አገር አድን ዘመቻ
የታሪክ ባለአደራ ነንና ሀገራችን ሊበታትኗት ከተነሱት ከሃዲዎችና ጎጠኛ ኃይሎች ሴራ በድል ለመወጣት ቆርጦ በመነሳት ኢሕአፓ እነሆ የሀገራችን ሉአላዊነት እንዳይደፈር መድብለ ፓርቲ እውን እንዲሆን፣ ሕዝባዊ መንግሥት እንዲቋቋም፣ የእምነትና የሃሳብ ነጻነት እንዲከበር፣ ኢትዮጵያዊያን በሰደት እንዳይሰቃዩና ከሃገራቸው እንዳይፈናቀሉ፣ ሕዝቡ ማብቂያ ለሌለው ጦርነት ማገዶ እንዳይሆን፣ ገበሬው ለሚያርሰው መሬት ባለቤትነት መብቱ እንዲከበር በመታገልና በማታገል ላይ ይገኛል። ትግሉን ለማጠናከርና ውጤት እንዲያፈራ ለማድረግ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከመቼውም በበለጠ በኢሕአፓ ጎን በመሰለፍ ሁለንተናዊ ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ሁለገቡን ትግል ለማፋፋምና አገር አጥፊውን ወያኔ ላንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ ገንዘብ አንዱ መሳሪያ ነው፡፡ ያለገንዘብ የሚገባደድ ትልምና እቅድ የለም። ኢሕአፓ ሁለገብ ትግሉን ለማፋፋምና ለማጠናከር ሀገር አድን ዘመቻ ግብረ ኃይል አቋቋሞ በዚህ ግብረ ኃይል አማካይነት የገንዘብ ድጋፍና እርዳታ በያካባቢው እያሰባሰበ ይገኛል። የሀገራችን ችግር መፍትሄ ፈላጊዎች እኛው ኢትዮጵያውያን ብቻ መሆናችንን ማመን ጥሪውን መቀበልና የተቻለንን ሁሉ በማድረግ አገራዊ ግዴታችንን መወጣት አማራጭ የሌለው ግዴታችን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቱን ተገፎ፣ በመላ ሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና የኑሮ ዋስትና ጠፍቶ፣ የሥራ እድልና የማህበራዊ ኑሮው እያሽቆለቆለ በሄደበት፣ ከድንቁርና፣ ከድህነት ያልተላቀቀው ወገናችን ስቃይ እየባሰ በሚታይበት፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች ለጎጠኞች ብቻ በሆነበት፣ ፍትህና እኩልነት በጠፋበት ማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ ይህን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል ትግሉን የድል ተስፋ ለማድረግ ደጋግሞ ኢሕአፓ ጥሪውን ያቀርባል።
ሕዝባችን ከዚህ ከጎጠኛ ወያኔ ቡድን ለመላቀቅ እየከፈለ ያለውን መሰዋዕትነት ከንቱ ሆኖ እንዳይቀርና የታሪክም ተጠያቂዎች እንዳንሆን በአንድነት በመነሳት ትግሉን በተቻለን መጠን እናጠናክረው። “ድር ቢያብር አንበሳን ያስር”
እንደሚባለው ሁላችን ተባብረን በአንድነት ከተነሳን ሀገራችን ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወያኔ ጎጠኛ ቡድን
እናላቅቃታለን
በመጨረሻም የሀገራችን ሉአላዊነት፣ የሕዝቧ የሥልጣን ምንጭነት በሕግ የሚረጋገጥበት፣ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ
የሕዝብና የሀገር አንድነት የሚጠበቅበት፣ የእምነትና የሃሳብ ነፃነት የሚከበርበት፣ በሕዝቡ ነፃና ርቱአዊ ምርጫ የሚካሄድበት ለማድረግ የማንኛውም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሃላፊነትና ግዴታ እንዳለበት በማመን በሀገራችን ላይ አንጃቦ ያለውን አደጋ ለመቋቋም ሁላችንም በአንድነት በመነሳት የገንዘብ እርዳታ በማድረግ ትግሉን ለድል እንድናበቃው እነሆ ኢሕአፓ ጥሪውን ሳይሰለች ደጋግሞ ያቀርባል።
የምታደርጉትን የገንዘብ እርዳታ ከታች ከተጠቀሱት መንገዶች ውስጥ በሚያመቻችሁ መሆናችሁን በትህትና እንገልጻለን፡
1. በአካባቢያችሁ ላለ የኢሕአፓ አገር አድን ዘመቻ ግብረሃይል አባላት በቀጥታ በመስጠት
2. ለ EPRP ብሎ check/money order በEPRP P.O. Box 73337 Washington DC 20056 በመላክ
ለበለጠ መረጃ: – 202- 291-4217 ይደውሉ ወይም በ espic@aol.com ኢሜል አድራሻ ይጻፉ
ኢትዮጵያ በታጋይ ልጆችዋ ነፃ ትወጣለች
የኢሕአፓ አገር አድን ዘመቻ ግብረሃይል
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
ETHIOPIAN PEOPLE’S REVOLUTIONARY PARTY (EPRP)
Posted By.Dawit Demelash
No comments:
Post a Comment