ከመሃል ያለው ኢዛና (እስራኤል ገደቡ)
ለ’ኢንቨስትመንት” አዲስ አበበ ያለፈው ወር በሄደ ጊዜ
ሂሩት
መለሰ – ከሮተርዳም
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።
የሮተርዳም
ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ
እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ
– የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት
ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት
አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ
በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ
ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ
ወታደር ጋር በመሆን የሰላም ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት
መልካምነት ሲሰብኩ ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።
አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ መሆኑን መናገር ጀምሯል። ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39392