Friday, July 19, 2013

ከደሴ/ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ወላይታ፣ አምቦ፣ ጂንካ መቀሌ እያለ እንቅስቃሴዉ ይቀጥላል!!


july.18.2013
የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ዛሬ ሐምሌ 11 ቀን ,2005 ዓ.ም ከረፋዱ
4 ሰዓት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ የህዝባው ንቅናቄ ዕቅዱን አፅድቋል፡፡
በዚሁም መሰረት በሚቀጥሉት የሀገራችን ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን
ጠርቷል፡፡ በየክልሉ ያሉ የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሮች ለፓርቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግብረኃይሉ
ያቀዳቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ከአዲስ አበባ አስቀድሞ በክልል ከተሞች ለማድረግ የተወሰነ ሲሆን
የህዝባዊ ንቅናቄው ማጠቃለያ የሚሆነው መስከረም አምስት ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይሆናል፡፡ ግብረ ኃይሉ መስከረም 5, 2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀደው ሰላማዊ ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የታሰሩበትን ሁለተኛ አመት ለመዘከር እንደሆነ ታውቋል፡፡
• ሐምሌ 21 በአዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች ህዝባዊ ስብሰባዎች ይደረጋሉ።
• ሐምሌ 28 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች፣ በወላይታ ሶዶና በመቀሌ ስብሰባዎች ሲደረጉ በባሀር ዳር ፣ በጂንካና በአርባ ምንጭ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ።
• ነሐሴ 5 ቀን በአዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች ሕዝባዊ ሰብሰባዎች ይደረጋሉ።
• ነሐሴ 12 ቀን (የሆያ ሆዬ ቀን) በአዳማ፣ በባሌ፣ በወሊሶ፣ በፍቼ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ።
• ነሐሴ 26 ቀን በድረደዋ፣ አዋሳ፣ አምቦና ደብረ ማርቆስ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ሲደረጉ፣ በጋምቤላና በአሶሳ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ።
• አዲስ የ2006 ዓ.ም እንደገባ መስክረም 5 ቀን በአዲስ አበባ ታልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል።
በአገሪቷ ካሉ ክልሎች በትግራይ መቀሌ፣ በኦሮሚያ ክልል በአምቦ፣ ፍቼ፣ አዳማና ፣ባሌ ፣ በአማራዉ ክልል ደሴን እና ጎንደርና ሳንጨምር በባህር ዳርና በደብረ ማርቆስ፣ በደቡብ ክልል በጂንካ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዓርባ ምንጭና አዋሳ፣ በበኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሳሶ እንዲሁም በጋምቤላ ክልል ለሰላም ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለነጻነት የሚደረጉ ሰላማዊና ኢትዮጵያዊ እንቅስቃሴዎች ይደረጋሉ።

No comments:

Post a Comment