የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ እንዳስታወቀው የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች መብትን በማፈንና በማሰር ኢትዮጵያ ከአስር የዓለማችን አገራት ውስጥ እንደምትገኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ውብሸት ታዬን ጨምሮ የዞን ፱ ጦማሪያኑ ናትናኤል ፈለቀ፣አቤል ዋበላ፣በፍቃዱ ኃይሉ አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አክሎ ገልጽዋል።
ኢትዮጵያ የጸረ ሽብር አዋጁን ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረችበት እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከ2009 ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች ታስረዋል። በ2014 17 ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን፣ በዚህ አመት ጋዜጠኞችን በማፈን አገሪቱ በአለም የ4ኛ ደረጃን ይዛለች።
የዞን 9 ጸሃፊዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጭቆና፣ ሙስናና የማህበራዊ ፍትህ እጦት ሲያጋልጡ መቆየታቸውን የገለጸው ሲፒጄ፣ በጋራ የሚጽፉዋቸው ጽሁፎች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ ሲታፈኑ ቆይተዋል ብሎአል። የዞን 9 ጸሃፊዎች መገናኛ ብዙሃን በገንዘብ እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በመንግስት በሚደርስበት አፈና በተደከሙበት ወቅት፣ ላደረጉት አስተዋጽኦ ሲፒጄ እውቅና እንደሰጣቸው በመግለጫው አስታውሷል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46715
No comments:
Post a Comment