Friday, September 20, 2013

አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት! "ህይወት እንደዋዛ"

the pic


ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ።
ቀን መስከረም 8: 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮኔትነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እምባ ሲያራጭ፡ ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንትራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል።
የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜ ያዊ መጠለያ ኮንቴነር፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ በተከታታይ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህልፈተ ህይወት መሰማቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ አስደንግጦል።
በተለይ ትላንት ማለዳ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 አካባቢ አስከሬንዋ ጊዜያዊ መጠለያ ኮንቴነር ውስጥ ሞታ የተገኘችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ህመሙ አገርሽቶባት ስታቃስት «ጣዕረሞት ስታሰማ»፡ እንደ ነበር የሚናገሩ ወገኖች ዲፕሎማቱ ትብብር እንዲያደርጉላት ስልክ ቢደወልላቸውም በወቅቱ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የወጣቷ ህይወት በሚያሳዝን ሁኔታ ማለፉን ይገልጻሉ።
ሟች እዚህ ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዲፕሎማቱ በኤምባሲው ሃላፊነት ወደ ሆስፒታል ወስደው ማስመርመር እና ህይወቷን ከሞት መታደግ ሲችሉ ባሳዩት ግዴለሽነት እና ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው አሰራር የወጣቷ ህይወት እዚህ በረሃ ላይ ቀርቷል ብለዋል። ወጣቷን ወደዚህ ግዜያዊ መጠለያ ግቢ ዲፕሎማቱ ከአሰሪዎችዋ ተረክበው ሲያመጧት “ሃኪም ቤት ውሰዱኝ ህይወቴን አጣሁ!! አድኑኝ ኧረ የወገን ያለህ!! ኧረ ያህገር ያለህ!! አናቴ ድረሺልኝ!!” እያለች ትማጸናቸው እንደነበረ በአካባቢው የነበሩ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል። የወጣቷ የሰውነት አቋም እና አጠቃላይ ሁኔታ ያዩ አንዳንድ ታዛቢዎች በውስጥዋ የቆየ በሽታ እንደሌለባት እና ወጣቷ አንጀቴ ተቃጠለ ውሃ ውሃ ስትል እንደነበር እና ሃኪም ቤት ውሰዱኝ እያለች ልብ በሚነካ ሁኔታ ስትማፀን የታዘቡ ወገኖች ምናልባትም ከምግብ ጋር የተቀልላቀለ መርዝ ነክ ነገር በልታ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ያጎላሉ።
በማያያዝ ዲፕሎማቱ ወጣቷን ከአሰሪዎቾ ተቀበለው ወደ መጠለያ ሲያመጧት ለአመታት የደከመኩበትን የወር ደሞዜን እባካቹ ከአስሪዪ ላይ ተቀበሉልኝ እያለች ትጮህ እንደ ነበረ እና ወደ መጨረሻ አካባቢ እየደከመች ስትመጣ ሟች በሚያሳዝን አንደበት ሆስፒታል በር ላይ ወስዳችሁ ጣሉኝ፡ የወግን ያለህ እያለች እስከ ዕለት ሞቷ ታለቅስ እንደ ነበረ እና ይህንንም ተማጽኖ ዲፕሎማቶቹ «የመንፈስ ጭንቀት ነው» ፡ «ስራ በዝቷባት ነው» ፡«ሃገር መግባት ፈልጋ ነው» ስታጭበረብር ነው» ወዘተ . . . በሚል ፌዝ በጭካኔ ሌሎችን ሰላም ትነሳለች በሚል ለብቻዋ ኮንቴነር ውስጥ፡ አስገብተው እንደቆለፉባት እና በነጋታው ወጣቷ ሞታ ማደሯን አንዳንድ የኮሚኒቲው አባላት እንባ እየተናነቃቸው ገልጸዋል ።
ይህ በዚህ እንዳለ ትላንት 4 ሰዓት ከ15 ደቂቃ አካባቢ በዲፕሎማቱ ትዕዛዝ የወጣቷ አስከሬን በሳውዲ የማዘጋጃ ሰራተኞች ተነስቶ ወደ አልታወቀ ስፍራ እንደተወሰደ እነዚህ የአይን ምስክሮች አክለው ገልጸዋል።
(Ethiopian Hagere በፌስቡክ ለጎልጉል የላኩልን – ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ)
    Posted Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment