Wednesday, September 23, 2015

የኣንድነት ችቦ እየተንቦገቦገ ነው


ከወያኔ የዘር ኣገዛዝ በፊት የኢትዮጵያ መለዮ ለባሾች ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ስለነበሩ ከሥልጠና ቦታቸው ጀምሮ በየደረሱበት የውጊያ ዐውደ ግንባርና የጦር ሠፈር ኑሮኣቸው እንደ ወንድማማች፣ እህትማማችና ጓደኛሞች የሚተያዩ  ነበሩ እንጂ የዘር ቆጠራ ውስጥ ኣይገቡም ነበር። ኣብሮ መብላትና መጠጣት፣ ኣብሮ መዝናናትና ለሞትም ሆነ ለድል ኣብሮ መሰለፍን ዓላማቸው ኣድርገው የሚንቀሳቀሱ ነበሩ። የትግል ኣጋራቸውን ሕይወት ከተቃራኒው ጦር ኣረር ለማዳን እንጂ ጓደኛቸውን መግደልና ማስገደል እንኳን ሊደረግ ታስቦም ኣያውቅም ነበር።

ወያኔ ሥልጣን ከያዘ በኋላ ችግር ሳይኖር ራሱ በራሱ ላይ ችግር በመፍጠሩ ሁለት ኣጣብቂኝ ውስጥ ገባ። ሌሎችን ማመን ስለኣልቻለ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በትግራይ ተወላጆች ብቻ ለማንቀሳቀስም ዓላማው ነበር። መለዮ ለባሾቹንም በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዳያዋቅር በቂ ሊሆኑለት ኣልቻሉም። ስንቱ ቦታ ይሰለፋሉ። በሆኑለት ደስ ባለው ነበር። ስለሆነም ሌሎችን በሁለተኛ ዜጋነት ቀጥሮ  ማሠራቱ ኣይቀሬ ሆነበት። የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ግን በመሪነት እንዲያገለግሉ ኣደረገ።

ይኸ የትግሬዎችን በበላይነት የማየቱ ተንኮል ሌሎችን እንዳያስነሳበት እያንዳንዱን ብሔር በጥርጣሬ እንዲተያዩ  የዘር ልዩነት መርዝ ጋታቸው። ስለሆነም ሁሉም እንደ ጭዳ በግ ወደ እርድ መነዳት ሆነ። ኣትግደለኝ፣ ኣታግለኝ፣ ኣታንገላታኝ፣ መብቴን ጠብቅልኝ፣ ወዘተ የሚል የመብትና የዜግነት ጥያቄዎች በራቸው ተዘጋ። የጋራ ጠላታቸውን ለመፋለም መዘጋጀት ሳይሆን እርስ በርስ እንዲፋጠጡ ሆነ። ሲዘምቱ ግን ወርቃማዎቹ ከኋላ ሆነው ወደፊት እያሉ ይነዱኣቸዋል፣ ወደ እሳቱ ይማግዱኣቸዋል። እንደ እንስሳ የተጠመዱ ፈንጂዎች ላይ እንዲሔዱ ኣደረጉኣቸው። የፈንጂ መሞከሪያ ኣደረጉኣቸው። የጠላት ጦር ሳይገድላቸው ራሱ ወያኔ ገዳያቸው ሆነ። እኔ ልቅደም፣ እኔ ልቅደም ይባባሉ ነበር እንጂ ኣንዱ ሌሎችን ወደ እሳት ወላፈን የሚገፈትርበት ጊዜ ኣልነበረም። ያንን ጊዜ ወያኔ እንደ ኋላቀር ቆጠረው።

በወርቃማው ዘር ላይ ተንተርሶ  በመሣሪያ ኃይል ሀገሪቱን የሚያሽከረክረው የወያኔ መንግሥት በሰሜን ጎንደር፣ በሰሜን ወሎና በሰሜን ኣፋር እያደረገ እንዳለው ጨርቆቹ ቢያልቁለት መሬቱ ስለሚለቀቅለት ወርቃማዎቹን ያሰፍርበታልና ጦርነትን ይፈልጋል፣ በሰበቡ ጨርቆቹ እንዲያልቁለት ይፈልጋል። “የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች፣ እነርሱም ያልቃሉ እርሷም ትሞታለች።” እንደተባለው ወያኔ መራሹ መለዮ ለባሽ እስከ ዛሬ ባየው የዘር ፖለቲካና የነርሱ መገለል ቆም ብለው እንዲያስቡ እያደረጋቸው ጀርባቸውን እየሰጡ ናቸው። ወያኔዎቹ በለኮሱት እሳት ራሳቸው ይቃጠሉበት እንጂ እኛ በምን ተዕዳችን እያሉ ናቸው። ወያኔ የማይሆንና ሊሆንም የማይችል መርዝ ላለፉት 24 ዓመታት ቢረጩም ለጊዜው ትንሽ ተሳክቶለት ቢፈነጩም ዘለቄታ ኣላገኘም። ኣሁን ወደ ዜሮ እየወረደ ነው።

ወያኔ ላለፉት ኣርባ ዓመታት የኢትዮጵያውያንን ኣንድነትና ኣብሮነት ለማፍረስ እየጣረና እያስገደደም እስከ ዛሬ ቢለፋም ሊሳከለት ኣልቻለም። እንዲያውም ራሱን እየለበለበው ከመሆንም ኣልፎ በሰሜኑ ኢትዮጵያችን በኩል የሚያቃጥለው የኣንድነት መሠረት ተጥሎ  ወደርሱ እየገሠገሠ ነው። ይህ ወያኔን እንደ ጎርፍ ውሃ ጠራርጎ  የሚወስደው በጠንካራ መሠረት ላይ የተጣለው የኣንድነት ኃይል በቅርቡ እንደታየው የተቃዋሚው  ሕዝባዊ ኃይል ከየብሔረሰቡ የተውጣጣ ሆኖ ተገኝቷል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ኣብሮነት ሊያለመልም ነው። ዱብ ዕዳ ሆኖበት ሊዋጥለት ያልተቻለውን ኣንድነትን የማፍረስ ዘመቻ የሚያፈርሱ ኃይሎች መፈጠራቸው የወያኔን መንደር እያፈራረሰው ነው። ይህ የሚያሳየን ወያኔ ለማፍረስ ደፋ ቀና ሲል የቆየውን የኣርባ ዓመት ትግል ድባቅ መታበት።
ወያኔ ከሰውም፣ ከእንስሳቱና ከደኖቹም ጋር የተጣላ ስለሆነ ተግባሩ መቀበሪያ ቦታም ሊያሳጣው ነው። ግዑዟንም መሬታችንን ደኖቿን ኣቃጥሎ ያራቆጣትና ያጎሳቆላት ስለሆነ ሲሞቱም ለመቃብራቸው ኣትመቻቸውም። ትተፋቸዋለች። ሬሳቸውን ኣውሬዎችና ኣሞራዎችም ኣይበሉም። እነርሱንም መከለያ ወይም መጠለያ ኣሳጥተዋቸዋልና ይጠየፉኣቸዋል።

ቸሩ ነኝ

ቸር ይግጠመን

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46866

No comments:

Post a Comment