ፒያሳ እየነደደች ነው፣ ታሪካዊው የጣይቱ ሆቴል እየተቃጠለ ነው
በአዲስ አበባ ፒያሳ በመባል በሚታወቀው ታሪካዊ ሰፈር ተገሽሮ ከመቶ አመት በላይ ያስቆጠረው የጣይቱ ሆቴል በ1898 ዓ.ም የተሰራ ሲሆን ኢትዮጵያውያን በታሪክ ቅርስነት ይኮሩበታል።
(ECADF News) ፒያሳ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ባካባቢው የደረሱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቅድምያ ገንዘብ በመጠየቃቸውና በሚከፈላቸው ገንዘብ መጠን ዙሪያ በፍጥነት ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው እሳቱ ጌዜ አግኝቶ ሊስፋፋ ችሏል።
አንድ የአዲስ
አበባ ነዋሪ እንዲህ በማለት ምሬታቸውን ገልጸዋል፣
“ፒያሳ ጣይቱ አከባቢ እያተቃጠለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው:: የእሳት አደጋ መኪና በቦታው ቢቆምም ውሃ የሚረጩት ከህዝቡ ጋር ሳንቲም እየተደራደሩ ባለበት ሁኔታ ንብረት እየተንቦለቦለ ነው:: ካጠፉት ብኋላ ገንዘብ ቢጠይቁ ምን ችግር አለው?”
ሌላኛው ወጣት
ደግሞ እንዲህ ብሏል፣
“ልብ የሚሰብር ዜና – ጣይቱ ሆቴል እየተቃጠለ ነው። በአካባቢው ያለነው ወጣቶች ቀርበን እንዳናጠፋ ፓሊስ እያገደ ነው።”
አሁንም ሌላኛው
ታዛቢ ሁኔታውን ሲገልጹ፣
“…እሳቱ ከተቀጣጠለ 5 ደቂቃ ብሗላ ወደ እሳት ኣደጋ ማጥፍያ ብርጌድ የተደወለ ቢሆንም በቦታው የተግኙት ግን ከኣንድ ሰዓት ንሗላ መሆኑ ታውቋል።” ብለዋል።
ሌላኛዋ የአዲስ
አበባ ነዋሪ ሁኔታው እጅግ አስቆጥቷቸዋል እንዲህ ይላሉ፣
“ምንም አይነት ማስተባቢያ አያስፈልግም ከታሪክ ጋር ፀብ ያለው ወያኔ ታሪካዊውን ጣይቱ ሆቴልን አንድዶታል! በቅርቡ እዚሁ ሆቴል አቅራቢያ ለልማት ይነሱ የተባሉ ቤቶት በእሳት አጋይቶ ሲያነሳቸው አይተናል አሁንም የ 5 ደቂቃ ርቀት እንኩዋን የሌለው እሳት አደጋ እሳቱ እንደተነሳ ሲደወልለት እሳቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ይህን ታሪካዊ ሆቴል ካወደመው በዋላ በቦታው ተገኝተዋል ታዲያ ይሄ የማን ስራ ነው? ነው ወይስ ወያኔ ለታሪክ እሚራራ ቡቡ ልብ አለው እያላችሁን ነው?
ከታሪክ እና ከህዝብ ጋር የተጣላ ገዢ ለእያንዳንዷ ጥፋት ተጠያቂ ነው ጣቶች ሁሉ ወደሱ ይቀሰራሉ!!”
የአዲስ አበባ
እና የሌሎችም ትልልቅ ከተሞች ነዋሪዎች በታሪካዊ የገበያ ስፍራዎችና በሌሎችም ታሪካዊ ቅርስነት ባላቸው ቤቶች እና ንብረት ላይ ለሚደርሱት የእሳት ቃጠሎዎች የመንግስት እጅ ሊኖርበት እንደሚችል ጥርጣሪያቸውን በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።
ታሪካዊ አመጣጥ
በአዲስ አበባ ( ኢትዮጵያ ) የመጀመሪያው ሆቴል አሁን ፒያሣ የሚገኘው ጣይቱ ሆቴል ነው::
ሆቴሉ በ1898 ዓ.ም በነሀሴ ወር ሥራውን ጀመረ። ሆቴሉን የማስተዳደር ሥራ እቴጌ ጣይቱ ተረክበው ሐላፊነቱን መወጣት ጀመሩ።
በ1900 ዓ.ም ጥቅምት 25 ቀን ምኒልክ በአዲስ አበባ ያሉ ዲፕሎማቶችንና የውጭ አገር ሰዎችን ጋብዘው ሆቴሉን አስመረቁ። የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጅም ሙሴ ፍሬደሪክ ሐል ነበር። በኃላ ግን አቶ ዘለቃ አጋርደው ተሾሙ።
እንደ አገር አባባል ጣይቱ እጅ የሚያስቆረጥም ወጥ እያሠሩ ገበያ ቢጠብቁ ጠፋ። እንኩዋን ምግብ መብላት ከግሪኮቹ ሻይ ቤት ገብቶ ሻይ መጠጣት ነውር ነበረና፣ ጣይቱ ጠዋት የሚያሠሩት ወጥ ለሠራተኞቹ የማታ ራት ይሆን ጀመር። የሚስታቸው ገበያ ማጣት ያሳሰባቸው አጤ ምኒልክ አንድ ቀን ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በአካባቢያቸው ላሉ መኩዋንንቶች “ጣይቱ ምግብ የሚሸጥበት ቤት ከፍታለችና ኑ እንሂድና ልጋብዛችሁ” ብለው ወሰዱዋቸው። መኩዋንንት በላ ጠጣና ምኒልክ 30 ብር ከፈሉ።
በማግሥቱ እንደተለመደው ገበያ ቢጠበቅ ጠፋ። ቀጥሎም ጠፋ፣ ቀጥሎም ጠፋ። እንደገና ምኒልክ ሆቴል ገብቶ መብላት ነውር ያለ መሆኑን ለመኩዋንንቱ ገልፀው እንደገና ምሣ ጋበዙ። በሌላው ቀን አሁንም ገበያ አልተገኘም። ቢጠበቅ ቢጠበቅ ድርሽ የሚል ሰው ጠፋ። በሌላ ቀን ደግሞ አጤ ምኒልክ ከችሎት ሊነሱ ሲሉ በዙሪያቸው ላሉ መኩዋንንት “ሰማችሁ ወዳጆቼ” አሉ። “በፈረንጅ አገር አንድ ቀን አንድ ሰው የጋበዘ እንደሆነ ያ የተጋበዘ ሰው በሌላ ቀን ደግሞ ብድሩን ይከፍላል ብድሩን ካልከፈለ ግን እንደ ነውር ይቆጠርበታል።” ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ መኩዋንንቱ “እርስዎን ፈርተንና አፍረን ነው እንጂ የሚሆንልን ከሆነ የምኒልክን ብድር ለመመለስ እኔ አለሁ” እያለ ተራ በተራ ከሆቴል ቤት ምኒልክንና ጣይቱን ይጋብዝ ጀመረ” ገበያ እየደራ ሄደ። ምሳችንን እቴጌ ሆቴል ሄደን እንብላ የሚለው ስለበዛም ስሙ እቴጌ ሆቴል ተባለ።
ጳውሎስ ኞኞ
አጤ ምኒልክ መፅሐፍ
አጤ ምኒልክ መፅሐፍ
http://ecadforum.com/Amharic/archives/14111/
No comments:
Post a Comment