Monday, October 12, 2015

ለማይቀረው እና ለመጨረሻው ትግል ከዚህ ፍሽስት ከወያኔ አገዛዝ ጋር ለሚደረገው ትንቅንቅ እራሳችንን በተገቢው መንገድ እናዘጋጅ !!!

ለሚደረገው ትንቅንቅ እራሳችንን በተገቢው መንገድ እናዘጋጅ የምልበት ምክንያት በርካታ እድሎችን ወይንም አጋጣሚዎችን በእኛ የዝግጅት ማነስ እንዲሁም ሁኔታዎችን አስቀድሞ ፖለቲካዊ ትንበያ ወይንም ትንተና ተሰጥቶ በዛላይ ተንተርሶ ለዛ የሚሆን ተመጣጣኝ ዝግጅት ባለመደረጉ የተገኙት ወርቃማ አጋጣሚዎች በሙሉ እንዲሁ እንደዋዛ አሳልፈናቸዋል:: ስለዚህም ታሪካዊ ጠላታችን ይሄንን እድል በአግባቡ ተጠቅሞ እንደ እባብ አፈር ልሰው ያሉባቸውን ችግሮች ቁጭብለው ለማስተካከል የማገገምያ ግዜ በእኛ ደካማነት ስላገኙ በመልሶ ማጥቃት የፈሪ ዱላቸውን አሳረፉብን::

እንደዛም ሆኖ በተፈጠረውም ችግር (ከባድ ምት) በቶሎ ማገገም ስላልተቻለ ገሚሱን ለስደት እኩሌታ ውን በአገር ውስጥ ሆነው በመሰባሰብ እንደገና በጥቂቱ ለማንሰራራት ሞክረው አዳዲስ እና ነባር የፖለቲካ ስሞችን በመጠቀምም እንደ አዲስ አባሎቻቸውን በመመዝገብ በተገኘችው ትናንሽ ቀዳዳዎችን ተጠቅመው የፓርቲያቸውን አላማ ለሕዝብ በማስተዋወቅ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ(የተሳካም ያልተሳካም)ፓርቲዎቻቸውን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮላቸው ነበር። ሕብረተሰብ በሚገባ የተቀበላቸውን ለአብነት ያህል ለመጥቀስ አንድነት፣መኢአድ እና ሰማያዊ በመባል ይታወቁ ነበር:: ነበር ያልኩበት ምክንያት ከእነዚህ ከላይ ከጠቀስኩዋቸው ሰዎስቱ ድርጅቶች(የፖለቲካ ፓርቲዎች) መካከል በጠራራ ጸሀይ ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ ቅንጅት ላይ የደረሰው በተመሳሳይ ሁኔታ በአንድነት እና መኢአድ ደርሶ አየነው ማነህ ባለሳምንት አትሉም? ከላይ በጥቅሉ ለማስቀመጥ እንደሞከርኩት በቢጫ ካርድ ሆናቹ ለተቀመጣችሁቱ አሁን ገዢው ፓርቲ ከሚያሳድርባቹ ጫና በመነሳት የተወሰኑትን አባል ወይንም አመራር በማሰር በማስፈራራት በናንተው መካከል ልዩነት በመፍጠር እናንተንም እንደ ሌሎቹ ችግር ውስጥ ሊከቱዋቹ ይችላሉ ወይንም ጠንካራ አመራሮችን በመለየት የተለያየ ታፔላ በመለጠፍ አገዛዙ የተለመደ ጨዋታውን ሊጫወት ይችል ይሆናል::

ስለዚም ችግሩ ደርሶ ጋቢ ተከናንባቹ ሶፋላይ ከመተኛታቹ በፊት አንድ በአንድ ሊመጡ ይችላሉ ብላቹ ያሰባችሁትን ችግሮች ሳትንቁ ከነመፍትሄው በማስቀመጥ ፣ ተተኪ አመራሮችን በማዘጋጀት ፣ ትግሉ እንዲቀጥል የበኩላችሁን ማድረግ ይጠበቅባቹኋል። በሀገር ውስጥ የሚደረገው ትግል በወያኔ የፈሪ በትር ለስደት የተዳረገውን ጨምሮ የለም ይሄንን የፋሽስት ስርአት ለማስወገድ ትክክለኛው አማራጭ በተጠናከረ በሁለገብ ትግል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ማስወገድ ነው በሚል በጠነከረ መንፈስ የትግል አቅጣጫ በማስቀመጥ በተቁዋቋመ በአጭር ግዜ በቀላሉ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዬጵያኖችን እና ትውልደ ኢትዬጵያኖችን በማስተባበር እና እንደ አለት የጠነከረ ሕዝባዊ መሰረት የያዘ ድርጅታዊ ተክለ ቁመና በመያዝ ወያኔ ከዚህ ቀደም እንደልብ ይፈነጭበት የነበረውን ይውጩን ማህበረሰብ ከጫፍ እስከጫፍ በማነቃነቅ በተጠናከረ ተቃውሞ እዛው ባለበት በሀገር ቤት ብቻ እንዲወሰኑ(እንዲያፈገፍጉ) አድርጎዋቸዋል::

በዚህም ሳያበቃ የትግል አድማሱን በማስፋት ጠንካራ ሕዝባዊ መሰረት ያለውን የውጭ እምቢተኝነት በማቋቋም በሂደትም በአላማ ተቀራራቢ ከሆነው በትጥቅ ትግሉም የካበተ ልምድ ካለው እና ከወያኔ ሰራዊት ጋር ለበርካታ ግዜ በመግጠም አንጸባራቂ ገድሎችን ከተጎናጸፈው ድርጅት ከአርበኞች ግንባር ጋር በመዋሀድ ትግሉን ወደላቀ ደረጃ በማሳደግ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንዲሉ ፣ ሁለቱም ድርጅቶች የተናጠል ህልውናቸውን በማክሰም የአርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄን መስርተው ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋርም በግንባር ወይንም በጥምረት እና ትብብር በማድረግ አብረው እንደሚሰሩ ከኢትዬጵያ ሳተላይት ቴሌቨዥን ጋዜጠኛ ከሲሳይ አጌና ጋር በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል:: የአርበኞች ግንቦት7 ዋና ሊቀመንበር ዶክተር ብርሀኑ ነጋም የሰጡትን ቃለ ምልልስ ላዳመጠ ሰው፣ ግንቦት7 ዋና ሊቀመንበር ዶክተር ብርሀኑ ነጋም የሰጡትን ቃለ ምልልስ ላዳመጠ ሰው፣ የድርጅቱን መግለጫዎች ላነበበ እና በተጨማሪም የኤርትራው ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቄን በግልጽ በኤርትራ በትጥቅ ትግል የሚቀሳቀሱትን ድርጅቶችን እንደሚረዱ ማሳወቃቸውን ለተመለከተ እና በተለይም በራስ መተማመናቸውን ላስተዋለ ሰው ታጋዬቻችን በከፍተኛ ሁናቴ ላይ እንደደረሱ ለማወቅ ጠንቁዋይ መሆን አይጠይቅም:: የወያኔም ግብአተ መሬት መፈጸሚያው እንደተቃረበ ለማንም ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስላል በውጩ የትግል እንቅስቃሴ በዚሁ ላይ ልግታና ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስ ።

ለማይቀረው እና ለመጨረሻው ትግል ከዚህ ፍሽስት ከወያኔ አገዛዝ ጋር ለሚደረገው ትንቅንቅ እራሳችንን በተገቢው መንገድ እናዘጋጅ የሚለው መልእክቴ በቀጥታ ወይም በዋነኛነት የሚጠልዋትን ሐገር በሚገዙት ጭራቆች ለተማረራቹ፣ በስቃይ እና በመከራ ውስጥ ላላችሁቱ ወገኖቼ እንባችሁን ሊያብሱ የቆረጡ የግፍ አገዛዙን ወደ መቀመቅ ሊከቱ ተዘጋጅተው ይጠብቁሀል እና ስለዚህም የሀገሬ ሰዎች አቅም ያላቹ ትግሉን በቀጥታ ያሉበት ድረስ በመሄድ መቀላቀል ይገባል እያልኩኝ ከላይ የጠቀስኩትን አማራጮች ለመጠቀም እድሉ ላልገጠማቹ የጽሁፌ ማጠቃለያ ላይ ላስቀምጠው ። በመጨረሻም መሳርያ አንስተው የትግል ጥሪ አቅርበውላቹ ነገር ግን በአንዳንድ ምክንያት ትግሉን መቀላቀል ላቃታቹ ሰዎች በአካባቢያቹ ሆናቹ ከምትተማመኑት ሰዎች ጋር በመሆን ተቡዋድናቹ ህዝባዊ እንቢተኝነት ሲነሳ ተገቢውን ተሳትፎ ማድረግ በተጠናከረ እና አንድ ወጥ በሆነ በተባበረ ትግል አሁን የተገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ወያኔን የስንግ ይዞ እራሱ አርቆ በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ግብአተ መሬቱን ለመፈጸም በቆራጥነት መዘጋጀት ያስፈልጋል ስል ጽሁፌን በዚሁ እቋጫለሁኝ ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ድል ለሠፊው ሕዝብ

ሰለሞን ነኝ ከኖርዌ,በርገን ቸር ይግጠመን

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47349

No comments:

Post a Comment