Tuesday, May 21, 2013


በጎጃም ህገወጥ እስርና አፈና ተባብሶ ቀጥሏል


በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ ሰዎች በግፍ እየታሰሩ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
በተለይ ሚያዚያ 18 ቀን 2005ዓ.ም. በወረዳው መራዊ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች መካከል አቶ አንሙት እና አቶ መንግስት በቀለ የተባሉ ወጣቶች በሌሊት በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ያሉበት እንደማይታወቅ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዲህ እንዳለ ግንቦት 3 ቀን 2005ዓ.ም. ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት መኮንን አድማስ በሚባል የፀጥታ ኃላፊ እና ወ/ሮ አሰለፈ ከበደ በሚባሉ የወረዳው ካቢኔ በወረዳው መራዊ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን ወ/ሮ ሙሉ ሲሳይ በሁለት ተሸከርካሪዎች በሄዱ የፀጥታ ኃይሎች አሽባሪ ነሽ፣ የደበቅሽውን ቦምብ አምጭ በሚል ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸው ተጠቁሟል፡፡
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍልም በጉዳዩ ዙሪያ ነበሩበት ወደተባሉት  የአካባቢው የፀጥታ ኃላፊ መኮንን አድማስ እና የወረዳው ካቢኔ ወ/ሮ አሰለፍ ከበደ ጋር ስለጉዳዩ ለማጣራት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ በአካባቢው በተለይም በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ አሁንም የተለያዩ ሰዎችን ለማሰር የፀጥታ ኃይሎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ምንጮቻችን ከስፍራው ጠቁመዋል፡፡
     Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment