Thursday, April 18, 2013



ኢሕአግ ሰራዊት በዋልድባ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (ዜና)
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከወያኔው የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊትEthiopian People Patriotic Front ውጊያ በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።
የግንባሩ ሰራዊት በዋልድባ ልዩ ስሙ ሰቋር በተባለ ቦታ በሚያዚያ 8-2005 ዓ.ም የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መመኪያ በሆነው የፈጥኖ ደራሽ ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 25 ያቆሰለ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያው የተካሄደ ሲሆን በዚሁ እለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት 25 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል የተቀዳጀ ሲሆን፣ በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር ማርኳል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረጋቸው አውደ-ውጊያዎች ላይ በድምሩ 46 የፈጥኖ ደራሾችን ከጥቅም ውጭ በማድረግና 64 በማቁሰል የግንባሩ ሰራዊት የተሰለፈበትን ሐገራዊ ተልዕኮውን በመፈፀም በጠላት ላይ ከፍተኛ የሕይወትና የንብረት ኪሳራ በማድረስ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።
የግንባሩ ሰራዊት ጥቃቱን በፈፀመበት አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ስርዓቱ በሚያራምደው የግፍ አገዛዝ ከፍተኛ ምሬትና ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትም የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በማበርከት ሐገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ግንባሩ ሰራዊት እየተቀላቀሉ እንደሚገኙም ታውቋል።
    Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment