Wednesday, March 19, 2014

አባ መላ ሳይበላ ተበላ! – ሆዳም! ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም!

              ከአዜብ ጌታቸው

አባ መላ ነኝ የሚለው የፓልቶኩ ብርሃኑ ዳምጤ ሰሞኑን የሰራው ስራ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው። ከአንድ ድርጅት ውልቅ ብለው በዚያው ጀንበር ሌላው ድርጅት ጥልቅ የሚሉ፤ ያም ሳይጥማቸው ወይም ሳይመቻቸው ይቀርና ወዲያው ደሞ ወደ ሌላ 3 4….. ድርጅት ጥልቅ ውልቅ የሚሉ ጥቂት የማይባሉ ቅብዝብዞችን አውቃለሁ።እነኚህ አይነቶቹ የቻሉትን ያህል እንደ ፌንጣ ዘለው ዘለው በመጨረሻ እዩኝ እዩኝ ያለ ……እንዲሉ፦ ራስን ብቻ አባል በሚያደርገው ዲፕሬሽን ወደ ተሰኘው ድርጅት ይገቡና ፍጻሜያቸውም እዛው ይሆናል።

ሰሞኑን በአባ መላ የታየው ዝላይ ግን በፌንጣ ተምሳሌት ከተገለጹት ቅብዝብዞች የተለየ ነው፡፡ አባ መላ ውልቅ ካለበት የወያኔ ጓዳ ያሞሌ ተመኑን ቀንሶ ዳግም ጥልቅ ብሏል። ስለዚህ ለአባ መላ ተግባር በተምሳሌነት የምትጠቀሰው ፌንጣ ሳትሆን የተፋውን መልሶ የሚውጠው ጉማሬ ይመስለኛል

ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ወያኔን ጉማሬ ብለው የገለጹበትም ምክንያት ይህው ነበር፡፤ በነገራችን ላይ ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ቃለ ምልልስ ላይአባ መላየሚለውን ቅጽል ያወጡለት ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን መሆናቸውn (he was my best friend) አይነት ድምጸት) ሲናገር ሰምቸዋለሁ፡፤ የሞተ አይጠይቅ ሆነና ዝም ብለን ሰማነው።

ይሁን እንጂ በበኩሌ እንደሚታየኝ ብርሃኑ ዳምጤ የተሰ| የተሰፋ ሙዝ የሚሸጥ የምናለሽ ተራ ቁጭ ይበሉ (ምንጭ አብሮ አደጉ) የብርቅየውን ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬን ጓደኝነት እንኳን በዕውን በልቦለድ ድርሰትም ቢካተት ለአንባቢ የሚጥም አይመስለኝም፡፤ ልቦለድም ቢሆን እኮ የገሃዱ ዓለም እንጂ የከሃዲው አለም ነጸብራቅ ነው አልተባለም።….
ወደ ቀምነገሩ ልመለስ፦ አዎ ብርሃኑ ዳምጤ እነ ሎሬት ጸጋዬን እየጠቃቀሰ ፕሮፊይሉን ከፍ ከፍ እያደረገ ቢቆይም ሰሞኑን በሰራው ታሪካዊ ክህደት ያበገነው አብሮ አደጉ ያለ ከፈን ምናለሽ ተራ ቀብሮታል።

ለዚህም ነው ብርሃኑ በሰሞኑ ተግባሩ ከማንም በላይ የጎዳው ራሱን ነው ያልኩት፡፤
ከልብ አጢናችሁት ከሆነ የብርሃኑ ዳምጤ ችግርሞራል አልባመሆኑ ነው። ሞራል አልባ ሰዎች የሌላውንም ሞራል ለመጨፍለቅ ሁለቴ ማሰብ አያስፈልጋቸውም። ሞራል አልባ ሰዎች ምን ይሉኝ? አይሉም።ምን ይሉኝ የሚለውን ጥያቄ በአግባቡና በቦታው ማንሳት፤ የሞራል ድቀት ከሚያስከትል አደጋ ያድናል። ብርሃኑ ዳምጤን መሰል ሰዎች ይህን ጥያቄ አያውቁትም።
ለዚህም ነው ትናትና እንኳን ለተሰዳቢው ለሰሚው በሚዘገንን ጸያፍ ስድብ ያበሻቀጣቸውን የወያኔ ባለስልጣናት ዛሬማሪኝ ብዬሻለሁእያዜመ የሚለማመጠው።
ግን ለምን?
ጥሩ ጥያቄ ነውሞራል አልባ ሰው የማንነቱ ነገር ብዙም አያስጨንቀውም። ተደፈረብኝ። ተገሰሰብኝ የሚለው እሱነት የለውም። ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም። ለሱ ማንነት? ከሚለውየስብዕናጥያቄ ይልቅ ምቾት፤ ድሎት፤ ቅንጦት፤…..የተመቸ ህይወት ቅድሚያ አላቸው። በአጭሩ ሞራል አልባ ሰዎች ከምንም ከምንም ይልቅ ለሆዳቸው ቅድሚያ ይሰጣሉ።ብርሃኑ ዳምጤም ያደረገው ይህንኑ ነው።

ከወያኔ ኩብለላ
የወያኔ ባለ ስልጣናት የአውራቸውን ሞት ተከትሎ በራሳቸው የውስጥ ችግር ተንጠው፤ ውጭ ለታሰሩት ውሾች ይሰ| የነበሩትን መደበኛ መሽሩፍ አቋረጡ። በዚህ ምክንያት አለን ከሚሏቸው ተናካሽ ውሾቻቸው አንዱ (አባ መላ) ሰንሰለቱን በጥሶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ተቀላቀለ።

በተቃዋሚው ጎራ ቆይታ፦
ሰንሰለቱን በጥሶ የመጣው አባ መላ አክቲቪስት ተባለና(ይታያችሁ ሞራል አልባ ሰው የሰባዊ መብት ተሟጋች ሲሆን) የድሮ ጌቶቹን አብጠለጠለልን። ሙታንታ ማድረግ የማያውቁ ፍልጦች የሚል .ሞራላዊ ስድብ አወረደባቸው። እግረ መንገዱንም ሙታንታን ያህል የግል ገበና ሁሉ አውቃለሁ አይነት ራሱን አካበደ።

የጦር ሃይሎች ኤታ ማዦር ሹሙን በዓለማችን የመጨረሻው ደደብ ጀነራል ሲል ተሳለቀበት። የጀኔራሉ ህጻን ልጅ የኦሮሚያውን ፕሬዘዳንት በልምጭ ሲገርፈውአባዱላ እንደ ፈርስ ያስካካ እንደነበር ገለጸልን፡፤ ሞራል አልባው አባ ዱላ ለሆዱ ብሎ በህጻን ተገረፈ ብሎ እራት ግብዣ ላይ ያየውን ተረከልን። እረ ማን ቀርቶየአዜብን አካላዊ ገጽታ አብጠለጠለየበረከትን ሴረኝነት አማሰለስብሃትን በዝሙት በስካርና በገዳይነት ወነጀለብቻ አብዛኞቹ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት እጅግ በሚዘገንነው በምናለሽ-ተራ ጩቤ ምላስ ተተለተሉ።ባለ ስልጣናቱ ተዘናግተው ምሱን ባለመስጠታቸውበሞራል አልባ አንደበቱ ዘመተባቸው። የአዜብ አፍንጫ ጠማማነት ምን የፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው ባይገባንም ፈገግ ማለታችን አልቀረም።

ብርሃኑ ዳምጤ እንዲህ እንዲህ እያለ በተቃዋሚው ጎራ ቆየ፡፤ ወደ ኢሳት ቢያንዣብብም …. በወያኔ የጎደለበትን ምሱን የሚተካበት ምናምኒት ሊያገኝ የቻለ አልመሰለኝም። ቀጠለና በሳውዲ መንግስት ግፍ የተፈጸመባቸውን ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት በተቋቋመው አለም አቀፍ ግብር ኃይል ገብቶ እድሉን ሞከረ፡፤ እንደ ልኳንዳ ቤት ውሻ አይኑ እየተንከራተተ ምራቁን ገርገጭ አድርጎ ከመዋጥ በስተቀር አሁንም ጠብ የሚል ነገር አልተገኝም። በዚህን ግዜ ብርሃኑ ዳምጤ፤ ከወያኔ ጉያ መውጣቴ ታሪካዊ ስህተት ነው ሲል፡ ታሪካዊ ስህተት ያለውን በታሪካዊ ሞት ሊያርመው ወሰነ።አመቺ ግዜም ጠበቀ።ረዳት ፓይለት ኃይለ መድህንን በቴሬሪስትነት በመፈረጅ ለወያኔ የመጀመሪያውን የምህረት ጥየቃ ደውል ደወለ! ኦሮማይ…….!

ዳግም ወደ ወያኔ
ብርሃኑ በደርሶ መልሱ ጉዞ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው ያልኩት ያለ ምክንያት አይደለም። በክብር የያዙትን ጌቶቹን አስቀይሞ ሲያበቃ ዛሬ ተመልሶ ለምህረት ደጅ መጥናቱ፤ ዋጋውን ዝቅ አድርጎ ራሱን ለዳግም ሽያጭ ማቅረቡ፤ እንደ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውም ስብዕናውን ማዝቀጡ እየታየኝ እንጂ

ከበድን መሃል ምኑን ይመርጧል አትበሉኝ እንጂ፦ በኔ እይታ ዛሬ ከሰሎሞን ተካልኝና ከቤን የዘቀጠ ሞራል ላይ የሚገኘው ብርሃኑ ነው። ይህን ለመረዳት ደግሞ ከቤን ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ማድመጥ ብቻ በቂ ነው፡፡
ቃለ መጠይቁ ቤን ሌጌቶቹ ባለው ታማኝነት በመኩራራት የሚሰነዝራቸው አስተያየቶችና ጥያቄዎችደግ አላደረክም ቢሆንም እንምርሃለንአይነት ድምጽ ነበራቸው፡፤ አባ መላም በአንጻሩ ጭራውን እየነሰነሰ ጌታው እግር ሥር እንደሚንከባለል ውሻ አይነት በልምምጥ ስሜት ነበር የሚመልሰው፡፤ ከባሪያም ተራ…..!
ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል!

ከብርሃኑ ዳምጤ ድፍረት ሁሉ ያስገረመኝ ታማኝ በየነንና ማንጓጠጥ መሞከሩ ነው። በርግጥ ወያኔ ከማንምና ከምንም በላይ ታማኝ ቢዋረድላት እንደምትደሰት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፤ በዚህ ስሌት ይመስላል ብርሃኑ ዳምጤ ታማኝን ለማብጠልጠል የሞከረው። ነገር ግን አልተሳካም፡፤ ወያኔም ቢሆን ጀግና ታከብራለች ሲሉ ሰምቻለሁና ከብርሃኑ የገለማ ቃል ይልቅ የታማኝን ግልጽ ጠላትነትን የምታከብር ይመስለኛል፡፤ ከሞተ ወዳጅ የቆመ ጠላት ይሻላል ይባል የለ። ብርሃኑ ለኛም ለወያኔም ሞቷል።
ይህን የምለው በታማኝ በየነና በአባ መላ መካከል ያለው ፍጹም የሆነ ልዩነት እየታየኝ ነው፡፤ ቃላቶች ካልተመሙብኝ እስኪ በንጽጽር ልግለጻቸው።

ታማኝ ከአላሙዲን የዶላር ማማ ላይእረ ወግድልኝ!” ብሎ ወርዶ ከተገፋው ወገኑ ጎን በመቆም ከፍተኛ የሞራል እርከን ላይ የሚገኝ የህዝብ ልጅ ነው።

ብርሃኑ ደግሞ በአንጻሩ በደም ከጨቀየው ከወያኔ ደጅ የወዳደቀ ምንምን አይቶ፤ ይሁን እስቲ ካወጣነው የሞራል ማማ ላይ ቁልቁል ተምዘግዝጎ የወረደ የግፈኞች ወዶ ገብ ባሪያ ነው።አለቀ።

በነገራችን ላይ ብርሃኑ የወያኔን የምህረት ደወል በቤን አማካኝነት ሲያስደውል፤ አብሮም የኢሳትንና የግንቦት ሰባትን ብዙ ሚስጥር ገጸ በረከት እንደሚያቀርብ ነግሮናል። እውነት እውነት እላችኋለሁ ብርሃኑ እስካሁን ከቀበጣጠራቸው ነገሮች ውጭ አንድም የሚያውቀው ነገር የለም። ለምን በሉኝ? ምክንያቱም ዋናው ቁጭቱ ወደ ሚስጥሩም ወደካዝና ሊያቀርቡት አለመፍቀዳቸው በመሆኑ ነው።ጨዋታ በጋራ ሂሳብ በግል ተባለ….አልወደደውም።

አክቲቪስት ስለመባሉ….
በኢሳት ጋዜጠኞች አክቲቪስት መባሉ ለኔ ብዙም እንደ ጥፋት አልታየኝም። አክቲቪስት የሚለው ስያሜ እንደ ወታደር ቤት በአገልግሎት ዘመን ተመዝኖ የሚሰጥ ሹመት ሳይሆን አመለካከትን ብቻ መሰረት አድርጎ የሚስጥ በመሆኑ ብርሃኑም ወያኔ ማብጠልጠል በጀመረበት ቅጽበት አክቲቪስት መባሉ አልተገቢነቱ አይታየኝም፡፤ በኔ አመለካከት
በእጅጉ የሚያስቆጨኝና ስህተት የምለውአክቲቪስትየሚለውን መጠሪያ መስጠቱ ሳይሆን አንድ 11ኛቢ ተማሪ (ከአብሮ አደጉ የሰማሁት ነው) የምናልሽ ተራ ቁጭ በሉ እነ ሙሉጌታ ሉሌን ከመሰሉ በሳል ሰዎች ጎን ፖለቲካ ሊተነትን መቀመጡ ነው። የሚያናድደኝ ከነታማኝ በየነና አበበ ገላው ሌሎችም ብርቅዬ ኢትዮጵያዊያን እኩል አለም አቀፍ ግብር ኃይል ውስጥ መግባቱ ነው።እኩያ ቢስ ..!” ይሉ ነበር ቀኛዝማች እንቶኔ እንዲህ አይነቱ ያለአቻ… ….ሲገጥማቸው። ይህ አይነቱ ስህተት እንዳይደገም ሊታሰብበት ይገባል ይመስለኛል።

አሁንም በኔ እይታ ብርሃኑ ዳምጤ (ከሟቹ አለቃው ከጠ/ አጸያፊ አባባል ልዋስና) ከመበስበስወደ.. መታደስ…. እንደገና ወደ መበስበስ ያደረገው የደርሶ መልስ እንቅስቃሴ በአጭሩ ሲቀመጥ፡
እንሆ ብርሃኑ ዳምጤ ጥቅም(ሆዱ) ስለጎደለበት ወያኔን ከድቶ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ገባ። የወያኔ ባለስልጣናትን በአጸያፊ ስድብ ማዋረድን ለተቃዋሚው ጎራ እንደ ገጸበረከት አቀረበ።አሁንም በተቃዋሚ ጎራ ለህሊና እንጂ ለሆድ የሚሆን ነገር በማጣቱ የአሞሌ ተመኑን ቀንሶ ራሱን ለቀድሞ ጌታው ዳግም ለሽያጭ አቀረበ። ይህው ነው። መጣ እነሱን ሰደበሄደ..ራሱን ሰደበ!

ብርሃኑ ዳምጤ ከዚህ በኋላስ?
ብርሃኑ ከዚህ በኋላ አይደለም ፖለቲካዊ ህይወት ሰዋዊም ህይወት የሚዋጣለት አይመስለኝም።በቅርቡ አንድ አብሮ አደጉ ብዙ ብዙ አሉታዊ ባህሪያቱን እንዳጋለጠው ሰምተናል። ብርሃኑ የሰሞኑ ተግባሩ ከራሱ ሌላ ማንንም ላለመጉዳቱ ሌላው መገለጫ በይደር ተይዞ የነበረ፤ በቀይ ሽብር ዘመን ከኢህአፓ ውልቅ ደርግ ጥልቅ ብሎ ያስቀጠፋቸውን ሁለት ወጣቶች ጉዳይ ከሟች ቤተሰቦች አንደበት ለማሰማት እንቅስቃሴ መጀመሩ ነው።ይህ ማስፈራሪያ ሳይሆን በቅርብ የማውቀው ወዳጄ እየሰራበት ያለ ጉዳይ ነው።
በኔ እይታ ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናትን ከሰደባቸው አጸያፊ ስድብ አኳያ እጃቸውን በምህረት የሚዘረጉለት አይመስለኝም። እንደ ሰሎሞን ተካልኝየቅንድቡ ውበትአይነት ሙገሳም የሚያዋጣ አይሆንም። እናም አባ መላ በፓልቶክ ውስጥ ተፈጥሮ በፓልቶክ ውስጥ ኖሮ በፓልቶክ ውስጥ ሞተ ! የሚለውን ዜና የምንሰማበት ግዜ እሩቅ አይሆንም።አባ መላ ሳይበላ ተበላ! ይሏል ይህ ነው…..

ለድህረ ገጾች
ኢሳቶችና ድህረ ገጾች ብርሃኑ የወያኔ ባለስልጣናት በአጸያፊ ስድብ ሲያዋርዳቸው የተቀዳውን ኦዲዮ እየመረጣችሁ በማስደመጥ የምህረት ጥያቄው ተቀባይነት እንዳይገኝ ብታደርጉ እኔን ያየህ ተቀጣ! ነውና አስቡበት….. እያልኩ ከአጼ ቲዎድሮስ ታሪክ ላይ በተዋስኳትና ስሟን ወደ ራሴ በቀየርኳት ስንኝ ልሰናበታችሁ….

ይህንን ሲሰማ ያጓራል ላመሉ
ማናትም ቢላችሁ አዜቧ ናት በሉ!

አዜብ ጌታቸው

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13694


No comments:

Post a Comment