ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
ህወሃት በእሱና በራሱ ጉጅሌ አባላቶቹና ሚዲያዎቹ “በአገራችን ታሪክ ያልታየ ክስሰት በዋናነት ዜጎች በአንድነት፣ ከድህነት በማውጣት በደስታ የተሞላ ህይወትን ለማምጣት የኢኮኖሚ እድገታችን እያደገ ነው ይለናል” ይህ በሬዲዮ አዲስ አበባ፣ በሬዲዮ ኢትዮጵያ እና በሬዲዮ ፋና ብቻ ነው። ይህ ውሸት እንደተጠበቀ ሆኖ አዲሱ የለውጥ ምእራፍ ደግሞ የወያኔ ቡችሎች በየጊዜው ከህወሃት መጋረጃ በስተጀርባ ያለውን የተደበቀውን እውነት ወይም ግንቦት 7 ሲል የነበረውን የሚያረጋግጡ መረጃዎችን መስማት መጀመራችን ነው።
ህወሃታዊ መነቃቃትን ለማምጣት ደካሞችንና ለሆዳቸው ያደሩ ባለስልጣናቱን ሰብስቦ ስለ እድገት ጎዳናና ኃይል የሚያመረቁ ትሩፋቶችን በሚዲያዎቹ ያስነግራል። የዜጎችን የስነ ልቦና ውድቀት በከፍተኛ ደረጃ የሚፈልገው ህወሃት ባሪያዎቹንና አገልጋዮቹን በጥቅማጥቅም በማሸነፍ እውነትን ይደብቁለት ዘንድ ሁሌም ሙከራ ያደርጋል። አንዱም ተሳክቶለት አያውቅም እንጅ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የሆነው ህወሃትና የእነሱ ተላላኪ ወያኔዎች ጦር ሰብቀው፣ መሣሪያ ወድረውና በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲያቸው ተጠቅመው ሀገሪቷን እና ህዝቡን ከፋፍለው በዘር ካርድ ተጫውተው የስልጣን እድሜያቸውን ማራዘም ተቀዳሚ አጀንዳቸው እንጂ መቼም ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና እድገት አስበውም አልመውትም አይውቁም፡፡ የሶማሊያው ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ሙሃመድ የተናገረውም ይህንኑ ነው ተደጋገመ እንጂ።
የከፋፍለህ ግዛ የጫካ ፖሊሲያቸውን ተጠቅመው ሀገሪቷን እንደተቆጣጠሩ ለመዝለቅ በማስብ የግል የሥልጣን እርካታቸውን ለመጠበቅ ብቸኛ ስልት ሆኖ ያገኙት የሶማሊያ ፕሬዝዳንቱ እንደሚሉት ለሶማሊያው “አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጉራጌው፣ አፋሩ ከተባበሩ ለሶማሊያ አይመቹም። ስለዚህ ህወሃትን ደግፉና እነሱን ውጉ፤ አማራውና ኦሮሞው መቼም አይስማሙም።” በዚሁ ያልተገራ አንደበታቸው ደግሞ የህወሃቶቹ የአማራ ጎጅሌ ተላላኪ ባለስልጣናት አማራ ክልል ይሄዱና “የሶማሊያና የኦሮሞው ሰርቶ አደር ህዝብ የእንገንጠል ጥያቄ ሊያቀርቡብህ ነው” ይላሉ፤ ለባለታሪኩ የኦሮሞ ህዝብም ሄደው “አማራ ሊገዛችሁ ነው” የሚል ቆሻሻ የዘርን ክፍፍል መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ፣ ያልበሰለ ራእያቸውን ለማስፈጸም ሺ ምላስ ይሆናሉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ በረዥም የታሪክ ዘመኑ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈታተኑትን ጠላቶቹንና ተላላኪዎቹን የተንኮል አጀንዳ ቀድሞ ስለሚያውቅ ልዩነቱን አስወግዶና ቅድሚያ ለሀገሩ፣ ለአንድነቱ ሰጥቶ መሰሪ ጥቃታቸውን በማክሸፍና በማኮላሸት ረገድ ከፍተኛ ሚና ያለው ህዝብ፣ በእነዚህ የህወሃት/ኢህአዴግ የዘር ድብቅ አጀንዳ አይንበረከክም አይከፋፈልም። አማራውም፣ አሮሞውም፣ ጉራጌውም፣ ትግሬውም፣ ቤንሻንጉሉም፣ ደቡቡ አንድ ነው። ተከባብሮ ያለ እና የሚኖር ታላቅ ህዝብ በመሆኑ ከጠላቶቹ ህወሃት ከሀገር አጥፊ ዘረኞች የሚመጣበትን ቀድሞውንም ጠንቅቆ ያውቀዋልና አይገርመንም፡፡
ባለ ብዙ ምላሱ የወያኔ መንግስት መርዶ ነጋሪ እየሆኑ ያስቸገሩት ግለገል ፍየሎች የዚሁ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በሽታ ተጠቂ (victim) ናቸው። ብቻቸውን በተለቀቁ፣ ተንፍሱ በተባሉ ጊዜ በጀሮዎቻቸው የሚሰማቸው የተደበቀውን የእውነት ያለህ ጩኸት ነው የሚናገሩት። የህዝባቸውን በደል፣ ሰቆቃ እና የወያኔን እውነተኛ ገፅታና ያለበትን ተጨባጭ የዕድገትና የልማት ሁኔታ ያወጣሉ፣ ይናገራሉ።
ፕሬዚዳንቱ እፎይ ብሎ አዩኝ አላዩኝ ሳይል ያደረገው ንግግርም “ እኛ እንዳደግን ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረስን ተደርጎ በየጊዜው የሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው። አሁን በእጄ የያዝኩት ሪፖርት እውነት ስለመሆኑ እርግጠኞች አይደለንም፤ ከአሁን በፊት ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶችም እንዲሁ ናቸው። ግምገማ ለማለፍ ተብሎ በውሸት የተሞሉ በቁጥር የታጀቡ የውሸት ሪፖርቶች ናቸው የሚቀርቡት እንጅ እኛ በድህነት አረንቋ ውስጥ ነን ” ብሏል። የሚገርመው ፕሬዝዳንቱ ይህንን ውሸት ህዝብ የሚያውቀው አልመሰለውም፤ ለሁሉም በርታ አይዞህ ሆድ አይባስህ እኛም እያልን ያለነው ይህኑን አይን ያወጣ ውሸት እንታገለው ነው የምንለው።
አቶ አብዲና ሌሎችም ለሆዳችሁ ያደራችሁ ባለሰልጣናት ራሳችሁን ቀይሩ ውስጣችሁን አውሩ በታሪክ ተጠያቂ አትሁኑ፣ ህሊናችሁን አዳምጡ እንጂ ለህዝብ ጠላት ለሆነው የህዝብ ድጋፍ ከሌለው ለህወሃት ፍርፋሪ በማደር ሀገራችን ለማጥፋት ሁሌ ከሚያስቡ ከህወሃት ቡድኖች ጋር አብራችሁ ወገንን ማታለልና በዘር ካርድ መጫዎት ይብቃችሁ። የዲሞክራሲ ሃይሉን ጎራ ተቀላቀሉ፣ መረጃ አቃብሉ።
የወያኔ እውነተኛ ገፅታ ራሳቸውም እንደሚያረጋግጡት ይህ በመሆኑ፣ በየቦታው ዜጋን በማፈናቀል ህዝብ በሀገሩ ስደተኛ እንዲሆን ፊትም የጀመረውን ድብቅ ሥራ አማራውን በማሰደድ ያላቸውን ጥላቻ በእጥፍ በማሳደግ በርካታ አባዎራዎችን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ህይዎታቸው ጉስቁል እንዲሆን እያደረጉ ነው። ታዲያ ይህን እውነት እየሰማን እሰከ መቼ እንተኛ ይሆን? ግንቦት 7 ንቅናቄ ተነሱ ኑ! ተቀላቀሉን ብለናል።
ወያኔን ማስወገድ የሁሉም ብሄሮች ጥቅም ነው። ሁሉም ህዝብም፣ ሁሉም ፓርቲ በወያኔ መወገድ ይስማማል። ታዲያ ማን ያስወግደው? ከጥንት ጀምሮ ብዙ ትውልድ ሀገሩን ከውስጥና ከውጭ ወራሪ ለመታደግ በዚህች የኢትዮጵያ ምድር ላይ መሰዋእት ከፍሏል፡፡ ወጥቷል፣ ወርዷል አልፏል፡፡ የሰው ልጅ ተፈጥሮ የለገሰችውን የቅብብሎሽ ህግ ተቀብሎ ለነጻነቱ፣ ለማንነቱ መከበር እምቢተኝነትን ሲቀባበል፣ ሲተካካ ኖሯል፡፡ ወደፊትም ይኖራል፡፡ በዚህ የአሁኑ ሂደት ደግሞ እኛ ባለተራዎች ነን እማማ ኢትዮጵያን ከህወሃት መንጋዎች መንጋጋ ፈልቅቆ የማውጣት! ስለዚህ ለነጻነታችን ከሰማይ የሚወርድ ምንም አይነት መና የለም። እኛው ለእኛው ለራሳችን መሰዋእት ከፍለን ወያኔን እናስወገድ ዘንድ ትግሉ፣ ወቅቱ አሁን ነው።
Posted By.Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment