Sunday, March 24, 2013

የመለስ ታጋዮች እና የህወአት ታጋዮች ፍጥጫ

በሚል ርዕስ አንድ ሰፋ ያለ ጽሁፍ ብጽፍ ድስ ይለኝ ነበር፡፡፡፡አንድ ቀን እግዜር ካለ አደርገው ይሆናል፡፡ ዝምብሎ መቸክቸክ ሳይሆን ለአቅመ መጻፍ ስደርስ አይሆንም አልልም፡፡በነገራችን ላይ ህወአት ተጠነካረ ነው የሚባለው ወይንስ ተመነቃቀረ፡?፡ እኔ ግን ሳስበው ምንቅርቅሩ ነው የወጣው፡፡ ደግሞ ለምን እንደሆነ አላውቅም የአቶ አባይ ጎጆ ቤት ጣሪያ ተቀዶ ዝናብ የሚያፈስ የሚያፈሰ ይመስለናል፡፡ ይሄ የእኔ ምኞትና እይታ ነው፡፡ለምን እንዲህ አልክ የሚለኝ ካለ ብዙ ባይሆንም እስቲ እ ዝም ብዬ የሆነ ነገር ልበል፡፡ በመጀመሪያ በአሁኑ ሰአት የመለስታጋዮች እንጂ የህወአት ታጋዮች የሉም ብዬ ልነሳ፡፡መለስ ከመሞቱም በፊት ገና አየሎም አርአያ ተገደለ የተባለ ሰሞን ነው አሁን ..የመለስ ራእይ ነው የምናስፈጽመወው.. የህወአት ራእይ ነው ..የምናስፈጽመው ብለው የሚከራከሩት፡፡ ይህንን ነገር የሰማሁት አንድ ጊዜ የሳሞራ የኑስ የጀነራልነት ሹመት ጉዳይ አስመልክቶ.. የመለስ አምልኮ ከሚለው መጽሀፍ ነው ከፍትህ ጋዜጣ፣፣ ከሁለቱ አንዱ እያነበብን እያለ በተነሳ ክርክር የተነሱ አንዳንድ ነጥቦች እንደ ዋዛ የሚታዩ አልመሰለኝም፡፡ አንዱ እውነቱን ነው ተመስገን ደሳለኝ አሁን ሳሞራ የኑስ ምን ሰርቶ ነው ጀነራል የተባለው ብሎ ጥያቄ ያነሳል፡፡ አንድ የሹመቱ ደጋፊ ደግሞ እና አማራ እንዲሾም ነበር የፈለከው እሱ እኮ ስንትና ስንት ተአምር የሰራ ሰው ነው ብሎ እያወራ ሳለ ሌላናው ሰው ጣልቃ ገብቶ ምን ሰራ .መለስንከሞት ስላዳነ የተሰጠው ገጸበረከት ነው ለምሳሌ እንክንፈ ገ/መድህን እነ ስዬ አሴሩት የተባለው ልክ መለስ ዜናዊ ከውጪ ሲመጣ እሱን የጫነችውን አውሮፕላን በአየር ላይ መተ የመጣል ወይም መቀሌ ላይ እንዲያርፍ ተደርጎ ገና ወጣሁ ሲል ጭጭ ሊያደርጉት ነበር የተባለው መረጃ በመስጠት ያከሸፈው ሳሞራ የኑስ ነው -ያ በማድረጉ ደግሞ የተሸለመው የተባለው ሹመት ነው ሲል ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ሳይሆን አይቀርም ብዬ የጠረጠርኩት ደግሞ ያ ለሳሞራ አግዞ ይከራከር የነበረው ሰው.. እሱማ ያለፈ ነገር ነው..ሲል ስለ ሰማሁት ነው፡፡ ዛሬ ተቃዋሚዎች ስዬን የሚያደንቁት ያኔ መለስን ሊገልላቸው ስላሰበ አይደል እንዴ ሌላማ ምን ምክንያት አላቸውና ሲልም ሰምቻለሁ፡;የመለስ ታጋዮች ስራቸው የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡ መለስ በህይወት እያለ … የታጋዮቻችን ደም ተረሳ፣ እናቶቻችን ልጆቻቸው አምነው የሰጡን እንደዚህ አይነት ግፍና ጭቆና እንዲኖር አልነበረም ምናምን ይሉ ነበር የተባሉትን የሚሉትን ታጥኮና አስታጥኮ እስኪበቃቸው አሳዷቸዋል ይባላል፡፡ የቱ ጋ እንዳሳደዳቸው ለእኔ ባይተየኝም፡፡ አሁን ከሞተ በኋላ ግን አንዳንድ የሚታዩ ነገሮች አሉ፡፡የመለስ ታጋዮች እና የህወአት ታጋዮች አንድ እንዳልሆኑ በዚህ ሰሞን ከተደረጉት ..አረንጓዴ የመለስ ካርድ እየሰጡ የማስገባትና ቀይ የመለስ ካርድ እየሰጡ የማስወጣት ነገር አይተናል፡፡መተካካት በሚል የመመንጠሪያ ጫወታ፡፡መንጣሪዎች የትግል አርማችን አላማ ግባችን መለስ ነው የእሱን ራእይ እናስፈጽማለን ሲሉ ነበር የሚባል ነገር እየተሰማ ነው፡፡ የትኛው መለስ ስንል በአሁኑ ወቅት የምናውቀው ሁለት ነገር አለ፡፡ ከመሞቱ በፊትና ከሞተ በኋላ ያለው መለስ፡፡ ሳይሞት በፊት መለስ አሁን እንደሚወራለት እንዲህ የቅዱስ ገብርኤል እኩያ አልነበረም የሳጥናኤል እንጂ፡፡ አሁን ግን እየተወራ ያለው ነገር የተለየነው መለስ ከስብእናው አንስቶ ሁለነመናው ቅዱስ ተደርጎ እንደ ግሪኩ ቅዱስ ጊዮርጊስና እንደ ኢትዮጵያዊው ተክለሐይማኖት በቅዳሴ ሰአት በቤተ መቅደስ ውስ ጥ ምስሉ ጠለጥፎ የአምልኮ ና የጸሎትና ስግደት ሳይቀር ሳይደረግለት አይቀርም፡፡ አሁን የኔ ጥያቄ የመለስ ታጋዮች ለየትናው መለስ ነው ለመታገል የወሰኑት የመለው ጥያቄ ነው፡፡ዛሬ እንኳን ወደ ጦር ሀይሎች አካባቢ ብትመጡ የፎቶግራፍ አውደርአዕይ ተብሎ የተተከለው ድንኳን ሁሉ በመለስ አምልኳዊ ምስል ነው የተሞላው፡፡ በቃልም በምስልም ሁሉም ነገር መለስ ነው፡፡ አንድንድ ሚረባ ነገር ሰሩ ተብለው ይሸለሙ የነበሩ ሰዎችም የአባታቸውና የጌታቸው መለስን ምስልን ምስል እየሳሙና እጠሳለሙ ነበር የሚቀበሉት፡፡ እንዴት ነው ነገሩ፡? ሁላችንም እንዲህ ለቆመው ምስል ለማሰገድ ነው ትግሉ፡፡ አልገባንም፡፡ እኔ ህወኣት የየሚባል ቅዱስ አለ እያልኩኝ ግን አይደለም፡፡ሲወራ እንደ ሰማሁት ግን የአየሎም አርአያ ራእይና የመለስ ራእይ በጣም ተራኒ ናቸው ሲባል ፡፡እንዳውም ሀየሎም የኤርትራን ሁሉ መገንጠል የማይደግፍና የህወአትም አላማ የኢትዮጵያ ነጻነትና አንድነት ማስጠበቅ አለበት የሚል እንደ ነበር ብዙ ሰዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ እዚህ ፌስቡክ ላይ ሳይቀር፡፡ አሁን እኔን እያስጨነቀኝ ያለው ጥያቔቄ እነዚህ የሀህወአት ታጋዮች ወይም የሀየሎም አላማ አራማጆች እጅእግራቸው አጣጥፈው እንደዛ የወደቁለትና የተዋደቁለት አላማ ለአንድ ግለሰብ ክብርና ስም አሳልፈው ይሰጣሉ ወይ ነው፡፡እኔ አይመስለኝም( ይቅርታ ነገ ብጨርሰው ይሻለኛል)
       Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment