Wednesday, September 30, 2015

አገር የምትኖረው በ3 ነገር ነው በወታደር በገበሬ እና በመምህር!!!

አገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንድትኖር በመሰሪ ሃሳቡ ሌት ተቀን የማይቆፍረው ግድጓድ የለም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን እንደ አሳቡ ሊሆንለት አልቻሉም  ዘር  ከዘር ሊያጋጭ ብዙ ጣረ አልተሳካለትም፤ ሐይማኖት ከሃይማኖት ሞከረ ይሄም አልሰራ አለው ሃሳቡ ሁሉ መና  ሲቀርበት  እራሱ ከሳሽ  እራሱ ፈራጅ  በሆነበት ፍርድ ቤት  የብዙሃን ነጽሃን  ሰው መሰቃያ  ወደ ሆነው ወህይኒ እየወረወረ ባልሰራበት ወንጀል ባላደረጉት  ድርጊት ንጽሐኑን ማሰቃየት ከጀመረ ድፍን 24 አመት አለፈ።

መምህር

አንድ አገር ከሚያስፈልጋት ዋናው መሰረታዊ ነገር መምህር ነው። መምህር ከሌለ የተማረን ህብረተሰብ ማግኝት አይቻልም።  መምህር በጠመኔው ለአገር የሚሆን ፍሬ ለህዝብ የሚጠቅም ዘር በሰው አእምሮ  ውስጥ የሚዘራ እና ብዙ ጥበቦች ባለ ብዙ እውቀት  ባለቤት አገርን በጥበብ የሚመራ ላገሩ በእውቀት የሚያገለግል ለአገር የሚጠቅመውን ካመነበት የሚሰራ ካላመነበት ደግሞ እንቢ የሚል  ማንኛውንም ነገር ሰለ ህዝብ ብሎ ስለ አገር  ብሎ ማድረግ የሚቻል ዜጋን የሚቀርጹት መምህራናን ናቸው።  ዛሬ  ወያኔ እያደረገ ያለው እኔ የምላቹሁን አድረጉ እኔ የምላቹሁን አስተምሩ እኔ የምላቹሁን  መመርያ ተቀበሉ  ብሎ አገርን የሚያጠፋ ሆኖ ሰላገኙት የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ  አገርን የሚያቀኑን መምህራን ትውልድን የሚቀርጹ  መምህራን በካድሬ በመተካት የተማረ እንዳይበቅልባት ያወቀ  እንዳይወጣባት ትምህርት ቤቶችና ዪንቨርስቲዎች ያቃጣሪወች መናህርያ  አድርጓታል። እንግዲህ ወገኔ የመምህራን መነካት የኢትዮጵያ አንዱ መሰረቱ እየተናጋ ነውና  ልትነቃ እና  የወያኔ አገር አጥፊነቱን አውቀን በቃህ ልንለው ይገባል።

ገበሬ

አገር የምትኖረው ገበሬው አምርቶ በሚያበቅለው ምርት ነው ገበሬው ጠንክሮ በማረስ አገርን በመመገቡ ሂደት የአገርን መሰረት ነው። ዛሬ  ገበሬው ከመሬቱ በማፈናቀል ለውጪ ባለሃብት  ለኢንቬስተር በመስጠት እንዲሁም በግድ  ማደበርያ  እንዲወስድ እያደረጉት  ባለ  እዳ በማድረግ እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር መሬቱን ጥሎ እንዲሄድ በማድረግ ተሳዳጅ አድርገውታል። ገበሬ የለም ማለት አገር የለችም ማለት ነው ።ገበሬው በማሰቃየት እረፍት በመንሳት  እስመርረውት ያሉት ወያኔወች ሃሳባቸውም ራያቸውም ሰለ  ኢትዮጵያ  እና ሰለ ሕዝቧ ስላልሆነ ስለሚያደርጉት ነገር  መጸጸት እንኳን አያሳዩም ስለዚህ ገበሬው ሲነካ የአገር መሰረት  መነካት ነውና ወገኔ እንግዲህ ንቃ።

ወታደር

አገር የምትጠበቀው በወታደር ነው አንድ አገር ጠንካራ የወታደር ከሌላት  ጠላት በቀላሉ ይዳፈራታል። ስለዚህ ጠንካር የወታደር ተቋም  ለአገር አጥርም መሰረት ነው። ዛሬ ግን ወያኔ እየሰራ ያለው የወታደር ተቋም  በወታደራዊ ስልጠና  እንዲሁም ትምርት በብቃት  የሚበልጣቸው እያሉ  ትግሬ በመሆኑ ብቻ  አዛዥ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል  ይሄ አካሄድ ለወያኔወች የአገር ማፍረስ አላማቸው ስለሆነ  ምንም አይሰማቸው  ለትግሬወች ግን  ጊዚያዊ ሹመት ሲሰጣቸው ሁሉንም ቦታ ያለ እውቀታቸው ቦታውን እንዲይዙት ሲደረግ ለምን ብላቹ መጠየቅ  ሲገባቹሁ የተሰጣችሁን ስልጣን ተቀብላቹ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ላይ  በደልና ጫና የምትፈጥሩ እንግዲህ እዳው በእጃቹ ነው። የወያኔ ባለስልጣን ባንተ ስም የአገርን ንብረት እየዘረፉ  እያሸሹ ይገኛሉ አንተ ግን  ከህብረተሰቡ ጋር የትም አትሄድም  ያኔ  በሰፈሩት መስፈርያ  እንዳይሆንባቹሁ የትግሬ ተወላጆች  በወታደር  ላይ የምታደርጉትን በደል ታቆሙ ዘንድ ያስፈልጋል። እንተም ከጥቂት የአገር አጥፊ እና ዘረፊ ጋር ባለመወገን አንድነታቹሁን የምታሳዩበት ጊዜ በጣም አጭር ነውና ይታሰብበት። ካለበለዚያ ግን  ወደ የኢትዮጵያ  የመከላከያ ሰራዊት ደምና ጉልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕዝብና  ሃብት እንደፈለጋቹ እየሆናቹ የምትኖሩበት ጊዜ ማብቂያው ይመጣል።

ወታደሩም እራሱንና  አገሩን ሕዝቡን የመጠበቅ ነጻ የማውጣት ሃላፊነት እንዳለበት ወያኔ የሚያውቅበት ጊዜ  ቅርብ ነው።  ወያኔወች የመከላከያ  ሰራዊት የሃገር መሰረት ስለሆነ ይህንም ለማፍረስ  እና ለመበተን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።  እውነት ነው መምህሩም ወደቀድሞ ቦታቸው  ተመልሰው ባላቸው እውቀት ጠመኔን ይዘው ያለምንም ተጽእኖ ዜጋን የሚያፈሩበት ጊዜ ቅርብ ነው። እውነት ነው ገበሬው ሞፈሩን አንስቶ  እርሻውን አስፍቶ  በትራክተር አርሶ  ሕዝቡን የሚመግብበት ቅርብ ነው ። እውነት ነው ወታደሩ ወያኔን የተባለ ወንበዴን አጥፍቶ ለሕዝቡና ለአገሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ቅርብ ነው ።


ሞት ለወያኔ!!!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47026

Tuesday, September 29, 2015

አርባ‬ ምንጭ የነበረው የአሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን አካባቢውን ለቆ እየወጣ ነው


አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡

‪‎ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡
አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡

በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡


ድሮን የታጠቀው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን የአርባ ምንጭን መሬት ለቆ መንቀሳቀስ የጀመረበት ምክንያት ለጊዜው በውል ተለይቶ ባይታወቅም መንግስት ነኝ በሚለው በህወሓት አገዛዝ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል አለመግባባት ተከስቶ ቅራኔ ሳይፈጠር እንዳልቀረ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ከአሁን በፊት ከአርባ ምንጭ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ላይ ተቀምጦ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል፡፡

ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡

የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ በህዝብ ላይ ሴራ በማቀነባበር የሚታወቀው ህወሓት ራሱ ግንብቶ ለግለሰቦች ያከራየውን የንግድ ማዕከል ነው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ድርጊቱን እንደፈፀሙት በማስመሰል ከህዝብ ለመነጠል ሲል ነው በተቀነባበረ ሂደት በእሳት የለቀቀው ፡፡

በህወሓት የተቀነባበረ ሴራ የተከሰተው ከባድ የእሳት አደጋ የደረሰው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም ሲሆን ከ40 በላይ ሱቆች ተበልተው ወደ አመድነት ተቀይረዋል፤ በሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ንብረትም ወድሟል፡፡



ህወሓት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱት የቦንብ ፍንዳታዎች ትግራይ ሆቴልን ጨምሮ እጁ እንዳለበት የአሜሪካ ኤምባሲ ለስቴት ዲፓርትመንት የላከውን ደብዳቤ በዋቢነት ጠቅሶ ዊክሊክስ የተባለው ድረ-ገፅ ማጋለጡ የሚታውስ ነው፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47004

Wednesday, September 23, 2015

የኣንድነት ችቦ እየተንቦገቦገ ነው


ከወያኔ የዘር ኣገዛዝ በፊት የኢትዮጵያ መለዮ ለባሾች ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ስለነበሩ ከሥልጠና ቦታቸው ጀምሮ በየደረሱበት የውጊያ ዐውደ ግንባርና የጦር ሠፈር ኑሮኣቸው እንደ ወንድማማች፣ እህትማማችና ጓደኛሞች የሚተያዩ  ነበሩ እንጂ የዘር ቆጠራ ውስጥ ኣይገቡም ነበር። ኣብሮ መብላትና መጠጣት፣ ኣብሮ መዝናናትና ለሞትም ሆነ ለድል ኣብሮ መሰለፍን ዓላማቸው ኣድርገው የሚንቀሳቀሱ ነበሩ። የትግል ኣጋራቸውን ሕይወት ከተቃራኒው ጦር ኣረር ለማዳን እንጂ ጓደኛቸውን መግደልና ማስገደል እንኳን ሊደረግ ታስቦም ኣያውቅም ነበር።

ወያኔ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ችግር ሳይኖር ራሱ በራሱ ላይ ችግር በመፍጠሩ ሁለት ኣጣብቂኝ ውስጥ ገባ። ሌሎችን ማመን ስለኣልቻለ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በትግራይ ተወላጆች ብቻ ለማንቀሳቀስም ዓላማው ነበር። መለዮ ለባሾቹንም በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዳያዋቅር በቂ ሊሆኑለት ኣልቻሉም። ስንቱ ቦታ ይሰለፋሉ። በሆኑለት ደስ ባለው ነበር። ስለሆነም ሌሎችን በሁለተኛ ዜጋነት ቀጥሮ  ማሠራቱ ኣይቀሬ ሆነበት። የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ግን በመሪነት እንዲያገለግሉ ኣደረገ።

ይኸ የትግሬዎችን በበላይነት የማየቱ ተንኮል ሌሎችን እንዳያስነሳበት እያንዳንዱን ብሔር በጥርጣሬ እንዲተያዩ  የዘር ልዩነት መርዝ ጋታቸው። ስለሆነም ሁሉም እንደ ጭዳ በግ ወደ እርድ መነዳት ሆነ። ኣትግደለኝ፣ ኣታግለኝ፣ ኣታንገላታኝ፣ መብቴን ጠብቅልኝ፣ ወዘተ የሚል የመብትና የዜግነት ጥያቄዎች በራቸው ተዘጋ። የጋራ ጠላታቸውን ለመፋለም መዘጋጀት ሳይሆን እርስ በርስ እንዲፋጠጡ ሆነ። ሲዘምቱ ግን ወርቃማዎቹ ከኋላ ሆነው ወደፊት እያሉ ይነዱኣቸዋል፣ ወደ እሳቱ ይማግዱኣቸዋል። እንደ እንስሳ የተጠመዱ ፈንጂዎች ላይ እንዲሔዱ ኣደረጉኣቸው። የፈንጂ መሞከሪያ ኣደረጉኣቸው። የጠላት ጦር ሳይገድላቸው ራሱ ወያኔ ገዳያቸው ሆነ። እኔ ልቅደም፣ እኔ ልቅደም ይባባሉ ነበር እንጂ ኣንዱ ሌሎችን ወደ እሳት ወላፈን የሚገፈትርበት ጊዜ ኣልነበረም። ያንን ጊዜ ወያኔ እንደ ኋላቀር ቆጠረው።

በወርቃማው ዘር ላይ ተንተርሶ  በመሣሪያ ኃይል ሀገሪቱን የሚያሽከረክረው የወያኔ መንግሥት በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በሰሜን ኣፋር እያደረገ እንዳለው ጨርቆቹ ቢያልቁለት መሬቱ ስለሚለቀቅለት ወርቃማዎቹን ያሰፍርበታልና ጦርነትን ይፈልጋል፣ በሰበቡ ጨርቆቹ እንዲያልቁለት ይፈልጋል። “የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች፣ እነርሱም ያልቃሉ እርሷም ትሞታለች።” እንደተባለው ወያኔ መራሹ መለዮ ለባሽ እስከ ዛሬ ባየው የዘር ፖለቲካና የነርሱ መገለል ቆም ብለው እንዲያስቡ እያደረጋቸው ጀርባቸውን እየሰጡ ናቸው። ወያኔዎቹ በለኮሱት እሳት ራሳቸው ይቃጠሉበት እንጂ እኛ በምን ተዕዳችን እያሉ ናቸው። ወያኔ የማይሆንና ሊሆንም የማይችል መርዝ ላለፉት 24 ዓመታት ቢረጩም ለጊዜው ትንሽ ተሳክቶለት ቢፈነጩም ዘለቄታ ኣላገኘም። ኣሁን ወደ ዜሮ እየወረደ ነው።

ወያኔ ላለፉት ኣርባ ዓመታት የኢትዮጵያውያንን ኣንድነትና ኣብሮነት ለማፍረስ እየጣረና እያስገደደም እስከ ዛሬ ቢለፋም ሊሳከለት ኣልቻለም። እንዲያውም ራሱን እየለበለበው ከመሆንም ኣልፎ በሰሜኑ ኢትዮጵያችን በኩል የሚያቃጥለው የኣንድነት መሠረት ተጥሎ  ወደርሱ እየገሠገሠ ነው። ይህ ወያኔን እንደ ጎርፍ ውሃ ጠራርጎ  የሚወስደው በጠንካራ መሠረት ላይ የተጣለው የኣንድነት ኃይል በቅርቡ እንደታየው የተቃዋሚው  ሕዝባዊ ኃይል ከየብሔረሰቡ የተውጣጣ ሆኖ ተገኝቷል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ኣብሮነት ሊያለመልም ነው። ዱብ ዕዳ ሆኖበት ሊዋጥለት ያልተቻለውን ኣንድነትን የማፍረስ ዘመቻ የሚያፈርሱ ኃይሎች መፈጠራቸው የወያኔን መንደር እያፈራረሰው ነው። ይህ የሚያሳየን ወያኔ ለማፍረስ ደፋ ቀና ሲል የቆየውን የኣርባ ዓመት ትግል ድባቅ መታበት።
ወያኔ ከሰውም፣ ከእንስሳቱና ከደኖቹም ጋር የተጣላ ስለሆነ ተግባሩ መቀበሪያ ቦታም ሊያሳጣው ነው። ግዑዟንም መሬታችንን ደኖቿን ኣቃጥሎ ያራቆጣትና ያጎሳቆላት ስለሆነ ሲሞቱም ለመቃብራቸው ኣትመቻቸውም። ትተፋቸዋለች። ሬሳቸውን ኣውሬዎችና ኣሞራዎችም ኣይበሉም። እነርሱንም መከለያ ወይም መጠለያ ኣሳጥተዋቸዋልና ይጠየፉኣቸዋል።

ቸሩ ነኝ

ቸር ይግጠመን

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46866

Monday, September 21, 2015

የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሥግብግቦቹ የብአዴን መሪዎች ከወያኔ ጋር አብረው የዐማራ ሕዝብን እያጠፉ ይገኛል


የብአዴን አባላት እና መሪዎች የዐማራን ሕዝብ እያሰቃዩ እና እያስፈጁ የሚያካብቱት ማንኛውም ሃብት በክህደትና በግፍ የተሰበሰበ በመሆኑ ለህዝብ የሚያስረክቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም።ለዚህ የክህደት ተግባራችው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፣ በባህርዳር እና በጎንደር በሰፊው እየተሳሳቡ አገር እየዘረፋ መሆኑን እያንዳንዷንም ተግባራቸውንም እየተከታተልን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን። እነኝህ ስግብግቦች በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

http://www.satenaw.com/amharic/archives/10430

Saturday, September 19, 2015

ዜጐችን ከቀያቸው ማፈናቀል የልማታዊነት መገለጫ አይሆንም !!

ዳዊት ደምመላሽ ( ኖርዎይ
   
     (ከዚህ ቀደም ከጉራ ፈረዳ የተፈናቀሉ አማሮች፡ ፎቶ ፋይል)

የህወሃት/ኢህአዴግ/ መራሹ መንግስት ዜጐችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ልማታዊ መንግስት ነኝ እያለ ነጋ ጠባ ይደሰኩርልናል አንድ መንግስት እንደ መንግስት መናገር የሚችለው ህዝቦቹን ከድህነትና ከኌላ ቀርነት እንዲሁም ከስደት ሲያላቅቅና የህዝቦችን አንድነት መልካም ግንኙነት ሲያጠናክር የሀገር ሉሃላዊነትንና ዳር ድንበርን ሲያስከብር ነው ።

ህዝቡ በኑሮ ውድነት የሚሰቃይበትና የበይ ተመልካች በሆነበት ቁርሱን በልቶ ምሳውን በማያገኝበት ወጣቱንና አገር ተረካቢውን ትውልድ ለስደት በመዳረግ በሰሃራና በሜድትራንያን ባህር እንዲሁም በተለያዩ ጐረቤት አገራት በእስር ቤት ውስጥ ታጉረው የመንግስት እያሉ ሰሚ ሳያገኙ ለአደጋዎች በተጋለጡበት የጐሳ ስሜት ተንሰራፍቶ አንዱ የበላይ ሌላኛው የበታች አንዱ ጐሳ አንዱን እንዲጠላና ሰላሙ እንዲናጋ ህዝቡ ወልዶ ከብዶ ከኖረበት መንደሩ በሐይል እየተፈናቀለ እንዲበታተን የሚያደርግ ቡድን የሚመራው መንግስት ጥፋታዊ እንጂ ልማታዊ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም ።

የህዝብን መብት ገፎ የሚፅፉ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮችንና አባላቶችን አገሪታ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች አጉሮ የአገሩን ሀብትና ለም መሬት ጭምር ቆርሶ ለባዕድ አሳልፎ እየሰጠና ተባብሮ የአገሪታን አንጡራ አብት እየመዘበሩ በውጭ አገራት ባሉ ትላልቅ ባንኮች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው በመቶ ቢሊዬን ዶላሮችን ዘርፈው እያስቀመጡ ባሉበት አገር ውስጥ ልማታዊ መንግስት አለ ብሎ ማመን ቀርቶ መናገሩ የስህተት ስህተት ነው ።

ለራሱ ህዝብ አክብሮትና ብሔራዊ ስሜት የሌለው ቡድን ከድሃው የኢትዬጵያ ህዝብ በተዘረፈው ገንዘብ የውጭ አገር ተባባሪዎቹን ለማስተናገድና ለመሳብ በአገሪቷ ውስጥ ትላልቅ ሆቴሎችንና መንገዶችን በመገንባቱ ብቻ ልማታዊ መንግስት ነው ብሎ መቀበልና ማስተጋባት ድንቁርና መገለጫ ነው።

በአጭሩ ልማት ሲተረጐም የህዝብ ኑሮ መሻሻልን፣ የሰብዓዊ መብት መከበርን፣ የዜጐችን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና መኖርን ፣የዲሞክራሲና የዜጐች መብትን መረጋገጣቸወን ማሳየት ይኖርበታል ።

ህዝቡ በሀገሩ ጉዳይ የማይመክርበት ፣ የማይወስንበት ሁኔታ ካለ ትርጉም የሚሰጥ ልማት ሊሆን አይችልም ልማት ማለት የጥቂቶቹን ከርስ ሞልቶ ማደር ብቻ ሳይሆን በህዝብ ውስጥ የመንፈስ እርካታም ጭምር ሲኖርና የሀገር ዜግነትና ባለቤትነት ሲገለጽ ብቻ ነው  ።

ይህ ከዚህ በላይ በአጭሩ ጠቅለል አድርጌ በዝርዝር የጠቀስኩት ሐሳብ የህወሃት / ኢህአዴግን ፖሊሲዎችን ምንነት ቁልጭ አድርጎ ከሚያሳየን መገለጫዎቹ አንኳር ነጥቦች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው በቀጣዩ ጽሁፌ ተመልሼ እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት ።

ኢትዬጵያ ለዘላለም
ትኑር !!

1.http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46772

2.http://ethioexplorer.com/2015/09/19/%E1%8B%9C%E1%8C%90%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%8A%A8%E1%89%80%E1%8B%AB%E1%89%B8%E1%8B%8D-%E1%88%9B%E1%8D%88%E1%8A%93%E1%89%80%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%88%8D%E1%88%9B%E1%89%B3%E1%8B%8A%E1%8A%90%E1%89%B5/
3.

Friday, September 18, 2015

ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል “ሕዝብ አስፈቅደን ውጊያ እንጀምራለን” ሃይለማርያም





በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረውተጋዳላይሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።

የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግን አልሸሸጉም።

አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸውቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛልማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያህወሃት ሊወረኝ ነውሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።


ኦምሃጀር በሚባለው ስፍራ የከረረ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እንደሰሙ የገለጹ በውጊያው የትኛው ወገን ድል እንደተቀዳጀ ለጊዜው መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። ውጊያው ጠርዙን አስፍቶ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
ከህወሃት በኩል ውጊያው ከሻዕቢያ ጋር እንደሆነ ቢገለጽም ከሌላ ወገንህወሃትን የወጋሁት እኔ ነኝባይ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አልተሰማም። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ህወሃትን በነፍጥ አንበረክካለሁ በማለት ማወጁና አመራሮቹም ወደ ውጊያው አውድ ማምራታቸው ይታወቃል። ህወሃት ኤርትራን በአራት አቅጣጫ የመውጋት እቅድ እንዳለው ጎልጉል መዘገቡ የሚታወስ ነው

ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከሰራዊቱ እየሸሹና እየተሰወሩ መሆናቸው ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ ጦሩ የመዋጋት ፍላጎት ያጣል የሚል ሥጋት እንዳለ የሚጠቁሙ ክፍሎችየአሁኑ የውጊያ አቅጣጫ በዚህ መልኩ እንዲሆን መደረጉ ይህንኑ ለመፈተንም ጭምር ነውብለዋል።

በሌላ ዜና በሶማሌ ያለው ሰራዊት የመመለስ ጥያቄ ማንሳቱና ሁለት ጄኔራሎች ጦሩን ለማወያየት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጦሩ መስዋዕትነት እየከፈለ በተደጋጋሚ የተቆጣጠረውን ቦታ እንዲለቅ ትዕዛዝ ሲቀበል መቆየቱ ሌላው የቅሬታው መነሻ ሲሆን በሶማሌ ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ይህንኑ ነቅፎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በህወሃት የሚመሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሶማሌ ስለተገደሉት ወገኖች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አክርረው አለመጠየቃቸው፣ ላለፉት አምስት ዓመታት 99.6 በመቶ ህወሃት የነገሰበት ማኅበርም (ፓርላማ) ለይስሙላ እንኳን ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ በርካቶች የሚተቹበት አገራዊ ጉዳይ ነው።

http://www.goolgule.com/tplf-starts-war-wounded-soilders-seen/

በአዲስ አበባ ዛሬ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ፈንጂ ተገኘ በሚል የወያኔ ደህነቶችና ፖሊሶች ወከባ ሲፈጥሩ ዋሉ

አምባሳደር ቪኪ ሐልድስተን ከዚህ ቀደም የስርኣቱ ደህነቶች ራሳቸው ፈንጂ ጠምደው ማፈንዳታቸውን መናገራቸውን ዊክሊክስ አጋልጦ ነበር




ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 በልዩ ስሙ ቦሌ ሚካኤል ታክሲ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት በሩ አካባቢ ዛሬ አርብ መስከረም 7 ቀን 2008 ከቀኑ 5 ሰዓት ተኩል ጀምሮ አነስተኛ ፈንጂ ተገኘ ተብሎ ህዝቡ በፖሊሶች ከአካባቢው እንዲርቅ በማድረግ ብዛት ያላቸው ደኅንነቶችና ፖሊሶች አካባቢው ተቆጣጥረውት መዋላቸውን የህብር ሬዲዮ ምንጮች ከስፍራው ገለጹ።

ህዝቡም ግማሹ በድንጋጤ ሲሯሯጥ አንዳንዱ ‹‹ይሄማ የተለመደ ድራማ ነው!›› በማለት ችላ ብሎ ውሸት በመሆኑ ተጠግቶ ለማየት ሲሞክር ፖሊሶቹም ግማሾቹ እየሳቁ ‹‹ እረ ሂዱ ›› በማለት በፌዝ ህዝቡን ሲያባሩ ማየታቸውን እነዚሁ ምንጮግ ገልጸው በዚህ ሳቢያ ንጹሃን ተወንጅለው ቢታሰሩ ያስገርማል ሲሉ ከወዲሁ ምንጮቻችን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የደኅንነት አባሎችና የአካባቢው የቀበሌ ሰራተኞች ከፈንጂ መከላከያ ልዩ ልብስ የተሰራላቸው ይመስል ፈንጂው አጠገብ በመቆም ለፈንጂውም ለኢህአዲግም ታማኝነታቸውን ለማሳየት የሚጥሩ አስመስለውት ነበር፡፡ በአካባቢው በድብቅ ለኢህአዲግ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችም በዛሬው ቀን ሰፊው ህዝብ እያንዳንዱን ባንዳ ለመለየት ችሏል ያሉት እነዚሁ ምንጮች አንዳንዶቹም አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ከደኅንነቶችን ጋር ሰላም በመባባል ማንነታቸውን አጋልጠዋል ሲሉ የታዘቡትን ጭምር ተቅሰዋል።

ፈንጂ የተባለውን ማን እንዳየው ለማጣራት የህብር ምንጮች ተጨማሪ የማጣራት ሙከራ ባገኙት መረጃ ፈንጂ ተብሎ የነበረው አረንጓዴ ከለር ያለውና አይተውት የማያውቁት ነገር ከሳይክል አጠገብ በማየታቸው በዕለቱ ተረኛ የነበሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥበቃ ደንግጠው መናገራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የፀረ ሽብር ሃይል በፍጥነት መጥቶ ካሜራውን ደግኖ የተመከሩ ፖሊሶችና ደኅንነቶችን በመቅረጽ ህዝቡ ላይ የስነ ልቦና ጫና ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ በዕለቱም የቦሌ ክፍለ ከተማ አየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ዋና ኃላፊ የሆኑት እና ፈላጭ ቆራጭ እየሆኑ የመጡት ኮማንደር ታፈረ ተጠምቀ ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ አዲስ በአይነቱም በይዘቱም ልዩ ልብስ ለብሰወው ቦታው ላይ በመገኘት ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ነበር፡ ያሉት እነዚሁ የዜና ምንጮቻችን ህዝቡና ፖሊሶች እንዲህም ደኅንነቶች በዚህ ሁኔታ ሰዉ ተፋጠው ቢቆሙም ከፎቁ ላይ ልጅ እግር ወጣት በመውረድ ወደ አቆማት ሳይክል ሲሄድ ሁሉም ሲጮህ ነሁኔታው ግራ የተጋባው ወጣት ‹‹ምንድን ነው?›› ብሎ ወደ ህዝቡ ቢያይ ‹‹ ከሳይክል ስር ፈንጂ አለ ዘወር በል›› ቢሉት ካሳይክል በታች ያለው የተቀመጠውን የሚያውቀው እቃ በመሆኑ ፈንጂ አይደለም ቀለል ያለ ኤሌክትሮኒክስ መሆኑን በአደባባይ ሲናገር ፖሊሶችና ደኅንነቶች በፍጥነት ያለምንም ጥያቄ ሳይክሉንና ልጁን በፖሊስ መኪና ይዘውት ወደ አልታወቀ ቦታ ሄደዋል፡፡ ነገሩ እንደታወቀ ሲያዩ እና ሁኔታው አላምር ሲላቸው ህዝቡን በታትነውታል፡፡

የፕ/ት ኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ተከትሎ <<የሽብር ጥቃት ታቅዷል ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አለህ>> በሚል ሀሰተኛ ክስ የታሰረውን ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ላይ አስቀድሞ ጭምር ክትትል ሲያደርጉና ከቤትም አስውጥተው እስር ቤት የወሰዱት ምርመራ ሲያደርጉበት የነበሩ ደኅንነቶች የዛሬው <<የፈንጂ ተገኘ>> የድራማው መሪ ተዋናይ ሆነው መዋላቸውን እነዚሁ የህብር ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል ፡፡

ስለ ሁኔታው ከአካባቢው እማኞች መካከል አንዳንዶች ሁኔታውን በመታዘብ ደግሞ ይሄን አሳበው ማንን ለማሰር እንደፈለጉ አልታወቀም፡፡ እንደለመዱት ሱማሌያውያንና ማፈሳቸው አይቀርም ለእራሳችንም ግን ያሳጋል ሲሉ ከወዲሁ ድራማው የተፈለገው ለአፈና መሆኑን ግምታቸውን ሰጥተዋል። ፈንጂ ተገኘ የተባለበት አካባቢ በአሁኑ ሰዓት የተለመደውን ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ሰሞኑን ከኤርትራ የከዱትን የትህዴን የቀድሞ ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስግዶም መዋሰት አቅቷቸው በተደጋጋሚ ሲደናገሩ በታየበት መግለጫ ላይ የኤርትራ መንግስት ግንቦት ሰባትን ጨምሮ በአገሩ ያሉ በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ነፍጥ ያነሱ የነጻነት ተዋጊዎችን በማሰማራት ለሽብር ይልካል ሲሉ መክሰሳቸውን ተከትሎ ስርዓቱ የሆነ ነገር እንዳያፈነዳ የሚል ግምት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.ኤ.አ ሴፕተምበር 16 ቀን 2006 በአዲስ አበባ ካራ ቆሬ አካባቢ በቤት ውስጥ የኦነግ አባል ሳይሆኑ ናቸው የተባሉና በቤት ውስጥ በያዙት ፈንጂ ፈንድቶባቸው ሞቱ የተባሉትና ኦነግና የኤርትራ መንግስት አፈነዱት በተባለው ሶስቱም በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመውና በጊዜው ዶ/ር መረራ ጉዲና የሚመሩት የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ(ኦብኮ) አባል በመሆናቸው አስቀድሞ በስርዓቱ በፈጠራ ወንጀል የታሰሩ ሲሆኑ የፈነዳውን ሆን ተብሎ በህወሃት-ኢህአዴግ አገዛዝ መሆኑን ዊክሊክስ የአሜሪካ ኤምባሲ የጊዜው ጉዳይ ፈጻሚ ሆኑት ቪኪ ሐድልስተን(Vicki J. Huddleston) ለመንግስታቸው የላኩትን የምስጢር መረጃ ማጋለጡ ይታወሳል።


በዛሬው የአዲስ አበባ የፈንጂ ተገኘ ድራማ የአገዛዙ መገናኛ ብዙሃን ምን ብለው የስርዓቱን የፈጠራ ውሸት እንደሚያቀርቡ እየጠበቅን ነው ሲሉ የህብር ሬዲዮ ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46766

Wednesday, September 16, 2015

የዞን ፱ ጦማሪያን የዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ


“ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ እንዳስታወቀው የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች መብትን በማፈንና በማሰር ኢትዮጵያ ከአስር የዓለማችን አገራት ውስጥ እንደምትገኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ውብሸት ታዬን ጨምሮ የዞን ፱ ጦማሪያኑ ናትናኤል ፈለቀ፣አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉ አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አክሎ ገልጽዋል።


ኢትዮጵያ የጸረ ሽብር አዋጁን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረችበት እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከ2009 ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች ታስረዋል። በ2014 17 ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን፣ በዚህ አመት ጋዜጠኞችን በማፈን አገሪቱ በአለም የ4ኛ ደረጃን ይዛለች።


የዞን 9 ጸሃፊዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጭቆና፣ ሙስናና የማህበራዊ ፍትህ እጦት ሲያጋልጡ መቆየታቸውን የገለጸው ሲፒጄ፣ በጋራ የሚጽፉዋቸው ጽሁፎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ ሲታፈኑ ቆይተዋል ብሎአል። የዞን 9 ጸሃፊዎች መገናኛ ብዙሃን በገንዘብ እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በመንግስት በሚደርስበት አፈና በተደከሙበት ወቅት፣ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሲፒጄ እውቅና እንደሰጣቸው በመግለጫው አስታውሷል።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46715

Sunday, September 13, 2015

የአመቱ ምርጥ ባለጌ ሰው! (በጌታቸው ረዳ)

መስከረም 1/2008 ዐ.ም አዲስ አመት የኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ “የአመቱ ባለጌ ሰው” አፈላልጎ በብልግናው የመረጠው “የአመቱ ባለጌ ሰው” ባሕርዳር የሚኖረው ፎቶግራፉ ከላይ የሚታዬው “አለምነህ መኮንን” /ን ነው። አለምነህ መኮንን በጎሳው “አማራ” ነው። ወያኔ “አማራ ክልል” ብሎ ጸረ አማራ አጀንዳው ለማራመድ እንዲመቸው ባለ ሁለቱ ሕበረ ቀለም (ቢጫና ቀይ) ባንዴራውን በቅጅ አዘጋጅቶ፤ እንደ ግኡዝ ዕጭቃ አድቦልቡሎ ወያኔ ከሰራቸው፤ ስብእናቸውን አውልቆ ጠርቦ በምስሉ የቀረጻቸው፤ እራሳቸወን የማይመስሉ፤ ትንንሽ ሕሊና ያላቸውን ሰዎችን ትግራይ ሜዳ ውስጥ የሕሊና አጠባ አድርጎ ተሸክሞአቸው አማራውን ሕብረተሰብ እንዲዘልፉለት ጎጃም ክ/ሐገር ባሕርዳር ውስጥ ከሾማቸው የወያኔ ብአዴን አማራዎች መካካል አለምነህ መኮንን ነው።

አለምነህ መኮንን ከነ ደመቀ እና ከነ ወንድወሰን የመሳሰሉ አማራዎች ሆኖ የወያኔ አሽከር ሆኖው ወያኔ ሲሞት ከወያኔ ጋር ለመሞት ከተዘጋጁ የአማራን ሕብረተሰብ ከሚያሰድቡና ከሚሳደቡት ማፈሪያዎቹ አንዱ ነው። ወያኔ እንደ አፓርታይድ በቋንቋ ክልሎ ካዘጋጃቸው አማራ ብሎ ከሚጠራቸው “ክፍለ አፓርታይድ” አካባቢዎች አንዱ ከሆነው “የአማራ ክልል” ምክትል ፕረዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሓለፊ ነው። አለቆቹ አማራን ስለዘለፈላቸው አሜሪካ ድረስ ልከው ሰሞኑን ካንሳስ ሲቲ አየር ማረፊያ ጣቢያ እንደታዬ ዜናዎች እየዘገቡ ነው።

ይህ ሰው አባቱን እናቱን ዘመዶቹን በጠቅላላ አማራውን ሕብረተሰብ
“ስንፋጭ” ትምክህት የተጠናወተው፡፤ትምክሕትነቱን ያልተወው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር፤ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ተግባብቶ መኖር የማይችል፤ የሸተተው እግሩ እንዳይሸት ከጫማው ስር ‘የባሕር ዛፍ ቅጠል ያደረግበታል”፤ /ዚስ ኢዝ ቴክኖሎጂ!………ባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው። ልሃጩን ማራገፍ አለበት! ይኼ ላሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም። ማንኛወም ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መነሻው አማራ ክልል ነው። ይላል። ምክንያቱንም ሲገልጽ “ትምክህተኝነትን አንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው። ያንን ምግብም እየተመገበ ያቅራራል።” እያለ ተሰብሳቢ ካድሬዎቹን ሳቅ በሳቅ እያደረገ በሕዝብ ክብር ሲያላግጥ በድምፁ የተቀዳ ዋልጌ ግለሰብ ነው።

ይህ ወላጆቹን እና ሕዝብን የሚሰድብ ስድ ግለሰብ፤ “አማራው ይህ ሰንፋጭ ትምክሕቱ በቤንሻንጉል እና በተቀሩት አካባቢዎች ለመሰደድ ምክንያት ሆኖታል።ሲል ተሳድቧል። ያውም እዛው በአማራዎች አገር ፤ አማራዎች በሚኖሩበት በባሕርዳር ከተማ! ወይ ዘመን! አያሰማን ጉድ የለ!

ከትንሽም ትንሽ ሰው መሆኑን የሚያሳይ “ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ፤ የተቀዳው ድምፅ ይፋ ሲሆን ‘የሚመልሰው በማጣቱ ተደናግጦ ለካድሬዎቹ ጋዜጠኞቹን ሰብስቦ (አፋጥጠው ከነማስረጃው ሊወጥሩት አንደማይችሉ ስላወቀ)፤ ይህ እኔ አልተናገርኩም፤ የቴክኖሎጂ “የቆርጦ ቀጥል ስራ ነው” ሲል ንግግሩ ከሚያሳውቅበት ድንጋጤ ጋር ወዲያ ወዲህ ሲረግጥና ሲዘላብድ ተደምጧል። አለቆቹና ካድሬ ጸሐፊዎቹ በወያኔ ድረገፆች ላይ (አውራምባ ድረገጽ፤ትግራይ ኦን ላይን፤አይጋ… ላይ የተጻፈውን ተመልከቱት)፤ እሱን ለመከላከል ሲሉ ያልፈነቀሉት የሽፋን ጥረት አልነበረም። ሆኖም አገር ውስጥ የሚገኘው ‘ዩዲጀ’ የተባለው ፓርቲ የፔትሽን /የፌርማ የማሰባሰብን ስራ በመስራት ከሥራው እንዲባረር ቢጥርም፤ “ክቡር መሪያችን ከሞታቸው በፊት….” እያለ ጌታውን መለስ ዜናዊን ሲያሞካሽ ያደመጡት ጌቶቹ ከሥራው ሊያግዱት አልፈለጉም እና እዛው ሆኖ አማራውን ሕዝብ መዝለፉን እንዲቀጥል አድርገዋል። ሆኖም የባሕር ዳር ሕዝብ በነቂስ በመውጣት “ከባዶ ጭንቅላት፤ ባዶ እግር ይሻላል!” የሚል መፈከር ይዘው አዳባባይ ወጥተው፤ “ስድ አደግ”፤ “ሙጀሊያም አፍ” እና “የወያኔ መጸዳጃ የሚል ቅጥያ ስም ተሰጥቶታል።

ይህ ስድ አደግ’ ሙጀሊያም፤ጉርፉጥ አፍ (ግረፉጥ ማለት ትግርኛ ነው፤ ባለጌ ያልታረመ ፤ ማለት ነው” አማራውን ሕዝብ የዘለፈበትን ስድ አንደበቱን ለማድመጥ የሚከተለውን የአውዲዮ አድራሻ ይጫኑ። የአመቱ ባለጌ ሰው እንዴት እንደመረጥኩት መረጃው እራሱ ይናገራል። አመሰግናለሁ፤ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)፤ በዚህ ሦሰት ቀን የሚወጣ ሌላ ዝግጅት ስላለ፤ እሱንም እንዳያመልጣችሁ ይሁን። “የአመቱ ባለጌ ሰው” ሲናገር በአንደበቱ ይኼውና አድምጡ። ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት የሕሊና ድኩማን ተሸክማ ትገኛለች።


ጌታቸው ረዳ/getachre@aol.com

http://satenaw.com/amharic/archives/10322

Friday, September 11, 2015

“ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በህወሃት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ አሰሙ” የፌስቡክ ተቃዋሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል !



የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ ላይ በጥንቃቄ ተመርጠው የተጠሩ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ፡፡ የትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በአባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት አንጃ አሳወቀ። አንጃው ይህንን አብዮታዊ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት አለፈ …?” በሚል አጀንዳ በየመንግሥት መስርያ ቤቶች፣ ከመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ካድሬዎችና ነዋሪዎች ውይይት በተካሄደበት ጊዜ ነው።

በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3/13/2007 ዓም በአቶ ተስፋአለም ተወልደብርሃን (የመቀሌ ከንቲባ) አቶ አሰፋ ተገኝ ምክትል ከንቲባ የተመራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆንየህወሓት ጉባኤ ምን ይመስላል?” የሚል አጀንዳ ተሰጥቶት ነበር። የትግራዩ አንጃ በጉባኤው ወቅት በፌስቡክና በተባራሪ ወሬ የአቶ አባይ ወልዱ ስም ክፉኛ ጠፍቷል በሚል እሳቤ የስም እዳሴ እያካሄዱ ነው።

1) ህወሓት ተከፋፍሏል የሚል ወሬ ውሸት ነው።

2) ዳዊት ገብረእግዚአብሔር በትግራይ የሰጠው ቃለ መጠይቆች ውሸት ናቸው።

3) በፌስቡክ የሚሰራጩ መልዕክቶች ውሸት ናቸው፤ እንዳታምኑ።

4) የጉባኤው ተሳታፊዎች ሚስጢር እንዲጠብቁ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም በቀጥታ ስርጭት ሊባል በሚችል ደረጃ የስብሰባው መረጃ በፌስቡክ ተዘግቧል።

5) በአሁኑ ሰዓት ሁለት ዓይነት ጠላቶች አሉን። ፊት ለፊት ወጥተው የሚታገሉን እንደ ዓረና የመሰሉ እና በውስጣችን ሆነው የሚታገሉን ኪራይ ሰብሳቢ ሃይሎች (ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በፌስቡክ ደረጃ ህወሓት መስለው ጀርባችን የሚወጉን ሃይሎች) ናቸው።

6) አባይ ወልዱ ሙስናን የሚጠየፍ፣ ታግሎ የሚያታግለን ጀግናና ብቁ መሪ ነው።

7) በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን።

8) ጉባኤው ፍፁም ዲሞክራሲያዊና በድል የተጠናቀቀ ነበር ወዘተ
የሚል ሃሳብ ወደ ተሳታፊዎች አቅርበዋል።

ተሰብሳቢዎቹ ታማኝ ካድሬዎችና አባላት በጥንቃቄ የተመረጡ ቢሆኑም ያቀረቡት ሃሳብና ተቃውሞ ግን ስብሰባው ላዘጋጀው አካል አስደንጋጭ ነበር።

ከተሳታፊው የቀረቡት ጥያቄዎች፤

) አባይ ወልዱ በጉባኤተኛ 20 (የፌስቡክ ማህበረሰብ ከክፍል 20ኛ፤ ከዩኒት 1 ብሎ የቀለደበት ነው) ደረጃ ተመርጦ እያለ በሊቀመንበርነት እንዴት ሊመረጥ ቻለ? እዚህ ላይ የጉባኤው ዲሞክራሲያዊነት የቱ ላይ ነው?

) እነ አርከበ በድምፅ እንዲሳተፉ የተደረገበት፣ ለማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይወዳደሩ የተከለከሉበት አሰራር በየትኛው ደንብ ይገኛል?

) ዘመኑ ያመጣው የፌስቡክ ቴክኖሎጂ ህዝቡ እንዳይጠቀም እርምጃ እንወስዳለን ማለታችሁ ጊዜው 21 ክፍለ ዘመን መሆኑ ስላልገባችሁ ነው? የሃይል እርምጃው ቴክኖሎጂውን ምን ያህል ይቆጣጠረዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?

) አቶ ዳዊትና ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚነሱት ጉዳይ በመሬት ያለና በየዕለቱ የሚያጋጥመን ሃቅ ሆኖ ሳለ አትመኑት፤ ውሸት ነው፤ ማለታችሁ ችግሮቹን ለመፍታት አቅም እንዳጠራችሁ አያመላክትም ወይ? የሚሉትና ሌሎች ፈታኝ ጥያቄዎችና ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆኑ የመቀሌ ከንቲባና ምክትሉ የሚመልሱት አጥተው አንገታቸው አቀርቅረው በሃፍረት ከስብሰባው ወጥተዋል።

የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎች የመሩት የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባዎች እየተካሄዱ ያሉ ሲሆኑ ዘመቻው አቶ አባይ ወልዱ የደረሰባቸው የይውረድልንና የስም ማጥፋት ዘመቻና የጠፋው ስም እንደገና የማደስ ስራ ተጠምደው ይገኛሉ።
የዚህ ዘመቻ ትኩረት ተደርጎ ያለው ፌስቡክና የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው። ሰብሳቢዎች በተለያዩ መድረኮች ፌስቡክ ወጣቱ ትውልድ በአሉታዊ ጎን እያበላሸው፣ የተቃውሞ መንፈስ እየበረዘውና እየበከለው በመሆኑ መንግስት እርምጃ ይወስዳል በማለት አዋጅ እያስነገሩ ይገኛሉ።

በክፍለ ከተሞች ከተካሄዱ ስብሰባዎች የሓወልቲ፣ ዓይደር፣ ሓድነትና ቀዳማይ ወያነ ተሰብሳቢዎች ከፍተኛ ውጥረት የተፈጠረ ሲሆን ባለመግባባት ሊበተን ችለዋል።

ፌስቡክ አስመልክተው ከቀረቡት የአብዮታዊ እርምጃ ይወሰዳል ዛቻ ለትግራዩ አንጃ ደጋፊዎች የቀረበ ግምገማበቁጥር እኛ እንበዛለን፣ ለኢንቴርኔት አክሰስ እኛ እንቀርባለን፣ እነዚህን በጣት የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተቃዋሚዎች መቃወምና ማሸነፍ ለምን አቃተን…?” የሚል ቁጭት አቅርበዋል።

እቺ ነገር መንግስቱ ሃይለማርያምትጥቅ አቀረብን፣ ስንቅ አቀረብን፣ አሁን የቀረን ልብ ማደል ነው። እንደ ወያነ ጠንክራችሁ አትዋጉም ወይ…!” ብሎ ያደረገው የተስፋ መቁረጥና የስርዓቱ ማብቅያ አመላካች ንግግር በእጅጉ ይመሳሰላል።
የህወሓት አንጃዎች ክፍፍል ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በነዶ/ ሰለሞን ዑንቋይ ለቀናት የፈጀ ሽምግልና ከመበተን እንደዳኑ ፀሓይ የሞቀ ሃቅ ለመካድ ቢሞክሩም ከህዝቡ የተሸፈነ ግን አልነበረም።

አሁን በመላ የትግራይ ወረዳዎች የአባይ ወልዱን ስም ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የአዲስ አበባው አንጃ ፊታውራሪ የሆኑት ደብረፅዮን 12 ጉባኤ ላይ በፌስቡክ የሚነሱ ሃሳቦች እንደ ትልቅ የሃሳብ ምንጭ ተቆጥረው በጉባኤው ቀርበው እንደተወያዩበትና ለጉባኤው እንደ ግብአት እንደተጠቀሙበት ለቪኦኤ መግለፃቸው ይታወሳል።
የአባይ ወልዱን ስም ለማጥፋት አገልግሎት ላይ ውለዋል የተባለው ፌስቡክና ተቃዋሚ ተጠቃሚዎች አብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል። የእርምጃው ዓይነት ምን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን በውል አልታወቀም። ሆኖም የኢንቴርኔት ማእከላት ሊዘጉ ይችላሉ። ማነው ትግራይ ሰሜን ኮርያ ያላት? ያው ውድድራችን ከሰሜን ኮርያ መሆኑ ነው።

ትግራይ ለምትገኙ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያውያን አብዮታዊ እርምጃ እንዳይወሰድባችሁ የመንፈስ ዝግጅት ብታደርጉ እንመክራለን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…!

http://www.goolgule.com/tplf-to-take-revolutionary-action-on-facebook-users/