Sunday, June 30, 2013

የዕለቱ ዜና ዘገባ ( ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ )    30.06.2013

ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑት.http://www.finote.org/Finot30_06_2013.mp3

      Posted By.Dawit Demelash
የውጭጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁንም በስብሰባ ላይ ተዋረዱ!!
    


    Posted By.Dawit Demelash

Saturday, June 29, 2013

በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀው መከላከያ ሂሳቡ እንዳይመረመር ታዘዘ



ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ባቀረበው ሪፖርት የመከላከያና የደህንነት ተቋማት
የፋይናንስ አያያዝ ከፍተኛ ችግር እንዳለበት ማመልከቱን ተከትሎ በየመ/ቤቶቹ የተነሳውን ቅሬታ ለመፍታት በቀጥታ
እነዚህን ተቋማት በተለየ ሁኔታ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል አዋጅ እየተረቀቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሚያዚያ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ለፓርላማው ባቀረቡት የ2004 ዓ.ም
የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ ሪፖርት በተለይ በዘጠኝ መ/ቤቶች 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር
ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኖ መገኘቱን፤ ከዚህ ውስጥ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብሩ የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑን
መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
እነዚህ ተቋማት ላወጡት ገንዘብ ትክክለኛ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ተጠይቀውም ማቅረብ አለመቻላቸውን ለፓርላማው
ሪፖርት ካደረጉ በኋላ በተለይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈረጌሳን ጨምሮ የተለያዩ ሹማምንት ሪፖርቱን
በአደባባይ እስከማብጠልጠል የደረሰ ትችት ሲያቀርቡ ተደምጠዋል፡፡ ዋናው መከራከሪያቸውም የመከላከያ ወጪ ሚስጢር
ነው የሚል ነበር፡፡
ይህንን ተከትሎ የፓርላማ አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ በቴሌቪዥን ቀርበው “ባልተሟላ ሰነድ
ወጪ ተደረገ ማለት ብሩ ተበላ ማለት አይደለም” በማለት ማብራሪያ ለመስጠትና ተቋሙን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ
ሞክረዋል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያቸው የሆነውን መግለጫ ትላንት ጠዋት
በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡበት ወቅት በተመሳሳይ መንገድ መከላከያን ኦዲት ማድረግ
ሚስጢር ማባከን መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ሁኔታውን ለማስተካከል አዲስ ሕግ እንደሚወጣ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ዋና ኦዲተር በአዋጅ ቁጥር 669/2002 መሰረት የፌዴራል የመንግስት ተቋማትን ኦዲት የማድረግና የማስደረግ ሙሉ ሥልጣን እንደተሰጠው ጠቅላይ ሚኒሰትሩ አስታውሰው በዚህ ሕግ መሰረት ባለፉት ዓመታትም መከላከያን ጨምሮ ሁሉንም ተቋማት ኦዲት ሲያደርግ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ በሚያዚያ ወር 2004 ዓ.ም የ2003 የሂሳብ ሪፖርት ለፓርላማው ቀርቦ እንደነበር በዚህም ሪፖርት መሰረት ከተወቀሱት ተቋማት መካከል መከላከያ አንዱ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ በ2003 በጀት ዓመት በመከላከያ 133 ነጥብ
8 ሚሊየን ብር ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩን፣ የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 19 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በወጪ
ተመዝግቦ መገኘቱን ሪፖርት አድርጓል፡፡  በተጨማሪም የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ካልተቻለው ገንዘብ መካከል 1
ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የመከላከያ ሲሆን ፣ 54 ነጥብ 3 ሚሊየን ደግሞ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ 33
ነጥብ 34 ሚሊየን ብር የአገር ውስጥ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ መሆኑ መጠቀሱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ መ/ቤቱ
እንደዘንድሮ ከፍተኛ ቅሬታ ያላቀረበ ሲሆን የዘንድሮ ቅሬታ ምናልባትም በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ላይ ተጽዕኖ በማሳደር
ነገሩን ለመሸፋፈን የታሰበ ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቷል፡፡
ምንጮቻችን እንደገለጹት በአገሪቱ ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጸምባቸው ተቋማት መካከል ግንባር ቀደሙ መከላከያ መሆኑን
አስታውሰው አንድ ወርሃዊ ደመወዙ 4 ሺ ብር የማይሞላ ከፍተኛ የመከላከያ ሹም በአዲስአበባ ቁልፍ ቦታዎች ጭምር
በሚሊየን ብር የሚገመቱ ቪላዎችንና ሕንጻዎችን የሚገነባበት እንዲሁም ትልልቅ ንግዶችን የሚያንቀሳቅስበት ሁኔታ
የአደባባይ ሚስጢር ነው በማለት የእነአቶ ኃይለማርያም ሙግት ጥቅሙ ለሙሰኞቹ ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ ሕግ በቀጣይ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ዋና ኦዲተር ሕጉ እስኪጸድቅ
መከላከያና የደህንነት ተቋማትን ኦዲት እንዳያደርግ መታዘዙንም ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ 60 ከፍተኛ ጀኔራሎች መካከል 58ቱ በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሀት አባል ሆነው የመጡ ናቸው።  መከላከያን ከላይ ሆነው የሚዘወሩት 7ቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በሙሉ የህወሀት ታጋዮች ናቸው። ባለፉት 22 አመታት በዚህ ከፍተኛ አመራር ውስጥ የሌላ ብሄር ተወላጅ ተካቶ አያውቅም።
በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሀይለማርያም በአባይ ግድብ ዙሪያ ከተቃዋሚዎች ጋር እንደማይነጋገሩ አስታውቀዋል።
Posted By.Dawit Demelash

ኦባማ – “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

“ግብረሰዶማዊነት ወደፊት!”
obama in senegal


በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን እየጎበኙ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሴኔጋል ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር እንደሚገባው አስታወቁ፡፡ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት ሰዶማውያንን የሚደግፍ ውሳኔ ሰሞኑን በማሳለፉ ደስታቸውን ገለጹ፡፡ የሴኔጋሉ አቻቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይወነጀሉ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናገሩ፡፡
ሰሞኑን በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ ጉብኝታቸውን በጀመሩባት ሴኔጋል የግብረሰዶማውያንን መብት በተመለከተ ለአፍሪካውያንና ለመሪዎቻቸው ማብራሪያና “ትምህርት” ሰጥተዋል፡፡ “መንግሥታት ዜጎቻቸውን እንዴት ሊያስተናገዷቸው ይገባል፤ ሕጉስ እንዴት ሊያያቸው ይገባል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊስተናገድ ይገባዋል” በማለት “ግብረሰዶማዊነት ወደፊት” የሚያስብል ንግግር አድርገዋል፡፡
አፍሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ኦባማ የአገራቸው ጠቅላይ ፍርድቤት የግብረሰዶማውያንን መብት ሊያስከብር የሚችል ውሳኔ ማስተላለፉ እንዳስደሰታቸው በጉብኝታቸው ወቅት ጠቁመዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ውሳኔ ለጋብቻ መጠበቅ ከለላ የሚያደርገውን Defense of Marriage Act (DOMA) የተባለው ሕግ ለወንድና ሴት ተጋቢዎች ብቻ በማለት ያስቀመጠው ከለላ የግብረሰዶማውያንን መብት ይጻረራል በማለት ነበር፡፡ ስለሆነም በፍርድቤቱ ውሳኔ መሠረት  በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል የተፈጸመ “ጋብቻ” ከፌዴራል መንግሥት የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞችን ሊያስከለክል አይገባም በማለት ወንድ ሚስትም ሆነ ሴት ባል ያላቸው ሁሉ የጥቅሙ ተካፋይ እንዲሆኑ ፈቅዶላቸዋል፡፡ እንዲሁም በካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት የሰዶማውያን ጋብቻ እንዲቀጥል ፈቃድ የሚሰጥ ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድቤቱ አስተላልፏል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ግብረሰዶማዊነት በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በበኩላቸው ግብረሰዶማውያን እንዳይከሰሱ ለማድረግ አገራቸው ዝግጁ አለመሆኗን ተናግረዋል፡፡ “በጣም በመቻቻል” የምንኖር ነን ያሉት የሴኔጋሉ መሪ አገራት ውስብስብ የሆኑ ሕጎችን በራሳቸው ጊዜ በተግባር ላይ እንደሚያውሉ በመጥቀስ የኦባማን ሃሳብ ተግሳጽ በተሞላበት ምላሽ አስተናግደውታል፡፡
በመቀጠልም አገራቸው ሴኔጋል ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት ያቆመች መሆኗን በመናገር አሜሪካ ግን ይህንን እስካሁን ተግባራዊ አለማድረጓን በመጥቀስ ኦባማን ተሳልቀውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ወንጀለኞችን በሞት የመቅጣት ህግ ከ30 በላይ ግዛቶች ውስጥ ተግባራዊ ሲሆን በተለይም በቴክሳስ በሰፊው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ወንጀለኞችን በሞት መቅጣት እንደገና ከተጀመረ ከ1974ዓም በኋላ የቴክሳስ ጠቅላይግዛት 500ኛዋን ወንጀለኛ ሰሞኑን በመግደል የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡

“ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ”

በፈረንሣይ አብዮት አካባቢ ህዝቡ መራቡን በተለይም የፈረንሣይ ጭሰኞች መቸገራቸውና በረሃብ እየተንገላቱ መሆናቸውን የተነገራት ልዕልት ማሪ አንቷኔ (“Qu’ils mangent de la brioche”) “ከራባቸው ኬክ ይብሉ” ብላ መልሳለች እየተባለ ለዘመናት ሲዘበትባት ኖሯል፡፡ ልዕልቲቱ ይህንን ለማለትዋ የተረጋገጠ ነገር ባይሆንም ነጻነት፣ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ … ለጠማው የአፍሪካ ሕዝብ ባራክ ኦባማ “የግብረሰዶማውያን መብት ሊከበር ይገባል” በማለት መሠረታዊውን የህዝብ ጥያቄ ችላ ማለታቸው “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” የማለት ያህል እንደሆነ ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ጠቁመዋል፡፡
በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት “ለውጥ” እና “ተስፋ” ቀዳሚ ዓላማቸው አድርገው የበርካታዎችን ቀልብ የሳቡት ባራክ ኦባማ፤ ለአፍሪካ መሠረታዊ ችግር እስካሁን ጆሮ አለመስጠታቸው ብዙ የተባለበት ነው፡፡ ሰሞኑን በአሜሪካ ምክርቤት “ኢትዮጵያ፤ ድኅረ መለስ” በሚል ርዕስ በተደረገው ምክክር የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የተናገሩትን በድጋሚ ያስታወሱም አሉ፡፡ በወቅቱ አቶ ኦባንግ ያሉት “ኦባማ ለምርጫ በተወዳደረ ጊዜ ጥቂት ደመወዝ የሚከፈላቸው ኢትዮጵያውያን የምርጫ ዘመቻውን ደግፈው ነበር፤ እስካሁን ከኦባማ የሰሙት ነገር የለም” በማለት ነበር፡፡
ከምዕራባውያን የሚመነጨውን ማንኛውንም ነገር – ከፖለቲካ እስከ ማኅበራዊ አመለካከት – ትክክለኛ አድርገው ለሚቀበሉ ግብረሰዶማዊነት ሥልጣኔ ይመስላቸዋል በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ የሃይማኖትና የማኅበረሰብ ሳይንስ ጉዳዮች ምሁር “ጋብቻ” የሚለውን ቃል ለሁለት ወንዶች መጠቀም እርስበራሱ የሚጋጭ ጉዳይ ነው በማለት ተመሳሳይ ጾታ ብሎ ጋብቻ ማለት የተሳከረ አነጋገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ “ይህ የሰዶማውያን መብት ይከበር የሚለው ጉዳይ በሕግ እየጸደቀ ሲሄድ ድርጊቱን ከሃይማኖታቸው አኳያ የሚቃወሙ ሰባኪያን የሃይማኖት ትምህርታቸውን በሚያስተምሩበት ቤ/ክ ይሁን መስጊድ ወይም ምኩራብ ግብረሰዶማዊነትን እየተቃወሙ ሰበካ ማድረግ በህግ የሚያስጠይቃቸው ይሆናል” በማለት ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን የማኅበረሰብ ቀውስ ጠቁመዋል፡፡
bush in africaበሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው ወቅት ዳግም የመመረጥ ፈተና የሌለባቸው የአሜሪካ መሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን የአፍሪካን የዱር እንስሳት እየጎበኙ ወደፊት ለሚሠሩት ፕሬዚዳንታዊ ቤተመጻህፍት (ፋውንዴሽን) ፎቶ እንደሚሰበስቡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ የባራክ ኦባማም ጉብኝት ከዚህ የተለየ አለመሆኑ ግልጽ ሲሆን “የአፍሪካ ልጅ” እየተባሉ ሲሞካሹ የኖሩት ፕሬዚዳንት ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ሲገቡ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ገጥሟቸዋል፡፡ ቅዳሜ የክብር ዶክትሬት በሚቀበሉበት የዮሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲም ተመሳሳይ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል፡፡
ዛሬ ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ደቡብ አፍሪካውያን “ይቻላል” (Yes! We can!) ለሚለው የኦባማ የምርጫ መፈክር “አትችልም!” (“No, You Can’t Obama,”) የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ “ኦባማ የመጣው አፍሪካንና ደቡብ አፍሪካን ለመዝረፍ ነው” በማለት ጠንካራ ተቃውሞውን የገለጸው አንዱ ተሰላፊ “አፍሪካውያን በብዙ መልኩ እየተሰቃዩ እያለ እርሱ ግን የአፍሪካን ሐብት፤ ወርቅ፣ አልማዝ፣ … ለመዝረፍ ነው የመጣው” ብሏል፡፡obama s africa
የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ፣ … ዕጦት ላንገላታውና በአምባገነኖች መዳፍ ሥር ለሚሰቃየው የአፍሪካ ሕዝብ በቃላት እንኳን ድጋፋቸውን ከመስጠት እስካሁን የተቆጠቡት ኦባማ አሜሪካ በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አገሮች ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ፍላጎቱ እንደሌላት በማያወላውል መልኩ ያረጋገጠ መሆኑ የብዙዎች ግንዛቤ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ኃይል ጥያቄ ውስጥ የሚጥልም ነው፡፡
በአውሮጳ የፖለቲካ ምጣኔሃብት ተመራማሪ የሆኑ እንደሚሉት “አሜሪካኖች እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዓይነቱን አምባገነናዊ አገዛዝ እስኪያስመልሰው ድረስ በዕርዳታ ገንዘብ ካሽሞነሞኑ በኋላ“ኢህአዴግን ምን እናድርገው” በማለት “ምክር ስጡን” እያሉ በሕዝብ ሰቆቃ ላይ ያላግጣሉ፡፡ ሲሻቸውም ደግሞ አፍሪካ ድረስ በመሄድ “ዴሞክራሲ ከራባችሁ ኬክ ብሉ” በማለት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አፍሪካውያን ችግር ያልሆነውን የግብረሰዶማውያን መብት መከበር ይሰብኩናል፡፡ ታዲያ ለዚህ ልግጫ መልሳችን መሆን የሚገባው “ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ነጻነታችንን አንለምንም፤ አሜሪካ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት እንድትሆንብን አንፈልግም” በማለት አቶ ኦባንግ ሜቶ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ምክርቤት በተካሄደው ምክክር የተናገሩትን ዓይነት ቁርጠኝነት ነው በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡
obama africa trip100ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው የኦባማ የአፍሪካ ጉብኝት በአሁኑ ጊዜ በበጀት ቀውስ ምክንያት በርካታ ሠራተኞች ደመወዛቸው እየተቆረጠ ባለባት አሜሪካ አነጋጋሪ መሆኑን ዋሺንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡ የደኅንነት ሰዎችን እንዲሁም 14ሊሞዚን፣ 56 ጥይት የማይበሳቸው ድጋፍ ሰጪ  መኪናዎች፣ ሙሉ የህክምና ባለሙያዎችን የያዘና ጀቶችን የጫነ መርከብ … ለፕሬዚዳንቱና ለቤተሰባቸው ጥበቃ በማድረግ ሥራ ላይ እንደሚውሉ ጋዜጣው ያብራራል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ በደቡብ አፍሪካ የሁለት ቀን ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰኞ ወደ ታንዛኒያ ያመራሉ፡፡ የአባታቸው የትውልድ አገር ነው የሚባለውን ኬኒያ ሳይረግጡ በዚያው ወደ አገራቸው እንደሚያቀኑ የጉዞ መርሃግብራቸው ያስረዳል፡
    Posted By.Dawit Demelash

የግል ባንኮች ህልውና አደጋ ላይ ነው ተባለ


የግል ባንኮች ህልውና አደጋ ላይ ነው ተባለ
የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት የቁጠባ ፕሮግራም መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲከናወን መደረጉ በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነና በአጭር ጊዜ የግል ባንክ ዘርፉን ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥል የባንክ ባለሙያዎች ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ እስካሁን ከ750ሺህ በላይ ግለሰቦች የቤቶች ልማት ቁጠባ ሂሣብ በንግድ ባንክ እንደከፈቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የግል ባንክ ባለሙያ፤ እሣቸው በሚሠሩበት ባንክ ደንበኛ የነበሩ ግለሠቦች በቤቶች የቁጠባ ፕሮግራም ተሣታፊ ለመሆን ከባንኩ ገንዘብ በማውጣት በመንግስት ባንኮች እያስቀመጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ሣምንታትም ባንኩ በዚህ አገልግሎት ተጠምዶ መቆየቱን የተናገሩት ባለሙያው፤ “በእነዚህ ጊዜያትም የባንክ ሂሣብ ለመክፈት ወደ ባንካችን የመጣ ደንበኛ አላጋጠመኝም” ብለዋል፡፡ በባንኩ ያላቸውን ገንዘብ ለማውጣት የሚመጡ ደንበኞች መበራከታቸውንና ይህም ባንኩ ራሱን ለማቋቋም ለዓመታት የደከመበትን ልፋቱ ከንቱ እንደሚያስቀረውና ቀጣይ ህልውናውንም አደጋ ላይ እንደሚጥለው ባለሙያው ይናገራሉ፡፡ ስማቸውና የሚሠሩበት ባንክ እንዲገለፅ ያልፈለጉ ሌላ ባለሙያም፤ በአሁን ሠአት ባንካቸው የውጭ ምንዛሬ እና የሃዋላ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባለፈ አዳዲስ የባንክ ሂሣብ የሚከፍቱ ደንበኞች እያስተናገደ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለም የባንኩ ህልውና አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
የኢዴፓ ሊ/መንበርና ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሼ ሠሙ በበኩላቸው፤ መንግስት መንግስታዊ በሆነው የንግድ ባንክ በኩል ብቻ ዜጐች እንዲቆጥቡ ማወጁ ከነፃ ገበያ ስርአት ጋር የሚቃረን መሆኑን ገልፀው ይህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ የህልውና አደጋ መጋረጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህ አካሄድ ከቀጠለም ያለ ጥርጥር ከሶስት እና አራት አመታት በኋላ የበርካታ የግል ባንኮች ህልውና እስከ መጨረሻው ሊያከትም ይችላል ብለዋል - አቶ ሙሼ፡፡ የቤቶች ልማት ቁጠባ ፕሮግራም ሁለት መሠረታዊ ተፅዕኖዎች አሉት የሚሉት አቶ ሙሼ፤ አንደኛው በግል ባንክ ውስጥ ከሚያስቀምጡ ደንበኞች ገንዘብ ላይ ማበደር አንዱ የባንኮች ተግባር መሆኑን ገልፀው፤ አሁን ግን ይህን ተግባር የሚያከናውኑበት ገንዘብ ወደ መንግስታዊ ባንክ እንዲሸሽ መደረጉን ይናገራሉ፡፡
ይሄም ብቻ ሳይሆን የግል ባንኮች በብዙ ዓመታት ያፈሯቸውን ነባር ደንበኞችም እንዲያጡ ያደርጋል ብለዋል፡፡ መንግስት የቀረፀው የቤቶች ልማት ፕሮግራም የግል ባንኮች አዳዲስ ደንበኞችን እንዳያፈሩ ማድረጉ ሁለተኛው ተፅዕኖ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በተቃራኒው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አዲዲስ ደንበኞችን እንዲያገኝ ይረዳዋል ብለዋል፡፡ ነባሩም ይሁን አዲስ ደንበኛ ከግል ባንኮች ወጥቶ ወደ መንግስት ባንክ መሄዱ የነፃ ገበያ ስርአት እንዲከስም ከማድረጉ ባሻገር ባንኮችም በህብረተሠቡ ዘንድ ለዘመናት የገነቡትን ጠንካራ እምነት እንዲያጡ ያደርጋል በማለት የግል ባንኮች ላይ የተጋረጠውን አደጋ ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ መንግስት የግል ባንኮች ከሚያበድሩት ገንዘብ ላይ 27 በመቶ የህዳሴውን ግድብ ቦንድ እንዲገዙ ማዘዙን ያስታወሡት አቶ ሙሼ፤ የአሁኑ የግል ባንኮችን ያገለለው የቤቶች ቁጠባ ፕሮግራም ሲጨመርበት በባንኮቹ ላይ የሚደርሰው ጉዳት የቱን ያህል እንደሆነ መገመት አያዳግትም ብለዋል፡፡ “መንግስት የግል ባንኮችን ለማጥፋት ታጥቆ መነሣቱ የሚገርመኝ ጉዳይ ነው” ያሉት አቶ ሙሼ፤ በዚህ አካሄድ ከሦስት እና አራት አመት በኋላ የግል ባንኮች ሊጠፉ እንደሚችሉ ምንም ጥያቄ የሚያስነሣ ጉዳይ አይደለም ይላሉ፡፡
ኢህአዴግ ጉልበትና አቅም ያለው የግል ዘርፍ እንዲፈጠር አይፈልግም የሚሉት አቶ ሙሼ፤ በግል ባንኮች ላይ እየደረሠ ያለው ጫናም የዚሁ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህ አባባላቸው ማስረጃ ሲያቀርቡም በቅርቡ የወጣ ጥናት ኢትዮጵያ በመንግስት ኢንቨስትመንት ከአለም 2ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ በግል ኢንቨስትመንት ግን በመጨረሻው ረድፍ ከተዘረዘሩት ሃገራት አንዷ ነች ብለዋል፡፡ አቶ ቡልቻ ደመቅሣ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊትም ከቻይና ለሚመጣ ማንኛውም እቃ በንግድ ባንክ በኩል ብቻ ግብይቱ ይፈፀም የሚል ህግ መፅደቁን አስታውሠው፣ ያሁኑ ሲጨመርበት በእርግጥም የግል ባንክ ዘርፉ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበታል ብለዋል፡፡ መንግስት በተደጋጋሚ በባንክ አሠራር ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ለዘለቄታው የማያዋጣ ተግባር መሆኑን የጠቆሙት አቶ ቡልቻ፤ እንዲህ ማድረጉም አገሪቱን የዓለም ንግድ ድርጅትን ከመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ማህበራት አባልነት እንዳገለላት በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
   
 Posted By.Dawit Demelash

Wednesday, June 26, 2013

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”

“ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”
tesfaye



“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር ዝዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤ መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኳ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝቷል፤ ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላርሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ … ባካችሁ ተውኝ … ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣ በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር፤ ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጥቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም ኢሜሌ ላይ የስኮላርሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ ነው እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል፤ እሱም ሪኮመንድ አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣ አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ… (ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡ ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም፡፡ስትደበደብ፣ ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ፤ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ? እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነው የነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝን ለመርዳት የምትፈልጉ አንባብያን ከፍኖተ ነፃነት መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ (ምንጭ ፍኖተ ነጻነት)
   Posted By.Dawit Demelash
የዕለቱ ዜና ዘገባ ( ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ )    26.06.2013




ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑት.http://www.finote.org/Fino26_06_2013.mp3

   Posted By.Dawit Demelash

Tuesday, June 25, 2013

ኦባንግ ከቴላቪቭ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ

“መኖር አለ፣ መሞት አለና ወደ ህሊናችን እንመለስ"
obang-in-israel-edited


እስራኤል ኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ፍላጎት የሚመረጥ የተረጋጋ መንግስት እንዲቆም ከመቼውም ጊዜ በላይ የምትንቀሳቀስበት ወቅት ላይ መሆኗን ለማሳሰብ በነገው እለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ አስታወቁ። የሒብሩ ዩኒቨርስቲ ምሁራንና ማህበረሰብ ለአቶ ኦባንግ መልክት ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ንግግር ያደርጋሉ። በእስራኤል የሚኖሩ ስደተኛ ወገኖችን አስመልክቶ ቃል እንደተገባላቸውም አመልክተዋል። አቶ ሳሙኤል አለባቸው “መኖርና መሞት ስላለ ወደ ህሊናችን ልንመለስ ይገባል” አሉ።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የአሜሪካ እንደራሴ (ኮንግረንስማን) ክሪስ ስሚዝ በመሩት የምክክር ሸንጎ ላይ ንግግርና ማብራሪያ ካሰሙ በኋላ ወዲያውኑ በቀጥታ ወደ እስራኤል አምርተው ነበር። ለሁለት ጉዳዮች ወደ እስራኤል ያመሩት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በነገው ዕለት እንደሚመክሩ ለጎልጉል ሲያስታውቁ ስለሚናገሩበት ጉዳይም ፍንጭ ሰጥተዋል።
የሚያገኟቸውን ባለስልጣናት ሳይዘረዝሩ ስለ ምክክሩ የተናገሩት አቶ ኦባንግ “ዛሬ እስራኤል ኢትዮጵያ ላይ ህዝብ አምኖና መርጦ የሚያቆመው መንግስት እንዲመሰረት ከማንም በላይ መስራት እንዳለበት ወቅታዊ እውነቶችን በማንሳት አሳስባለሁ” ብለዋል። “እስራኤል” አሉ ጥቁሩ ሰው “እስራኤል አሁን ባለው የኢህአዴግ ተጨባጭ ሁኔታ ዝምታን አትመርጥም። ዝም ልበል ካለች የመጀመሪያዋ ተጎጂ አገር ትሆናለች። የምንግባባበት ወቅት ላይ ስለደረስን በማስረጃ እንነጋገራለን። ቀና ምላሽ እንጠብቃለን” በማለት አስረድተዋል፡፡hebrew-university
ምክክሩ እንዴት ሊዘጋጅ እንደቻለ ተጠይቀው “እቅድ ተይዞለት የተሰራ፣ ጊዜው ሲደርስ የተደረገ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በሒብሩ ዩኒቨርስቲ የሕግ ፋኩልቲ ተገኝተው ለምሁራኖችና ተተኪ ፖለቲከኞችና የአዲሱ ትውልድ አባላቶች ንግግር እንደሚያቀርቡ አቶ ኦባንግ አስገንዝበዋል።
በዩኒቨርስቲው በሚያደርጉት ንግግር የሁሉንም ስሜት የሚነካ፣ ከራሳቸውና ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት አንጻር  የወደፊቱን በመተንበይ መንግስታቸው ኢትዮጵያ ላይ ያለውን አቋም በተረጋጋ መሰረት ላይ እንዲተክል የቀረበለትን ጥሪ እንዲቀበል ድጋፍ እንዲያደርጉ እንደሚጠይቁ ታውቋል።
በህንድ አገር ያቀረቡትን የትግል ጥሪ ተቀብለው ካራቱሪ ላይ ዘመቻ የጀመሩ “የመሃትማ ጋንዲ ፍሬዎች“  መገኘታቸውን አቶ ኦባንግ አስታውሰዋል። አሁንም በነጻ አውጪ ሰም አገር እየመራ ያለው ህወሃት እየፈጸመ ያለውን አሰቃቂ ተግባር ናዚ ከፈጸመው ተግባር ጋር እንዲመዝኑት በስፋት በመረጃ የተደገፈ ንግግር እንደሚያደርጉ ከገለጻቸው ለመረዳት ተችሏል። ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚያቀርቡም አመልክተዋል።
አቶ ኦባንግ እስራኤል ስለሄዱበት ሌላው አንገብጋቢ ጉዳይ ሲያስረዱ፣ በመጀመሪያ የገለጹት “በመደራጀት ድል ይገኛል” በሚል መገረማቸውን በመግለጽ ነው። የተደረገላቸው አቀባበል ልባቸውን እንደነካው፣ የተሰራው ስራና የተገኘው ውጤት ደግሞ እንዳረካቸው የገለጹት የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል አመራር አባላትን በማመስገን ነው።
ከተቋቋመ አስር ወር ያልሞላው ማህበር በእስራኤል የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ውስጥ እየሰሩ የዜጎችን መረጃ በማበላሸት፣ በማስተርጎም ስራ ወቅት መረጃ በማዛባት፣ በማሳሳትና ዓ.ም. በማሳከር የስደት ማመልከቻቸው እንዲበላሽ ሲያደርጉ የነበሩ የህወሃት አባላት ላይ ማስረጃ በማሰባሰብ ባካሄዱት ትግል ድል ተቀዳጅተዋል። የእስራኤል የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት የቀረበለትን ማስረጃ ተመልክቶ የወያኔ አባላት የሆኑትን ሰራተኞች እንዲያስወግድ የተደረገው ጥረት አድካሚ እንደነበር ወ/ሮ ጽጌ ማርያም አቤ ለጎልጉል ተናግረዋል።israel israel 1
የማህበሩ የፋይናንስ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ጽጌ ማሪያም አብረዋቸው የሚኖሩ የህወሃት ደጋፊዎች አገር ቤት እንደሚያደርጉት በማስፈራራት፣ በካሜራና በቪዲዮ በመቅረጽ ምስላችንን ለኤምባሲ በመስጠት፣ ወደ አገር ቤት የሚሄዱ እንደሚታሰሩ ወዘተ ተግባራት በመዘርዘር እንደሚያስፈራሩ አመልክተዋል። አገሩ ግን ኢትዮጵያ ባለመሆኑ ከጫጫታ እንደማያልፍ የተናገሩት ጽጌ ማርያም፣ “ስንሰባሰብ፤ ገንዘብ በመሰብሰብ አሸባሪዎችን ሊረዱ ነው። የአክራሪ ደጋፊዎች ናቸው፤ ወዘተ በሚል ለፖሊስ ይከሱናል። አሁን ግን ሁሉም ዝምታውን ሰብሮ ተባብሯል። እነሱም ሟምተዋል” ብለዋል።
የማህበሩ ጸሐፊ አቶ ጥላሁን በሻህ በበኩላቸው ከትናንት በስቲያ አቶ ኦባንግ በተገኙበት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገኙት የህወሃት ሰዎች ስብሰባውን ለማወክ ጥረት አድርገው አንደነበር አመልክተዋል። አቶ ኦባንግን ጥያቄ እንጠይቃለን በማለት “አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለህም” በማለት ለመዛለፍ እንደሞከሩም ተናግረዋል። ስብሰባው ሲጀመር አገር ቤት ህወሃት በበደኖ ያስፈጸመውን ጭፍጨፋ ያካተተ ቀንጭብ ምስል (ቪዲዮ ክሊፕ) መታየቱ ያናደዳቸው የህወሃት ደጋፊዎች “ይህ በኃይለሥላሴ አስተዳደር ወቅት የተፈጸመና እናንተ ቆርጣችሁ ቀጥላችሁ ያዘጋጃችሁት ነው” ማለታቸውን አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።
በበደኖ እልቂት ቤተሰቦቿን ያጣች አንድ እህት ባጋጣሚ ስብሰባው ላይ ተገኝታ ስለነበር በሰማቸው ክህደት የተነሳ ራስዋን መቆጣጠር ተስኗት እያነባች መነሳቷን አቶ ጥላሁን ያስታውሳሉ። ጭፋጨፋውን ህወሃት በውክልና አስፈጽሞ ከኦነግ ጋር ሲጣላ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ጭፋጨፋው ከተከናወነ ከሁለት ዓመት በኋላ  ይፋ መሆኑንን “እኔ እማኝ ነኝ” በማለት መናገሯን አመልክተዋል።
በስብሰባው ላይ የተገኙ ወገኖች ቢበሳጩም ራሳቸውን በመቆጣጠርና አስቀድሞ በማህበሩ በተሰጠ መመሪያ መሰረት በሰላም የተፈለገለትን ዓላማ አሳክቶ መጠናቀቁን አቶ ጥላሁን አስረድተዋል። ከአቶ ጥላሁን በሻና ጽጌ ማርያም አቤ ጋር ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ሙሉ ሪፖርት በቀጣይ እናቀርባለን።
በስብሰባው ላይ “ኢትዮጵያዊ አይደለህም” የተባሉት አቶ ኦባንግ ምን ምላሽ እንደሰጡ ተጠይቀው “ምን ምላሽ እሰጠዋለሁ! ከመለስ የሚገኘው ትምህርት ውጤቱ ይህ ነው። የመለስ ፍሬዎች መጠናቸው እዚህ ድረስ ነው። እኔም ሆንኩ መላው ጋምቤላ ህዝብ ስለ ኢትዮጵያዊነታቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ ተሰምቶ አይታወቅም። ለአገራቸው ከመሞት ውጪ በባንዳነት ስማቸው ተነስቶም ሆነ ተከስሰው አያውቅም። እንዲህ ዓይነት ሰዎችን ጭምር ነጻ ለመውጣት እንደምንሰራ ግን ነግሬያቸዋለሁ። እምነታችን ጥላቻ ስላልሆነ ላይገባቸው ይችላል። እኛ እንደዚህ ነን” ብለዋል።israel meeting
ጉባኤው በእስር ላይ ባሉት የሰላም ታጋይ አቶ አንዷለም አራጌ ስም የተሰየመ ሲሆን ማህበሩ ከጎናቸው መቆሙን ለመግለጽ ውስን አንድ ሺህ ዶላር ለቤተሰብ ለማድረስ መወሰኑን አስታውቋል። በስም የሚታወቁና የማይታወቁትን የህሊና እስረኞች ከልብ ለመደገፍና አለኝታነታቸውን ለመግለጽ ወደፊትም እንሰራለን ብለዋል። አዳዲስ መሪዎችንም እናበረታታለን ብለዋል።
የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ሳሙዔል አለባቸው ጉባኤውን ሲከፍቱ “መኖር አለ፤ መሞት አለ። በጉባኤው ላይ ገለልተኞች፣ ተቃዋሚዎችና አገር ቤት ያለውን አገዛዝ የሚደግፉ አሉ። ሁሉንም መሆን ይቻላል ግን በስርዓት እናድርገው” በማለት ተናግረዋል። አቶ ኦባንግ ከሚመሩት የጋራ ንቅናቄ ጋር በመሆን በጀመሩት ፕሮጀክት በስደት ከለላ ካገኙ በኋላ ወገኖቻቸውን የሚሰልሉትን በማጋለጥና በወንጀል ለማስቀጣት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል። ሰማያዊ ፓርቲ ለፈጸመው ታላቅ ተግባርና ህዝብ ለፈጸመው አኩሪ ገድል ክብር እንዳላቸው አመልክተዋል። ለጉባኤው መሳካት ትብብር ላደረጉላቸው ሚዲያዎች ምስጋና አቅርበዋል። የሽግግር ካውንስል ላደረገላቸው ተደጋጋሚ ትብብር ያላቸውን አድናቆት ሰንዝረዋል። የአቶ ኦባንግ በመካከላቸው መገኘት ታላቅ ክብር እንደተሰማቸው አስታውቀዋል።
     Posted By.Dawit Demelash

Monday, June 24, 2013

የዕለቱ ዜና ዘገባ ( ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ )    23.06.2013



ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑት http://www.finote.org/Finot23_06_2013.mp


      Posted By.Dawit Demelash

“አሜሪካ አቋማን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ ናት” ክሪስ ስሚዝ

"አሸባሪነትን መዋጋት የግፍ ማከናወኛ ሽፋን አይሆንም"
gear 1


ኢህአዴግ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም ከአሜሪካ ጋር የመሰረተውን ግንኙነት አስታክኮ የሚፈጽመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ተገለጸ። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ የምትመረምርበት ወቅት ላይ ትገኛለች ተባለ። ኢህአዴግ ጸረሽብርተኝነትን ለአፈናና ለበጀት ማሟያ እየተጠቀመበት እንደማይቀጥል ተመለከተ።
አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው እንደራሴ (ኮንግረስማን) ክሪስ ስሚዝ ያስታወቁት ሽብርተኛነትን አስመልክቶ ጠንካራ ማሳሰቢያ በማስቀመጥ ነው።
እንደራሴ ስሚዝ የኢትዮጵያ ጉዳይ የተደመጠበትን የምክክር ሸንጎ ከዘጉ በኋላ በተለይ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት “አሜሪካ በኢህአዴግ ላይ ያላትን አቋም የምትመረምርበት ወቅት ላይ ትገኛለች” ብለዋል።
አሜሪካ ከሰብአዊ ርዳታ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግና በተለይም ኢትዮጵያና አሜሪካ አሸባሪነትን በመዋጋት በኩል አብረው እንደሚሰሩ ያመለከቱት እንደራሴው፣ “ሽብርንና ሽብርተኛነትን የመታገል ትብብር ግን የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመርገጥ ፍቃድ ማግኛ አይደለም። የመብት ረገጣ ሽፋን ሊሆን አይገባም” በማለት የኢህአዴግና የመሪዎቹን ተግባር ኮንነዋል።
“አንድ አገር ገና ለገና ሽብርተኛነትን ለመዋጋት ከአሜሪካ ጎን ስለቆመ ብቻ የህዝብ ሰብአዊ መብቶችና የዴሞክራሲ አተገባበር ላይ ዝም ሊባል አይገባም” በማለት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ስሚዝ፣ ሽብርን መዋጋት የኢትዮጵያ የራስዋም ፍላጎት አንደሆነ አመልክተዋል።
“ስለዚህ” አሉ ክሪስ ስሚዝ፣ “ስለዚህ የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል”
“ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በአዲስ አበባው መንግስት ላይ የማያወላውል ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ማሳየት አለባቸው” ሲሉ የተደመጡት ክሪስ ስሚዝ “ከዚህ ቀደም አርቅቄ፣ አስተዋውቄ፣ ለውይይት አቅርቤው የነበረውን ኤች አር 2003 ህግ እንደገና በማሻሻል ለድምጽ አቀርበዋለሁ” ብለዋል።
“የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ህገደንብ” የሚል ስያሜ ያለው ህግ፣ ኢትዮጵያን የሚመራው ኢህአዴግ ከአሜሪካ መንግስት ለሚፈልገው ማናቸውም ድጋፍ መሟላት የሚገባቸውን የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብት ግብአቶችን በቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ነው። እንደራሴ ክሪስ እንደገና ለድምጽ እንደሚያቀርቡት ደጋግመው የገለጹት ይህ ህግ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ አፍስሶ በአሜሪካን ጎትጓቾች (ሎቢዪስቶች) ዘመቻ ያካሄደበት ነው።
መለስን ”አሮጋንት/ዕብሪተኛ/“ በመለት የገለጹት ክሪስ ስሚዝ “ከመለስ ሞት በኋላ ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ አቅጣጫ ታመራለች” የሚል እምነት እንደነበራቸው በመናገር “የሰማሁት ምስክርነት ከዚህ የተለየ፣ ተስፋ ከተደረገው ተቃራኒ ነው” ብለዋል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ “ብዙዎች” ሲሉ በጥንቃቄ የገለጹዋቸው አካላት ከመለስ ሞት በኋላ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ መንግድ ታመራለች የሚል እምነት እንደነበራቸው ሳይሸሽጉ ተናግረዋል። በውል የተየው ነገር ኢትዮጵያዊያን ወደ ባሰበት ችግርና የመብት ረገጣ የመዘዋወራቸው ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል። ይህም አሳሳቢ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በማብቂያቸውም “አሁን ፖሊሲያችንን ዳግም የመፈተሽያ ጊዜ ላይ ነን። ቁም ነገሩ ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር መቆሙ ላይ ነው። ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር እንቆማለን” የሚል ከተለመደው የአሜሪካ አቋም የተለየ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ኦባንግ ሜቶና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የተገኙበትን የምክክር ሸንጎ ተከትሎ እስካሁን ድረስ የኢህአዴግ አቋምና ምላሽ አልታወቀም። ይሁን እንጂ ቀደምሲል ኤች አር 2003 ህግ ሆኖ እንዳይጸድቅ ኢህአዴግና ወዳጅ ባለሃብቶች ተመሳሳይ ተግባር ለማከናወን ሩጫ መጀመራቸው ተሰምቷል። በተጨማሪም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዲፕሎማሲ ጅምናስቲክ መጀመሩ ታውቋል።
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በተለያየ ወቅት መለስ በሽብርተኛ ትግል ሰበብ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እያምታቱ እንደሆነ በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል። ሆን ተብሎ በተሽከርካሪዎች ላይ የተቀነባበረ የፈንጂ ማፈንዳት፣ ህዝብን የማሸበር ተግባር እንደሚፈጸም በማመልከት ተቃዋሚዎች ሲጮሁ ሰሚ አልነበራቸውም። የሹልክዓምድ (ዊኪሊክስ) መረጃ ይህንኑ ይፋ ማድረጉና ኢህአዴግ ራሱ ፈንጂ አፈንድቶ “አሸባሪዎች ፈንጂ አፈነዱ” በሚል እንደሚያምታታ ማጋለጡ ይታወሳል።
አቶ መለስ አሜሪካና ምዕራባዊያን ሰብአዊ መብትን፣ ምርጫንና የዲሞክራሲ መብቶችን አስመልክቶ ጥያቄ ሲያቀርቡላቸው “ጦራችንን ከሶማሊያ እናስወጣለን፣ ቀጠናው ቢተራመስ ተጠያቂ አይደለንም” የሚል ምላሽ  እየሰጡ ያስፈራሩ እንደነበር የሚጠቁሙ የጎልጉል ምንጮች “ኢህአዴግ ብር ሲፈልግና ካዝናው ሲጎድል ዘወትር የሚያነሳው የሽብርና አሸባሪዎችን የመታገል ውለታ ድርጎ ነው” ብለዋል። በ1997 ምርጫ ወቅት የተሸነፈው ኢህአዴግ በወቅቱ አሜሪካን ጫና ልታደርግ ስትሞክር “ሰራዊታችንን ይዘን ወደ ክልላችን እንገባለን። ተቃዋሚዎች ጦር የላቸውም። በቀጣናው ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ አይደለንም” በማለት አቶ መለስ አሜሪካን ጫናዋን አቁማ ከህወሃት ጎን እንድትቆም ማድረጋቸውን ለጉዳዩ ቅርብ የሆነ ይናገራሉ። ያም ሆነ ይህ እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ኢህአዴግ የውጪውን ዓለም የሚጋልብበትን የፖለቲካ “ጆከሩን” ወይም “ሽብርን መታገል” መርጠው ” ካሁን በኋላ በዚህ ሂሳብ መጫወት አይቻልም” ማለታቸው ቀጣዩን የፖለቲካ ጨዋታ እንደሚያከረው ተገምቷል።
  Posted By.Dawit Demelash

Sunday, June 23, 2013

የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል

ዛሬ ወያኔ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር እስከቻሉ ድረስ የአማራ ህዝብ መራቆት፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሰቆቃና ሞት የማይለዩት ህዝብ እንደሆነ ይቀጥላል።

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ይህን በእብሪትና በጥላቻ የተሞላ በወያኔ የሚፈጸም በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የባላጌዎች ጥቃት ማስቆም የሚቻለው የወያኔን እብሪት በጠመንጃ እና በተባበረ የህዝብ አመጽ ማስተንፈስ እስከተቻለ ብቻ ነው ብሎ ያምናል። እስካሁን ወያኔ በከንቱ ያፈሰሰውን የንጹሃን አማሮች ደም መፋረድ የሚቻለው ከጠምንጃ አፈሙዝ በሚወጣ እሳት ብቻ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል። ከንፈር መምጠጥ፣ ዋይታ፣ ኡኡታ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሰላማዊ ሰልፍና በየፈረንጅ በር ደጅ መጽናት ወያኔ የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር የወያኔ እንጨት ሰባሪና ውሃ ተሸካሚ አድርጎ፣ ነጻነቱንና ክብሩን ገፎ አዋርዶ ለመግዛት የዘረጋውን መርሃ ግብር እንዲያጥፍ አያደርገውም።
ወያኔ ይሉኝታ ያልዘራበት፣ ትእግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ ሳቢነትን እንደሞኝነት የሚቆጥር በአማራው ላይ ቂምና ጥላቻን ሰንቆ የተነሳ ጨካኝ ድርጅት ነው። ይህን ድርጅት ስለጀግንነቱና ስለወርቅ ዘርነቱ እጅግ የተሳሳተና የተጋነነ ግምት ያለው፣ ማንም ምንም አያደርገኝም በሚል ትምክህት ተወጥሮ የሚኖር ድርጅት ነው። ከእንዲህ አይነቱ በራሱ ፕሮፓጋንዳና ከንቱ ውዳሴ ከሰከረ ድርጅት ጋር የሚደረግ ትግል ያለምንም መወላወል በከፍተኛ እልህና ጭካኔ የሚካሄድ ብቻ ነው። የአማራውን ሰቆቃ ለማስቆም ወያኔ “እዩኝ እዩኝ” እንዳለለ “ደብቁኝ ደብቁኝ” እስከሚል የሚዘምቱበት እና ክንዳቸውን የሚያሳዩት ጀግኖችን ይሻል። ከወያኔ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠው ገድለው ለመሞ ት የቆረጡ የወገን ደምመላሾችን ይጠይቃል። ቤታቸውን ዱርና ገደሉን አድርገው፣ “ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል” የሚሉ ቁጡዎችን ይፈልጋል። የአማራውን ህዝብ እልቂት ለማቆም፣ የወንድ ልጅ እናት በገመድ የምትታጠቅበት፣ ልጇን አሞራ እንጂ ሰው የማይቀብርበት ሌላ ታሪካዊ ዘመን መምጣቱን ሁላችንም መቀበል ይኖርብናል።
የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል አባላት ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በሚያሳየው እብሪት ተቃጥለናል። በግነናል። የእዚህ እብሪት ማርከሻ ጠመንጃ ነው፡ እሳትና አርር ብቻ ነው ብለናል። ሌላው ሁሉ አማራጭ ተፈትሿል፣ተሞክሯል፣ታይቷል ሌላ አማራጭ የለም ብለናል። የቀረው አንድ ምርጫ ነው፦:መሞ ት ወይም መግደል ። እኛ ይህን አውቀን ከያለንበት ተጠራርተን የአማራን ህዝብ በቀላሉ ልንደርስበት በምንችልበት ምድር እየተሰባሰብን ነው። የከፋህ፣ የመረረህ፣የተበደልክ በቃኝ ያልክ ና ተቀላቀለን፣ የወገናችንን የአሳርና የመከራ ዘመን ማብቃት በወያኔ ቀብር ላይ እናረጋግጥ ።
ውድመት ለአማራ ህዝብ ጠላት ለዘረኛው ወያኔ!!!!!!!!!
ድል በወያኔ ለሚረገጡ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!!!!!!!!!!!!
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል
  Posted By,Dawit Demelash

Saturday, June 22, 2013

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ?

“ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”
hearing3


አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ “ክፉ ጠረን” አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ። አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” የዛሬ 22ዓመት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከተናገሩት፡፡
“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ (የነጻነት መንገዱን አትዝጉብን)። ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ … እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ አለ … እሱም እርቅ ነው … ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚው በኩል ዓመኔታ የሚጣልባቸው አሉ … ” አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡
“የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ የማይቀር ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። … ሕዝብ በጭቆና አገዛዝ እየተገዛ ዝም ብሎ የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል … ዝም ብሎ ግን አይቀመጥም … ይፈነዳል … ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፡፡
አቶ መለስ “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው … እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” ክሪስ ስሚዝ፡፡
“እድሜ ልካችሁን አትገዙም ብለን መክረናቸዋል” ዶናልድ ያማሞቶ፡፡
 hearing1የምክክሩ መድረክ
“ኢትዮጵያ ድኅረ መለስ፤ የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች የወደፊት ዕጣ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ፤ ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ጸሐፊ ዶናልድ ያማሞቶ፣ የአሜሪካ የዓለምአቀፍ የልማት ተራድዖ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ኤሪል ጋስት፤ የማይክል አንሳሪ የአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ፒተር ፓሃም እንዲሁም በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግሥት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አዶቴ አክዌ የተጋበዙበት የምክክር ሸንጎ ላይ የቀረቡት ሃሳቦች በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ነበሩ። ሰብሳቢው በአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በአፍሪካ፣ በዓለምአቀፍ ጤናና ሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ንዑስኮሚቴ ሰብሳቢ ክሪስቶፈር ስሚዝ ደግሞ ኢህአዴግ ከፍተኛ ገንዘብ አፍስሶ ያኮላሽው ኤችአር2003 የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረቂቅ ህግ ከሟቹ ዶናልድ ፔይን ጋር በማዘጋጀት በምክርቤት ለማስወሰን ያስቻሉ ነበሩ።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት የግንቦት 7 ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደ እምነታቸው ንግግር አድርገዋል። ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። በምክክር ሸንጎው ላይ ከተጋበዙት መካካል ኢህአዴግ በቀጥታ ባለመወከሉ “ያለመመጣጠን (ያለመወከል)” ችግር አልነበረም፡፡ ኢህአዴግም ተገኝቶ ቢሆን ኖር ሊናገረው ከሚችለው በላይ ተናጋሪና ተከራካሪ ስለነበረው የኢህአዴግ መኖር አስፈላጊ አልነበረም የሚል አስተያየት ስብሰባውን በአካል ተገኝተው ከታዘቡና በቀጥታ ስርጭት ከተከታተሉ ወገኖች  ተደምጧል።
ያም ሆኖ ግን ምክክሩ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የበላይ ሰው ክሪስ ስሚዝ ቢሮ በመገኘት አሉ የሚሏቸውን መከራከሪያዎች አቅርበው ነበር። የጎልጉል ምንጮች ለማረጋገጥ እንደቻሉት ኢህአዴግ ምክክሩን ተከትሎ ኤች አር 2003 ረቂቅ ሕግ እንዳይጸድቅ የተጠቀመበትን መንገድ ገና ካሁኑ በድጋሚ ጀምሯል።
ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እያደር የእግር እሳት ሆኖ ያለፈውን የ1997 ምርጫ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ከኢህአዴግ መሪ አቶ መለስ ጋር በርካታ ዲፕሎማቶች ተነጋግረዋል። አንዱ ከኒውጀርሲ ጠቅላይግዛት የአሜሪካ ም/ቤት ተወካይ ክሪስ ስሚዝ ነበሩ። “ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል የተዘጋጀውን የምክክር ሸንጎ በመሪነታቸው ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው …” በማለት ነበር የገለጹዋቸው። የርሳቸው ገለጻ ታዲያ ከሁለት ዓስርተ ዓመታት በፊት ኢህአዴግ እንዲነግስ ሲወሰን ከቃል በላይ እሳት እየተፉ ንግግር ያደረጉትን ኢትዮጵያዊ አስታወሰ – የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው የኢትዮጵያን ተላልፎ መሰጠት በዚሁ በሰኔ ወር ከ22ዓመት በፊት አስረግጠው በማስረጃና በማስጠንቀቂያ በመቃወመ፣ በማሳሰብ፣ እንደማይሆን በመምከር፣ አድሮ እንደሚያቃጥል በማስጠንቀቅ፣ ላቀረቡት ንግግር የክሪስ ስሚዝ ገለጻ በማረጋገጫነት የሚቆም እውነት ይሆናል።
አሜሪካ ራስዋ ቀብታና ባርካ በትረ ሹመት የሰጠቻቸውን ሰዎች ከ22ዓመት በኋላ መልሳ “ገምግሙልኝ” ማለቷ አስገራሚ የሚሆንባቸው ጥቂት አይደሉም። ሰብሳቢው በመግቢያቸው የተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት ወቅታዊ መገለጫ፣ ቀደም ሲል ሚ/ር ያማሞቶን በመጥቀስ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረጋቸውን መረጃዎች ለተከታተሉ “አሜሪካኖቹ ምን የማያውቁት ነገር አለና ነው የሚጠይቁት ያሰኛል” በሚል የሚገረሙ በርካታዎች ናቸው።
obang at hearingለዚህ ይመስላል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ታሪካዊውን የኮሎኔል ጎሹ “ትንቢትና የኢትዮጵያ ህዝብን የሚወክል የምልጃ መቃተት” በማስታወስ ቀዳሚ የሆኑት። አስከትለውም “አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት። (ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ)” የሚል መልክት አስተላለፉ።
የጋራ ንቅናቄው መሪ በድርጅታቸው መርህ ላይ ተመሥርተው በሰጡት የምስክርነት ቃል “ህወሓት እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየመራ እንደሆነ፤ መለስ ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) ዓይነት መሪ እንደነበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 22ዓመታት በመከራ ውስጥ ያለና የዛሬ 8ዓመት በዚሁ ቦታ ላይ ያማሞቶ ኢትዮጵያ በአቋራጭ መንገድ (ክሮስሮድ) ላይ እንደምትገኝ” መናገሩ አቶ ኦባንግ ካስታወሱ በኋላ “መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከስምንት ዓመት በኋላ አሁም አንሻገርም ወይ፤ አናቋርጠውም ወይ” በማለት ተሰብሳቢውን ያስደመመ ለሰብሳቢዎቹ ግልጽ ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡
አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም “ኢትዮጵያውያን የምንጠይቀው በጣም ቀላል ጥያቄ ነው፤ አሜሪካኖች የሚመኩበትን ሰብዓዊ መብት እኛ ተነፍገናል፤ የራሳችን ክሪስ ስሚዝ ይኑሩን ብቻ ነው የምንለው” ካሉ በኋላ በኃይለሥላሴም ሆነ በመንግሥቱ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ዕድላቸውን እንደተነፈጉ አስታውሰዋል፡፡ በወቅቱም በዚሁ ም/ቤት የዛሬ 22ዓመት በወርሃ ሰኔ ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ የዛሬዋን ኢትዮጵያን መተንበያቸውን አቶ ኦባንግ በንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡ አሁንም የኢትዮጵያውያንን ቁርጠኛ አቋም ምን እንደሆነ ለአሜሪካውያኑ ግልጽ አድርገዋል “አሜሪካ እንድታድነን አይደለም የምንጠይቀው፤ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፤ በነጻነት መንገዳችን ላይ ግን ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ኦባማ ለፕሬዚዳንትነት ሲወዳደር በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሚያገኙት ጥቂት ደመወዝ ለምርጫው ዘመቻ ረድተው ነበር፤ ከኦባማ ግን የሰማነው ነገር እስካሁን ምንም የለም፤ ነጻነታችንን እየለመንን አይደለም፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን” በማለት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን የነጻነት መንፈስ የቀሰቀሰ ንግግር አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲ ለውጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ሰጥቻለሁ እንደሚል ከጠቀሱ በኋላ “ይህ ሁሉ ገንዘብ የት ነው የገባው፤ የት ነው የሄደው” በማለት ኢህአዴግ ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይ ሥልጣኑን እንደተቆጣጠረ፤ ሙስሊሙ መሪውን እንምረጥ ሲል አሸባሪ ተብሎ እንደሚፈረጅ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር አገርና መሬት ብቻ ሳይሆን የምንጋራው በደም የተሳሰርን መሆናችን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ አንድ ጊዜም እንኳን ጦርነት ሰብከውም ሆነ መሳሪያ አንስተው የማያውቁ መሆናቸውን የተናገሩት ኦባንግ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት “አሸባሪ” መባላቸውን በመናገር የኢህአዴግን አሸባሪነት አጋልጠዋል፡፡ እስካሁን በአገራችን ላይ የፈሰሰው ደም በቂ እንደሆነ የጠቆሙት የጋራ ንቅናቄው መሪ፤ በኤድስና ምግብ በማጣት የረደሰብን ዕልቂት በቂ እንደሆነና ከእንግዲህ ወዲህ መጋደል እንደሌለብን ሆኖም ከኢህዴግም ሆነ ከተቃዋሚ በኩል አመኔታ የሚጣልባቸው ሰዎች ስላሉ እስካሁን ያልተሞከረውን የዕርቅ መንገድ (ሥራ) በኢትዮጵያ መከናወን እንዳለበት አቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመሩት ድርጅት መርህና በሚታገሉለት የማዕዘን ሃሳብ ላይ ተተርሰው ሃሳባቸውን አጠቃልለዋል፡፡
በምክክር ሸንጎው ላይ የተገኙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው የንግግራቸውና የማሳሰቢያቸው ማሳረጊያ ሊባል የሚችል መልዕክት አስተላልፈዋል። ዶ/ር ብርሃኑ “አስተውሉ፣ ልብ ብላችሁ ተገንዘቡ” በማለት ያሳሰቡት ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወዱ ሁሉ የሚጠበቡበት፣ እንዲከሰት የማይፈልጉትን የመጨረሻው ስጋት ነው።nega
በምክሩ ላይ በቀዳሚነት ምልከታቸውን ያብራሩት ዶ/ር ብርሀኑ ኢህአዴግ የዘረጋው የአፈና ስርዓት ያስመረረው ህዝብ፣ ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚያንኮታኩታቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሆን ብሎ የሚተናኮለው ህዝብ፣ ያለው ብቸኛ አማራጭ ብረት ማንሳት ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል። በቅርቡ የኢህአዴግ የአፈና ስርዓት ፈተና እንደሚገጥመው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አለመረጋጋት ቀጣናውን በሙሉ እንደሚረብሽና የአሜሪካንን ጥቅም በእጅጉ እንደሚጎዳ ዶ/ር ብርሃኑ በግልጽ በማስረዳት አሜሪካ ገንዘቧን በተገቢው ቦታ ላይ ማዋል እንዳለባት ምክር ሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተቃዋሚ ኃይሎች አማራጭ ከማጣት የተነሳ ብረት ማንሳታቸውን የጠቆሙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር፤ ሕዝብ ዝም ብሎ በአስከፊ አገዛዝ ሥር እየኖረ እንደማይቀጥል አስጠንቅቀዋል፡፡ በመሆኑም አማራጭ ሲጠፋ ባገኘው መንገድ ሁሉ መብቱን ወደማስጠበቅ እንደሚገፋና በአሁኑ ወቅትም የተቃዋሚ ኃይሎች በመተባበር በኢህአዴግ ላይ ጥቃት መሰንዘር የሚስችላቸውን ብቃትና ኅብረት እንደፈጠሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለውም ኢህአዴግ በምንም መልኩ የማይሰማና በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን ለማስረከብ የማይችል መሆኑን በተለይ በ1997 ምርጫ ካስታወቀ ወዲህ በግልጽ የሚከተለው መርህ በራሱ ማስረጃ እንደሆነ ዶ/ር ብርሃኑ በጥያቄ መልክ ለቀረበላቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢህአዴግ የደምሥር የውጭ ዕርዳታ እንሆነ የተናገሩት የግንቦት 7 መሪ አሜሪካ ከአውሮጳውያን ጋር በመተባበርና ለእያንዳንዱ የተሃድሶ ዕርምጃ ቀነ ገደብ በመሥጠት በተሰጠው ገደብ ውስጥ እስረኞች ካልተፈቱ፤ የምርጫ ኮሚሽን ካልተቀየረ፤ ወዘተ በማለት ዕርዳታው እንደሚቆም በማስጠንቀቅ አሜሪካውያኑ ለኢህአዴግ መመሪያ ቢሰጡ ለገንዘብ ሲል ኢህአዴግ ሊታዘዝ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም በድጋሚ የሰብሳቢውን ስም በመጥራት ትኩረት የጠየቁት ዶ/ር ብርሃኑ “የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ብለዋል።
ከክሪስ አንደበት
ሰብሳቢው ክሪስ ስሚዝ በምክርቤት ስብሰባ ላይ ድምጽ መስጠት በሚገባቸው ረቂቅ ህጎች ላይ ሲሳተፉ ስለነበር ምክከሩ የጀመረው ከታቀደው ሰዓት 1፡30 ያህል ዘግይቶ በመሆኑ ይቅርታ በመጠየቅ ነበር መንበራቸው ላይ ተሰይመው ንግግር ጀመሩት። የምክክሩ ሊቀመንበር አቶ መለስ የዘረጉት አገዛዝ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ልዩ ባህሪው እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ምክከሩን ከፈቱ። ምክክሩ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶችና የዴሞክራሲ ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩርና የአሜሪካ መንግሥት ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያመላከት ምክር የሚካሄድበት እንደሆነ አስገነዘቡ።
ኢትዮጵያ እስላማዊ አሸባሪነትን በቀጣናው በመዋጋት የአሜሪካ ደጋፊ አገር ሆና መቆየቷን፣ ሆኖም ግን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚፈጽመው ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት ተጠያቂ ማድረግ እስካሁን አለመቻሉን ሳይሸሽጉ ተናገሩ።smith3
የፖለቲካ ድርጅቶች በነጻነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን፣ መንግስታዊ ባልሆኑ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች (መያዶች) ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ፣ ጋዘጠኞች እንደሚታሰሩ፣ በርካታ ዜጎች ከመሬታቸው እንደሚፈናቀሉ ወዘተ በመዘርዘር አስረዱ።
የአሜሪካ የዕርዳታ ድርጅት – ዩኤስኤይድ እንደሚለው ከሆነ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግልጽ ግንኙነት ማድረግ ወደፊት የዴሞክራሲና የለውጥ ሂደቶችን ለማሳካት ይረዳል ተብሎ ቢታሰብም፣ በክሪስ ስሚዝ አመለካከት ግን እምነቱ ሊተገበር የሚችል ቢመስልም እስካሁን ምንም ፍሬ እንዳላመጣ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል።
እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ስልታዊ አፈናና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ለሌሎች አገራት መጥፎ ምሳሌ እየሆነ መሄዱን ሊቀመንበር ስሚዝ ጠቅሰዋል፡፡ ንጹሃን ዜጎች ስቃይ፣ ድብደባ እንደሚደርስባቸው፣ በኤሌክትሪክ እንደሚጠበሱና የግዳጅ ወሲብ እንደሚፈጸምባቸው፣ የአምነስቲ ሪፖርት መዘገቡን ክሪስ ስሚዝ በእማኝነት ተናግረዋል፡፡
ራሳቸው ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ረቂቅ ህግ አዘጋጅተው እንደነበርና በወቅቱ የነበረው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ግን ኢትዮጵያን በአሸባሪነት ላይ ወዳጅ በማድረጉ ምክንያት በነበረው ቸልተኝነት የተነሳ ተፈጻሚ ሳይሆን መቅረቱን አስታውቀዋል። ሚ/ር ስሚዝ እነዚህን ጉልህ ህጸጾች በመጠቆም ምክክሩ ላይ ተናጋሪ እንዲሆኑ የተጋበዙትን ክፍሎች በየተራ በማስተዋወቅ ጋብዘዋል። ከንግግሩ በኋላም ጥያቄዎችን ጠይቀዋል። ሌሎች ተሳታፊዎችም ጥያቄ በመሰንዘር ማብራሪያ እንዲወስዱ ተደርጓል።
ያማማቶ ምን አሉ?
ያማሞቶ በመግቢያ ንግግራቸው መለስን አወድሰዋል። አፍሪካን በዓለም መድረክ ከፍ እንድትል ያደረጉ መሪ በማለት አመስግነው ኢትዮጵያ ተሰሚነቷ እንዲጨምር ያደረጉ፣ ተሟጋችና ጎበዝ ተናጋሪ እንደነበሩ መስክረዋል። ኢኮኖሚውን አሳድገዋል፣ ኢትዮጵያን በቀጣናውና በዓለም ታዋቂ አድርገዋል፣ በሶማሊያ ተሟጋች፣ በሱዳን አስታራቂ፣ በአፍሪካ የአየርንብረት ጉዳይ ደግሞ አንደበተ ርዕቱ አፈቀላጤ ነበሩ በማለት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ከሚደረድረው በላይ ቃል አከማችተው ምስጋና ቸረዋቸዋል።
ያማማቶ በማያያዝ እንደ አምባሳደርነታቸው በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ አስመልክቶ አቶ መለስን ማነጋገራቸውን ጠቁመዋል። በሰብዓዊ መብቱን መጓደል ዙሪያም በተመሳሳይ መነጋገራቸውን  አክለዋል።
ካሊፎርኒያ ሎሳንጅለስ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ወረዳ ተወካይ የምክርቤት አባል ሚስዝ ባስ፤ ያማሞቶን መስቀለኛ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር። ጠያቂዋ “የኢህአዴግ መንግሥት ዋናው ችግር ምንድነው? ለምንድነው ይህንን ሁሉ መከራና አፈና የሚያካሂደው” በማለት የመገረም የሚመስል ጥያቄ ጠይቀዋል። ያማሞቶ እንደ መንተባተብ ሲሉ “ችግሩ ምንድ ነው?” በማለት ባስ በድጋሚ ጥያቄያቸውን ወረወሩ። “ችግሩ እንዳለ ነው” ሲሉ ደግመው መልስ የሰጡት ያማሞቶ “ጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም አፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ እንዳሉት ነው፣ የዴሞክራሲ እሴቶች አስፈላጊ ናቸው፣ መጥፎ ህጎች መወገድ አለባቸው፣ እንስራ፣ እንሞክር ብለዋል” አሉና መለሱ።
ኮንግሬስማን ሜዶውስ በኢትዮጵያ ኢህአዴግ ሁሉን ተቆጣጥሮዋል፤ እኛ አሜሪካኖች ምን ልናደርግ እንችላለን? እንዴት ነው ልናስተካክለው የምንችለው? የሚል ጥያቄ ለያማሞቶ ወረወሩ። ያማሞቶም  “ከምርጫው በኋላ ደስተኞች አለመሆናችንን ተናግረናል፡፡ ከበስተጀርባና በፊትለፊት እየሰራን ያለነው ነገር አለ፡፡ ጊዜ የሚወስድ ነው፡፡ ለምሳሌ በሴቶች ላይ የሚደረግ የመብት ጉዳይ አለ እናም ይህንን ከዩስኤድ ጋር እየሰራን ነው” አሉ፡፡
ሜዶውስ የረኩ አይመስልም “እና ያለው ፍርሃት ምንድርነው?” ሲሉ በድጋሚ መልስ መፈለጋቸውን አመለከቱ። “ነግረናቸዋል ፣ ለዘላለም ልትገዙ አትችሉም። ስለዚህ የተቃዋሚውን ተሳትፎ ማበረታታት አለባችሁ ። እነዚህ ተቃዋሚዎች አንድ ቀን መንግሥት ይሆናሉ። ስለዚህ ዝግጅት መደረግ አለበት ብለናቸዋል” የሚል የደፈና መልስ ከያማሞቶ ተሰጠ።
ጋንት፤ የዩኤስ ኤይድ ረዳት ዳይሬክተር
የሴፍቲኔት ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑንና በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እየተረጋጋች እንደሆነ፣ ከዚህም ጋር በማከል ኢኮኖሚው እያደገ እንደሆነ ልክ የኢህአዴግ ወኪል መስለው ተናገሩ። ሰብሳቢው ስሚዝ “ቶርቸር በየቦታው አለ እና ይህንን እንዴት ነው ለማስታረቅ ወይም ለማቆም የሚቻለው?” ሲሉ ማብራሪያ ጠየቁ። ሚ/ር ጋንት “አስቸጋሪ ነገር ነው። ቶርቸር እንዳለ እናውቃለን ግን ዋናው ሥራችን መልካም ነገሮችን ለማበረታታት ነው የምንሞክረው” የሚል ምላሽ ሰጡ።
በሚ/ር ጋንት ንግግር ላይ ተንተርሰው ተጨማሪ ጥያቄ ያቀረቡት ክሪስ ስሚዝ፣ ኢትዮጵያ ትምህርትን አስመልክቶ የሚሊኒየም ጎል ተሳክቷል ማለታቸውን ጠቅሰው “ጋንት ግን እኮ ጥራቱ በጣም የዘቀጠ እንደሆነ ነው ሪፖርቱ የሚያሳየው” ሲሉ ሞገቱዋቸው። የዩኤስ አይዲው ዳይሬክተር ጋንት “አዎ ችግር አለ ግን በርካታ መምህራን ተሰማርተዋል በትምህርቱ በኩል ዕድገት አለ” የሚል መልስ መመለሳቸው ለግንዛቤ ያህል የሚጠቀስ ሆኖ አግኝተነዋል።
ያማሞቶና ጋንት ያቀረቡትን ንግግርና ምስጋና ያደመጡ፣ በአካል ተገኝተው የተከታቱተሉ እንዳሉት በምክክሩ ላይ ኢህአዴግ ቢገኝም የሚጨምረው ምንም ነገር ሊኖር እንደማይችል አመልክተዋል።
ዳግም HR2003
የዛሬ አስር ዓመት፤ ኤች አር 2003 በምክር ቤት ደረጃ ከፍተኛ የሸንጎ (ኮንግሬስ) አባላትን ድጋፍ ካገኘ በኋላ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) አጽድቆት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ ፖሊሲ ሆኖ እንዲጸድቅ ባለመደረጉ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች መከኑ። የህጉ መርቀቅና እንዲጸድቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያስበረገገው ኢህአዴግ ጡረተኛ የሴኔት አባላት ከሚመሩት ዲኤልኤ ፓይፐር ከተባለ የጎትጓች (ሎቢ) ቡድን ጋር ከፍተኛ በጀት በጅቶ ታገለ። ባፈሰሰላቸው መጠን ጎትጓቾቹ ባልደረቦቻቸውን ጠመዘዙና ህጉ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው አዲስ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ህግ እንዳይሆን ተደረገ። ይህንኑ ህግ በማዘጋጀት ከሟቹ የምክርቤት አባል ዶናልድ ፔይን ጋር በወቅቱ ብዙ ደከሙት ክሪስ ስሚዝ የወቅቱን የቡሽ አስተዳደርን በንዝላልነት መድበው አሁን ይሀንኑ ህግ ተግባራዊ የሚደረግበትን አግባብ እንደሚገፉበት አመልክተዋል።
እንዴት እዚህ ተደረሰ?
የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድረጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ (ህወሓት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው። ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱ አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል። ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ  የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረዋል።
ይህ የምክክር ሸንጎ እንዴት ሊዘጋጅ ቻለ ለሚለው ጥያቄ በርካታ ጥረቶች መካሄዳቸውን በመግለጽ ዝርዝር ያላቀረቡት አቶ ኦባንግ ሐሙስ በተካሄደው ምክክር በመካከል ላይ ሚ/ር ስሚዝና ሌሎቹ ተወካዮች በምክርቤት ድምጽ መስጠት ስለነበረባቸው ምክክሩ ተቋርጦ እንደገና ሲጀመር ያልታዩበትን ምክንያት ተናግረዋል። ምክክሩ በተባለው ሰዓት ተጀምሮ ያልቃል የሚል እምነት ስለነበራቸው ሌላ ተደራራቢ የጉዞ መርሃግብር አመቻችተው እንደነበር አመልክተዋል።
“አሁን ስራ ላይ ነኝ” ያሉት አቶ ኦባንግ “እስራኤል አገር ለሁለት ከፍተኛ ጉዳዮች መጓዝ ነበረብኝ። አንዱ የወገኖቻችን ጉዳይ ነው። ሌላኛው ደግሞ የአገራችን ጉዳይ ነው። ከጉዞዬ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት እችላለሁ” በማለት ሁለተኛው ስብሰባ ሲካሄድ እርሳቸው ወደ እስራኤል ለሥራ እየተጓዙ እንደነበር አስታውቀዋል።
 Posted By.Dawit Demelash

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ (ገብረመድህን አርአያ)

June 22, 2013

አቶ ገብረመድህን አርአያ*
ከአውስትራሊያ

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::

ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::
ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::
ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::
Gebremedhin Araya former TPLF
አቶ ገብረመድህን እርአያ
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::
በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::
በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤
1) ደርግ እንደ ፖለቲካ ተቋም እና ስርዓት
2) መለዮ ለባሹ እንደ አገር መከላከያ ሰራዊት
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያዊ የሆነ እና በዘመናዊነቱ በአፍሪካ ጭምር ተወዳዳሪ ያልነበረው እንደነበር ነው:: የደርግ ስርዓት ከወታደሩ በወጡ ሰዎች ቢመሰረትም ሰራዊቱ ግን በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለመሆኑ ከጥያቄ ውስጥ ሊያስግባው የሚችል አንዳችም መከራከሪያ ሊቀርብ አይችልም:: አገራችን ዘመናዊ ጦር ማደረጀት ከጀመረችበት ከሃያኛው ክፍለዘመን መባቻ ጀምሮ በስንት ወጪ እና ጥረት የገነባችውን ጦር የ “ደርግ ጦር” የሚል ቅጽል በመስጠት ከፍተኛ የሆነ የስም እና የሞራል ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙበት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ወያኔ እና ሻዕቢያ ናቸው::
ይህ ጦር ደሙን አፍስሶ ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፤ ራበኝ ፣ ደክመኝ ሳይል ወያኔ እና ሻዕቢያን እግር እግራቸውን እየተከታተለ ሲደመሥሳቸው እና ሲያጠፋቸው የነበረ የኢትዮጵያ ብርቅ ልጅ ነው:: የዛሬው የወያኔ ዘረኛ ሰራዊት ግን እንኳን ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሊከላከል ይቅርና ራሱ የወያኔ ሰራዊት ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ የአንድ ጎጠኛና ዘረኛ ታጣቂ ቡድን ነው:: አሁን ያለው በዘር የተደራጀው ቅጥረኛ እና ባንዳ ሰራዊት በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ የለም::
የደርግ መንግስት በስልጣን በቆየበት 17 አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ቀይ ባህርን የጠበቀ ፤ ከገንጣይ እና አስገንጣዮች አገሪቷን እየተከላከለ ሉዓላዊነትን የጠበቀ የኢትዮጵያ ስርዓት ነበር::
በሚከተለው ርዕዮተ አለም ቀስ በቀስ እየተዳከመ በመሄድ እንደነበረው አገርና ህዝብ ለማዳን አልቻለም:: ደርግ በተዳከመ ጊዜም ሰራዊቱ ይዳከማል:: አንድ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከመንግስት የሚቀርብለት ነገሮች ብዙ ናቸው:: ይህ አልሆነም:: ሰራዊቱም መንግስት በመዳከሙ ምክንያት የነበረው አልበገር ባይነት ስሜቱ እና ጀግንነቱ የውጊያ ብቃቱ ተስፋ በመቁረጡ ችግር እየፈጠረለት ሄደ ቢሆንም ግን ወያኔም ሆነ ሻዕቢያ አሁንም ፈቀቅ ሊሉ አልቻሉም:: የማይበገር የኢትዮጵያ ሰራዊት መሆኑን ያውቁታል እና::
ይህ በዚሁ እንዳለ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት መንግስቱ ሃይለማሪያም ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለቀው ዚምባብዌ ሃራሬ ገቡ:: እዛም ጥገኝነት ጠየቁ:: መሆን የማይገባውን ስራ ሰሩ:: በኢትዮጵያ ሃገራቸው ሰርተው ሂወታቸው ቢያልፍ ታላቅ ስምና ክብር ያገኙ ነበር:: ግን አላደረጉትም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰራዊት ተበተነ::
ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፕሬዚደንት መንግስቱ እግር የተተኩት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን በዜና እወጃ የኢትዮጵያ ሰራዊት የነበርከው በያለህበት ቦታ መሳሪያህን ለህወሃት(ኢህአዴግ) እና ለሻዕቢያ እያስረከብክ ወደ ምትፈልግበት ሂድ፤ ሻዕቢያም ኤርትራን ህወሃትም ኢትዮጵያን እንዲቆጣጠሩ ፈቅደናል በማለት ፍጹም ክህደት በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ እና ህዝብዋን ለደመኛ ጠላቶች አሳልፈው ሰጡ::
ያን በወታደራዊ ሳይንስ እና የጦር ውጊያ የተከማቸ እውቀት እና ችሎታ የነበረውን የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እልም ባለ ገደል ወረወሩት:: ለስንት አመታት የሃገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ እና የጠበቀ ጦር ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. ካልምንም መተዳደሪያ እና የአገልግሎት ክፍያ በየበረሃው ተበተነ:: በስንት ሚሊዮን የሚቆጠሩ የምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ አየር ወለድ እና አየር መቃወሚያ አባላት እና ቤተሰቦች ለመከራ እና ለችግር ተዳረጉ::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔና ሻዕቢያ:: ሻዕቢያ ኤርትራን ሲቆጣጠር ወያኔ ህወሃት ደግሞ ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፈንደቀለት ጸሃይ አዲስ አበባን ግንቦት 20 ቀን 1983 ተቆጣጠረ:: ኢትዮጵያም ለፋሺስት መሪዎች ተዳረገች:: ሰራዊቱ እየጫነ ካለምንም ችግር ካለ ምንም ውጊያ ወያኔ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ:: ከግንቦት 20 ቀን ጀምሮ ወያኔ በከፊል የተቆጣጠረው ወሎ ፣ ጎንደር እና ጎጃም ብቻ ነበር:: ቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ ደቡብ ምስራቅ-ምዕራብ ወያኔ የገባው ከሶስት ወር በኋላ ነበር እንጂ:: ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠረም:: ወደ አዳዲስ ክፍለ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ገንዘብ በመክፈል በነዋሪዎች እየተመራ ነው:: ምክንያቱም ወያኔ ህወሃት ከትግራይ አይወጣም ነበር::
ስለሆነም ለኢትዮጵያ ነጻነትና ዲሞክራሲ ስል ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ የሚለው ከንቱ ውሃ የማይቋጥር መፈክሩ ይህ ትልቅ ምስክርነት የሚያሳየው ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደማያውቃት ነው::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ምን ይዛ መጣች? በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወያኔ ህወሃት በመለስ ዜናዊ የሚመራው የማፍያ ፋሺስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺስቶች መንደላቀቂያ ሆነ:: እነሱም ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራን አስገንጥለው የቀይ ባህር ንግስት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደብ ወይም የባህር በርዋን አጥታ አንገትዋ የተቆረጠ ዝግ አገር አደረጉዋት::
ወያኔ ህወሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ ብሎ ያመጣውን የዘረኝነት ህጉን በኢትዮጵያ ዘረጋ::
ይህ በዚህ እንዳለ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እና ግንቦት 20 ምን ይዞለት መጣ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ከግንቦት ሃያ ቀን ምን ተጠቀመ? ምን እድገት አገኘ? ፍትህና ነጻነቱ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቱስ እንዴት ሆነ? የሃገሪቷ ሃብትስ በትክክል ለህዝብ ጥቅም ዋለ ወይስ ምን ሆነ? የትምህርት እድገቱስ? የዘመናዊ ቴክኖሎጂስ ለህዝብ ተስፋፋ ወይ? ሌላም ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል:: ለሰው ልጅ አደገኛ ጠንቅ ዕጽ መስፋፋት ለምን? ሽርሙጥና መስፋፋት ለምን? ስራ አጥነት ፣ የወንጀል ድርጊት መስፋፋት እንዴት እና ለምን? የህዝብ መፈናቀል ለምን? የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ ስለምን ተደረገ? ወዘተ ::
ወደ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ከ17 አመታት በፊት ወያኔ ህወሃት እንደተፈጠረ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. የትግራይ ህዝብ የአደረበትን ስሜት ባጭሩ ልዳሥ::
ወያኔ ህወሃት በዚሁ ቀንና ወር ደደቢት በረሃ ሲወጣ የትግራይ ህዝብ የዚሁ እኩይ ድርጅት ማንነቱን አያውቅም ነበር:: ቀስ በቀስም በየቦታው ብቅ ጥልቅ ሲል የትግራይ ህዝብ አልተቀበለውም::በህዝቡ ወያኔ ህወዋት ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ምክንያት ጭንቀትን ንዴት የተነሳ በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ:: አስገድዶ ንብረቱን መውረስ እና አስገድዶ እርዳታ እንዲሰጥ ተደረገ:: ምክንያቱም የሚከላከልለት ረዳት የሌለው ህዝብ ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ጀብሃ ሶስቱ በየፊናቸው አስቸገሩት:: የትግራይ ህዝብ ከየቦታው እየተለቀመ ተገደለ::
ከዚህም ቀጠል በማድረግ ወያኔ ህወሃት በሃይማኖት ጣልቃ በመግባት ክርስቲያን ጸረ ክርስትና እስላሙ ጸረ እስልምና ሃይማኖታቸውን እንዲያወግዙ የተቻለውን ቢሰራም አልሆነለትም::
ጸረ ህወሃት እና ጸረ ሻዕቢያ እየተባሉ ያልሆነ ያላሰቡት ብዙ ፣  ብዙ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች ሃለዋ ወያኔ (06) እየገቡ እሱም/እርሳውም ተገድለው ቤት ያፈራው ሃብታቸው ተወርሰው ህጻናት አልባሌ ቦታ ወድቀው ቀርተዋል::
በየከተማው ወያኔ ህወሃት ሽብርተኞች () በማሰማራት በጠራራ ጸሃይ ብዙ ሰው ገድለዋል:: ህወሃት የትግራይን ህዝብ እንደግሉ መሳሪያ አድርጎ የሚናገረው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያ ትግሉ ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ለወደፊትም አልተቀበለውም:: አይቀበለውምም:: ህወሃት የሚቀልደው ያለ ጉልበቱ ተማምኖ ነው:: ለዚሁም ዋና ምስክር ምርጫ 97 ዓ.ም. ትግራይ ወያኔ አልመረጠውም:: ለወደፊቱም ወያኔን አይመርጥም:: ሁለቱ ሊታረቅ የማይችል ቂም አላቸውና::
ወያኔ ህወሃት የትግራይ ወጣት ሴት ፣ ወንድ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት በማያውቁት የኤርትራ በረሃዎች ሞተዋል:: እዛው አጥንታቸው ተበታትኖ መቅረቱ የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን ደም እያለቀሰ ያለበት ጊዜ ነው::
በአጠቃላይ በትግሉ ወቅት በትግራይ ህዝብ ወያኔ ህወሃት የፈጸመው ግፍ በከፍተኛ ወንጀል የሚይስጠይቀው ነው:: የትግራይ ህዝብ ወያኔ የተፈጠረባት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. በሚከበርበት ጊዜ በየቦታው የሚጠራበት ስም አለው:: በተምቤን አካባቢ “የተረገመች ቀን” ሲላት በአድዋና አክሱም አካባቢ “የጨለማ ቀን”" ሲለው በሽሬ አካባቢ ደግሞ “የእልቂት ዘመን” ይለዋል::
ወያኔ ህወሃት በለስ ቀንቶት አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ግንቦት 20,1983  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በደመኛ ጠላታቸው የወደቁበት እና በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ የመጣበት ቀን ነው::
ከዚሁ ቀን መነሻ በማድረግ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ የነበረው ቂም በቀል በማያቋርጥ ሁኔታ በ22 አመት የወያኔ ህወሃት አገዛዝ የወረደበት ግፍና ሰቆቃ ቀጥለን ባጭር ባጭሩ እንመልከት::
ግንቦት 21 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔ ኤርትራን አስገነጠለ:: ኢትዮጵያንም ካለ ባህር በር አስቀራት::
ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ዝነኛው ምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ ፖሊስ ወዘተ የጠላይ ጦር በማለት ይደርግ ስርዓት በራሱ ሂደት ተመናምኖ በወደቀበት ለብዙ አመታት የሃገሩ ዳር ድንበር ሲያስከብር ከጠላት ሲከላከል የነበረው ካለምንም ጡረታና መተዳደሪያ የ”ጠላት ጦር” በማለት ለልመና እና ለችግር ዳረገው:: የሚይስተዳድራቸው ቤተሰቡ በሚልዮኖች የሚቆጠር ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ተበታትነው ቀሩ:: ከትግራይ ይዟቸው የመጣ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሃገር መከላከያ ሰራዊት አደረገ:: ቀሪዎቹን ታጋዮች ደግሞ ፖሊስ ፣ ደህንነት በማለት ዘረኛ ሰራዊት በኢትዮጵያ አቋቋመ:: ይህም በምንም አይነት ኢትዮጵያን የማይወክሉ ሁሉም ከላይ እስከ ታች ለነዚህ ተሰጠ:: እነዚህም በፊናቸው በኢትዮጵያ ህዝብ አስከፊ ሰቆቃና ግድያ በህዝቡ እየፈጸሙ ይገኛሉ::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማራ:: ዘር ማጥፋቱን ገና ከ1969 ዓ.ም. የጀመረው ሲሆን በበለጠ ደግሞ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አማራው ከያለበት እየተፈለገ ዘሩን ማጥፋት ተጧጧፈ ቀጥሎም ኦሮሞ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፣ ቤኑሻንጉል ወዘተ :: በትግራይ ውስጥም አደገኛ ጠላት ናቸው የሚላቸውን በዘዴ አጠፋቸው::
ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአማራው ቋንቋ ስለሆነ ይህ ቋንቋ የትምህክተኛና የነፍጠኛው ቋንቋ በየትኛውም ክልል እንድይነገር በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ መገናኛው እና ሃሳብ ለሃሳብ የሚለዋወጥበት ለስንት ሺህ አመታት ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ህወሃት እያጠፋው ይገኛል:: በየትኛውም ክልል አማርኛ መናገር በህጉ ከለከለው::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ሲያበቃ ለዘመናት ኢትዮጵያዊው ህዝብ በፈለገው ቦታ ሲኖርና በጋብቻ በደም የተዋሃደው ህዝብ ከየክልላችሁ ከሌላ ቦታ የመጣውን ተስፋፊ ህዝብ አስወጡ በማለት እርስ በርሱ በማጋጨት ብዙ ሂወት ጠፍቶ ንብረቱም ተዘርፎ በየበረሃው ተበትኖ ግንቦት 20 ቀን 1983 ይዞት የመጣውን መከራ ገፈት ቀማሽ ሆነ:: በተለይ አማራው::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ አልበቃ ብሎት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በምትደዳርበት ገዳሪፍ በተባለው የሱዳን ግዛት አስተዳዳሪ በነበረው ሻለቃ ጉዌን የወሰን መስመር ለጣልያኖች ይጠቅማል በማለት በ1903 እ.ኤ.አ በህገወጥ መንገድ የነደፈው የመስመር ክልል በአጼ ምኒልክ ኋላም በአጼ ሃይለስላሴ እና በደርግ መንግስት ውድቅ የተደረገው እና ተቀባይነት ያጣውን ወያኔ ህወሃት ከየት እንዳገኘው ሳይታወቅ የኢትዮጵያን የወሰን ድምበር በመጻረር ለወዳጁ ሱዳን ከሰቲት ሁመራ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ወደውስጥ ከ40 እስከ 60 ኪ.ሜ. የሚዘልቅ እና 1,600ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ለሱዳን መንግስት የአንዲት ኢትዮጵያን ሰፊና ለም መሬት የሸጠ ወያኔ የሱዳን መንግስት ለውለታው ከገዳሪፍ እስከ መቀሌ የባቡር መንገድ እንደሚዘረጋ የሃገራችንን ሉአላዊነት በመድፈር ለግል ጥቅሙ ሃገራችን እያወደመ ያለ ስርዓት ነው:: የግንቦት 20 ቀን 1983 መዘዝ::
ወያኔ ህወሃት በተፈጥሮ ባህሪው አምባገነን እና ሽብርተኛ ድርጅት እሱን የሚቃወም እና የሚፈጽመው ግፍ እንዲነሳበት አይፈልግም:: ፍላጎቱ ተሳስተሃል አትበሉኝ:: ስለኔ አትናገሩ ከሚለው ፋሺስታዊ ባህሪው በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ እንዲኖር አይፈልግም:: የህዝቡ በነጻነት መናገር እና ሃሳቡን መግለጽ ለወያኔ እንደ እሳት የሚለበልበው ለመሆን የፕሬስ ነጻነት ያገደው:: ይህም እንደ ገዢ ፓርቲ ህወሃት የታገደ ነው:: በዚሁ ፖለቲካዊ ውሳኔ የነጻ ፕሬስ በማደን ፣ በማሰር ፣ በማንገላታት ሳያበቃ ብዙ የፕሬስ ጋዜጠኞች ሃገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመከራን ስደት ተዳረጉ:: ነጻ ፕሬስ በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ::
ወያኔ ህወሃት የሽግግር መንግስት ብሎ ከሰኔ ወር 1983 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 1985 ዓ.ም.  በስልጣን በቆየበት ምርጫ በማለት በጸረ ዲሞክራሲያዊ መንገድ በ1987 ዓ.ም. , በ1992 ዓ.ም. , በ1997 ዓ.ም. እና በ2002 ዓ.ም. በማካሄድ በተለይ በ1997ዓ.ም. ቅንጅት በተለያዩ ፓርቲዎች ቀስተ ደመና ፣ መኢአድ ፣ ኢዴሊ ፣ ኢዴአፓ-መድህን ወዘተ በተጠናከረ ማዕከላዊ ፓርቲ “ቅንጅት” ተብሎ እንደተመሰረተ እምነቱ መሰረታዊ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲና እድገት ፣ ብልጽግና ፣ ፍትህ ፣ ነጻነት ፣ ከዘረኝነት የጸዳ በምርጫው ለመወዳደር በቀረበበት ምርጫም ተካሂዶ መሉ በሙሉ አሽንፎ ሲወጣ በአንጻሩ ወያኔ -ህወሃት/ኢህአዴግ በዜሮ ተሸንፎ ከምርጫ የወጣው በጉልበቱ ምርጫውን በመንጠቅ ድምጻችን አይነጠቅም ብለው የወጣውን ሰላማዊ ዜጎች በአግአዚ ቅልብ የመለስ ዜናዊ ጦሮች ግደሉት ብሎ ትዕዛዝ በመስጠት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ሲገደሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በየወህኒ ቤት በማሰር ወያኔ ህዝብ ያጠፋበት ቀን የሌባው አይነ ደርቁ ወያኔ በ2002  ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ እንደልማዱ ኮረጆውን በመገልበጥ 99.6% አሸነፍኩ ብሎ ኢትዮጵያና ህዝብዋን ማውደሙን ቀጠለ:: ይህ ሁሉ ችግርን ግድያ ሰቆቃ የግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. ውጤት ነው::
ወያኔ ህወሃት በፕሮግራም እንዳስቀመጠው የኤርትራ ጥያቄ ያላንዳች ጥርጥር ሃቀኛና ታሪካዊ መሰረት ያለወ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ነው በማለት ወያኔ ያመነበት ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የማያምንበት የኤርትራ ህዝብም ያላመነበት በኢትዮጳዊነታቸእው የማያምኑ መሆናቸው አንዳች ጥርጣሬ የለውም:: ድርጊቱ የወያኔ ብቻ ነው:: ይህ በዚህ እንዳለ አሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኤርትራ ግዛት አልነበረችም ሁሉ ተከታታይ ዘመናት በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሆና ስትተዳደር እንደነበረች ሁሉ ኢትዮጵያ በትክክል የሚያውቀው ሃቅ ነው:: አሰብን በኤርትራ ካርታ ጨምሮ በ1967 ዓ.ም. ያወጣው ወያኔ ብቻ መሆኑን በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት ይህን የታሪክ እና የሃገር ክህደት የፈጸመው ሆን ተብሎ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ያደረጉት ኢትዮጵያና ህዝብዋ ጠላት ብለው ስለአስቀመጡት የፈጸሙት ጥቃት ነው:: ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ እንደተቆጣጠረ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጣች::
ይህን በተመለከተ ወያኔ/ህወሃት እና ሻዕቢያ እንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ ከግንቦት 5 ቀን እስከ ግንቦት 9 ቀን 1983 ዓ.ም. የቀድሞው የአሜሪካ  ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔው መሪ መልስ ዜናዊ ባሉበት ስብሰባ ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ህዝብ ስላለባት የባህር በር ያስፈልጋታል:: አሰብም ከኤርትራ ያልተካለለ በመሆኑ በአጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ስርዓትም ከኤርትራ ውጭ ሆኖ በወሎ አፋር የተካለለ ስለነበር ቀደም ሲልም አሰብ ከኤርትራ ውጪ ሆኖ በጣሊያንም ብዙ ያልተደፈረች የኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበረች ይታወቃል:: አሰብ የኢትዮጵያ የባርህ በር መሆን አለበት ብለው ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጣም ተናዶ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ የወደቀች ሃገር የነበሩ አመራር አጼ ኃይለስላሴ ሆኑ ደርግ ያስቀመጡት ካርታ ህወሃት አይቀበልም:: አሰብ የኤርትራ መሬት ነው:: እኛ አሁን በኢትዮጵያ ስልጣን የምንቆጣጠረው የወደብ ችግር አይኖረንም:: ችግር አይፈጠርብንም:: ብንፈልግ ጂቡቲን አሊያም የሶማሊያ እና የኬኒያን ወደቦች እንጠቀማለን:: አሰብ የኤርትራ ስለሆነ እምነታችንም ይህ በመሆኑ አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም::
ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር እና ሌሎች አደረዳሪዎች አቶ መለስ ዜናዊ አሰብን የኤርትራ ነው ፤ የወደብ ችግር የለብንም ብለው እኛንም ስለአሳመኑን አሰብ በኤርትራ ውስጥ መካተቱን ተቀብለናል በመለት ሲዘጉት ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪካዊና ጥንታዊው የባህር በርዎችዋን አሳጥቶ ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያን በጠላቶችዋ እጅ የወደቀችበት የኢትዮጵያ ህዝብም በድቅድቅ ጨለማ እና ጭቆና ፋሽስት ስርዓት ይዛ የመጣች ይህች ግንቦት የተረገመች ቀን ናት:: በምስራቅ-ምዕራብ-ሰሜን-ደቡብ የሚገኙ ኢትይጵያውያንም እየተረገመች ነው::
ወያኔ ህወሃት በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በለስ ቀንቶት ወሮ በተቆጣጠረበት ወቅት የኢትዮጵያን ሃብት-ንብረት ወያኔና ሻዕቢያ ተባብረው ዘረፉት:: የወላድ መሃን የሆነችው ኢትዮጵያ ተከላካይ የሌላት ሁለት ከደደቢትን ከሳህል በረሃ የመጡት ሙሉ ሰራዊታቸውን በማሰማራት ሃብትዋን ንብረትዋን ዘርፈውታል:: የተለያዩ ተቋማት ተዘርፈዋል:: ጠቅላላ ጥሬ ገንዘብዋ ተዘርፏል:: ጥሬ ህብቶቿ ተዘርፏል:: የቀራት ነገር የለም:: ለውጪ ገበያ ለሺያጭ የሚመረት ቡና ፣ ሰሊጥ ፣ አደንጓሬ ወዘተ አይን ባወጣው ዝርፊያ ቀን እና ሌሊት ተፈጽሞባታል:: ዝርፊያው በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የጀመረው እስከ አሁን ቀጥለውበታል:: ኤርትራ የቡናና የቅባት ምግብ አምራች በመሆን በአለም ገበያ አቅራቢ ሆና ከዓለም 3ኛውን ደረጃ ያዘች:: ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ጥሬ ሃብት ዋና ገንዘብ ወያኔ ህወሃት መሪዎች 1. መለስ ዜናዊ እና ባለቤቱ አዜብ መስፍን 2.ስብሃት ነጋ 3.አባይ ጸሃዬ 4.ስዩም መስፍን 5.አርከበ እቁባይ 6.አዲስ አለም ባሌማ 7. አባዲ ዘሙ 8.ጸጋይ በርሄ እና ባለቤቱ ቅዱሳን ነጋ 9.ተክለወይኒ አሰፍ 10.ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወዘተ ሆነው ኢፈርተን አቋቁመው ስልጣኑንም ተቆጣጥረው የናጠጡ ባለብዙ ፋብሪካዎች ትልልቅ ተቋማት መስርተው ቱጃር በለሃብቶች ሆነዋል:: ወያኔ ህወሃት ወደ ስልጣን ባልበቃበት ጊዜ በአጼ ኃይለስላሴና በደርግ ስርዓት ነጻ ተቋም በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያገለግሉ የነበሩትን ብሄራዊ ባንክን ፣ ንግድ ባንክን ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ፣ እርሻ ትራንስፖርት ፣ መአድናት ወዘተ ወያኔን ስልጣን እንደጨበጠ ሁሉን ከህዝብ በጉልበቱ ነጥቆ በመቆጣጠር የሃገርና የህዝብ ሃብት የህወሃት ተቋማት ሆኑ:: ይህም ወያኔ ህወሃት በከፍተኛ ወንጀል የሚጠየቅበት ከዋናዎቹ አንዱ ነው::
ወያኔ ከኢትዮጵያ የዘረፈው ገንዝብ እና ጥሬ ሃብት ኢፈርት በትግርኛ ት.እ.ም.ት የሚል ስያሜ በመስጠት በትግራይ ህዝብ ስም ሲያጭበረብር የትግራይ ህዝብ መነገጃ ማድረጉም ህወሃት በዚሁ ሌብነቱ በወንጀል የሚያስጠይቀው ነው:: በትግራይ ህዝብ ስም የወያኔ መሪዎች ነገዱበት እንጂ የትግራይ ህዝብ ከት.እ.ም.ት ተጠቃሚ አይደለም:: ህዝቡም ራሱ የሚናገረው ሃቅ ይህ ነው::
ወያኔ ህወሃት ድርጅት ነው ስንልም ህወሃት የተመሰረተውና እስከ አሁንም ያለው ህወሃት ግለሰቦች ተደራጅተው የፈጠሩት የማፍያ ስብስብ እንጂ በምንም ተአምር የትግራይ ህዝብን የማይወክል ነው:: በድርጅቱ የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ያቀፈ:: ህዝብ ሌላ፤ ህወሃት ሌላ:: ህወሃትን የመሰረቱት ሰዎችም ጸረ ህዝብ እና ጸረኢትዮጵያ ናቸው:: ይህ ህወሃት ተብሎ የሚጠራ በሻዕቢያ የተመሰረተ ኤርትራን ነጻ ለማውጣትና ትግራይም የአማራው ቅኝ ግዛት በማለት የተነሳ ከጥዋቱ ኢትዮጵያዊነቱን የካደ የከሃዲዎች ስብስብ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች የገደለ ጸረ ህዝብ ነው:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ህወሃትን በእውቅና አልተቀበለውም::
ወያኔ ህወሃት ገና በ1968 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መሬት እጠቀማለሁ በማለቱ ከባድሜ እስከ አፋር ቡሬ የመሬት ቆዳ ስፋት 1.ታች አዲያቦ 2. ላይ አዲያቦ 3.ጭላ ወይም አንከረ ባሩካ 4. አሕሰኣ 5.እገላ 6.ዛላምበሳ  በዚሁ ውስጥ የሚጠቃለሉ ኢሮብ ፣ ጻልገዳ ፣ ዓውዳ ፣ አይጋ ፣ ሶቦያ ፣ ወዘተ 7.የአፋር መሬት  እስከ ቡሬ 8. አሰብ የኤርትራ መሆንዋን በዚሁ ፊርማቸው በ1969 ዓ.ም. አረጋግጠዋል:: 1. መለስ ዜናዊ 2.አባይ ጸሃዬ 3.ስብሃት ነጋ በዋናነት የሚጠቀሱ በትክክል የኤርትራን መሬት ነው በማለት ፈርመው የሰጡት ህዳር ወር 1969 ዓ.ም. ነው:: በዚሁ መሰረት የትግራይ ህዝብ 1.በሻዕቢያ 2.በጀብሃ 3.በህወሃት  በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ትተዳደራለህ ብለው በመወሰን ህዝቡም በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ቁም ስቃዩን በማየት ተገደለ:: ንብረት ሃብቱ ተዘረፈ:: አቤት የሚባልበት በማጣት በየስደቱ ተበታተነ:: ወያኔ ይህን ወንጀል እንደፈጸመ በአንጻሩ ከሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ለም ወሬት ነጥቆ ወሰደ::
የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዋና ጦሱ ከላይ እንደተጠቀሰው ነው:: የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መንስኤ   ው በግልጽ የሚታወቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት አመራር የሚያላክኩት በኢኮኖሚ ችግር የተፈጠረነው ሲሉ በተደጋጋሚ በተለይ የወያኔው መሪ ነበር መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳመን ለከት በሌለው ውሸቱ ሲለፋደድ ሃገር ሙሉ ያውቃል:: ቀሪዎቹ የሱ የአመራር አባላቱ ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃየ ፣ ስዩም መስፍን ፣ አርከበ እቁባይ ወዘተ የመለስ ዜናዊን ሃሳብ በማስተጋባት በየውጪ ሃገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳመን ብዙ ውጣ ውረድ ቢያደርጉም እስከ ዛሬ ተቀባይነት አላገኙም::
የጦርነቱ መንስዔ በኢኮኖሚ ሳይሆን በትክክለኛው አነጋገር በተጨባጭ ሁኔታው የመሬት ይገባኛል ነው:: ሻዕቢያ የኔ ግዛት ነው:: ከዚህ ቀደምም በ1969 ዓ.ም. ተስማምተን እናንተም የኤርትራ መሬት ነው በማለት ያመናችሁበትን አስረክቡን በማለት ወደ ጦርነቱ ሻዕቢያ እና ወያኔ ገቡ:: እውነቱ ይህ ነው:: ይህ በዚሁ እንዳለም የኢኮኖሚው ጉዳይም አስተዋስኦ ያደረገበት አለ:: ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ከ1983 ዓ.ም. ግንቦት ወር ጀምሮ እስከ 1990ዓ.ም.  የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ የግላችን የኢትዮጵያ ሃብት ደግሞ የጋራችን ተባብለው በህወሃት መሪዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሁለቱ ማለት ሻዕቢያና ወያኔ የሃገራችን ኢትዮጵያን ጥሬ ሃብትዋን መዓድኗን እና ሃገሪቱ ያፈራችውን የተለያዩ ፋብሪካዎቸ እና ባንኮችን አብረው ተባብረው ዘርፈዋል:: ኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ኤርትራውያን ጤፍ በየአይነቱ ዳጉሳ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ ወዘተ በርካሽ ዋጋ ኤርትራ ሲሸጥ የኢትዮጵያ ገበያ ባዶ ቀረ:: ስለዚህ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ያ የለመዱት በሰው ሃገር ሃብት ሲንደላቀቁ የቆዩት አሁን ሲያጡት ለጦርነቱ አስተዋጽኦ ያደረገም ነበር:: በጣም ከሚገርሙ ነገሮች እና አሳዛኝ የሆነው ሁለቱ መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በስልክ ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ብዙ ሰዎች ተናግረዋል:: ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃዬ እና ሌሎቹ የወያኔ መሪዎች በጣም የደመቀ ግንኙነት ከጦርነቱ ዋዜማ አንስቶ የወያኔ መሪዎች ይገናኙ እንደነበር ምስጢሩም የሚያውቁ ሰዎች ተናግረውታል::
ኢሳያስ አፈወርቂ ላቀረበው የአንድ ቢሊዮን ብር ላክልን መለስ ዜናዊ ሳያቅማማ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተፈቅዶ ገንዘቡ አስመራ እንደገባ በቀናት የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መቀሌ ውስጥ(ሃይደር) የሚገኘው የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤት በሚግ አውሮፕላን ደበደበው:: ከተዋጊ አውሮፕላኖቹ የተጣለው ክላስተር ቦምብ ወድያውኑ 53 ህጻናትና አስተማሪዎች ሲሞቱ 185 ደግሞ ከባዱ ቁስል ደረሰባቸው:: ለዚሁም ተጠያቂው መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ ናቸው::
የሻዕቢያ ተዋጊ ጀቶች እንደገና ተመልሰው ቦምብ ጭነው 48 ሰላማዊ ሰዎችን 10 ህጻናትን ሲገድሉ 150 ሰዎች አቆሰሉ:: በማለት ቢ.ቢ.ሲ. እና ሲ.ኤን.ኤን. የዘገቡት ዋቢ ነው:: ይህ ጥቃት የደረሰው በግንቦት ወር መጨረሻ 1990 ዓ.ም. ሆኖ አስራት አብርሃም በአሳማኝ ሁኔታ ከ’ሃገር በስተጀርባ’ በሚል መጽሃፉ እንደገለጸው መለስ ዜናዊን ኢሳያስ አፈወርቂ እስከ ታህሳስ ወር 1991 ዓ.ም. ይገናኙ እንደነበሩም ያስረዳል:: መለስ ዜናዊን ግብረአበሮቹ እነ ስብሃት ነጋ ወዘተ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ የባዕዳን ቅኝ ገዢዎች መሆናቸው በግልጽ የሚያሳይ እውነታ ነው::
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ሆን ብሎ ያሰናከለው መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ መሆናቸው ሲታወቅ ምክንያቱም በ1969 ዓ.ም. ከላይ የተጠቀሰ መሬት የኤርትራ ነው ብሎ ወያኔ የፈረመበት በመሆኑ ይህም በአልጀርሱ ስምምነት ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ አሳልፎ ለኤርትራ መስጠቱ የ1969 ዓ.ም. ትልቁ ማሳያ ነው:: የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት እነማን መሩት? ይህን እንመልከት::
1. መለስ ዜናዊ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ……………………………ኤርትራዊ
2. ጻድቃን ገብረተንሳኤ የጦሩ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ……………………………….ኤርትራዊ
3. ሳሞራ የኑስ…ከፍተኛ ጀነራል…………………………………………………….ኤርትራዊ(በናቱ ከርከበት በአባቱ ሱዳናዊ)
እነዚህ ሶስቱ አመራር በምንም ተአምር ለኢትዮጵያ ይሰራሉ?? ጦርነቱን በትክክል ይመራሉ ብሎ ማሰብ “ላም አለችኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” አይነት ነው:: እነዚህ ትልቁ ምኞታቸው የኤርትራ ሰራዊትና ህዝብ እንዳይጎዳ ኢትዮጵያዊው ሰራዊት ቢያልቅ ምንም የማይሰማቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም የውጊያና ጦርነት አመራር ብቃት የሌላቸው በአጋጣሚ የተገኘው ጠ/ሚኒስቴርነት እና ጀነራልነት ከንቱ ነው:: ጠቅላላ የወያኔ ህወሃት መሪዎች ጀነራሎች እና ወታደሮች ከወታደራዊ ሳይንስ ያላቸው ርቀት ሰማይና መሬት ነው:: በ1991 ዓ.ም. ያለቀው ሰራዊት ተጠያቂም ናቸው::
2ኛው በዚሁ ኢትዮ ኤርትራ ውጊያ ሲመሩ የነበሩ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ታዛዦች ናቸው:: አታድርጉ ከተባሉ አያደርጉም:: በዋናነት ጎልተው የሚጠቀሱም::
1. ሰዓረ መኮንን
2.ዮሃንስ ገ/መስቀል (ቦጅቦጅ)
3.ታደሰ ወረደ
4.አብርሃ ወ/ማሪያም(ኳርተር)
5.ብርሃነ ነጋሽ ወዘተ ሲሆኑ ሌሎችም አሉ::
ስለሆነም በ1991ዓ.ም የደረሰው ውድመት ከ100,000ሺ ሰራዊት የሞተበት ወደ 200,000 የሚጠጋ ሰራዊት አካለ ጎዶሎ የሆነበት ግምቱ አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት የወደመበት ተጠያቂው ማነው??
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተፈጠረበት ምክንያት እና ሰበቡ ምንድነው?? እነዚህ ሁልቱ ጥያቄዎች መልስ በግልጽ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁኝ::
1) በኢትዮ-ኤርትራ ለደረሰው ግድያና በጦርነት የወደመው ሃብትና ንብረት ተጠያቂዎች::
1. መለስ ዜናዊ
2. ስብሃት ነጋ
3.አባይ ጸሃዬ
4. አርከበ እቁባይ
5. ጻድቃን ገ/ተንሳኤ
6. ሳሞራ የኑስ
7. ስዩም መስፍን
እነዚህ በሰው ህይወት ለደረሰው እልቂትና ጉዳት በሃገሪቱ የደረሰው ከፍተኛ ውድመት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው::
2) በጦርነቱ የወደመው ሃብት እና ንብረት ተጠያቂውስ ማነው? ለሚለው::
1. መለስ ዜናዊ
2.ስብሃት ነጋ
3.ጻድቃን ገ/ተንሳኤ
4.አበበ ተክለሃይማኖት
5.ገዛኢ አበራ
6.ጀነራሉ በባለ ሌላ ማእረግ
7.ስዩም መስፍን
8.ብአዴን, ኦህዴድ እና የደቡብ ህዝብ ንቅናቄ
9. በወቅቱ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሙሉ
10. የህወሃት ካድሬና ደጋፊዎች በሙሉ::
እነዚህም ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ሲሆኑ፤
3. የጦርነቱ መንስኤ ለሚለው ጥያቄ የህወሃት አመራር በ1969 ዓ.ም. ሻዕቢያ ላቀረበው የመሬት ይገባኛል በወቅቱ አምነት ተቀብለው በፊርማቸው ባረጋገጡት መሰረት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የሌለው የህወሃት ጥቂት የማፍያ ስብስብ በፈጸሙት ነገር ከሃዲዎች ከሻዕቢያ ጥቅም እናገኛለን ብለው የፈጸሙት ሚያዝያ ወር 1991 ዓ.ም. የፈነዳ ጦርነት ነው:: ተጠያቂዎቹም ህወሃቶች ናቸው::
በብዙ በርካታ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ሊከሳቸው ዝግጅቱን አጠናቅቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነው:: ህወሃት እና መሪዎቹ ይከሰሳሉ:: አዎን ለፍርድም ይቀርባሉ::
የአይደ መዋእለ ህጻናት የአየር ጥቃትም የትግራይ ህዝብ ካቀረባቸው ክሾች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በዚሁም በዋናነት የሚጠቀሱ መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ መሆናቸው ነው::
ግንቦት 20 ቀን1983 ዓ.ም. ይህን አይነት አሰቃቂ ድርጊቶችን አስከትላ ነው ብቅ ያለችው:: የተረገመችው ይህቺ ቀን ኢትዮጵያ ለምለም አገራችንን ለከሃዲ ባንዳዎች አሳልፋ የሰጠች::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ይዛው የመጣችው ሰቆቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገው የሃገሩ ግዛት የመኖር ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን መብቱን በህወሃት ከፋፍለህ ግዛ በሚመቸው ሃገራችን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ጠባብ ብሄረተኛ በሆነው መንገድ የዘር ፌደራሊዝም መሰረት ይህ የእቅድ ሃሳቡም አማራውን ለማጥፋት እና ለማክሰም የተቀነባበረ ሴራ ነው:: ይባስ ብሎም ሸዋ ጠ/ግዛት ለሌሎች ብሄራት በመስጠት ጎጃም በጌምድር ጠ/ግዛት ወሎ ጠ/ግዛት በታትነው አማራው መኖሪያ አልባ ተደረገ:: በተለያዩ ጠ/ግዛት ይኖር የነበረው አማራ ውጣ እየተባለ በወያኔ ህወሃት ከህጻን እስክ ሽማግሌ እየተገደለ በየበረሃው ወድቆ የዘሩን ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል:: ቀስ በቀስም ኦሮሞ ጋምቤላ አፋር ወዘተ ተመሳሳይ እጣ ደረሰባቸው:: በጠቅላላው ከተወለደበት ካደገበት ኢትዮጵያዊ ከመሬቱ የተፈናቀለ 24 ሚሊዮን ሲሆን በወያኔ ህወሃት የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ጥናቶች የሚያመለክቱተ 7.9ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ወያኔ ህወሃት እንደገደላቸው ያሳያሉ::
ግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሁለቱ ሃይማኖቶች እስልምናእና ክርስትና በእጁ አስገብቶ ለመቆጣጠር እና ቀስ በቀስም ሃይማኖቶቹን ለማክሰም ተነሳ::
1. የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ለብዙ ዘመናት ወግና ህግጋቱን ጠብቆ የመጣ በብዙ ሚሊዮን እስልምና ተከታይ ያለው የኢትዮጵያ ቅርስና የምንኮራበት ሃይማኖት ዛሬ በወያኔ ህወሃት ተደፍሮ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሙሉ መብታቸውን ተነጥቀው በእስራት መከራ እየተሰቃዩ በገዛ ሃገራቸው ለክፉ ችግር ተዳርገዋል::
2.የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በክፉ አደጋ ወድቃለች ቤተ ክርስቲያና እየተቃጠሉ ታሪካዊ ቅርሶችዋን በወያኔ ተዘረፉ::ወያኔ የሚቃወሙ ብጹአን አባቶች ለስደት ተዳርገዋል:: ብዙም ተገድለዋል:: ይህን ሁሉ የፈጸመው የወያኔ አባል የነበረው አባ ገብረመድህን ወይም አባ ጳውሎስ የሚባል በወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ካደረገው ብዙ ወንጀል በቤተ ክርስቲያናችን ፈጽመዋል::
ለመሆኑ አቡነ ጳውሎስ ማነው??
አቡነ ጳውሎስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ ያደጉትም እንዳባገሪማ ገጠር ነው:: እንዳባገሪማ የተባለበት ምክንያት በአክሱም ዘመነ መንግስት በንጉስ አልአሜዳ ብ470ዓ.ም. ከመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ አባ ገሪማ ሲሆኑ ከአድዋ በስተምስራቅ የ18 ኪሎ ሜትር ርቀት የምተገኘው ተራራማ ቦታ አባ ገሪማ በጣም አስደናቂ ሆኖ የተሰራው ቤተ ክርስቲያናቸው በማነጽ እዛው ሞተው እዛው ስለተቀበሩ በዚሁ ምክንያት እንዳባገሪማ ተብላ ትጠራለች::የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያዋረዱን የቤተ ክርስቲያኗን ህገ ደንብ እና ቀኖናውን የለወጡ እና ያፈረሱ ፣ ለስጋቸው ያደሩ: አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሃይማኖት ለማጥፋት ጸረ ክርስትና የሆኑት ጳውሎስ የአድዋ ልጅ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ህጋዊ ሊቀ ቅዱሳን ፓትሪያርክ በቤተ ክርስቲያኑ ህግና ደንብ የተሾሙት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ወያኔ በሃይል አስወግዶ አባ ጳውሎስን ሾመ:: ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ወግና ስርዓቱን ለማጥፋት የታቀደ ነው:: የቤተ ክርስቲያኑን ህግና ደንብ የሚጻረርም ነው::
አቡነ ጳውሎስ የወያኔ ህወሃት በአባልነት የመለለመሉት በ1976 ዓ.ም. ነበር:: በወቅቱ የሚነገረው ዶ/ር አባ ገብረመድህን የተባሉ የኛ አባል ስለሆኑ ትግራይ ሃገራችን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነጻ በምትወጣበት እኚሁ የትግራይ ፓትሪያርክ ይሆናሉ በማለት ስብሃት ነጋ በለመደው ወሬ ማዛመት በታጋይ ውስጥ ተሰራጨ:: ቢሆንም ግን ታጋዩ ብዙ ስሜት አልሰጠውም:: ምክንያቱም ሃይማኖት የለሽ የወያኔ አመራር በትግሉ ወቅት እግዚያብሄር የሚባል አማልክት የሚባሉ በፍጹም የሉም:: ይህ ለአማራው አገዛዝ እንዲመችለት የፈጠረው ከንቱ ሃሳብ ነው:: በማለት ስለአስተማሩን የአባ ገብረመድህንም ይህን ድባብ የሸፈነው ነበር::
ንገሩ እንደገና በ1980 ዓ.ም. መጀመሪያ ታድሶ መጣ የህወሃት አባል አባ ገ/መድህን ከአሜሪካ ሱዳን ድርስ መጥተው ስብሃት ነጋ የወቅቱ የህወሃት ሊቀ መንበርና መለስ ዜናዊ ሱዳን ድረስ በመሄድ እንደተገናኙ በድጋፍ መልክም $15,000 የአሜሪካን ዶላር መስጠታቸውን የሄዱት ሁልቱ የወያኔ አመራሮች በድብቅ ሳይሆን በግልጽ የተናገሩት ነበር:: ከዚሁም በተጨማሪ ሱዳን ካርቱም ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው በውስጡ የሚገኙ ቀሳውስት ካህናት ወደ ህወሃት አባልነት መልምለው በሶስተኛው ቀን ወደ መጡበት መመለሳቸም ተነገረ::ስብሃት ነጋ አቡነ ጳውሎስ የህወሃት መሪህ ባህታ(vanguard) ናቸው በማለት ይጠራቸዋል::
እንግዲህ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ይህ ሆኖ ትግሬ በመሆናቸው ብቻም በደርግ መታሰራቸውን ብዙ ግፍ ተፈጸመብኝ የሚሉት አቡነ ጳውሎስ የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባላት እውነት ይሁን አይሁን ለነሱ ልተው:: ከሆነም አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ በቂም በቀል ማወካቸው ከአንድ መናኝ አባት መፈጸም የሌለበት ፈጽመዋል:: ነብሳቸውም ለሲዖል ተዳርጋለች::
አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርኩ ስልጣን አግባብ በሌለው መንገድ የተረከቡት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናት በምርጥ ካድሬነታቸው በዋልድባና በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ግፍ ከመፈጸማቸው በላይ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከየቤተ ክርስቲያኑ በማስወጣት ሸጠዋል::
ይህ ሁሉ በእስልምና ሃይማኖትና በክርስትና መዘዙ ይዞት የመጣው ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የተረገመች ቀን ናት::
ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያውያን እንደተቆጣጠረ ብዙ የዝርፊያ ተቋማት አመቻችቶ ነበር:: አገራችንን የተቆጣጠረው 1. ዋና ኢፈርት 2. ለም የኢትዮጵያ መሬት ለባዕዳን መሸጥ 3. ኢትዮጵያውያን ከተወለዱበትና ካደጉበት መሬት ማፈናቀል 4. ገዢ የሆኑት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተቋማት በህወሃት ቁጥጥር ውስጥ መዋል 5. ኢትዮጵያዊው የሃገሩ ዳር ድንበር ጠባቂ አማራው ማጥፋት ከዚህም ጎን ለጎን አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ማጥፋት እና ማክሰም:: 6.የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀ.አየር ኃይል ለ. ምድር ጦር ሐ.ባህር ሃይል መ.ፖሊስ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ የራሱን የህወሃትን ታጋዮች ከትግራይ የመጡ ሁሉ የኢትዮፕያ ምድር ጦርና አየር ኃይል ለማድረግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በራኡ መዳፍ ውስጥ ለማስገባትና ለመቆጣጠር ደህንነቱም ከላይ እስከ ታች በትግሬዎች ማዋቅር አላማው ነበር::
ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ የወያኔ አመራር መለስና ስብሃት ነጋ ባወጡት እቅድ ተግባራዊ ተደርገዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ በእርሻ የሚተዳደረው መሬቱን ተቀምቶ ለባዕዳን ሳውዲ አረቢያ ፣ ህንድ ፣ እና ለቻይና ወዘተ ህወሃቶች ሸጡት:: በሽያጭ የተገኘው ገንዘብም ሆነ በነ መለስ ዜንዊና ባለቤቱ ወ/ሮ አዜብ እጅ ሲገባ ከመሬቱ የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በየበረሃው ወድቆ ለክፉ ችግርና መከራ ተዳርገዋል::
ወያኔ ህወሃት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማርቶ ህዝበ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ነው:: አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ጠላት ነው ብለው ወያኔዎቹ ፈረጁት:: ለመሆኑ የቋንቋ ጠላት አለን?? ይህ ሁሉ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የመጣ የኢትዮጵያ ህልውና አጠያያቂም ሆነ:: ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያፈረሰ ህዝብዋንም ለችግር እና ለመከራ የዳረገ በጥቁር ታሪክ የሚመዘገብ የፋሺስት ወያኔ ህወሃት አገዛዝ ስርዓትና የጨለማ ዘመን በማለት ታሪ ዘግቦታል::
ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አንቺ ጥቁር የታሪክ አተላ ቀን የስንቱን ኢትዮጵያዊያን ህይወት በላሽ?! ስንቱን ኢትዮጵያዊ ምሁራን የነጻ ፕሬስ እውቅ ጋዜጠኞች ለስደት ለመከራ ዳረግሽ?! ስንቱን ወጣት ሴት እና ወንድ ከሃገሩ ጠፍቶ የባህር ቀለብ ሆነ:: ስንቱስ በስደት ሂወቱ እየማቀቀ ለክፉ መከራ ተዳረገ:: ስንቱ ቤተ ሰብ አፈናቅለሽ የስንቱን ቤት አፈረሽው:: ወጣት የሴት ህጻናት ሽርሙጥና ዳረግሽ:: አደንዛዥ እጽ እና አሺሽ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ተራ የንግድ ገቢ ሆኖ ወጣቱ ትምህርት ተከልክሎ እቅቀት እና ስልጣኔ በኢትዮጵያ የጠፋበት ዛሬ በኢትዮጵያ ስራ አጥነት የተስፋፋበት የወንጀል ድርጊት በስፋት የሚፈጸምበት ህጻናት በየቆሻሻው የተጣሉ ምግብ አይነት ነክ እየለቀሙ የሚበሉበት የጎዳና ተዳዳሪ ጠዋሪ ማደሪትይ ያጡ ህጻናት ለአቀመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ወንድ ሴት ማደሪያቸው በየመንገዱ ሆነ:: ህጻናት በርሃብ በየመንገዱ በየትምህርት ቤቱ አእምሮዋቸውን እየሳቱ የሚወድቁበ እርጉዝ ሴት መኖሪያ አልባ ሆና በየዱር ገደሉ እየወለደች ከተወለዱ ህጻናት ከ10 ህጻናት 6 በ3 እና በ 4 ወራቸው እየሞቱ ህክምና ጠፋ:: ውሃ ጠፋ:: መብራት ጠፋ:: አረ ስንት ጉድ ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የወረደው ግፍ::
የወያኔ ህወሃት አባል ድርጅቶች ህወሃት ራሱ የነዚህ ቤተሰብ ልጆች ውጭ አገር እየተንደላቀቁ ሲማሩ ሃገር ውስጥ ያሉ አመራሩ ደጋፊዎች በኑሮ ተንደላቀው በሙስና ተዘፍቀው የሃገር እና የህዝብ ሃብት እየዘረፉ ቀኑ ለነሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የችግር ጨለማ መብቱ የተረገጠ ባሪያ ጥዋት ማታ በወያኔ ስርዓት የሚሰቃይ ግዞተኛ ባዕድ ሆኖ ያለበት ዘመን ነው::
ይህ ክፉ አረመኔያዊ የህወሃት አገዛዝ በዚሁ መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይቀጥል ሁሉ ኢትዮጵያዊ በአንድነት ይነሳ በህዝባዊ ትግል ወያኔን ከስረ መሰረቱ ነቅለን እንጣለው::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ገብረመድህን አርአያ
አውስትራሊያ
አቶ ገብረመድህን አርአያ የቀድሞ ህወሀት ፋየናንስ ክፍል ሀላፊ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ህወሀትን ከለቀቁ በሗላ የድርጅቱት ጸረ-ኢትዮጵያዊነትና ወንጀሎቹን በማጋለጥ ይታወቃሉ። አቶ ገብረመድህን ባሁኑ ሰዓት በአውስትራሊያ በስደት ይኖራሉ።
     Posted By.Dawit Demelash