Thursday, March 6, 2014

(ሰበር ዜና) መርዝ ተሰጥቷቸዋል የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ አረፉ

(-ሐበሻ) መርዝ ተሰጥቷቸው ነው ለዚህ የበቁት የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ለህክምና ብዙ ገንዘብ ወጣባቸው በሚል ሕገወጥ በሆነ መንገድ ከስልጣናቸው እርሳቸው ባላወቁበት በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተደርጎ የተነገረባቸው የኦሮሚያው ክልል ፕረዚዳንት ኦቦ አለማየሁ አቶምሳ በተሰጣቸው የተመረዘ ምግብ ምክንያት የጀመራቸው በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ጸንቶ በተደጋጋሚ በተለያዩ ሃገራት ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ግን በባንኮክ ታይላድ ለህክምና በሄዱበት ሆስፒታል ሕይወታቸው አልፏል።

45 ዓመታቸው በታይላንድ ባንኮክ ሕይወታቸው ያለፈው ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ በምን ምክንያት የተመረዘ ምግብ እንደተሰጣቸው ባይታወቅም ከርሳቸው ጋር ምግቡን በልቶ የነበረ ግለሰብም እስካሁን በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ለዘ-ሐበሻ ቅርብ የሆኑ የኦነግ የመረጃ ምንጮችኦህዴድን የድሮው ኦህዴድ እንዳይሆን ሊያደርጉ የሚችሉ ሰው ስላልነበሩ በሕወሓቶች መርዝ እንዲሰጣቸው ተደርጓልየሚል አመለካከት ያላቸው መሆኑን ገልጸው ሕወሓት አቶ ዓለማየሁን ቀጠፋቸው ሲሉ ይተቻሉ

ከየካቲት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በባንኮክ ህክምና ላይ የከረሙት በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ 1961 . ተወለዱት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ሕይወታቸው በእንዲህ ያለ ሴራ ማረፉ በኢሕአዴጎች መካከል አለመተማመንን ሊፈጥር እንደሚችል የተለያዩ የፖለቲካ ታዛቢዎች እየገለጹ ነው።
የኦህዴድ/ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አቶ ዓለማየሁንላለፉት 24 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ እና መላው የአገሪቱ ህዝቦች ዛሬ ለደረሱበት የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ተጠቃሚነት እንዲበቁ በቁርጠኝነት የታገሉ ነባር ታጋይ ነበሩካለ በኋላ 1981 ዓመተ ምህረት የደርግን ስርዓት ለመገርሰስ ሲካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል መቀላቀላቸውን፣ 1988 እስከ 1994 ድረስም የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት እና የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ማገልገላቸውን፣ 2002 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነ 2003 . ጀምሮ ደግሞ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር መሆናቸውን ጠቅሷል። ሆኖም ግን ድርጅቱ እንደተጠበቀው አቶ አለማየሁ በተመረዘ ምግብ መሞታቸውን ከሴራው በስተጀርባ ማን እንዳለ ያስቀመጠው ነገር አለመኖሩን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ለዘ-ሐበሻ በደረሱ መረጃዎች ቀጣዩ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት / አስቴር ማሞ ይሆናሉ የሚለው ግምት ሚዛን እየደፋ ነው።

 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13390

No comments:

Post a Comment