Sunday, January 25, 2015

የአንድነት አባላት ላይ የታጠቁ ፖሊስና የደህንነት ሃይሎች ከፍተኛ ድብደባ አድርሰዋል፡፡


 በዛሬው ዕለት አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ፡፡ ሰልፈኞቹ ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ጽ/ቤት መንቀሳቀስ እንደጀመሩ በህወሃት/ኢህአዴግ የታጠቁ ፖሊስና የደህንነት ሃይሎች ከፍተኛ ድብደባ አድርሰዋል፡፡ የአንድነት በርካታ አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡ ዳግማዊ አይኑ ማየት አልቻለም፡፡ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ግርማ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል) ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ የነፃነት ጥያቄው በድብደባ አይቀለበስም!!! ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው ወደ ሀኪም ቤት ተወሰደው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡ ። ሴቶች እህቶቻችን እተደበደቡም ብትፈልጉም ግደሉን እያሉ ወደ ፊት ለመሄድ እየተሞከረ ነው። እጅግ በጣም ጭካኔ የተሞላበት ፣ አረመኔያዊ ተግባር በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ነው። 





http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17060





No comments:

Post a Comment