Tuesday, April 16, 2013

ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የተመለሱት ተፈናቃዮች ባዶ ሜዳ ላይ ተጥለዋል

april 16.2013
ከፍኖተ ሠላም ከተማ ወደ ተፈናቀልንበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞን ያሶ ወረዳ ከተመለስን በኃላ ሜዳ ላይ ተጥለናል ሲሉ ተፈናቃዮች አማረሩ፡፡
ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ‹‹ከነበርንበት ቦታ ስንፈናቀል በፖሊስ እተደበደብን ነው፡፡ ከፍኖተ ሠላም ከተማም በፖሊስ ተከበን ዛቻና ስድብ ከተፈፀመብን በኋላ ወደ ተፈናቅልንበት ያሶ ከተማ እንድንመለስ ተደረግን፡፡ከመመለሳችን በፊት የአካባቢው ህብረተሰብ እንዳይቀበለን የጥላቻና የዘር ቅስቀሳ ተከናውኖብናል፡፡አማራ ተቀብሎ መሬቱ ላይ የሚያሰፍር የክልሉ ነዋሪ ቢኖር መሬቱ እየተቆረሰ እንደሚሰጥበት  በአካባቢው ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል፡፡በዚህ ምክንያት ወደ የቦታችን መመለስ አልቻልንም፡፡››ሲሉ እየደረሰብን ነው ያሉትን በደል ለዝግግት ክፍላችን አስታውቀዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ ለዝግጅት ክፍላችን እንደሚገልጹት‹‹በአሁኑ ጊዜ ያሶ ከተማ ውስጥ ከብት ገበያ  ሜዳ ላይ ፀሀይና ዝናብ እተፈራረቀብን ይገኛል፡፡ወደ ቦታችን ትመለሳላችሁ ብለው ያመጡን ከልብ አምነውበት ሳየሆን የደረሰባቸውን ውግዘት ለማስቆምነና የፈፀሙትን ወንጀል  ለማረሳሳት ታስቦ ነው፡፡››ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ተፈናቃዮች በመጨረሻም ባስተላለፉት መልእክትም ‹‹በአንሁኑ ጊዜ የምንበላውም የምንጠለልበት ቦታም አላገኘንም፡፡ተመልሰን የመጣነውም ተገደን ነው፡፡እተፈሠፀመብን ያለውን ግፍና በደል ለሚመለከተው ሁሉ አሳውቁልን›› ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡
ከፍኖተ ሠላም ከተማ ወደ ተፈናቀልንበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞን ያሶ ወረዳ ከተመለስን በኃላ ሜዳ ላይ ተጥለናል ሲሉ ተፈናቃዮች አማረሩ፡፡
ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ‹‹ከነበርንበት ቦታ ስንፈናቀል በፖሊስ እተደበደብን ነው፡፡ ከፍኖተ ሠላም ከተማም በፖሊስ ተከበን ዛቻና ስድብ ከተፈፀመብን በኋላ ወደ ተፈናቅልንበት ያሶ ከተማ እንድንመለስ ተደረግን፡፡ከመመለሳችን በፊት የአካባቢው ህብረተሰብ እንዳይቀበለን የጥላቻና የዘር ቅስቀሳ ተከናውኖብናል፡፡አማራ ተቀብሎ መሬቱ ላይ የሚያሰፍር የክልሉ ነዋሪ ቢኖር መሬቱ እየተቆረሰ እንደሚሰጥበት  በአካባቢው ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል፡፡በዚህ ምክንያት ወደ የቦታችን መመለስ አልቻልንም፡፡››ሲሉ እየደረሰብን ነው ያሉትን በደል ለዝግግት ክፍላችን አስታውቀዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ በተደጋጋሚ ለዝግጅት ክፍላችን እንደሚገልጹት‹‹በአሁኑ ጊዜ ያሶ ከተማ ውስጥ ከብት ገበያ  ሜዳ ላይ ፀሀይና ዝናብ እተፈራረቀብን ይገኛል፡፡ወደ ቦታችን ትመለሳላችሁ ብለው ያመጡን ከልብ አምነውበት ሳየሆን የደረሰባቸውን ውግዘት ለማስቆምነና የፈፀሙትን ወንጀል  ለማረሳሳት ታስቦ ነው፡፡››ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ተፈናቃዮች በመጨረሻም ባስተላለፉት መልእክትም ‹‹በአንሁኑ ጊዜ የምንበላውም የምንጠለልበት ቦታም አላገኘንም፡፡ተመልሰን የመጣነውም ተገደን ነው፡፡እተፈሠፀመብን ያለውን ግፍና በደል ለሚመለከተው ሁሉ አሳውቁልን›› ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡
  Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment