ማፈናቀሉ እስከመቼ ?
ብስራት ወልደሚካኤል
ህወሓት/ኢህአዴግ በህይወቱ ከሚፈራውና ከሚጠላው ነገር አንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ ማየትና መስማት ነው፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ አባላት በባህሪያቸው በውሸት፣ በተንኮልና በዕውቀት አስተሳሰብ አድማስ ደካማ ስለሆኑ የዜጎችን አንድነትና ብሔራዊነት ስሜትን አጥብቀው ይጠላሉ፤ ይህንንም በማሰራጨት የማሃይሞችን ርካሽ ፖለቲካ አራምደውበታል፣እያራመዱም ይገኛሉ፡፡ የዚህ ዋነኛ ተባባሪ ደግሞ በህወሓት የሚነዱት ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የሀገሪቱን አንድነትና ደህንነት አደጋ ላይ በመጣላቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዝምታ ሊያልፍ ስለማይገባ እስካሁን ለፈፀሙት ሁሉ አስፈላጊውን ሰነድ በእጃችን ማስገባት፣ ድርጊቱን የፈፀሙትንና ተባባሪዎቹን ስም ዝርዝር ከነ ሙሉ አድራሻቸው መያዝ፣ ጉዳት የደረሰባቸውና ሚደርስባቸው ዜጎችን መርዳትና መንከባከብ እንዲሁም ወንጀለኞችን በተለያዩ ማኀበራዊ ሚዲያዎች(Facebook, blog, twitter,….) ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በማጋለጥ ለህግ እንዲቀርቡና ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን የውዴታ ግዴታ መሆን ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ዛሬ በሰፊው የአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ በህወሓት/ኢህአዴግ እየደረሰ ያለው ግፍ በተመሳሳይ መልኩ ነገ በሌሎችም ላይ ይደርሳል፤ ከዚህ በፊትም ደርሷልና፡፡
ስለዚህ በቅርቡ በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ለረጅም ጊዜ ሀብት ንብረት አፍርተውና ተዋልደው የኖሩ የአማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀል ስራ የተሰራውን መረጃ በሚመለከት ፣
አሁን ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ለሞት.ለስቃይና ለመከራ እንዲደረጉ የተደረገበትን ምክንያት በዝርዝር በማጣርት መረጃውን ይፋ በማድረግ ሁሉም ዜጋ በጋራ ሊያወግዝና የተፈናቀሉትም ወደነበሩበት ስፍራ በክብር እንዲመለሱ ለማድረግ በሀግር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለዚህም በሀገር ውስጥ ያሉ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ወደስፍራው በመሄድ አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ መረጃውን ለህዝብ ይፋ ማድረግና የድርጊቱ ፈፃሚዎችም በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ፣
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ይህን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ በማጋለጥ ለኢህአዴግ የሚደረገው የለጋሾች ድጋፍ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚውል ማረጋገጥና ድጋፉ እንዲቋረጥ ከማድረግ በተጨማሪ መረጃውን ለሚሰበስቡ ሀገር ውስጥ ላሉ ሀገር ወዳድ ሰባዓዊ ባለሙያዎች የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የሙያ ድጋፍ ማድረግ፣
በተለይ ወንጀሉ የሚፈፀምባቸው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖቻችን ወኪል ነኝ የሚለውን ብአዴን/ኢህአዴግ አባላት ጉዳዩን አጥብቀው በመጠየቅ ለድርጅቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ በማቋረጥ ለህዝብ እና ለሀገር ያላቸውን ወገንተኝነት ማረጋገጥ፣ ከፓርቲውም በይፋ በመልቀቅ ህዝባዊ ዓላማ ያለውን ትግል መቀላቀልና የወንጀል ተባባሪ አለመሆናቸውን በተግባር በማሳየት ከነገ ተጠያቂነት እራሳቸውን ነፃ ማድረግ፣
የሌላው ማኀበረሰብ ኢትዮጵያዊያን ድርጊቱን በጋራ በማውገዝ አሁን እየተፈፀመ ያለው ዘግናኝና አሰቃቂ ወንጀል ወደ ሌሎችም መዛመቱ ስለማይቀር “ማፈናቀሉ እስከመቼ?” በሚል ሁሉም በጋራ በመንቀሳቀስ በራሱ ተስፋ የቆረጠውን ዘረኝነት አገዛዝ እርቃኑን በማስቀረት ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን በማፅናት የዜጎች ሰብዓዊ መብት በሙሉ መከበሩን ለማረጋገጥ የዜጎች ከሀገራቸው መፈናቀል፣ መሰደድ፣ በግፍ መታሰርና መገደል ማብቃት አለበት እላለሁ፡፡ አለበለዚያ ነገ ሁላችንም ከሀገራችን መፈናቀላችን አይቀሬ ስለሆነ ዛሬውኑ ቆም ብለን በማሰብ ማድረግ ያለብንን መወሰን ያለብን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ማንም ኢትዮጵያዊነታችንን ሲፈልግ ወስዶ እንካችሁ፤ ሳይፈልግ ዜግነታችሁን እኔ የምሰጣችሁ ስፍር ብቻ ነው ሲሉ መፍቀድ ባርነትን ከመምረጥ ውጭ ምን ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን? እኔ በበኩሌ ባርነትን በፍፁም አልመርጥም፣ አልደግፍምም፡፡
Posted By. Dawit Demelash

No comments:
Post a Comment