Monday, August 31, 2015

የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች ጭምብል ለብሰው በሌሊት የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ቤት ሰብረው በመግባት አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም ላይ ናቸው

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች ማንነታቸው እዳይታወቅ ጭምብል ለብሰው በሌሊት የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ቤት ሰብረው በመግባት አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም ላይ ናቸው!

በጎንደርና አካባቢው በተለይም ደግሞ በደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ውስጥ የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ጭምብል አጥልቀው በሌሊት እየተንቀሳቀሱ የሰፈር ቤት ሰርሳሪዎችን በመምሰል የአገዛዙ ደጋፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ቤት ሰብረው በመግባት ሰዎቹን በጩቤና በጥይት በመግደል ንብረታቸውን በመዝረፍ ስራ ላይ በሰፊው ተሰማርተዋል፡፡

ራሱን በመንግስትነት የሚጠራው ህወሓት የማፊያ ቡድን በውድቅት ሌሊት የሚፈፅመው አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ በርካታ የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ሰለባ የሆኑ ሲሆን የሰ/ጎንደር ደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ የሆነው የሰባት ልጆች አባት አቶ አብዬ ታረቀኝ አንደኛው ነው፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት የህወሓት የአየር ኃይል አዛዥ የነበረው ሜ/ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያም ከነበረበት የኃላፊነት ቦታው ተወግዶ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለ እንደማይታወቅ የመከላከያ ምንጮቻችን ገለፁ፡፡


ገና ከበርሃ ጀምሮ እነመለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋን በአጃቢነት እያገለገለ ጥሩ ቅርርብ የነበረውና ከመከላከያ ኤታማጆር ሹሙ ሳሞራ የኑስ ጋር ዶሮና ጥሬ ሆኖ የቆየው ሞላ ኃ/ማሪያም የመለስን ሞት ተከትሎ ከአየር ኃይል አዛዥነቱ የተወገደ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የብላቴ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ቀጥሎም የጦላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ አዛዥ ሆኖ የቆየ ሲሆን አሁን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በአጠቃላይ ከመከላከያ ተወግዷል፡፡ በምን ሁኔታ ላይ እደሚገኝም በውል እደማይታወቅ የመከላከያ ምንጮቻችን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46302

No comments:

Post a Comment