Tuesday, February 23, 2016

በኦሮሚያ ክልል ከ20 በላይ ዜጎች ትናንትና ዛሬ ተገደሉ

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም የአጋዚ ጦር በወሰደው የሃይል እርምጃ ከእሁድ ምሽት ጀምሮ 20 በላይ ዜጎች መገደላቸውንና 42 በላይ መቁሰላቸው ታወቀ።

በኦሮሚያ ክልል በሃረርጌ መቻራ፣ በደኖ፣ ጨለንቆ፣ አወዳይ፣ ሜጨታ፣ አብሮራና፣ ሃሮማያ በወለጋ ደምቢደሎ፣ ቄለም፣ ሳሲዶ፣ ወረዳ ባሎ ከተማ በአርሲ በቆጂ፣ በቡሌ ሆራ በገናሌ፣ በምስራቅ ሸዋ አዳሚቱሉ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ የነበረ ሲሆን ከባድ መሳሪያ ታንክና መትረየስ የታጠቁ የአጋዚ ጦር በተማሪዎችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ በመተኮስ 20 በላይ ኢትዮጵያውያንን መግደሉ ታውቋል።

በወለጋ ቄለምና ባሎ ከተማ አመኑ ተረፈ፣ ገለታ ነገሮ፣ ቢሉሱማ አብዲሳ፣ ቶሌራ መርጋ እና አርገኔ የተባለች ሴት በሰቃቂ ሁኔታ በመግስት ሃይሎች ተገድለዋል።

በሃረርጌ በመቻራ በበደኖና፣ ጨለንቆ ሃሰን አብደላ፣ አሳድ ኢብራሂም እና ሮባ ማሞ የተባሉ ወጣቶች በጥይት ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።

በመቻራ ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች ደረቱ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ ሌላ ወጣት አስከሬን ተሸክመው ጎዳና ላይ ሲወጡ ታይተዋል።

በዚሁ ከተማ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ 20 በላይ ሰዎች ወደገለምሶ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ታውቋል።
ተቃውሞ ከተነሳበት ህዳር 1, 2008 ጀምሮ ተቃውሞው የጸረ-ሰላም ሃይሎች ነው ከዚያም የመልካም አስተዳደር ቸግር ያመጣው ነው ሲል የተለያዩ መግለጫዎችን ያወጣው የመንግስት፣ በአርሲ-ሸሸማኔ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ጉዳዩ የጸረ-ሰላም ሃይሎችና አክራሪዎች ነው በማለት ንብረቶችን መውደማቸውን ገልጿል።ይሁን እንጂ የመከላከያ ሰራዊትና ፊዴራል ፖሊስ በወሰዱት የሃይል እርምጃ፣ ስለሞቱት ዜጎች ቁጥር እስካሁን አልተገለጸም።

ባለፉት 3 ወራት በተካሄደው ተቃውሞ 300 በላይ ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ፣ ቁጥሩ በውል ያልተገመቱ ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ 5000 በላይ ዜጎች ለእስር ተዳርገዋል


ኢሳት (የካቲት 22 2008)

http://www.satenaw.com/amharic/archives/13320

No comments:

Post a Comment