንንን ህዝብን ያህል ነገር እንዴት እንዲህ ታረክሳለህ ተብሎ ሊጠየቅ ሲገባ እርስዎን ጨምሮ ሌሎች የድርጅቱ አባላት ባንድ ላይ ሰውየው የህዝብ ተቆርቋሪ እንደሆነና የተወራበት ሁሉ የጠላት ወሬ እንደሆነ ልታሳምኑን ስትደክሙ ሰምተን እጅግ አዝነናል:: በህዝብ ላይ ያን ያልተገረዘ የባለጌ መላሱን ያስረዘመውን ስድ አደግ ሰው ልትቀጡ ወይም ልትገስጹ ሲገባ ከህዝብ በላይ አድርጋችሁ በማየት የተገላቢጦሽ ለህዝብ የተቆረቆሩትን ሰዎች ወረፋችሁ::

5. በአማራ ክልል የሚኖሩ ብሄረሰቦች በዞን ተደራጅተው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ሲደረግ አማሮች በብዛት በሚገኙባቸው ሌሎች ክልሎች ግን ይህ እድል አልተሰጠም: ሌላው ቀርቶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እንኳ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ዕድሉን አላገኙም:: ታዲያ እናንተ የታዘዛችሁትን ከመፈጸም አልፋችሁ እንዲህ የተዛነፈ አሰራር ሲታይ ምን ያደረጋችሁት ነገር አለ?

6. የአዊ ዞን ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአማረኛ እንዲማሩ ተስማምተው ያሳለፉትን ውሳኔ ከበላይ የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የብሄሩን መብት ገፍፋችሁ አዊወች በአዊኛ እንዲማሩ አደረጋችሁ: ይህን ውሳኔውን ያሳለፉትን ሰዎችም “የመንግስትን ፖሊሲ ተቃርነው የቆሙ” በማለት ፈርጃችሁ ከስራ እስከማባረር ድረስ የደረሰ ቅጣት ቀጣችኋቸው::


7. ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬት ላይ የህዝብ ቁጣ ሲባባስ “የምንሰጠው መሬት የለም: ከሌላ የወሰድነውም የለም:: የራሳችን የሆነውን አንሰጥም የሌላውንም አንፈልግም” ብለው ነበር:: ይሁንና በተጨባጭ ከመተማና ካካባቢው በሱዳን ወታደሮች በሀይል እንደተፈናቀሉ ተፈናቃዮቹ አዲሳበባ ድረስ በአካል ተገኝተው ለፓርላማው አቤቱታ ማቅረባቸው በተጨማሪም ለአሜሪካው የአማረኛ ሬዲዮ ስርጭት (VOA) ቃለምልልስ መስጠታቸው አይዘነጋም:: አቶ መለስ ይህንን አስመልክቶ ከፓርላማው ለቀረባቸው ጥያቄ ሲመልሱ “አንድም ሰው አልተፈናቀለም” ብለው ሙልጭ አድርገው 
ዋሽተው ነበር:: እርስወም ድንበሩን በተመለከተ ለቀረበልወት ጥያቄ ከአቶ መለስ የተለየ መልስ አይደለም የሰጡት::

8. ከ10 አመት በፊት በተደረገው የህዝብ ቆጠራ ከሌሎች ክልሎች በተለየ መልኩ በአዲስአበባና በአማራ ክልል ብቻ ፕሮጀክት ከተደረገው ቁጥር በእጅጉ ማነሱ ይታወቃል:: በአዲስ አበባ ከሚኖረው ህዝብ መሀል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አማራው መሆኑን ያጡታል ብየ አላስብም:: ታዲያ ይህ የአማሮች በ2.5 ሚሊዮን ቁጥር መቀነስ መላው ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን በንዴት ሲያርገፈገፋቸው ብአዴን ግን አንድም ሰው እንዳልጎደለበት ሆኖ ማስተባበያ በአቶ አዲሱ ለገሰ በኩል ሲሰጥ ነበር::
9. በአማራ ክልል ላይ ብቻ ያተኮረ በቤተሰብ ዕቅድ ስም እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወያኔ ተቀርጾ በናንተ የሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ነው:: የቤተሰብ ብዛትን መመጠን በሚል ምክንያት በአማራ ክልል ህዝብ ላይ ብቻ ያተኮረ የሴቶችን ማህጸን መቋጠር: የወንዶችን የዘር ፍሬ ማኮላሸት የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው:: አሁን ደግሞ ስልቱ ተቀይሮ የአማራ ሴቶችን የበሽታ መከላከያ ክትባት በማስመሰል መሀን የሚያደርግ መድሀኒት እንዲከተቡ ሲደረግ ብአዴን የወያኔን አላማ ለማስፈጸም ቀዳሚ ሆኖ የተሰለፈ ቡድን ነው::

10. አማሮችን ትጥቅ አስፈቱ የሚል መመሪያ በወረደላችሁ ጊዜ ምን ያህል ግፍ እንደፈጸማችሁ ትዝ ብሏችሁ ያውቃል? ወያኔ ይህን መመሪያ ሲያስተላልፍ ምክንያት እየፈጠረ አማሮችን ለመበቀል ካለው ፍላጎት በመነሳት ነበር:: ይህን ለማድረግ ደግሞ በራሱ ሰዎች ሳይሆን ህዝቡን እንወክለዋለን በምትሉት በናንተ ቢፈጸም ከተጠያቂነት ነጻ እንደሚሆን አሰበና “ህገወጥ መሳሪያ ታጣቂወችን መሳሪያቸውን እንዲያስገቡ አድርጉ” ሲል ትዕዛዝ ሰጣችሁ:: ይህን የበላይ ትእዛዝ ለማስፈጸም ነበር መሳሪያ ያልነበረውን ሳይቀር አስራችሁ የገረፋችሁት ብሎም የገደላችሁት:: የናንተ ህዝባዊነት መገለጫ የሰውን ክብር ገፋችሁ አባቶችን ሳይቀር ማሰቃየት ነው?

11. ለመሆኑ ቁልፍ በተባሉት የወታደራዊና የሲቭል ተቋማት ውስጥ የአማሮች ድርሻ ምን ያህል ነው? ይህስ አሳስቧችሁ ያውቃል? ወያኔ ገንዘብ የሚታፈስባቸውንና ስልጣንን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተቋማትን ተቆጣጥሮ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ያገር ሀብት ዘርፎ ከሀገር ሲያስወጣ ምን ያደረጋችሁት ነገር አለ? የሀገር ሀብት ለሁሉም ክልሎች እንጅ ለአንድ ቡድን ብቻ አገልግሎት እንዳይሰጥ ለማድረግ የሰራችሁት ስራስ ምን አለ?

12. የብድርና የቁጠባ ወይም የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አገልግሎት ለሁሉም አማራ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ነው የምታከፋፍሉት? አገልግሎት ማግኘት የህዝብ መብት ነው:: እናንተ በአመራር ላይ የተቀመጣችሁ አገልግሎት ለማግኘት ሳይሆን ያለአድልዖ አገልግሎት ለመስጠት ነው:: ግን እናንተ በተግባር እያደረጋችሁ ያላችሁት ምንድን ነው? የአማራው ህዝብ በሙሉ እንደናንተ ፍጹም የወያኔ ሎሌ ሆኖ የታዘዘውን እንዲፈጽም: ሲገድሉት እንዲሞት ለማድረግ ስንት ግፍ ሰራችሁ? ጠላትና ወዳጅ በማለት ከፍላችሁ እንደናንተ ሊሆን ያልፈቀደውን ሰላማዊ ዜጋ በተለያየ መንገድ አላሰቃያችሁም?

13. ህዝቡ የፖለቲካ አማራጭ የማግኘት መብቱ በህገመንግስቱ የተጠበቀ ነው:: ይህንን የህዝብ መብት አክብራችሁ ህዝቡ በመረጠው እንዲተዳደር ምን አድርጋችኋል? በግድ ውጣ ተብሎ እንዲመርጥ የተደረገን ህዝብ ምርጫውን ነፍጋችሁ እጅ እጅ በሚል ውሸት እኛ ተመረጥን ስትሉ የብዙሀኑን መብት የነፈጋችሁና በህዝብ ላይ በጉልበት የነገሳችሁ አምባገነኖች እንደሆናችሁ አስተውላችሁት ታውቃላችሁ? መቸ ነው ወደህሊናችሁ የምትመለሱት?

14. ክልሎች ታሪክ እየጠቀሱ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሲያነሱ የአማራ ክልል ግን በግላጭ በታሪክ የሚታወቀውን መሬቱን ማስከበር አልቻለም:: አንዳንድ የዋህ ሰዎች በአንድነት እስከኖርን ድረስ አንድ አካባቢ በዚህ ወይም በዚያ ክልል ቢካተት ችግር የለውም ሲሉ ይደመጣሉ:: እንደእኔ ከሆነ ይህ አባባል ፍጹም ስህተት ነው:: የመገንጠል መብት በተከበረበት ሀገር ትክክለኛ የራስን መሬት ሳይዙ ህገመንግስቱን ማጽደቅ አደጋው ቀላል አይደለም:: ዛሬ እየኖርን ያለነው አንድነቷ በተጠበቀ ሀገር ውስጥ አይደለም:: ህገመንግስቱም ቢሆን በአንድነት ለመቀጠላችን ዋስትና የሚሰጥ አይደለም:: የፈለገውን ማድረግ እየቻለ ያለው ወያኔ የተፈራረምንበትን ህገመንግስት መሰረት በማድረግ ነገ ብድግ ብሎ ለመገንጠል ወስኛለሁ ቢል በምን ነው ልንከላከል የምንችለው? የክልል መንግስታት ተፈራርመው ያጸደቁት ህገመንግስት በአለም አቀፍ መድረክ ተቀባይነት የማይኖረው ይመስላችኋል? በርግጥ በአሁኑ ጊዜ ከትግራይ ውጪ ያሉት ክልሎች መገንጠል እንፈልጋለን የማለት ድፍረቱ አይኖራቸውም: ድፍረቱ ቢኖራቸው እንኳ ወያኔ ጥያቄውን ለማዳፈንና ጥያቄ አቅራቢወችን ለመበቀል የሚሄድበት መንገድ አያጣም:: ነገር ግን የወያኔ ፈቃድ ሆኖ ክልሎች እንዲገነጣጠሉ ቢያደርግ ታሪካዊ መሬታችን ነው የምንለውን አካባቢ እንዴት ነው ማስመለስ የምንችለው? የአማራ ክልል ለመሆኑ ታሪካዊ መኖሪያ አካባቢው የቱ ነው? ይህ ጥያቄ ከተመለሰ በኋላ ነበር ህገመንግስቱ ቢፈረምም መፈረም የነበረበት:: ድርጅታችሁ አላግባብ የተወሰደበትን መሬት ለማስመለስ ያደረገው ምን ነገር አለ? “አማራ ነን:: ያላግባብ ወደትግራይ ክልል እንድንካተት ተደርገናል” እያሉ ለሚጮሁት የወልቃይት ወገኖቻችንስ ምን አደረጋችሁ? ታዲያ ለአማራው ህዝብ መብትና እኩልነት ያደረጋችሁት የሚያስፎክር ትግል የት አለ!

በርግጥ ማንም አሌ የማይለው ነገር ቢኖር አማራው ሀገሩ ኢትዮጵያ መሆኗን ነው: የኖረውም የሀገሪቱን ዳር ድንበር ለማስከበር: ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢወች ነው:: ይህችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አስከብሮ ለእኛ ያስረከበ ህዝብ እንደጠላት እየታደነ ሲገደል አባሪ ከመሆን ውጭ ለክልሉና ለህዝቡ ያበረከታችሁት አንድም አኩሪ ስራ የለም:: እናንተ የአማራውን ህዝብ የምታኮሩ ሳትሆኑ የምታሳፍሩ: የምታስከብሩ ሳትሆኑ የምታዋርዱ ሙሉ ትኩረታችሁን በሰፈር እየተደራጃችሁ ስልጣን ለመያዝ በርስ በርስ ሽኩቻ ጊዜአችሁን የምታባክኑ እንጥፍጣፊ ህዝባዊ ስሜት የሌላችሁ የምትገርሙ ሰዎች ናችሁ:: አይናችሁን ጨፍናችሁ በምትዋሹት ውሸት የአማራው ህዝብ አምኖ ይቀበለናል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል:: ብታምኑም ባታምኑም ህዝቡ እናንተን ህሊና የሚባል ነገር የሌላችሁ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ሮቦቶች እንደሆናችሁ አድርጎ ነው የሚያያችሁ:: ወያኔም ቢሆን በፈለገው መንገድ ሊያሰልፋችሁ የሚችል ጅሎች አድርጎ እንደሚያያችሁና እንደሚታዘባችሁ አንጠራጠርም::

ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ከፓርላማ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ የዶ/ር ደብረጽዮንን ስሜት ሳትገነዘቡ የቀራችሁ አይመስለኝም:: መቸም ኃይለማርያም ከራሳቸው የፈለቀች አንዲትም ቃል ሊናገሩ ድፍረት ይኖራቸዋል ተብሎ አይታሰብም:: ታዲያ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ በወያኔ ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን መልስ ሸምድደው ገብተው “መንግሥታችን ርምጃ ይወስዳል…” ምናምን ሲሉ ዶክተሩ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው የፌዝ ፈገግታ ሲያሳዩ ነበር:: ዶ/ር ደብረጽዮን “ነገ ቃላችንን አጥፈን ተቃራኒውን ለማድረግ ብንወስንና ይህንን ባደባባይ ተናገር ብንለው ያው እንደለመደው መንግስታችን እንዲህ ያደርጋል እያለ መናገሩ አይቀርም:: የነዚህ ሰዎች ሰውነት ከምኑ ላይ ነው?” የሚል አይነት የግርምት ፈገግታ ነበር ሲያሳዩ የነበሩት:: ወያኔ እንዲህ የሚያሾፈው በሁላችሁም ላይ ነው::


አማራን የሚያህል ትልቅና ታሪካዊ ህዝብ እንወክላለን ብላችሁ ግን ለውርደትና ለእልቂት ስትዳርጉት: ለዚህ ውለታችሁ የሚሰጣችሁ ክፍያ በአናሳው ቡድን እንዲህ መሳቂያ መሳለቂያ መሆን ከሆነ ምን አይነት ህሊና ቢኖራችሁ ነው አሜን ብላችሁ ተሸክማችኋቸው የምትኖሩት:: “አማራ ሆዳም ነው” እንደሚሉን እናውቃለን:: የህዝብ ክብርና ነጻነት ከምንም በላይ አይደለም እንዴ! ባትበሉት ባትጠጡት ባፍንጫችሁ ቢወጣ ምን ነበረበት::

እስከቀበሌ ድረስ በዘለቀው አደረጃጀታችሁ ተጠቅማችሁ “መላው የአማራ ህዝብ ሆይ ደምና አጥንት ከፍለህ ባስከበርሀት ሀገር ላይ መኖር ተከልክለህ ዘርፈ ብዙ ግፍ እየተፈጸምብህ ስለሆነ ይህንን ባንተ ላይ ያነጣጠረ ሰቆቃ ለማስወገድ ከጎናችን ተሰልፈህ መብትህን እንድታስከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::” የሚል አዋጅ ብታስነግሩ አማራው “ሆ” ብሎ ተነስቶ የተበላሸውን ለማስተካከል ጊዜ ይፈጅበት ነበር!

ለነገሩ ወያኔ ከራሱ ክልል ውጪ ላሉት ክልሎች ባለስልጣናትን ሲያስቀምጥ በተጠና መንገድ ሆድ እንጅ ህሊና የሌላቸውን ስለህዝብና ስለሀገር ደንታ ቢሶችን መርጦ ነው:: ለዚያም ነው አማራው ከያለበት እየተያዘ ግፍ ሲፈጸምበት አንድም ተቃውሞ ያላሰማችሁት! እናንተም ብትሆኑ አፋችሁ ያውራ እንጅ ለህዝብ ቀርቶ ለራሳችሁ እንደማትሆኑ ልባችሁ አሳምሮ ያውቃል:: ሙሉአለም ሲገደል ምን አደረጋችሁ? ታምራት ላይኔ በአደባባይ “በትግል ያልተሸነፈ ሰው በስኳር ተሸንፎ እጁን ሰጠ” ተብሎ ሲቀለድበት: ራሱን አዋርዶ “ቢመክሩኝ አልሰማ ብየ” ብሎ ቀበጣጥሮ ይቅርታ እንኳ ተነፍጎት ወህኒ ሲወርድ ከማጨብጨብ ውጪ ምን ሰራችሁ? ለነገሩ እንደፖለቲከኛ ሳይሆን እንደሆደ ቡቡ ህጻን በፍርሀት የቀባጠረ ሰው ሲመራው ከነበረ ድርጅት ምን ይጠበቃል?


የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ እናንተም ሆናችሁ ጌቶቻችሁ ከፍርድ አታመልጡም: የውሻን ደም ከንቱ የማያስቀር ግፍን የሚቆጥር አምላክ አለ:: እስከዚያው ድረስ እናንተ ስልጣን ላይ ተቀምጣችሁ ለምታገኙት ፍርፋሪ አማራውን ረግጣችሁ እንድትይዙ የእድል በር የከፈተላችሁን የልደት ቀናችሁን በፌስታ ስታከብሩ እኛ ደግሞ ያችን የተረገመች ቀን በሀዘን እናስታውሳታለን:: መቸም ከአንጎል ክፍላችሁ የሆነ የጎደለ ነገር አለ መሰለኝ ጸጸትና ቁጭት ይሰማችኋል ብየ አላምንም:: የህዝብን አስተያየት በግብአትነት ተጠቅማችሁ ራሳችሁን ወደውስጥ አይታችሁ ስህተታችሁን ለማረም ከመሞከር ይልቅ የሚተቿችሁን ለማጥፋት የምትተጉ እንደሆናችሁ ግን እናውቃለን:: እስካሁን በሰራችሁት ስራ ክብር ያገኛችሁ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል:: እና ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር ነውና በስራችሁ ከማፈርና ከማዘን አልፈን ምነው ሳትወለዱ በናታችሁ ማህጸን ውስጥ ውሀ ሆናችሁ በቀራችሁ ነበር ብለን ድርጅታችሁ የተወለደበትን ቀን ብቻ ሳይሆን እናንተ የብአዴን ሰዎች እራሳችሁ የየተወለዳችሁበትን ቀን ሳይቀር እረግመናል::

 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47815

Wednesday, October 28, 2015

በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት አለ” የሚለው ተረት ተረት ነው ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ


ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊቀመንበር እና የመድረክ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ይህን ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበውን የውይይት ግብዣ ተቃዋሚዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ለፓርላማ አባላት መናገራቸውን ተከትሎ ነው።

መንግስት በጠራው የአምስት ኣመታት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ያልተሳተፉ እንደመድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢአድ ያሉ ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያት ውሃ ያማያነሳ ነው ያሉት አቶ ሃይለማርያም ፣ ፓርቲዎቹ ያልተሳተፉት በሕጋዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት አይደለም በማለት መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ከየትኛው መንግስት ጋር እንደሚወያዩ እናያለን ሲሉ ዝተዋል፡፡

ዶ/ር መረራ ሲናገሩ፣ “በቅድሚያ አንነጋገርም አላልንም፣ ቅድሚያ መሰረታዊ በሆኑት የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ለምሳሌ ነጻ ምርጫን ፣ ነጻ ሚዲያን፣ በነጻነት መንቀሳቀስንንና በመሳሰሉት መሰረታዊ መብቶች ጉዳይ እንነጋገር ” ነው ያለው ካሉ በሁዋላ፣ እነሱ በሚሉት ጉዳይ ላይ ለመነጋገርም ፣ በር ዘግቶ ሳይሆን፣ በነጻ ሜዳ፣ ለህዝብ በቀጥታ በሚተላለፍ መልኩ መሆን አለበት በማለት በጽሁፍ መግለጻቸውን ተናግረዋል።

መድረኩን ተጠቅማችሁ ለምን ሃሳባችሁን ለማስተላለፍ አልቻላችሁም በሚል ለተጠየቁት ዶ/ር መረራ፣ የኢህአዴግ ፖሊሲ ስልጣን ወይም ሞት በመሆኑ፣ የልጅ ስራ መጫወቱ ትርጉም የለውም ብለዋል።

አገሪቱ አደጋ ውስጥ ናት ያሉት ዶ/ር መረራ ዲሞክራሲው የፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ መግባቱን፣ አገሪቱ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እያመራች መሆኑዋንና የሚባለው ዲሞክራሲ፣ ሰላምና መረጋጋት አለመኖሩን እንዲሁም ረሃብና ድህነት ታሪክ ሆኗል የሚባለውም ተረት ነው በማለት ገልጸዋል።

http://www.satenaw.com/amharic/archives/10863

Monday, October 26, 2015

በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ፡፡

ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡፡

እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡


በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47730

Wednesday, October 21, 2015

ከሕወሐት መከላከያ ማዕከላዊ ዕዝ እና ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እየከዳ መሆኑ ታወቀ

የህወሓት አባላት በሆኑ የይስሙላህ የጦር መኮንኖች ከታች እስከላይ ተጠርንፎ በጉልበት ተይዞ በአገር መከላከያ ስም እየተጠራ ነገር ግን በፀረ-ህዝብነት ሳይወድ በግድ እንዲሰለፍ እየተደረገ የሚገኘው ሰራዊት ስርዓቱን መክዳቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ፈፅሞ ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡በተለይም ደግሞ ማዕከላዊ ዕዝ እና ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት የከዳባቸው መሆናቸው ታውቋል፡፡

በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ ውስጥ የሰራዊቱ አባላት ስርዓቱን ጥሎ መክዳት ተባብሶ የቀጠለ በመሆኑ የሰራዊቱ አባላት የትምህርት ማስረጃቸውንና ሌሎችን ሰነዶች ለመያዣነት እየተነጠቁ ይገኛሉ፡፡

በማዕከላዊ ዕዝ እና በምዕራብ ዕዝ በሰፊው እየተተገበረ የሚገኘው ይህ የትምህርት ማስረጃ እና ሌሎችም የግል ሰነዶች ንጥቂያ በተለይም የሙያተኛ መኮንኖችን መክዳት ለመግታት ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን ድርጊቱ በሰራዊቱ ውስጥ እልህና ቁጣን ቀስቅሶ ይገኛል፡፡ ከጫፍ የደረሰ ኩርፊያም ጭምር አስከትሏል፡፡

በማዕከላዊ ዕዝ ዕና በምዕራብ ዕዝ ውስጥ ሲከዱ ተይዘው በቁጥጥር ስር የዋሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሰራዊቱ አባላት እንዳሉ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡



በሌላ በኩል ደግሞ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ባልተጠበቀ ሰዓት ጥቃት ሊከፍቱ ይችላሉ ተብሎ በመስጋቱ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ታዞ በአካባቢው ከፍተኛ ጥበቃ አየተደረገ ይገኛል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47580

Tuesday, October 20, 2015

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ ተሸላሚ ሆነ

በሽብርተኝነት ተከስሶ 18 አመት የተፈረደበትና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ ደረጃ አንድ ሰብዓዊነት (PEN Canada’s One Humanity Award) ሽልማት ተሸላሚ መሆኑን ፔን ካናዳ ይፋ አድርጓል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በፈረንጆቹ ግንቦት 2012 የባርባር ጎልድ ስሚዝ ሽልማት እንዲሁም በሰኔ 2014 የጎልደን ፔን ሽልማትን ተሸላሚ እንደሆነ ይታወሳል፡፡ በካናዳ ቶሮንቶ እየተደረገ በሚገኘው 36ኛው ዓለም አቀፍ የፀሃፊዎች ፌስቲባል የፔን ካናዳ ደረጃ አንድ ሰብዓዊነት ሽልማትን ተሸልሟል፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 የአረብ አብዮትን ተከትሎ መንግስት ለውጥ የማያደርግ ከሆነ ተመሳሳይ ህዝባዊ ንቅናቄ በኢትዮጵያም ሊከሰት ይችላል የሚል አስተያየቱን ማንጸባረቁን ተከትሎ ለእስር የተዳረገውና በፀረ ሽብር ህጉ ተከስሶ 18 አመት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በበርካታ የሰብአዊ መብት ተቋማት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ዓለማቀፍ መብቱን መጠቀሙን በማስታወስ እስክንድር የህሊና እስረኛ እንደሆነ በመግለፅ ከእስር እንዲለቀቅ መጠየቃቸውን ቀጥለዋል፡፡ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ከእስር እንዲለቅ ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡


በአሁኑ ወቅት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በእስር ቤቱ ከሚደረግበት ከፍተኛ ቁጥጥርና ጫና ባሻገር ከቤተሰብ ውጭ እንዳይጠየቅ ተከልክሎ ይገኛል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47557

Friday, October 16, 2015

ከአዲስ አበባ አስተዳደር የተባረሩት ከ800 በላይ ሠራኞች ከባድ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተመድበው ሲሰሩ ከቆዩት ከ800 በላይ ሰራተኞች በመቀነሳቸው ምክንያት ለከባድ ማህበራዊ ችግር እንደተጋለጡ ተዘገበ::

የደህሚት ራድዮ እንደዘገበው የኢህአዴግ ካድሬዎች ስልጣናቸውን ለማደላደል ሲሉ ላይና ታች በሚሉበት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ባሉት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሲሰሩ የቆዩትን ሲቪል ሰራተኞች 800 የሚሆኑትን በተለያዩ ምክንያቶችን በመፈጠር በዚህ ሳምንት ውስጥ ተቀንሰው እንዲወጡ በመደረጉ ምክንያት ያለ ስራ ተጥለው በመቅረታቸው የተነሳ ቤተሰቦቻቸው ለከባድ ማህበራዊ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ተገለፀ።

መረጃው በመጨመር ከሲቪል ሰራተኞች ጋር የትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ ነው ተብለው ከሃላፊነታቸው የተቀነሱት የገዢው ቡዱን ካድሬዎች ግን በመንግስት ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ተደርጎላቸው በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅተው እንዲሰሩና ከሌላው ዜጋ የበለጠ ሃብት አፍረተው እንዲኖሩ ሁኔታዎችን እንደተመቻቸላቸው ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።


አስተዳደሩ በሙስና የተጨማለቁ ከፍተኛ አመራሮችና ሲቪል ሰራተኞችን ህግ ፊት በማቅረብ እንዲ ጠየቁ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ቢገልፅም በተግባር ግን የበታች ሲቪል ሰራተኞች ለመክሰስ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ ሲሆን ይህ ግን ወደ በላይ አመራሮች እንዳይሸጋገር ታስቦ እየተከተለው ያለው የስርአቱ አስመሳይ አካሄድ እንደሆነና ከዚህም አልፎ እርምጃ እንዲወስድ የፖለቲካ ቁርጠኝነቱን እንደሚያንሰው የህግ ባለሞያዎች ዋቢ በማድረግ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47464

Thursday, October 15, 2015

የኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ሰቆቃ ዛሬም ከወደ ደ/አፍሪካ ይጣራል “ይህ አስር ቤት ለእኔ በምድር ላይ ያለ ሴኦል ሆኖ ነው የሚታየኝ” ይለናል የ 15 አመቱ ልጅ ኢትዮጵያዊ እስረኛ

በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን ለመለወጥ/ለማሻሻል በማለት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ በጎረቤት ማላዊ በኩል ለማቋረጥ የሞከሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በፖሊስ ተይዘው የተፈረደባቸወን የገንዘብ እና የእስራት ቅጣት ቢጨርሱም በአሳቃቂው የማላዊ እሰር ቤት ወስጥ ፈዳቸውን እያዩ እንደሚገኙ የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (አጃንስ ፈራንስ ፕሬስ ) እሮብ ጥቅምት 14 2015 አኤአ አ ዘግቧል።

“ለተሻለ ኑሮ ወደ ደ/አፍሪካ ለመሻገር የቋመጡት ኢትዮጵዊያን ሰደተኞች ምኞታቸው ቅዠት ሆነ። “ ያለው ዜና ዘገባው ከመዲናይቱ ሎላንግዊ 85 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው እና ለ 800 እስረኞች ተብሎ በተገነባው የዲደዛ እስር ቤት ውስጥ ወደ 2,650 የሚጠጉ እስረኞች ከእነዚህ መካከል 317 በላይ ኢትዮጵያዊያኖች ያለ በቂ ምግብ እና ውሃ አቅርቦት እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብሏል።የ15 አመቱ ኢያሱ ታዲዮስ ባለፈው ሃምሌ ወር ከ 29 ጓደኞቹ ጋር ማላዊ ውስጥ ታሰረው በፍርድ ቤት የተጣለባቸውን የገንዘብ አና የእሰራት ቅጣት ቢፈጽሙም “ወደ አገራቸው የሚያጓጉዛቸ ተቋም በመታጣቱ ለተጨማሪ ሰቆቃ ተጋልጠዋል ተብሏል።እያሱ ሰለደረሰበት ሰቆቃ ሲናገር “ይህ እሰር ቤት ለእኔ በምድር ላይ ያለ ሲኦል ሆኖ ነው የሚታየኝ። ቀድሞ የነበረኝ ሕልም እና ተሰፋ ሁሉ እዚህ ላይ ተገቷል ። ከ 5 ጓደኞቼ ጋር የተጣለብን 62 ዶላር ቅጣትን ብንከፍልም እና እስራቱን ብንጨርስም እስከ አሁን ድረስ አልተፈታንም ። አሁን የምፈልገው ነገር ቢኖር ወደ አገሬ መመለስ ብቻ ነው ።” በማለት ሰውነቱ በደካም እና በረሃብ የጠወለገው ታዳጊው ወጣት ኢያሱ በማላዊው እስርቤት ውስጥ የደረሰበትን ሰቆቃ እና መጥፎ ገጠመኝ በመግለጽ “የድረሱልን” ጥሪውን አቅርቧል።


ባለፈው መሰከረም ወር በአሜሪካው የስደት ተመላሾች ደረጅት አማካኝነት 70 ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ነፍሳችውን ብቻ አትርፈው ወደ አገራቸው በበጎ ፍቃደተኝነት የተመለሱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በእሰራት ላይ ያሉተን 317 ወገኖቻችንን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ በትንሹ የ አሜሪካ 200,000 ዶላር እንደሚያሰፈልግ ተገምቷል።የአለም አቀፉ ከሰደት ተመላሾች ድርጀት ተሰፋ የጠፋባቸው ኢትዮጵያዊያኑ ሰደተኞችን ወደ አገራቸው ለማጓጓዝ የበኩሉን ጥረት ቢያደረግም የአለማቀፉ ማህበረሰብ ወቅታዊ ትኩረቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ (የሶሪያ ሰደተኞች) ላይ በመሆኑ አትዮጵያዊያኑ ሰደተኞች አሰተዋሽ አጥተዋል ተብሏል ። የደርጅቱ ዋና ሹም የሆኑት ሚስስ ካትሪን ሳኒ በበኩላቸው “እነዚህ ማስኪን ነፍሳት ከአገራቸው /ከኢትዮጵያ / እርቀው እንደዚህ አይነቱ አሰከፊ ሁኔታ ውስጥ መውደቃቸው በእጅጉ ያሳዝናል” በማለት በኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ችግርን በሃዘኔታ ለማስረዳት ሞክረዋል።

በዚህ አጋጣሚ አገሪቱ በኢኮኖሚዋ “አድጋለች፣ ተመንደጋለች፣ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ ገባዋን ሰፈኖባታል” ከተባለ ለምን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ፖለቲከኞች ያልሆኑ ነገር ግን የወደፊቱ አገር ተረካቢ የሆኑ ሕጻናት እና ወጣቶች አስከፊውን የባህር እና የየብስ ጉዞ በማድረግ ለእንደዚህ አይነቱ እጅግ ዘግናኝ እና አሳቃቂ ችግር ይጋለጣሉ? ብለው የሚጠይቁ ወገኖች ተበራክተዋል።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47441