Tuesday, April 5, 2016

ባለፉት 3 ሳምንታት በኦሮምያ 2ሺህ 627 ሰዎች ታስረዋል


 መድረክ፤ ባለፉት 3 ሳምንታት ከአዲስ አበባ ከተማ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ ተቃውሞዎች የተሳተፉ 2ሺህ 627 ሰዎች በመንግስት ሃይሎች ታስረዋል ማለቱን ሮይተርስ ትናንት ዘገበ፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ መንግስት ተቃዋሚዎችን ያሰረው በቀጣይ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች እንዳይደረጉ ለመከላከል በማሰብ ነው ሲሉ መናገራቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በኦሮምያ ክልል በሚገኙ 12 የተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ 627 ሰዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር ውለዋል ማለታቸውንም ገልጿል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ በኦሮምያ ክልል በተደረጉ ተቃውሞዎች ከ200 ያህል፤ ሰዎች ሳይገደሉ አልቀሩም ማለታቸውንም ዘገባው አስታውሷል። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግሥት ኃላፊዎችን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ሮይተርስ ጠቁሟል፡፡

 ምንጭ – አዲስ አድማስ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/52989

No comments:

Post a Comment