Wednesday, February 11, 2015

በኦሮምያ ክልል የፌደራል ፖሊሶች ሁለት የቤተሰብ አባላትን በጥይት መትተው አመለጡ


በምእራብ ሸዋ ዞን በባኮ ወረዳ በቴቢ ከተማ ከሩሰንጎት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት አቶ ተሙሻ በርጫ እና የ13 አመት ታዳጊ ልጃቸው ፋንቱ ተሙሻ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች በጥይት ተመትተው አምቦ ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ዘገበ::

እንደ ኢሳት ዘገባ ከሆነ ታዳጊዋ ወጣት አንገቷ አካባቢ በጥይት ስትመታ፣ አባቷ ደግሞ እግራቸውን በሁለት ጥይቶች ተመተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑም ታውቋል።


ማንነታቸው ያልታወቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ቀበሌው በመሄድ፣ አቶ ተሙሻን አሸባሪዎችን አስጠግተህ ትቀልባለህ ብለው በጥይት እንደመቱዋቸውና የአካባቢው ነዋሪዎች ሆ ብለው ሲወጡ፣ በመጡበት መኪና ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

አሸባሪ የተባሉት ሃይሎች እንማን እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ነዋሪዎች ግን ምናልባትም ለምርጫ ቅስቀሳ የመጡ የተቃዋሚ አባላትን ሊሆን ይችላል ይላሉ። ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38938

No comments:

Post a Comment