Thursday, February 26, 2015

ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ

‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!
መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን
በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ
የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ
ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም
በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው
ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን
በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም
ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡

አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡
ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው
መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን
እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ
አይደለምና!!!


አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!



ድምጻችን ይሰማ!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39339

No comments:

Post a Comment