ህዝቡም ግማሹ በድንጋጤ ሲሯሯጥ አንዳንዱ ‹‹ይሄማ የተለመደ ድራማ ነው!›› በማለት ችላ ብሎ ውሸት በመሆኑ ተጠግቶ ለማየት ሲሞክር ፖሊሶቹም ግማሾቹ እየሳቁ ‹‹ እረ ሂዱ ›› በማለት በፌዝ ህዝቡን ሲያባሩ ማየታቸውን እነዚሁ ምንጮግ ገልጸው በዚህ ሳቢያ ንጹሃን ተወንጅለው ቢታሰሩ ያስገርማል ሲሉ ከወዲሁ ምንጮቻችን ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የደኅንነት አባሎችና የአካባቢው የቀበሌ ሰራተኞች ከፈንጂ መከላከያ ልዩ ልብስ የተሰራላቸው ይመስል ፈንጂው አጠገብ በመቆም ለፈንጂውም ለኢህአዲግም ታማኝነታቸውን ለማሳየት የሚጥሩ አስመስለውት ነበር፡፡ በአካባቢው በድብቅ ለኢህአዲግ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችም በዛሬው ቀን ሰፊው ህዝብ እያንዳንዱን ባንዳ ለመለየት ችሏል ያሉት እነዚሁ ምንጮች አንዳንዶቹም አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ከደኅንነቶችን ጋር ሰላም በመባባል ማንነታቸውን አጋልጠዋል ሲሉ የታዘቡትን ጭምር ተቅሰዋል።
ፈንጂ የተባለውን ማን እንዳየው ለማጣራት የህብር ምንጮች ተጨማሪ የማጣራት ሙከራ ባገኙት መረጃ ፈንጂ ተብሎ የነበረው አረንጓዴ ከለር ያለውና አይተውት የማያውቁት ነገር ከሳይክል አጠገብ በማየታቸው በዕለቱ ተረኛ የነበሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥበቃ ደንግጠው መናገራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የፀረ ሽብር ሃይል በፍጥነት መጥቶ ካሜራውን ደግኖ የተመከሩ ፖሊሶችና ደኅንነቶችን በመቅረጽ ህዝቡ ላይ የስነ ልቦና ጫና ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ በዕለቱም የቦሌ ክፍለ ከተማ አየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ዋና ኃላፊ የሆኑት እና ፈላጭ ቆራጭ እየሆኑ የመጡት ኮማንደር ታፈረ ተጠምቀ ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ አዲስ በአይነቱም በይዘቱም ልዩ ልብስ ለብሰወው ቦታው ላይ በመገኘት ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ነበር፡ ያሉት እነዚሁ የዜና ምንጮቻችን ህዝቡና ፖሊሶች እንዲህም ደኅንነቶች በዚህ ሁኔታ ሰዉ ተፋጠው ቢቆሙም ከፎቁ ላይ ልጅ እግር ወጣት በመውረድ ወደ አቆማት ሳይክል ሲሄድ ሁሉም ሲጮህ ነሁኔታው ግራ የተጋባው ወጣት ‹‹ምንድን ነው?›› ብሎ ወደ ህዝቡ ቢያይ ‹‹ ከሳይክል ስር ፈንጂ አለ ዘወር በል›› ቢሉት ካሳይክል በታች ያለው የተቀመጠውን የሚያውቀው እቃ በመሆኑ ፈንጂ አይደለም ቀለል ያለ ኤሌክትሮኒክስ መሆኑን በአደባባይ ሲናገር ፖሊሶችና ደኅንነቶች በፍጥነት ያለምንም ጥያቄ ሳይክሉንና ልጁን በፖሊስ መኪና ይዘውት ወደ አልታወቀ ቦታ ሄደዋል፡፡ ነገሩ እንደታወቀ ሲያዩ እና ሁኔታው አላምር ሲላቸው ህዝቡን በታትነውታል፡፡
የፕ/ት ኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ተከትሎ <<የሽብር ጥቃት ታቅዷል ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አለህ>> በሚል ሀሰተኛ ክስ የታሰረውን ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ላይ አስቀድሞ ጭምር ክትትል ሲያደርጉና ከቤትም አስውጥተው እስር ቤት የወሰዱት ምርመራ ሲያደርጉበት የነበሩ ደኅንነቶች የዛሬው <<የፈንጂ ተገኘ>> የድራማው መሪ ተዋናይ ሆነው መዋላቸውን እነዚሁ የህብር ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል ፡፡
ስለ ሁኔታው
ከአካባቢው እማኞች መካከል አንዳንዶች ሁኔታውን በመታዘብ ደግሞ ይሄን አሳበው ማንን ለማሰር እንደፈለጉ አልታወቀም፡፡ እንደለመዱት
ሱማሌያውያንና ማፈሳቸው አይቀርም ለእራሳችንም ግን ያሳጋል ሲሉ ከወዲሁ ድራማው የተፈለገው ለአፈና መሆኑን ግምታቸውን ሰጥተዋል።
ፈንጂ ተገኘ የተባለበት አካባቢ በአሁኑ ሰዓት የተለመደውን ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ እ.ኤ.አ ሴፕተምበር 16 ቀን 2006 በአዲስ አበባ ካራ ቆሬ አካባቢ በቤት ውስጥ የኦነግ አባል ሳይሆኑ ናቸው የተባሉና በቤት ውስጥ በያዙት ፈንጂ ፈንድቶባቸው ሞቱ የተባሉትና ኦነግና የኤርትራ መንግስት አፈነዱት በተባለው ሶስቱም በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመውና በጊዜው ዶ/ር መረራ ጉዲና የሚመሩት የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ(ኦብኮ) አባል በመሆናቸው አስቀድሞ በስርዓቱ በፈጠራ ወንጀል የታሰሩ ሲሆኑ የፈነዳውን ሆን ተብሎ በህወሃት-ኢህአዴግ አገዛዝ መሆኑን ዊክሊክስ የአሜሪካ ኤምባሲ የጊዜው ጉዳይ ፈጻሚ ሆኑት ቪኪ ሐድልስተን(Vicki J. Huddleston) ለመንግስታቸው የላኩትን የምስጢር መረጃ ማጋለጡ ይታወሳል።
በዛሬው የአዲስ አበባ የፈንጂ ተገኘ ድራማ የአገዛዙ መገናኛ ብዙሃን ምን ብለው የስርዓቱን የፈጠራ ውሸት እንደሚያቀርቡ እየጠበቅን ነው ሲሉ የህብር ሬዲዮ ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46766
No comments:
Post a Comment