Tuesday, July 7, 2015

በአፋር ክልል ወጣቶች ለውትድርና በግዴታ እየታፈሱ ነው


በአፋር ክልል የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መንግስት የአፋር ህዝብን ደካማ ጎኑን በመጠቀም ወጣቶችን ለውትድርና እያፈሰ ይገኛል።

አለም አቀፍ የምግብ ተረድዖ ድሪጅት በእንግለዘኛ ምህጻሩ WFP ( worlid food program ) ለኢትዮጲያ ህዝብ የሚሰጠው የእርዳታ እህል ለውትድር መደልያ በመጠቀም በአፈር ክልል በብዙ ወረዳዎች እርዳታን ለማገኘት ከአንድ አባወራ ቢያንስ አንድ ሰው ለውትርና መመዝግብ አለበት።

የወያኔ መንግስት የመዕራባዊያን ድጋፍ ላለማጣት የገዛ ወታደሮቹን በሰላም አስከባሪነት ሽፋን በሶማሊያ እና በዳርፎር በማሰማራት እየፈጃቸው መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አፈሳው እየተካሄደ ይገኛል።

በአፋር ክልል 80% የሚሆን ህዝብ ከውጭ በሚገኘው እርዳታ የሚተዳደር ሲሆን ወያኔ ይህን ደካማ ጎናቸውን በመጠቀም እርዳታ ለማገኘት አንድ ሰው ከአንድ አባወራ ለውትድርና ስልጠና መመዝግብ አለበት ይላል።

በአፋር ክልል ይህ ህገ ወጥ ድርግት ተግባራዊ የሚሆነው በአብደፓ የአፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪነት ስሆን በየቀበሌው አስተዳደሮች አማካኝነት ትዕዛዙ ወደ ህዝብ እንዲወርድ እየተረገ ይገኛል።


በአፋር ክልል ባሉ በ32 ወረዳዎች ይህ ጉዳይ ወቅታዊ እና አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል።


ከአኩ ኢብን አፋር

 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44858

No comments:

Post a Comment