በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት የተከሰሱት 16 የፖለቲካ
ፓርቲ አመራሮች ዛሬ ሀምሌ 17/2007 ዓ.ም የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ አመራሮቹ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም በጠበቆቻቸው
በኩል የክስ መቃወሚያና የዋስትና ጥያቄ አቅርበው፣ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም አቃቤ ህግ ለጥያቄው መቃወሚያ እንዲያሰማ ቀጠሮ ተሰጥቶት
ተቃውሞ ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም የተከሳሾቹ ጠበቃዎች ደንበኞቻቸው በሽብር ወንጀል ያልተሳተፉ በመሆናቸው በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው
ትክክል አለመሆኑን፣ ቢቻል ክሱ ተዘግቶ እንዲሰናበቱ፣ ይህ ባይሆን እንኳ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ
ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ብይን እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ለዛሬ ተቀጥሮ ነበር፡፡ ይሁንና ዛሬ ሀምሌ
17/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ምድብ ችሎት በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ‹‹በመረጃ የሚረጋገጥ ይሆናል›› በሚል ጠበቆች
ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል፡፡
በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ የተከሰሱት አመራሮች፡-
1ኛ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን
2ኛ በላይነህ ሲሳይ
3ኛ አለባቸው ማሞ
4ኛ አወቀ ሞኝሆዴ
5ኛ ዘሪሁን በሬ
6ኛ ወርቅየ ምስጋናው
7ኛ አማረ መስፍን
8ኛ ተስፋየ ታሪኩ
9ኛ ቢሆነኝ አለነ
10ኛ ተፈሪ ፈንታሁን
11ኛ ፈረጀ ሙሉ
12ኛ አትርሳው አስቻለው
13ኛ እንግዳው ቃኘው
14ኛ አንጋው ተገኘ
15ኛ አግባው ሰጠኝ
16ኛ አባይ ዘውዱ ናቸው፡፡
በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ የተከሰሱት 16 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የአቃቤ ህግን ምስክር ለመስማት ለነሃሴ 12ና 13/2007 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት በልደታ ፍርድ ቤት የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ተቀጥረው የነበሩት እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለሀምሌ 28/2007 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45344
No comments:
Post a Comment