Saturday, March 22, 2014

በሀገሩም ሆነ በስደት በሰላም ሰርቶ ለመኖር ያልታለው የኢትዬጵያ ህዝብ


በሀገሩም ሆነ በስደት በሰላም ሰርቶ ለመኖር  ያልታለው የኢትዬጵያ ህዝብ
ገሩም ሆነ በስደት በሰላም ሰርቶ ለመኖር  ያልታለው የኢትዬጵያ ህዝብ
March 22, 2014
ዳዊት ደመላሽ ( ኖርዌይ )

Madenate.dawit@gmail.com

ይህንን ዜና ያልሰማ  ኢትዬጵያዊ   ያለ አይመስለይም  ምን አልባት በጉዞ ላይ የነበራችሁ ወይንም በያዝነውና ባጋመስነው በፋሲካ ጾም በሱባኤ ላይ ሆናችው ከኮመፒውተሮቻችው የራቃችው ልትሆኑ ትችላላችው  በያዝነው ሳምንት ላይ ከወደ ኩዌት አንድ ልብ የሚሰብር ዜና በፌስ ቡክ እና በትዊተር የተመለከትነው ይህን ዜና እንደተመለከትኩ አንድ የማውቀው ጓደኛዬ ከሁለት ዓመት በፊት በኮንትራት ሄዶ ስለነበር በቀጥታ ወደ ጓደኛዬ  ስልኬን አንስቼ ነው ሀሎ በማለት በቅድሚያ የእግዜአብሄር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ በቀጥታ እሱ ያለበትን ሁኔታ ጠይቄው ቀጥታ ወደ ጉዳዩ ነው የገባውት  እኔስ በሰላም ወጥቼ ኤጄንሲዬ ቢሮ ሆኜ ነው የማወራክ በማለት የተፈጠረው  ነገር ከ ሀ እስከ ፐ በዝርዝ አጫወተኝ ። ወንጀሉን ፈጽማለች ስለተባለችውም ልጅም  በአሰሪዋ የተፈፀመባትን ኢሰብአዊ ድርጊት በደንብ አድርጐ አጫወተኝ እኔም ከአዳመጥኩት በኋላ ለራሴ እንዴት የሴት ልጅ እናት ሆና እንዲህ ዓይነት ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ነገርን ለመፈፀም  ተነሳሳች ካልኩኝ በኋላ አንድ ነገር ትዝ አለኝ አጥሩን ካልነቀነቁ  ይባል የለ መንግስት  ተብዬው ህዝቡ ቢደበደብ ቢሰቀል ቢታረደ ቢሞት ግድ እንደሌለው አሰሪዎቻቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገሪቷ ፖርላማ ትላንትና ከቀትር በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ተቀምጦ በኢትዬጵያውያኖች ላይ ብቻ አዋጅ በማውጣት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። ከኮንትራት ውጭ በስራ ላይ የሚገኙ ኢትዬጵያውያኖችን በሶስት ቀን ከሀገር እንዲወጡ የታዘዙ ሲሆን፣ በኮንትራት የመጡትን የቤት ሰራተኞች ኮንትራታቸው ባለቀ በ 24 ሰዓት ውስጥ እንዲወጡ የሚያስገድድ ነው ፣፣ የእኔን ወዳጅ ለስራ ያመጣው ኢትዬጵያዊ ኤጀንት በመሆኑ በእሱ በኩል የመጡትን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ቢሮው በመውሰድ ህይወታቸውን ሊታደግ ችላል፣፣ በዚህ አጋጣሚ እሱን ሳላመሰግነው አላልፍም ፣፣
ሰብሳቢ፥ ሰሚና አለሁላችሁ የሚሏቸውን ያጡ ኢትዬጵያውያን እህቶቻችን በየቤታችዉ በአሰርዎቻቸው ዕጣ እያወጡባቸዉ እያረዷቸው ነው፣፣  ውድ ኢትዬጵያውያኖች ለነዚህ ወገኖቻችን ድምፃችንን ልናሰማላቸው ይገባል መንግስት እንደሆን የለንም ፣፣በዛሬው እለት ልክ የመንፉዋ የሳውዲው ዓይነት አንድ ተብሎ ደውሉ ተደውላል፣፣  ኢትዬጵያውያን በብዛት ይኖሩበታል በሚባሉበት በአወሊ፣በደብሊ፤እና በጀሀራ በድምሩ 85 የሚሆኑ ኢትዬጵያውያኖችን በለበሱት በሌሊት ልብስ ፖሊስ ሃይሉን ጠንከር አድርጎ ለሊት በመምጣት ይዘዋቸዉ በቆሞጥ እየደበደቧቸዉ  በመኪና ጭነው ወስደዋቸዉ በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ ።ይህ ሁሉ ሲሆን ከዘበኛ እስከ አምባሳደር የአንድ ዘር ስብስብ ወደ ሆነው የኢትዬጵያ ኤምባሲ ስልክ ደውለዉ የይድረሱልን ጥሪ ቢያሰሙም ማንም አልደረሰላቸዉም፣፣ ስለ ጉዳዩ ምንም አይነት መግለጫ አልተሰጠም፥ የታሰሩትንም አልጠየቋቸዉም፣፣ እንዲሁም በአካል ወደ ኢምባሲው በመሄድ  እየደረሰባቸው ስላለዉ ችግር  አቤቱታ  ሊያቀርቡም ቢሞክሩም አማርኛን በደንብ አጣርቶ መናገር በማይችለው ዘበኛ ተባረዋል፣፣ ይህ ኤምባሲ ኢትዬጵያውያኖችን ለመታደግ የቆመ ሳይሆን የህውሀት ኢህአዴግ መፈንጫና ለይስሙላ የቆመ ተቋም ነዉ፣፣ ይህ ግፍ፥ በደልና ስቃይ በኢትዮጵያዉያን ላይ ብቻ ለምን አነጣጠረ ? በአረቡም ዓለም ሆነ በተቀሩትም የዓማችን ክፍሎች በኢትዮጵዉያን ላይ ለምደርሰዉ ስቃይ ዋነኛዉ መንስኤ ለወገኑና ለህዝቡ ተቆርቋሪ መንግስት ስለሌን ነው፣፣ የይስሙላዉ ጠቅላይ ሚንስቴር ሀይለማርያም ጥሪ ቢደረግለትም እስከአሁን መልስ አልሰጠም ። ይህንን የወንበዴ ቡድን ከነሰንኮፉ ነቅለን በአንድነት ክንዳችንን አጠንክረን ልዩነታችንን ትተን አንድ በመሆን ልናስወግደው ይገባል፣፣
ቀጣዪ ጽሁፌ እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት።
ዳዊት ደመላሽ ኖርዌይ
ኢትዬጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!


https://www.maledatimes.com/?p=15904    

http://www.assimba.org/Articles/Beselam_Serto_Menor_Yaltadele_YEthiopiaHizb.pdf  

http://africaim.com/hawasa-delay-reduction-and-capacity-enhancement-program/

    http://abbaymedia.com/amharic/2014/03/22/%E1%89%A0%E1%88%80%E1%8C%88%E1%88%A9%E1%88%9D-%E1%88%86%E1%8A%90-%E1%89%A0%E1%88%B5%E1%8B%B0%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9D-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%89%B6-%E1%88%88%E1%88%98%E1%8A%96/                                                                        

No comments:

Post a Comment