Sunday, August 14, 2016

ግራ የገባው ኢህአዴግ ለአዲስ አበባ ወጣቶች በነፍስ ወከፍ አስር ሺህ ብድር ሊሰጥ ነው።

በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በተነሣው ህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት መቆሚያ መቀመጫ ያጣው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የአዲስ አበባ ወጣትን ከጎኑ ለማሰለፍ ያስችለው ዘንድ በማሰብ የአዲስ አበባን ወጣት ለሶስት በማደራጀት ለየቡድኑ 30 ሺህ ብር በነፍስ ወከፍ 10 ሺህ ለማበደር መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል።

አርብ እለት አስቸኳይ ስብሰባ የተሰበሰበው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት በአቶ ተስፋይ ኪዳነማሪያም በኩል ለምክር ቤቱ የቀረበውን ሐሳብ የተቀበለው ምክር ቤቱ ገንዘቡን በአዲስ አበባ ከሚገኙ የኢህአዴግ ደጋፊ ባለሐብቶች እንዲሰበሰብ ያዘዘ ሲሆን ይህንንም ጉዳይ የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በኃላፊነት ወስዶ እንዲመራው የተወሰነ ሲሆን የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ደግሞ ከነገው ሰኞ ጀምሮ ወጣቶችን በማሳመን የማደራጀት ሥራ እንዲሠራ ወጣቶች በየስብሰባው የሚያነሱትን ነጥብ ትክክለኛ መሆኑን በመቀበል ይቅርታ በመጠየቅ ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ ወጣት ጋር በጋራ በመስራት የአዲስ አበባን ወጣት ተጠቃሚ ለማድረግ ማሰቡን መግለፅ የአዲስ አበባ ወጣትን ማሳመን እንዳለባቸው የወሰነ ሲሆን ይህ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ ግን አዲስ አበባ ላይ ትንሽ ኮሽታ ከተነሳ ኢህአዴግ የማይጣው ችግር ውስጥ እንደሚገባ አቶ ተስፋይ ኪዳነማርያም ለምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።

ይህ የአዲስ አበባን ወጣት በገንዘብ አታልዬ እይዛለሁ የሚለው ፖለቲካዊ ቁማር የተበላበት መሆኑን ሁሉም የኢህአዴግ አመራሮች ሊያውቁት ይገባል። እኔም ሆንኩኝ ሌሎች የአዲስ አበባ ልጆች የምንጠይቃቸው ዋና ዋና አምስት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።

1,
ከአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት መካከል አንድም የአዲስ አበባ ተወላጅ የለም በመሆኑም እንዴት የአዲስ አበባ ምክርቤት የእኛ የአዲስ አበባ ወጣቶችን መወከል ይችላል?

2,
ምንም እንኳን የተባለሸ ምክርቤት ቢሆንም በፌዴሬሽን ምክርቤት ውስጥ አዲስ አበባ አንድም ተወካይ የላትም ይህ ጉዳይ የአዲስ አበባ ወጣቶችን መናቅ አይደለም ወይ?

3,
የአዲስ አበባ ተወላጆች በተወለድንበት ከተማ ስደተኞች ስንሆን ጥቂት ከሌላ ክልል የመጡ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከተማችንን ቀምተውናል ይህ ሊቆም ይገባዋል? አዲስ አበባ ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ከተማ መሆን አለባት።

4,
በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በአማራውና በኦሮሞው ህዝብ ላይ የሚደረገው ማንኛውም አይነት ጅምላ ግድያ የኛም ሞት በመሆኑ በአማራውና በኦሮሞው ላይ የሚካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ ሊቆም ይገባል።

5,
ኢህአዴግ የአዲስ አበባና የተቀረው ኢትዮጵያዊያንን የመምራት ምንም አይነት ሞራላዊም ሆነ የእውቀት ክህሎት ስለሌለው በአስቸኳይ ሥልጣኑን ለሕዝቡ ያስርክብ።።።።።

በመሆኑም ኢህአዴግ እስከዛሬ በአዲስ አበባና በተቀረው ኢትዮጵያዊ ላይ የፈፀመውን ግፍ ለመቀጠል በማሰብ የአዲስ አበባን ወጣት በገንዘብ በመደለል ለመያዝ መሞከር የማያዋጣና ለአዲስ አበባ ህዝብ ያለውን ንቀት የሚያሳይ በመሆኑም ሁላችንም የአዲስ አበባ ወጣቶች የምናወግዘው ነው።

http://www.mereja.com/amharic/509028

No comments:

Post a Comment