Thursday, February 5, 2015

የአንድነት ለዴሞክራሲናለፍትህ ፓርቲ የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዛሬ በይፋ ተዘግቷል!



ሰሞኑን ገዢው የኢህአዲግ መንግስትና ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ የከፈቱትን ዘመቻ ተከትሎ በተላለፈው ውሳኔ የአንድነት ፓርቲን ለኢህአዲግ ተለጣፊዎች መስጠታቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ እውነተኛ የአንድነት ፓርቲ አባላትና መዋቅሮች ለዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት እውቅና በመስጠት የህዝብን የትግል መንፈስና ተስፋ ውሀ አንቸልስበትም፤ እኛ የህዝብ እንጂ የስርአቱ ተለጣፊ አይደለንም በመሆኑም ኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ የወሰዱት የአንድነትን ስምና ባዶ ቢሮ እንጂ በፓርቲው ውስጥ የተገነባውን የትግል መንፈስ ባለመሆኑ የትግሉን አቅጣጫ በመቀየር የለውጥ ጉዟችንን እናሳካለን በማለት በአሁኑ ሰዓት ከሰማያዊ ጋር አብሮ ለመታገል የወሰኑ ሲሆን ይህን ተከትሎም በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ቢሮዎች በመዘጋት ላይ ሲሆኑ በአባላት የግል አስተዋፅኦ የተከፈተው የኮምቦልቻ አንድነት ፅ/ቤጽም ከሁለት ወር በፊት በይፋ ተከፍቶ በይፋ ተዘግቷል!!!! የአንድነት ትግል ግን በሰማያዊ ቤት ይቀጥላል!!! …….ድል የህዝብ ነው!!

http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17205

No comments:

Post a Comment