ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ
ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ
ዩኔስኮ፣ አለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፈንስ ኢንሼቲቭ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስዎች፣ ሲፒጄ፣ ፔን ኢንተርናሽናል፣ ዶሀ ፍሪደም ሴንተር፣ አርቲክል 19ንና ሌሎች ያልጠቀስኳችሁ በርካታ አለምአቀፍ ድርጅቶች ለጉዳዬ የሰጣችሁት ትኩረት በኢትዮጵያ ያለውን አምባገነን ስርዓት በማጋለጥ በኩል ትልቁን ድርሻ ተጫውቷልና ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርብላችኋለሁ፡፡
መፈታቴን እንደራሳቸው ጉዳይ ቆጥረው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደ ማርቲን ሽቢዬ፣ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም፣ አና ጎሜዝ፣ ናኒ ጃንሰን፣ ክርስቲያን አማንፑርና ሌሎች ዘርዝሬ መጨረስ የማልችላቸው በርካታ ግለሰቦች ለጉዳዩ የነበራቸውን ጠንካራ መሰጠት አብዝቼ አደንቃለሁ፡፡
ምንም እንኳን በአስከፋ ሁኔታ ተገልዬ የቆየሁባቸውና ጤናዬ ተቃውሶ የነበረባቸው መጥፎ ጊዜያትን ያሳለፍኩ ቢሆንም ከእስር የወጣሁት ግን ሁኔታዎቹ ሞራሌን ሳይሰብሩትና ይልቁንም ለዲሞክራሲ በተለይ ደግሞ ለፕሬስ ነፃነት መከበር የምችለውን ሁሉ ለማድረግ የበለጠ ቁርጠኝነት ኖሮኝ ነው፡፡
በድጋሚ አመሰግናለሁ
ርዕዮት አለሙ
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45297
No comments:
Post a Comment