Sunday, July 17, 2016

እናት ኢትዮጵያ በአንድነት በሚያምኑ በልጆቿ ነፃ ትወጣለች!!


የወያኔ ዘረኛ ቡድን ከጅማሮው ይዞ የተነሳውን አማራን የማጥፋት ኢትዮጵያንም የማፈራረስ ሴራ በተግባር ለመፈጸም ደፋ ቀና እያለ ሲገኝ በግልጽም ይሁን በድብቅ በተለያየ መንገድ ስልጣንን እና ጠብመንጃን መከታ በማድረግ በብአዴን ካድሬዎች እየታገዘ ከባድ ወንጀሎችን በአማራው ሕዝብ ላይ ፈጽሟል:: እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ሕዝብን የአማራ ማንነት በመደለዝ የትግራይ ክልል አካል እንዲሆኑ በማድረግ የሚፈጽመውን ደባ የተቃወሙ የወልቃይት ሕዝቦችን በማሰቃየት፣ በመግደልና በማሰር ላይ ይገኛል:: ይህንን የሕወሓት በሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ሽብር በመቃወም እንዲሁም የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ክልል አካልና ማንነቱ አማራ ነው ያሉ ሕጋዊና ሰላማዊ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አባላትን ለማፈን ሰሞኑን የተንቀሳቀሰው የሕወሓት ዘረኛ ቡድን በጎንደር ሕዝብ እፍረትን ተከናንቧል:: ይህን ተከትሎ የወልቃት ሕዝብ የወከላቸውን ኮሚቴ አባላትን በመያዝና በማንገላታት በቀጣይነት ለሕዝብ ያለውን ንቀት በማሳየት ተደጋጋሚ ወንጀሎች እየፈጸመ ይገኛል:: በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሕወሓት መሪነት የሚደረገውን ማንኛውም ግድያ እስር አፈና ማሳደድ እና ተመሳሳይ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እንደ ኢትዮጵያዊነቴ አጥብቄ እቃወማለሁ/አወግዛለሁ:: በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደረግ የዘረኝነት ዘመቻ ይቁም!!!
እናት ኢትዮጵያ በልጆቿ ነፃ ትወጣለች!!

ዳዊት ደምመላሽ

No comments:

Post a Comment