Thursday, May 16, 2013



ባለ ራእዩ ወያኔ/ኢህአዴግ በሙስና ቅሌት እራሱን አጋለጠ

እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌይ
may 16.2013
ባለ ራእዩ የወያኔ  መንግስት ባልታወቀ ወይም ሆን ተብሎ በተሰራ የቴክኔክ ብልሽት በዚህ ሰሞን በአባላትና ጀሌዎቹ ላይ ለ22 አመታት ታይቶ በማይታወቅ የሙስና ቅሌት ሰበብ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እያጎሯቸው ይገኛል። የሚገርመው ደጋፊዎቻቸው ከሐገር ቤት እስከ ዲያስፖራው  ብዙ ሲለፈልፉላቸው ይሰማ ነበር ልማታዊ መንግስታችን፤ ልማታዊ ሚኒስትሮቻችን ፤ ልማታዊው መሪያችን  በማለት ከሰብአዊ መብት ጥበቃ በፊት መንገድ ስራና የአፓርታማ ግንባታ ይቅደም በማለት  መቆሚያና መቀመጫ አሳጥተውን ነበር አሁን ምን ይውጣቸው ይሆን? እንደ ለመዱት ልማታዊ ሙስና ነው ብለው እንዳያስደነግጡን እንፈራለን።

haገራችንን ኢትዮጵያን ወያኔ /ኢህአዴግ ከተቆጣጠራት ጊዜ ጀምሮ ማለትም እ.ኤ.አ ከ1991 ዓ.ም ሐገሪቷንና ህዝቧን በመሳሪያ አግቶ በዘር በሃይማኖት ከፋፍለው  እንዲሁም ከቁጥጥር ውጪ  በሆነ የሰብአዊ መብት እረገጣ እና የኢኮኖሚ ቀውስ አድርሰውባታል አሁንም እያደረሱባትም ይገኛሉ።
 
ዝባችንም ከተወለደበት እና ካደገበት ቀዬው ሰላምን ፍለጋና ኑሮውን ለመምራት ሲል እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ ማያውቅበት ሐገር ለመኖር ሲሰደድ፤ በየበረሐው ሲደበደብ፤ እንዲሁም ሲገደል እና በህይወት እያለ ሰውነቱ እየተቀደደ የውስጥ አካሉ  ሲሸጥ  እያየንና እየሰማንም ነው።
 
ይህ ሁሉ በደል እና ስቃይ በህዝባችን እየደረሰ ባለበት ጊዜ ስልጣኑን ተቆጣጥረው ያሉት የወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት እኛ እናውቅላችኋለን፤ እናስተዳድራችኋለን በማለት የባለ እራዩን የዘረኛውንና የገንጣዩን መለስ ዜናዊ አመራር  አላማ ለማስፈጸም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን በማለት በህግ ላይ ህግ በማውጣት ህዝቡ ቀና ብሎ  እንዳያያቸው በተበላሸና በከረፋ የህግ የበላይነት
ስም ህዝቡን በማፈን፤ ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ነገር ግን በአሸባሪነት ስም የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የእምነት ስርዓታችንንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን ምርጫ እምነታችን በሚፈቅደው መንገድ ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጎችን በአሸባሪነት በመወንጀልና በመክሰስ እንዲሁም በዋልድባ ገዳም አባቶቻችንን በማሳደድና በመዝረፍ ሲያሰቃዩ  እነሱ ግን  በቅሌትና በሙስና የሀገሪቷን ሃብት እና ንብረት  ለግል ጥቅማቸው በማዋል እንዲሁም የሀገሪቷን ጥሬ ሃብትና ንብረት ወደ ውጪ በማሽሽ  በውጪ በሚገኙ ዘመዶቻቸው ስምና የነሱ ተባባሪ ወዳጅ መንግስታት ሐገሮች ባንክ ውስጥ በማስቀመጥ ሐገራችንን ኢትዮጵያን  በአለም ታይቶ በማይታወቅ የኑሮ እድገት የኋልዮሽ እሽቅድምድም ውስጥ በማስገባት ለከፋ ችግር አጋልጠዋታል።
እውነት አሁን ወያኔ/ኢህአዴግ ሀገራችንን ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ አመታት ከግብረ አበሮቹና ከጀሌዎቹ ጋር በመተባበር ሲያደማትና ሲበዘብዛት  ቆይቶ አሁን  በሙስና ቅሌት ያዝኳቸው በማለት ግብረ አበሮቹን በገሃድ ያጋለጠበትና አሳዶ  ወደ ወይኒ የወረወረበትን  ምክንያት እውነት ለሐገራች ተቆርቋሪነቱን ለማሳየት ይሆን ? ወይስ የማናውቀው መፍረክረክ ተፈጠረባቸው ? ይህንን ጥያቄ  እሱ እራሱ ባለጉዳዩ ይመልሰው ወይም እነሱ እንደ ጀመሩት እራስ በራሳቸው ተበላልተው ያልቁልናል ብለን ዝም ብለን እንመልከት?
እኔ እንደማስበው ወያኔ/ኢህአዴግ በአሁን ሰአት እያረጀ የመጣ ትልቅ የግራር ዛፍ ነው ብዬ አምናለሁ ምክንያቱም ስርአቱ ውስጥ የመፍረክረክ ሁኔታና የመበስበስ ባህሪይ ማሳየቱ ከውስጡ ያሉት ሞተር የነበሩት እራሳቸውን ወደ ማግለል ደረጃ ላይ ደርሰው እያየናቸው ነው ስለዚህ የበሰበሰውን ስርአት በደንብ እንዲበሰብስ አድርጎ የመጣል ሐላፊነት ያለብን ይመስለኛል ለዛም ዋና መፍትሄ የሚሆነው ስርአቱን ፊት ለፊት እና በተለያየ መንገድ የሚታገሉትን ድርጅቶችን ሆነ ግለሰቦችን አንድ በማድረግ ልዩ ነታችንን ትተን በአንድነት መፋለም ያስፈልጋል ብዬ አምናለው ያለ በለዚያ ስርአቱ በሰበሰ አረጀ እራሱ ይወድቃል ብለን ቁጭ ብለን የምንጠብቅ ከሆነ እራሳችን በስብሰን ከዚህ በበለጠ በከፋ  አገዛዝ እንደምንገዛ ጥርጥር የለኝም።
                                 
መልክት ለወያኔ ደጋፊዎች 
 
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የወያኔን ስርአት የምትደግፉ ወገኑቻችን  በአሁን ሰአት አለማችን በቴክኖሎጂ አድጋ  አንድ ሆናለች  የትም ሆናችሁ የትም ስለ ሃገራችሁም ሆነ ስለምትፈልጉት ነገር ቤት ቁጭ ብላችሁ ማየትም መስማትም ትችላላችሁ  ስለዚህ ማሳሰብ የምፈልገው ነገር ሐገራችን ኢትዮጵያ ከየት ወዴት እንደምትሄድ እና በስርአቱ ውስጥ ምን ያህል እንዝላልነትና ሐላፊነት የጎደለው አገዛዝ እንዳለ ለናተም የተደበቀ ነገር ያለ አይመስለኝም እድሜ ለቴክኖሎጂ የለፈውን እንተወውና አሁን በቅርቡም በመገናኛ ቦዙሃን እንደሚደመጠው በሐገራች ላይ ምን ያህል ምዝበራና ዘረፋ እየተካሄደባትና ኢ ሰብአዊ ድርጊት በህዝባችን ላይ እየደረሰ እንደሆን ለናተ መንገር  ለቀባሪው አረዱት ማለት ነው  ስለዚህ ጠንቅቃችሁ ታቁታላችሁ ። እግዚአብሄር በሰጣችሁ ጭንቅላት በመጠቀም ወደ ሰውኛ አስተሳሰብ ተመልሳችሁ ጊዜው  ሳይረፍድ ከጭቁኑ ኢትዮጵያዊ ጋር ጎን ለጎን በመቆም በአፓርታይድ አገዛዝ ስር የወደቀችውን ሐገራችንን ነጻ ለማውጣት እንታገል   በማለት ወንድማዊ መልእክቴን አስተላልፋለሁ። 
መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለግንዛቤ ሰሞኑን ከወጡት ዜናዎች መካከል በጥቂቱ

          Posted by.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment