ከተደበደቡት ዘጠኝ ሰዎች መካከል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ተጎጅዎች ወደ አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ መጥተው በግል ክሊኒኮች እየታከሙ መሆናቸውን አስታማሚዎች የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ቻግኒ ከተማ እየታከሙት የሚገኙት ግለሰቦች አቶ በለጠ መንግስቴ፣ አቶ ጥላሁን ገበየሁ፣ አቶ አቸነፍ ወንዴ የተባሉ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡ በወረዳው ከ5200 በላይ ግለሰቦች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን እስከአሁን ሁሉም ሙሉ በሙሉ ወደ ነበሩበት አልተመለሱም፡፡ የሄዱትም በስበብ አስባቡ ችግር ላይ እንደሆኑ ለመረዳት ተችላል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች “ይህ ጊዜን እያሳለሰ የሚደረግ በአንድ ብሄር ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት መንግስት በአስቸኳይ ማስቆም ካልቻለ አገሪቱንም ለከፋ ችግር ሊጋልጣት ይችላል፡፡” በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ከተደበደቡት ዘጠኝ ሰዎች መካከል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ተጎጅዎች ወደ አማራ ክልል ቻግኒ ከተማ መጥተው በግል ክሊኒኮች እየታከሙ መሆናቸውን አስታማሚዎች የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸው ቻግኒ ከተማ እየታከሙት የሚገኙት ግለሰቦች አቶ በለጠ መንግስቴ፣ አቶ ጥላሁን ገበየሁ፣ አቶ አቸነፍ ወንዴ የተባሉ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡ በወረዳው ከ5200 በላይ ግለሰቦች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን እስከአሁን ሁሉም ሙሉ በሙሉ ወደ ነበሩበት አልተመለሱም፡፡ የሄዱትም በስበብ አስባቡ ችግር ላይ እንደሆኑ ለመረዳት ተችላል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች “ይህ ጊዜን እያሳለሰ የሚደረግ በአንድ ብሄር ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት መንግስት በአስቸኳይ ማስቆም ካልቻለ አገሪቱንም ለከፋ ችግር ሊጋልጣት ይችላል፡፡” በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል፡
No comments:
Post a Comment