Saturday, April 20, 2013

ዜና በጨዋታ፤ …አማራ ኦሮሞ እስላም ክርስቲያኑ… ባንድ ላይ ተባብረው በ…ያዲግ ጨከኑ

  

524625_10151537859584373_1860470982_nየቃላት መፍቻ… “…ያዲግ” የተባለው ኢህአዴግ በትክክል መጥራት ሲያቅተን ነው አሉ…!
“ኢህአዴግ እና ኢጣሊያን ዋነኛ የሚታወቁበት የአገዛዝ ስልት ከፋፍሎ የመግዛት ስልት ነው፡፡” እያሉ ምሁራኖች ይተነትናሉ፡፡ እኛም ኢህአዴግ ችርቻሮ ትወዳለች ብለን ብዙ ጊዜ ተናግረናል፡፡ በተደጋጋሚ እንዳየነው …ያዲግ ስታጠቃ እየነጠለች ነው፡፡ ሙስሊሙን ለብቻ፣ ክርስቲያኑን ለብቻ፣ ቆለኛውን ለብቻ፣ ደገኛውን ለብቻ፣ አማራውን ለብቻ ኦሮሞውን ለብቻ…
ታድያ ከሆነ ጊዜ በኋላ ይሄ ችርቻሮ ብዙ ያዋጣ አይመስለኝም፡፡ ክርስቲያኑ በሙስሊሙ ጥቃት አብሮ “ተክቢር” ሲል አሮሞው በአማራው ጥቃት አርማውን ይዞ “አሌሊ…” ሲል አማራው በኦሮሞው ጥቃት “ዘራፍ ወንዱ” ብሎ ሲነሳ እያየን ነው፡፡ … ይቺን ነው መሸሽ አሉ አብዬ መሸሻ ብለን እንቀጥላለን…
ዛሬ ሚያዝያ 12/2005 ዓ.ም በኖርዌይ ወይዘሮ መብራት በየነ የሚመሩት “የወዲህ በሉ” ቡድን ከስደተኞች ብር ወዲህ በሉ ለማለት ስብሰባ ጠርቶ ነበር፡፡ በስብሰባው በርካታ ኢትዮጵያውያን ቢገኙም፤ ለመንግስት ገንዘብ አለሰጡም… ለተወካዮቹ ሃርድ ሰጥተው አባረሯቸው እንጂ!
ኢትዮጵያውያኑ ያለ ኮከብ የሚያበራውን የኢትዮጵያ ባንዲራ እና መንግስት አሸባሪ የሚለው የኦነግንአርማ የያዙ ሲሆን ከያዙት መፈክር ውስጥ ደግሞ በቤኒሻንጉል ክልል የተደረገውን የአማርኛ ተናጋሪዎችን መባረር፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረገው የእምነት ነፃነት ግፊያ የሚያወግዙ ይገኙበታል፡፡ “ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” ም ተብሏል፡፡
ይህንን ሁሉ ውግዘት ቁጭ ብለው ሲኮመኩሙ የቆዩት ዲፕሎማት ወይዘሮም ምንም አማራጭ አለነበራቸውም … ካላችሁማ እመለሳለሁ እንጂ ምን አደርጋለሁ… ብለው ባዶ ቦርሳቸውን ሲመለሱ አልደብቃችሁም አንጀቴን በልተውታል፡፡
ዜናውን ከማብቃቴ በፊት ርዕሳችንን እንደግማታለን
አማራ ኦሮሞ እስላም ክርስቲያኑ
ባንድ ላይ ተባብረው በ…ያዲግ ጨከኑ… ኑ ኑ  ኑ… ብለንም የገደል ማሚቶ እናበጅለታለን!



    
    Posted By.Dawit Demelash

No comments:

Post a Comment