Tuesday, February 10, 2015

ተቃዋሚዎችን በጥላቻ የሚመለከተው ወያኔ አሁንም የክስ ዋራንት ለመቁረጥ አሰፍስፏል

በተጭበረበረ ፖለቲካ አገር አስተዳድራለሁ የሚለው ወያኔ ተቃዋሚዎች በመንግስታዊ ተቋማት ላይ አፍራሽ ተልእኮ ያራምዳሉ በማለት ሊያጠቃቸው መነሳቱን በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ያለእፍረት እየተነፈሰ መሆኑ በመስማት ላይ ነን::በፍትህ እና በምርጫ ቦድ እንዲሁም በማስተዳድራቸው ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ዲሞክራሲ እንዳያብብ እንቅፋት እየሆኑ ነው ያለው ወያኔ ራሱን የዲሞክራሲ ጠበቃ አድርጎ በመሳል በአፍራሾች ላይ እርምጃ እውስዳለሁ ሲል ሰበብ እየፈጠረ መሆኑን አድበልብሎ የሰራቸው እና የፈጠራ ውጤቶቹ የሆኑ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚባሉትን ካድሬዎቹን ሲያስደሰኩር ሰምተናል::
በመፍረከስከስ ላይ መሆኑን የሚያሳብቅበት ወያኔ በአንድነት ፓርቲ ላይ የማፍረስ እንዲሁም መኢአድን የመበጥበጥ ስራ ከሰራ በኋላ ተበደልም የሚሉ የፍትህ ያለ በሚሉበት ሰአት በሌላ ወንጀል ሰማያዊን ለማሸግ ማሰፍሰፉን እርግጫው ይናገርበታል::በአገሪቱ እያደረገ ያለው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ወንጀሎች ከማህበራዊ ድቀት ጋር ተደምረው ለምርጫ ቢቀርብ እንደሚሸነፍ ያረጋገጠው እና አከርካሪው የተመታው ወያኔ ላለመሞት በሚያደርገው መፈራገጥ ያሸንፉኛል ያላቸውን ፓርቲዎች እና ግለሰቦችን ጠልፎ በመጣል በመሳሪያ ሃይሉ ተማምኖ ወደ እስር ቤት ለመወርወር ማሰፍሰፉ አምባገነንነቱ ምን ያህል አግጥጦ እንደወጣ ያሳያል::
ዲሞክራሲያዊ ተቋማት የሚባሉት እንደ ምርጫ ቦርድ እና የፍትህ አካላት ነጻ እና ገለልተኛ ባልሆኑበት አገር ነጻነትን እና መብትን ለማስከበር የሚታገሉ ድርጅቶችን ለመዋጥ ባሰፈሰፈ የፖለቲካ ዘንዶ ራሱ እንደሚዋጥ ያላሰበው ወያኔ ነጻ እፓርቲዎች እና ግለሰቦች ሊታዘዙልኝ አልቻሉም እንደኔ ሊያስቡ አልቻሉም በሚል በጥላቻ የተሞላው ወያኔ የፓርቲ አመራሮችን ሰብስቦ ለማሰር ማሰፍሰፉ በሃገሪቱ እየተስፋፋ ያለው ህገወጥ መንግስታዊ አሸባሪነት ሃገር ወዳዶችን እና ለውጥ ፈላጊዎች አጥፍቶ ለመጥፋት ምን ያህን እንደተነሳ በገሃድ ይመሰክራል::
የፍትህ አካላት እና ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ከነሚዲያ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር በዋሉበት አገር ዜጎች በሰበብ አይታሰሩም አይሰደዱም አይገደሉም ማለት ዘበት ነው::ኢሕአዴግ መሰሎቹን ይዞ ወደ ሚያጭበረብረው ምርጫ ለመዝለቅ እንዲያስችለው ጠንካሮችን ከጨዋታው ውጪ በማድረግ ግስጋሴውን ተያይዞታል::የአውሮፓ ህብረት የመሰሉ ሃገሮች ለውጥ አልባ በሆነ ምርጫ እስጥ በታዛቢነት አንሳተፍም በማለት እጃቸውን የሰበሰቡ ሲሆን ወያኔ እንደ ምርጫ ቦርድ ያሉ አጋሮቹን ይዞ ሆይሆይታውን በመቀጠል ንጹሃንን በማሰር ፓርቲዎችን በማፍረስ ላይ ነው::ይህንን የተቃወሙ የለውጥ ሃይሎችንም በአፍራሽነት በመፈረጅ ላይ መሆኑን የራሱ ሚዲያዎች እየተናገሩ ነው::
ህዝብን በፖለቲካ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስክ ቁም ስቅሉን እያሳየው ነው:: የሃገሪቱ ህገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ እና ውጪ በፖለቲካ መስክ የአይናቸው ቀለም ያላማረ ተቃዋሚዎች ይደበደባሉ ይታሰራሉ ይገረፋሉ በፍርድ ቤት በሃሰት መረጃ ከህግ ትእዛዛት ውጭ የረዥም አመት እስር ይከናነባሉ:: እንደ መንግስት ባለስልጣናት ሳይሰርቁ ደፋ ቀና ብለው ያፈሩት ንብረት ይወረሳል::ከዛም አለፍ ካለ በአደባባይ ይረሸናሉ:: በደህንነት ሃይሎች ይገደላሉ:: ይህ የሚያሳየው የጸጥታ ሃይሎች ከህግ በላይ ሆነው ፍትህን መግደላቸው ነው:: የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳይንቀሳቀሱ የጸጥታ ሃይሎች እንቅፋት ከመሆን አልፈው ወደ አንድ ፓርቲ ያደላ ኮንትሮባንዳዊ ፖለቲካ እየፈጸሙ ነው::ሕዝቦች ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ አምባገነኖች የሚያደርሱት ጭቆና ትግሉን ያፋፍመዋል እንጂ አያዳክመውም:: በሃገር ውስጥ ይሁን በውጪ ሃገር የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ለወያኔ መውደቅ ከበፊቱ በበለጠ ለትግላችን ስኬት እስከ ድል ደጃፎች ድረስ በመገስገስ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ነጻነታችንን በማረጋገጥ የወያኔን አምባገነን ስርአት በመጣል የጋራ አገራችንን ለመገንባት የምንነሳበት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን ለማረጋገጥ እወዳለሁ::#ምንሊክሳልሳዊ
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17252

No comments:

Post a Comment