Thursday, April 18, 2013

ታላቋ ትግራይን” የመመስረት የ 21 ዓመታት ጉዞ



በ1968 ዓ ም ባወጣው ማንፌስቶ ህወሓት “ታላቋን ትግራይ” ከኢትዮጵያ ገንጥሎ የራሷን ሪፐብሊክ እንድትመሠረት የማድረግ ግብ ነድፎ እንደነበር የግንባሩ መስራች አባላትThe 1976 TPLF Manifesto TPLF’s “Republic of Greater Tigray” የመሰከሩት ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያዊነቱ በሚኮራው የትግራይ ሕዝብ ማንፌስቶው ተቀባይነት እንደማያገኝ የሕወሓት መሪዎች ሲረዱ ትተነዋል ብለው ቢያውጁም እነመለስና ስብሀት ግን ለ 21 ዓመታት ሲፈፅሙት የኖሩት ያን ግብ ለማሳካት ነበር። ዋና ዋናወቹን ክንውኖች እንመልከት፦
1ኛ. ህወሓት ጫካ እያለ የሰራውን “የታላቋን ትግራይ” ካርታ እውን ለማድረግ ከጎንደርና ከወሎ ሰፋፊ ለም መሬቶችን በማንአለብኝነት በመውሰድ ወደትግራይ ከለለ። ኢትዮጵያን በዘር ሸነሸነ፤ ኢትዮጵያዊያንን በዘር በመከፋፈል ስለ አንድነታቸው ሳይሆን ስለልዩነታቸው እያሰቡ እንዳይተባበሩ ለማድረግ ተጣጣረ፤ በኢትዮጵያዊነት ላይም ዘመተ።
2ኛ. ሕወሓት ባረቀቀው አዲስ ህገ መንግስት “የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል ድረስ” የሚል አንቀፅ አስገባ፤ በአንቀፅ 39 ላይ ተቃውሞ ሲነሳ መለስ ንዴቱን መቆጣጠር ተስኖት በቁጣ መልስ ይሰጥ እንደነበር እናስታውሳለን።
3ኛ. በትግራይ ውስጥ ታላላቅ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፤ ይህ ዕቅድ በመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት በአብዛኛው የተከናወነ ሲሆን ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ በስፋት ሲሰራ ቆይቷል። በሁመራ የሚመረተው ጥጥ ለአድዋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃነት ሲያገለግል ሰሊጡ ደግሞ ወደውጭ እየተላከ የወያኔ መሪዎችን የዶላር ክምችት በማድለብ ላይ ይገኛል። ሞሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ደግሞ ምርቱን ወደ ሱዳን ይልካል፤ መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ በበኩሉ የተሽከርካሪ ገበያውን ለመቆጣጠር እየተጋ ይገኛል።
4ኛ. ሁለቱን ታላላቅ ጎሣዎች ማለትም ኦሮሞውንና አማራውን ማዳከም፤ ሕወሓት ገና ጫካ እያለ ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለመበታተን በአማራው ሕዝብና በኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት ላይ መዝመት እንዳለበት የነደፈው ግብ እንደነበርና አሁንም እየተገበረው እንዳለ ወንድማችን አቶ ገብረመድህን አርአያ በየጊዜው ሲያስታውሰን ቆይቷል። ባለፉት 21 ዓመታት ወያኔ በተለይ የአማራ ተወላጆችን ሲረሽን፣ በገደል ሲወረውር፣ ከቤት ንብረታቸው ሲያፈናቅል ኖሯል፤ አሁንም ይህን እኩይ ዓላማውን ቀጥሎበታል። እጅግ በርካታ የኦሮሞ ምሁራንና ተማሪዎችን መግደል፣ በአሸባሪነት መክሰስና በእስር ቤት ማጎሩንም ቀጥሏል።
5ኛ. ትግራይን በኃይል አቅርቦት ራሷን ማስቻል፣ በመጀመሪያ ወያኔ ጭስ አባይ ቁጥር 2 ብሎ ከሰራው የኃይል ማመንጫ የሚነሳ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እስከ ትግራይ ዘረጋ፤ የአባይ ውሀ የተጠለፈው ፏፏቴው ከመድረሱ በፊት ስለሆነ ወደጭስ አባይ የሚጎርፈው ሀገር ጎብኝ በእጅጉ ቀነሰ፤ ከዚያም የተከዜን ኃይል ማመንጫ ገነባ፤ አሁን ደግሞ በመቀሌ አካባቢ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታ በፈረንሳይ ኩባንያ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
6ኛ. ትግራይ የራሷ ወደብ እንዲኖራት ማድረግና ከወደብ የሚያገናኛት የባቡር ሀዲድ መዘርጋት፣ ከጥቂት ወራት በፊት አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ በታጁራ ወደብ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው ተመልሰዋል፤ በመለስ ዕቅድ መሠረት ያ ወደብ በቀጥታ በባቡር መስመር የሚገናኘው ከትግራይ ጋር ነው።
7ኛ ትግራይን በማዕድን ሀብት ማበልፀግ፣ እስካሁን ድረስ በትግራይ የማዕድን ፍለጋ በስፋት ሲካሄድ ቆይቷል፤ በቅርቡ የተገኘው የወርቅ ማዕድን ለወያኔ ተስፋ ሰጪ ሆኗል፤ በግዙፉ የኤፈርት ኩባንያ የሚካሄዱ የማዕድን ፍለጋ ፕሮጀክቶች እየተበራከቱ ነው።
8ኛ. የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በሕወሓት ኩባንያዎች ቁጥጥር ሥር ማድረግ፤ ባለፉት 21 ዓመታት ከሕወሓት ጋር ንክኪ የሌላቸውን ነጋዴዎች ከገበያ በማስወጣት ወያኔ የሀገር ውስጡንና የውጭውን ንግድ ተቆጣጥሯል። በይፋ ጤፍ ወደውጭ እንዳይላክ ቢያውጅም የራሱ ነጋዴዎች በኮንትሮባንድ ጤፍ ወደውጭ እየላኩ የጤፍ ዋጋ እጅግ እንዲንር አድርገዋል፤ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በልቶ ማደር እያቃተው ነው።
ስለዚህ ወያኔ እስከቻለ ድረስ በስልጣን ላይ ተቀምጦ ኢትዮጵያን ለመግዛት፣ ከስልጣን ቢባረር ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል መሠረቱን ጥሎ አጠናቋል። በዘረኝነት መርዝ እስከእለተሞቱ ተለክፎ የነበረው የመለስ “ራዕይ” ይህ ነበር፦ ኢትዮጵያን መበታተን፣ አማራውን ማዳከምና ማጥፋት፣ ሌሎች ብሔረሰቦችን እርስ በእርስ ማናከስ፣ “ታላቋ
ትግራይ” ን መመሠረት። ይህን የዘረኝነትና ፀረ ኢትዮጵያዊነት “ራዕይ” ነው እናስቀጥላለን የሚባለው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

    Posted By.Dawit Demelash 

No comments:

Post a Comment