Sunday, February 22, 2015

የሕወሓት አስተዳደር በአዲስ አበባ ዙሪያ በአዳማ እና ደብረዘይት ማስተር ፕላኑን በሚቃወም ቅስቀሳ ተረብሿል

መላው ኢትዮጵያውያን ለሚደረገው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከጎናችን እንዲቆሙ ሲሉ አስተባባሪዎች ጠይቀዋል::
(ምንሊክ ሳልሳዊ) ከመሃል ሃገር ከሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በወጣቶች ማህበር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ዙሪያ በናዝሬት/አዳማ እና ደብረዘይት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም እንዲሁም የወያኔው ጀሌ አባይ ጸሃዬ የሚባለው የተናገረውን ጸረ ሕዝብ አፍራሽ አነጋገር በመቃወም ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል::ይህ ቅስቀሳ ወያኔን አስጨንቆ የያዘው ሲሆን ሊያስቆመው የማይችል ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመጽ ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት አስከትሏል::

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላይ በተደረገ ተቃውሞ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን የተቹ የተቃወሙ እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ስለገበሬዎች መብት አቤት ያሉ ወጣቶች ተገለዋል ታስረዋል ተደብድበዋል በአፋኝ ሃይሎች ተሰውረዋል::ይህ ቁስል ሳይጠገን የሕወሓት ጀሌዎች በሃዋሳ በተደረገ ስብሰባ ላይ ባደረጉት እብሪት የተሞላ ንግግር ልክ እናስገባለን ብለው መዛታቸው በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል::ይህንን ቁጣ ተከትሎ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ ህዝብን የማስተባበር ስራ እና የቅስቀሳ ስራ እየተሰራ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን ከአስተባባሪዎች ጎን እንዲቆም ጥሪዎች አስተባባሪዎቹ ጠይቀዋል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39198

No comments:

Post a Comment