Friday, July 5, 2013

ከድጡ ወደ ማጡ! የቀበሮ ባሕታዊ በሎንደን

July 4, 2013


ወንድሙ መኰንን፣ ሎንደን

መግቢያ
Debretsion Mariam London Ethiopian Orthodox Church
በዓለም ዙሪያ የተበተናችሁ ወገኖቻችን በኛ ሎንደን በምንኖረው የኦርቶዶክስ ሀማኖት ተከታይ በሆንን ኢትዮጵያውያን ላይ በአንድ መነኵሴ ነኝ ባይ የቀበሮ ባሕታዊ ግለሰብ አማካኝነትና በወያኔ ቀጠረኞች የደረሰብንን ይቅር የማይባል በደል ዕለት በዕለት እንደምትከታተሉና መጨረሻችንን ለማየት በጉጉት እንደምትጠባበቁ እዚህ ያሉት ወንድሞችና እህቶች በሚገባ ያውቁታል። ያመሰግናሉም። ታዲያ ከዚያች ቀውጢ የሁዳዴ ጾም መያዢያ ማግስት፣ ጀምሮ የተዘጋብን ቤተክርስትያን ጉድይ እስካሁን እልባት ሳያገኝ፣ ቀርቶ ሕጻናቱም፣ አይቆርቡም፣ አዛውንቱም፣ ወይዛዝርቱም እግዚአብሔርን ማምለኪያ ቦታ አላገኙም። ይኸ በደል ባንድ ካኽን ንኝ ባይ ሲፈጸም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪአው መሆን አለበት። ብቻ በየሰንበቱ፣ “አንድ ሐሙስ የቀራችሁ፣ የእንጨት ሽበት፣ ሽሜ ጉጉ”እያተባሉ በወያኔ ሶልዲ በተገዙ ስድ ወጣቶች እየተሰደቡ፣ ሴቶችም ለጆሮ በሚቀፍ ስደብ እየተሸማቀቁ፣ቤተክርስቲያኗ ቅጥር ገቢ እየገቡ ሕንጻዋን እየተሳለሙ፣ ከሕዝብ ጋር ከሚንከራተቱ አንድ ቄስ፣ አንድ መሪ ጌታ፣ እና በመምሕር ታሪኩን ጨምሮ በዛ ካሉ ዲያቆናት መሪነት ሜዳ ላይ እየጸለዩ፣ አራት ወራት አሳለፈዋል። ምን ላይ ደረሰ እያላችሁ የምትጠይቁ በዝታችኋል። ሁለቱ አዋጊ ጳጳሳትም፣ አቡነ ገብርኤልና አቡነ ቀውስቶስ፣ የትም ቦታመንቀሳቀስ በማይገባቸው የሱባኤ ሰሞን አገረ ስብከታቸውን ጥለው ሕንጻውን ሊቀሙን ቢመጡም፣ በተደረገው ርብርብ ሳይሳካላቸው ቀርቶ “አባ” ተባዩን የቀበሮ ባህታዊ፣ “በርታ” ብለው ወደመጡበት ተመልሰዋል። “በመነኵሴ ነኝ” ባዩ አመጸኛ ግለሰብ አዝማችነት፣ ተዝቆ፣ ተዝቆ በማያልቀው የወያኔ ገነዘብ ኪራይ ከፋይነት ተደለለው፣ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን ረግጠው በማያውቁ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጋጠ-ወጦች (ጋንግስተሮች) እስከመገፋት መገፍተር፣ደርሷል። እና አባ ተባዩም ንብረት እስከመስረቅና ማጋዝ ጀምረው ነበር። እንዲያም ሁኖ፣ እስካሁን ሕዝበ ክርስቲያኑ ቤተክስቲያኑን እየጠበቀና እየተከላከለ ይገኛል። ግፉ ግን በዝቷል። ሁለንተናው ዘቅጧል። ነገሩ ሁሉ ከድጡ ወደማጡ ተብሎ ቢደመደም ይበጃል። “አባባሱባት” ነበር ያልኳችሁ ባለፈው? እሱን እርሱት። ያሁኑ ይባስ።
የመዳን ንሰሐ ለጥቃት ሲያጋልጥ
ባለፈው ሳምንት የተፈጽመው አሳፋሪ ወንጀል፣ በታሪካችን ምንጊዜም “በምዕምን ላይ ደረሰ” ሲባል ተሰምቶም የማይታወቅ ጉድ ነው። ፈረንጆች “Abuse of Trust” ይሉታል።  ያመኑት ፈረስ በደንደስ እንደሚሉት ነው። በመጨረሻው ጽሑፌ ከአንባቢዎቼ የተልያየሁት “ብጹዐን አባቶች ለታስታርቁን ወይስ ልታዋጉን መጣችሁ?” በማለት በሞነጫጨርኩት መጣጥፍ ነበር። አባዛኛው መልዕክቱ ቢገባውም፣ ሌሎች ሰዎች ነገሩን እያባባስኩ እንጂ እየረዳሁ አለመሆኔን ስላሳሰቡኝ፣ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም ላለመጻፍ አቅጄ ቆየሁ። የኔ ዝምታ ግን “ትሻልን ፈትቼ ትብስና አገባሁ” ቢጤ ሆኖብንና አሸንፈው ጭጭ ያሰኙኝ መሰላቸው። የኔ መተው ነገሩን አልከተተውም። ጳጳሳቱ ወደመጡበት በመመለሳቸው፣ የወያኔን ይሁንታ ተጨምሮበት፣ የቀበሮ ባህታዊው ባሰባቸው። በነጋ በጠባ ሕዝቡን “በምን ላቁስለው?” እያሉ ሲያልሙ የሚያድሩ ይመስላሉ። ፓትርያርኩ በሞቱላቸው ጊዜ፣ ይኸን ሕዝብ በምን ቆሽቱን ላድብን ብለው፣ ለታጋይ ጳውሎስ ፍትሀት አደርጋለሁ ብለው ተነስተው እንደአንጫጩን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሌላ አገኙ። የቤተክርስቲያናችንን መሠረት የናደ፣ እንኳን ከአንድ የአሀይምኖት አባት ነኝ ብሎ ከሚመጻደቅ ይቅርና፣ ከመርካቶ ዱሩየም የማይጠበቅ፣ በጣም የወረደ ተግባር ፈጸሙ። “ቤተክርስቲያናችንን ይጎዳል፣ ዝም በሉ” ለምትሉን፣ ዝምታ ለበጓም አልበጃት፣ ዝም አንልም። ዝም እማ ካልን ዲያብሎስ ይነግሳል። በዓለም ዙሪያ ያሉት ክርስቲያን ወንድሞችና እየቶቻችን የደረሰብንን በደል አውቀው፣ በጸሎታቸው እንዲተባበሩን፣ በደሉ ይታወቅ። የሎንደንማ ሕዝብ በተፈጽመው አስነዋሪ ነገር ተደናግጦ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ግራ ገብቶት ቁጭ ብሏል። አንዳንዱ፣ “ተው ከእግዚአብሔር ያግኙት”ይሉናል። ኤዲያ! እግዚአብሔር በአምሳያው የፈጠረን የምንችለውን አድርገን የማንችለውን ልንተውለት ነው። የምንችለውንም፣ የማንችለውንም ለሱ መተውማ ስንፍና ነው። የተጎዱት ያቃስታሉ። እንዴት ዝም እንላለን? ከመሀላችን አንዳችን ተጎዳን ማለት፣ ሁላችንም ተጎድተናል ማለት ነው። ነውሩን እራሱ ይደብቅ እንጂ እኔ ጫካ አይደለሁም የምደብቅለት። አልደብቅለትም። ያበጠው ይፈንዳ! ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

     Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment