Wednesday, August 31, 2016

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ጎንደርና ጎጃምን እንደሶሪያ ሊጠፋ ተዘጋጅቷል – ታንኮች ጭምር ከነቀምት ቡሬ ጎጃም እየተጓዙ ነው

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አማራውን በተለይም ጎጃም እና ጎንደርን እንደ ሶሪያና ሕዝቧ ሊያወድማት እየተዘጋጀ ነው:: ዛሬ የሕወሃት ተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመከላከያ ሰራዊቱ አማራውን እንዲያጠፋ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ በደሴ መስመር ብረት ለበስ መኪናዎችና የጦር መሳሪያዎች ወደ ጎጃም እና ጎንደር እየተጓዙ መሆናቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል::

እንደ ምንጮች ዘገባ ጨጨሆ ላይ እነዚህን በደሴ መንገድ እየተጋዙ ያሉትን የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮችን ህዝብ እንዲያስቆማቸው ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ምን ላይ እንደደረሰ ግን -ሐበሻ ለማወቅ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

በሌላ በኩልም ከነቀምት ወደ ቡሬ ጎጃም የጦር ታንኮች እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል:: የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሆነ በጎጃም እና ጎንደር ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ እልቂት ለማድረስ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ቆርጦ በመነሳቱ ታንኮችን ጭምር እያጋጋዘ ነው::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/65064

No comments:

Post a Comment