Thursday, July 31, 2014

አስቂኙ ክስና አስቂኙ ማስረጃ የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነውመቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል:
ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባትየምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰትእድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁንግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸውክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡
ክሱ በአጭሩ
በአስሩ ተከሳሾች ላይ የተጠቀሱት የክስ አይነቶች ሁለት ሲሆኑ አንዱ የሽብር ተግባርን ማቀድ ማሴር ማነሳሳትና መፈጸም ሲሆን(የጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ አራት) ሁለተኛው ህገ መንግሰታዊ ስርአቱን በሃይል መናድ( የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀጽ 238)የሚሉ ናቸው ፡። ክሱ ላይ በፓርላማ በሽብተኝነት ላይ ከተፈረጁ ድርጅቶች ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል በህቡእ በመደራጀት የሽብርተግባር ላይ መሰማራት እና የመሳሰሉት ክሶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ ከሶቹ ሲጠቃለሉ
1. ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
2. ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
3. Security ina boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
4. አመጽ ቡድኖችን ማደራጀትና አመጽ ማነሳሳት  የሚሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል
ከዚህ በፊትምእነደተናገርነው  ማንኛቸውም የዞን9 ጦማርያን በፓርላማ በሽብርከተፈረጁ ወገኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለንም፡፡  ብዙ  የዞን9 ነዋሪያንንም አንደሚረዱት አብዛኛዎቹ የዞን9 ጦማርያን እነዚህአካላት ላይ በሚያደርጉት ከፍተኛ ትችት እየታወቁ ጉዳዩን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ መሞከር ፣መንግስት የፈረጃቸውንድርጅቶች እነደፈለገ ማንንም ሰው ለመክሰስ አንደሚጠቀምበት ከማሳየት ባለፈ ትርጉም የማይኖረው ነው፡፡ ለማጠቃለል ያህልማንኛቸውም የዞን9 አባላት አገር ውስጥም ሆነ ውጪ አገር ያለ የፓለቲካ ደርጅት አባላት አይደሉም፡፡ ይህንን የሚያሳይ መረጃምመንግሰት ለማቅረብ አንደማይችልም አናውቃለን፡፡ ( የማስረጃ ዝርዝር ላይ ወደታች የምንመለስበት ይሆናል)

ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር
በክሱ ላይ ስሙያልተጠቀሰ የህቡእ ሽብር ድርጅት በመመስረት ተከሰናል፡፡ በመሰረቱ መንግስት ዞን9 የሚለውን ስም አንድም ቦታ በክሱ ላይለመጠቀም ያልፈለገው የጦማርያኑን ቡድን ይበልጥ ታዋቂ እነዳይሆን ለማድረግ አንደሆነ አንገምታለን፡፡ ይህ አስቂኝ ክስ አንድምቦታ ላይ የዞን9 ስም ባያነሳም በደፈናው በህቡዕ መደራጀት ብሎ ከሶናል፡፡ በመሰረቱ መንግሰት እኛን ለማግኘት ምንም አይነትየደህንነት ስራ እነዳላስፈለገው አናውቃለን፣. ምክንያቱም ሁሉም የዞን ፱ ጦማርያን ስማቸውና ፎቶአቸውን ማስቀመጣቸው ቋሚየምንስማማበት እሴት ስለነበር ነው፡፡ የምንጽፈው ነገር በተናጠል ሃላፊነትን አንድንወስድ አንዲሁም ሌሎችን ሃሳብ መግለጽንለማበረታታት በማሰብ በአደባባይ  እነዲታይ የወሰነውን የጦማርያንንስብስብ ‹‹ህቡዕ›› ብሎ መጥራት ማንን ለማሞኘት አንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ዞን፱ ድብቅ እነዳልሆነ እያንዳንዱ ጽሁፍምበተናጠል ሃላፊነቱን የሚወስድ ጸሃፊ የቡድን ጽሁፎች ሲሆኑ ደሞ የቡድን ሃላፌነት አንደምወስድ ማንም የጦማራችን አንባቢያውቀዋል፡፡ መንግስት የዞን፱ አይነት ጦማሮችንም ሆኑ የአንተርኔት አንቅስቃሴዎቸን የሚመዘግብበት አሰራር አለመኖሩ ደሞ የእኛጥፋት ተብሎ ሊቆጠር አይችልም፡፡ተሰብስቦ መጦመርን የሚከለክል ምንም አይነት የህግ ክልከላም የለም፡፡ በመሆኑም ተሰብስበንመጻፋችን  ራሳችንን ገልጸን ሃሳባችንን መግለጻችን የጣስነው ምንምሕግ የለም፡፡ፓሊስም ሆነ መንግሰት ሶስት ወር በፈጀ ምርመራው ህቡዕን ትርጉም ትርጉም በሚገባ አለማወቁም ጉዳዩን አስተዛዛቢባስ ሲልም መሳለቂያ ያደርገዋል፡።

Security in a boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
Security in a box ኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የኢንተርኔትአንቅስቃሴን በጥንቃቄ ለማድረግ የሚረዳ ኦፕን ሶርስ የስልጠና ማንዋል ሲሆን ይህንን ስልጠና መውሰድ በምንም መልኩ ወንጀልሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የስልጠና ማንዋል ለማንኛውም የሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚያሳስባቸው ሰዎችአንዲያገኙት ሆኖ የተዘጋጅ  ፍሮንት ላየን ዲፌንደርስ እናታክቲካል ቴክ የተባሉ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ያዘጋጁት ስልጠና ነው፡፡ በመሰረቱ ይህንን ስልጠና ወንጀል አድርጎከማቅረብ በፊት ጎግል ላይ አስገብቶ መፈለግና ውጤቱን ማየት ከአንደዚህ አይነት አሳፋሪ ክስ ያድን ነበር፡፡ ይህ በበጎ መልኩአንረዳው ካልን የፍትህ አካላቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ያላቸውን ከፍተኛ ርቀት የሚያሳይና መንግሰትም በሰፊውና በቅንጅት ሊሰራበትየሚገባ ክፍተት ሲሆን ከዚያ ባለፈ ካየነው ደሞ መንግሰት እሱ የማያውቀውን ማንኛውንም ነገር ያለምንም የህግ ክልከላ  ወንጀል ብሎ ለመፈረጅ ያለውን ጉጉት ያሳያል ያ በራሱ ደሞ መንግስትንራሱን ህገ ወጥ እነደሚያደርገው ያለምንም የህግ እውቀት ማሰብ ብቻ ለሚችል ሰው የሚገለጥ ሀቅ ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ወንጀልተብለው የተለያዩ ስልጠናዎች በሚል የተጠቀሱት የኮምኒኬሽን ስልጠና የስትራቴጂክ ስልጠና የአድቮኬሲ ስልጠና የመሳሰሉትመሆናቸውን ለመጥቀስ አንወዳለን፡፡ በመሰረቱ በተለያዩ ድርጅቶች ግብዣ ስልጠና መውሰድና የሰብአዊ መብት ፎረሞች ላይ መገኘትንወንጀል የሚያደርግ ህግ አለመኖሩን መንቀሳቀስም የዜጎች ሰብአዊ መብት መሆኑን ለአቃቢ ህግ ህግና ፓሊስ ካላወቁ ማን ሊያውቅነው ??
የተደራጁት የአመጽቡድኖችን ማደራጀት  እና 48 ሺህ ብር ለአመጽ ማከፋፈል
መንግሰት የአመጽቡድኖችን ማደራጀት በሚል ያቀረበውን ክስ ለመመለስ ያህል አንድ ጥያቄ ብቻ አንጠይቃለን? የታሉ የተደራጁት ቡድኖች?  ምንም የተደራጀ ቡድን በሌለበት ይህንን ክስ ማቅረብ በፍትህ ስርአቱማፌዝ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምን ይባላል? በ48 ሺህ ብር የአመጽ ማነሳሳት ክሱን ከብሩ ማነስ በላይ ይበልጥ አስቂኝየሚያደርገው የማስረጃው ዝርዝር ላይ ያለው ማስረጃ እና ክሱ የተለያዩ መሆናቸው ነው፡፡ ክሱ 48,000 ብር ከውጪ በመቀበልበማለት በደፈናው ላኪውን ሳይጠቅስ ያለፈው እና ለሽብር ተግባር የተባለው አርቲክል 19 ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትለታሰሩ ጋዜጠኞች ቤተሰቦች የሚደረግ ድጋፍ ሲሆን በወቅቱ ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ባንክ ስለሚሰራ ተቀብሎ ለጋዜጠኛ ርዩት አለሙቤተሰቦች እስር ቤት መመላለሻ ተብሎ የተሰጠ ድጋፍ ነው፡፡
የተያያዘው የባንክደረሰኝም ያንን የሚያሳይ ሲሆን ክሱ ላይ በይፋ መጥቀስ ያልተፈለገው ለምን ይሆን? (ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹን መታሰር ተከትሎመንግስት ፋይል የከፈተበትን ከሰብአዊ መብት ተቋማት ነን ከሚሉ ድርጅቶች የሃሳብና የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል ሶሻል ሚዲያንበመጠቀም አመጽ ማነሳሳት የሚለውን ክስ ተከትሎ የተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራመስራት ወንጀል ሊሆን አይገባም በሚል ርእስ እስሩን የሚያወግዝ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል)
ማስረጃውሲገመገም
እስካሁን በእጃችን የደረሰውን የማስረጃ ዝርዝር በሶሰት ከፍለን ማየት አንችላለን ፡፡ከማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ አብዛኛውን ቦታ የሚይዘው በተለያየ ወቅት የተጻፉ የጦማርያኑ ጽሁፎች ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ላይ ደሞ ጭራሽየመረጃ ዝርዝር ለማቅረብም አልተቻለም፡፡(አቃቤ ህግ የሁሉንም የበይነ መረብ ዘመቻዎች መግለጫ እና እቅድ እንደማስረጃአቅርቧል)  በሁለተኛ ደረጃ የቀረቡት የተለያዩ የጉዞ ትኬቶችአለም አቀፍ ስብሰባ ማስታወሻዎች አንዲሁም ፕረዘንቴሽኖች  ሲሆኑሁሉም ጦማርያኑ ያደረጓቸው አለም አቀፍ ጉዞዎችን የሚያሳዩ የተሳተፉባቸው ሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትየተመለከቱ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ የተደረጉ ጉዞዎችን ናቸው፡፡
በማስረጃ ዝርዝር ውስጥከተካተቱት የሽብር ተግባር የተደረጉ ጉዞዎች ተብለው መሆኑ ይበልጥ ክሱን አሳፋሪ ያደርገዋል፡፡ መንግሰት ጉዞዎቹ የተደረጉትምሆነ የስልጠና ግብዣዎቹ የመጡት ከአለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አንደሆነ እያወቀና እና ማስረጃው ላይም በግልጽእየታየ የሽብር ቡድኞች ብሎ ግንቦት ሰባትና ኦነግን ጣልቃ ማስገባቱ አስገራሚ ነው፡፡ (የፍርድ ሂደቱ ላይ እነዚህ ተቋማት ጋርየተደረጉ ግንኙነቶቸን አንዴት ብለው በፓርላማ ከተፈረጁ የሽብር ተቋማት ጋር እነደሚያገናኛቸው አብረን የምናየው ይሆናል)  በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የተደረጉ የስልክልውውጦች ሲሆኑ በፍርድ ቤት ሂደቱ ውስጥ በዝርዝር የምናያቸው ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ተከሳሽ ቤት ተገኘ የተባለውና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት ከግንቦት ሰባት ጋር የተገናኙ ዶክመንቶች እናየአባላት መጽሄት ሲሆን በፍተሻው ወቅት ፓሊሶች ራሳቸው ፍሪጅ በስተጀርባ አገኘን ብለው በፍተሻ ወቅት ከፍተኛ አለመግባባትተፈጥሮ የራሳቸውን ምስክሮች ብቻ አስፈርመው መሄዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
እንዲሁም ፓሊስ 18 የሰው ማስረጃ ለማሰማት የስም ዝርዝር ማስገባቱን እና የስም ዝርዝሩም እጃችን ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከፍርድቤት ለሚመጣው የፍርድ ውጤት ሳይሆን በአጠቃላይ የፍትህ ስርአትን ማክበር ሃላፊነት ስላለብን ብቻ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ ላለማካተትወስነናል፡፡
እንደማጠቃለያ
የዞን፱ ጦማርያን ከዚህ በፊትም በተለያየ ወቅትአንደተናገርነው የመንግሰት ይህን ሁሉ ጊዜ ወስዶ ይዞ የመጣው ማስረጃ የአደባበይ ጽሁፎች እና በተለያየ ወቅት የተደረጉ የአደባባይሁነቶች( public events) ጥርቅም መሆኑ የክሱን ፓለቲካዊነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ጦማርያኑ የፍርድ ቤት ስርአቱን የተለያዩአለም አቀፍ የወንጀል ስነስርዓት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ህጉን አክብረው የሚከታተሉ ሲሆን እኛም ሂደቱን በተቻለ መጠን ለዞን ፱ነዋሪያን ለማሳየት ለማሳወቅ የምንጥር መሆኑን ለማሳወቅ አንወዳለን፡፡ በተደጋጋሚ ተፈትኖ የወደቀው የአገራችን ፍርድ ቤት እና የፍትህስርአት ገለልተኝነት ይህንን እድል በመጠቀም ራሱን ለማሻሻል መፍቀዱን እነዲያሳይና ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን አይቶ ክሱን እነዲዘጋጥሪ እያደረግን ይህንን በማድረግ የአገሪቱን የፍትህ ሂደት አንድ ደረጃ የማራመዱን እድል ዳኞች እንዲጠቀሙበት መንግስትን ከወራትበፌት የሰራውን ስህተት ለማስተካከል እድሉ ዛሬም ያልመሸ መሆኑን ለማስታወስ አንወዳለን፡፡
የታሰራችሁ ጦማርያንን እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ለከፈላችሁት መስዋእትነት ውለታችሁ አለብን፡፡ እንኮራባችኋለን!!
ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ሰነዶች ለፈገግታ ያህል
ዞን ዘጠኝ ላይ የታተሙ ጽሁፎች
  1. ነጻነትና ዳቦ - በናትናኤል ፈለቀ
  2. ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል - በናትናኤል ፈለቀ
  3. ስደትና ፍቅር - በሰለሞን አብርሃም(ከአውሮጳ)
  4. ዋኤል ጎኒሞ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ….? - በበፍቃዱ ሃይሉ
  5. ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት? - በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤል
  6. እኛና ሶማልያ – በናትናኤል ፈለቀ
  7. ድምፃችን ይሰማ - በእንዳልካቸው ሃይለሚካኤልና እና በፍቃዱ ሃይሉ
  8. እንዴት እንደመጥ - በማህሌት ፋንታሁን
  9. የመለስ ውርስ እና ራዕይ - በሶሊያና ሽመልስ
  10. የቅድመ ምርመራ ቅድመ ምርምራ - በማህሌት ፋንታሁን
  11. ትግራይና ሕዋሐት ምንና ምን ናቸው ? -በበፍቃዱ ሃይሉ
  12. ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ በዘላለም ክብረት

ከበፍቃዱ ብሎግ(www.befeqe.com) የተገኙ 
  1. ከ21 አመት በኋላ ዴሞክራሲ ሲሰላ
  2. ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት መመሪያ በማክበር መሥራት ይቻላል?
  3. አብዮት ወረት ነው
  4. የእህአዴግ ‹‹ትርፍ›› እና ኪሳራ
  5. የኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች
  6. ከእከሌን አሰሩት እስከ እከሌን አገዱት
  7. ሰማኒያ ሚሊዮን እስከምንደርስ እንታገላለን
  8. “ድር ቢያብር” ለአምባገነኖች ምናቸው ነው ?
ከሌሎች ብዙ ዝርዝሮች በጥቂቱ
  1. “ኢትዮጵያዊ ማንነት ከሌለ ትግሬያዊ ማንነት የለም” – (በአብርሃ ደስታጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  2. “መንግስት የለም ወይ ?” የምንና ምን አይነት መንግስት(የመስፍን ነጋሽጽሑፍ ከፌስቡክ የተወሰደ ) /በበፍቃዱ ቤት የተገኘ/
  3. የሁለተኛው ዘመቻ ዕቅድ ( ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  4. የ2ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ (ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አሁኑኑ)
  5. ዳዊት ሰለሞን ስለአዲሱ የጋዜጠኞች ፎረም ፕሬዚዳንት ፌስቡክ  ላይ የፃፈው እና አጥናፍ ለበፍቄ ኢሜል የደረገለት ጽሑፍ
  6.  “ፍርሃታችንየት ያደርሰናል ?” በሚል በኤልያስ ገብሩ ተጽፎ በፍቄ ላፕቶፕ ውስጥ የተገኘ(ለዕንቁ መጽሄት ተዘጋጅቶ ያልታተመ ጽሑፍ)
  7. የ3ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ ( ዴሞክራሲን በተግባር እናውል የሰላማዊሰልፍ መብታቸን ይመለስ)
  8. “ሰልፍና ሰይፍ ” በሚል በበፍቄ ተጽፎ ነገር ግን ያልታተመ ጽሁፍ ከላፕቶፑ
  9. የ1ኛው ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ(draft ሕገ መንግሰቱ ይከበር)
  10. የ4ኛው ዘመቻ ዕቅድ( ኑ ኢትዪጲያዊ ህልም አብረን እናልም)
  11. ጋዜጠኛ አስማማው ለድምፃችን ይሰማ የፌስቡክ ገጽ ያዘጋጀቸው ጥያቄዎችከኢሜሉ (ለአዲስ ጉዳይ መጽሄት)
  12. ስለ ዞን 9 ዘመቻዎች globalvoicseonline.org ላይ የታተሙጽሑፎች
  13. በናትናኤል በኩል ለርዕዮት ዓለሙ ቤተሰቦች ከ Article 19 የተላከ48,170.25(ብር) የዌስተርን ዩኒየን ኮፒ
  14.  “የተቃውሞሰልፉ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች” በሚል አዲስ ጉዳይ ላይ የታተመ ጽሁፍ (draft)
  15. ማሒ ስለ ርዕዮት ዓለሙ እና ስለ አዲስ ዘመን “አዝማሚያ ጥናት ” በቀልድየጻፈችው ጽሑፍ፡፡
  16. የዞን 9 ወደፊት ለመስራት የታቀዱ ሶስት ፕሮጄክት ፕሮፓዛሎች ( ምርጫ2007 ሪፓርት የማድረግ ስራ፣ የኢትዮጲያ የነጻነት ኢንዴክስ ማዘጋጃት ስራ ፣ ገጠሪቷ ኢትዮጲያ ላይ ለመስራት የታሰበ ዶክመንተሪእቅድ)
  17. እና ሌሎችም ትርኪሚርኪዎች (ለምሳሌ የዳንኤል ብርሃነ ጽሑፍ፣ የናቲ የ10ኛክፍል ግጥም)

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32988

Monday, July 28, 2014

Is Andargachew Tsige A Terrorist?



http://www.zehabesha.com/adeola-fayehun-is-andargachew-tsige-a-terrorist-video/

Sunday, July 27, 2014

ሕወሓት አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ ራሷን በራሷ ያጋለጠችባቸው 4 ቅጥፈቶች




ስንታየሁ ከሚኒሶታ
እንደተጠበቀው በሕወሓት መንግስት በሚመራው የኢትዮጵያ ፖሊስ ፕሮግራም ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲቀርቡ ተደርጓል። የአቶ አንዳርጋቸው በቲቪ መቅረብ ከዚህ ቀደም በአንዷለም አራጌ፣ በብርቱካን ሚደቅሳ፣ በደበበ እሸቱ፣ በአቡበከር አህመድ ላይ የተለመደ በመሆኑ ብዙም አስገራሚ አልሆነም። ሆኖም ግን ቪድዮውን ልብ ብሎ ለተመለከተው ወያኔ እንዳሰበው ትርፍ ሳይሆን የበለጠ ኪሳራ እንዳገኘበት ለመረዳት ችያለሁ። ለዚህም ነው ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ የረሳቻቸው 4 ቅጥፈቶች ስል ለዚህ አስተያየቴ ር ዕስ የሰጠሁት።
1ኛ. ቪድዮው በጣም ኤዲት እንደተደረገ ያስታውቃል
ሕወሓት ያዘጋጀው የቪድዮ ካሜራ ማንና አቀናባሪው ደንጋጣ እንደሆነ ቪድዮው ያስታውቅበታል። በጣም ተቆራርጦ መቀጣጠሉ ከማስታወቁም በላይ ቢያንስ ከዚህ የተሻለ ኤዲቲንግ ሥራ መሥራት ይችል የነበረ ቢሆንም ይህን ባለማድረጉ ለፕሮፓጋንዳ ሥራ የተዘጋጀውን ቪድዮ ኪሳራ ላይ ጥሎታል። ቪድዮ አቀናባሪው ሆን ብሎ ሕዝብ መቆራረጡን እንዲያውቅ ያደረገ ከሆነ ልናደንቀው የሚገባ ሲሆን፤ ሆኖም ግን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከሆነ ይህ ቪድዮ ቅንብሩ አይመጥንም።
2ኛ. ቪድዮው በተደጋጋሚ የተቀረጸ መሆኑ ያስታውቃል።
ቪድዮውን ልብ ብላችሁ ከተመለከታችሁት በተለያየ ጊዜ የተቀረጸ መሆኑ ያስታውቃል። ይህም የሚፈልጉትን ለማግኘት ብዙ ማይል እንደተጓዙ ያሳያል። ምንም እንኳ ተመሳሳይ ቀን የተቀረጸ ለማስመሰል አንድ ዓይነት ቱታ ቢያስለብሱትም 3 የተለያዩ የውስጥ ቲሸርቶች ይታያሉ። አንዱ ነጭ፣ ሌላኛው ሰማያዊና 3ኛው ቀይ ቲሸርቶች። በሌላ በኩል ቪድዮው ሊያልቅ ሲል የምታዩት ቱታ ደግሞ የተለየ ነው።
3ኛ. ውሃዋ የለችም።
እንግዲህ ወያኔ ሌላው የረሳችው አቶ አንዳርጋቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዳሉ ለስመሰልና ንጹህና የተገዛ ውሃ አጠገባቸው አስቀምጣ ነበር። ቪድዮው ግን በተለያየ ጊዜ የተቀረጸ ለመሆኑ የሚያስታውቀው በሌላኛው የቪድዮ ክፍል ውስጥ ውሃዋ የለችም።
4ኛ. ቶርች የሚደረግ ሰው እንዳለ ይሰማል
ይሄ ትልቁ ወያኔን ራሱን በራሱ ያጋለጠበት ክፍል ነው። ቪድዮው ተጀምሮ ከ1 ደቂቃ በኋላ ያለውን ስትመለከቱት አንዳርጋቸው በሚናገርበት ወቅት ከጀርባው የድብደባና የሲቃ ድምጽ ይሰማል። ይህም ምን ያህን በወያኔ እስር ቤቶች የሚደረጉትን ቶርቸሮች የሚያሳይ ነው። ይህ ለወያኔ ትልቁ ኪሳራ ሊባል የሚችል ደካማው የፕሮፓጋንዳ ቪድዮው ሊባል ይችላል። ራሱን በራሱ ቶርቸር አድራጊ መሆኑን መስክሯልና ይህንን የሚመለከታቸው አካላት ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ማሳየት ይኖርባቸዋል፤ አንዳርጋቸውም እንዲህ ያለው ቶርቸር እንደደረሰበት ማሳያ ሊሆነን ይችላል እላለሁ።
ቪድዮውን ተመልከቱትና ፍረዱ። በመጨረሻም ለወያኔ የማስተላልፈው መል ዕክት አለኝ – እንደሁልጊዜው ለዛሬውም አልተሳካም!
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32930

Thursday, July 24, 2014

የምርጫ ነገር

july 24th,2014

በመቀሌ አንዳንድ ጓደኞቼን «የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ትፈልጋላቹህ ? ለምን ገብታቹህ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ አታደርጉም ? » ስላቸው «ዝም ብለን ለምን እንለፋልን። እንደተለመደው ይዘርፉታል። የህዝብ ድምጽ አይከበርም» አሉኝ። በጣም ገረመኝ ። ምክንያቱም ድሮስ አንባገነን ስርዓቶች ፍትሓዊ ምርጫ እንዲካሄድ ይፈልጋሉ እንዴ? አንባገነን መንግስታት በሚመሩት ሃገር ነጻ፣ ፍትሓዊ እና ተአማኒ ምርጫ ይካሄድ ዘንድ አስገዳጅ ሁኔታ መፈጠር አለበት። አለበለዚያ አንባገነኖች ፍትሓዊ ምርጫ እንዲያካህዱ ባህሪያቸው አይፈቅድላቸውም።

ባለፉት 23 አመታት ፍትሓዊ ምርጫ ቢደረግ ኖሮ፣ ኢህአዴግ እስካሁን ስልጣን ላይ አይቆይም ነበር። ስለዚህ ዜጎች በሃቀኛ ተቀዋሚ ፓርቲዎች ስር ተደራጅተው፣ ስርዓቱ ካላስገደዱት መጪው ምርጫም እንደለመደው አጭበርብሮ ስልጣን ላይ ለመቆየት እንደሚፈልግ አሁን በሃቀኛ ተቀዋሚዎች ላይ እየደረሰ ካለው አፈና መገንዘብ ይቻላል።
ሃቀኛ ተቀዋሚ እያልኩ ያለሁት በስመ ተቀዋሚ ኢህአዴግ ስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚፈልጉ የይስሙላ ተቀዋሚዎች ስላሉ ነው። እነዚህ በህዝብ እና በሃገር እየቀለዱ ያሉ ግለሰቦች እና ተቃዋሚ ነን የሚሉ፣ ማንም ሰው የማይከተላቸው እና የእለት ጉርሳቸው ኢህአዴግ የሚቆርጥላቸው ናቸው።
ስለዚህ ዜጎች ላለፉት 23 ዓመታት ከጫንቃቸው አልወርድም ብሎ በምርጫ ስም በየ 5 ዓመቱ በህዝብ እና በሀገር ላይ እየቀለደ ያለ ስርዓት የከፋፍለህ ግዛ ስልቱ በማክሸፍ፣ ሁሉም ዜጋ ፤አገሪትዋን ከጥፋት ለመታደግ የበኩሉን ጥረት ማድረግ አለበት።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጽሃን ዜጎች በእስር ቤት እየማቀቁ ነው። «ነገስ ማን ይታሰር ይሆን ?» እያልን ሁሌ የሰቀቀን ሕይወት ከመምራት ሁላችን፣ እንደ አብርሃ ደስታ፣ ከፍርሃት ቆፈን በመውጣት፣ ለመብታችን መቆም መቻል አለብን። ከአንባገነኖች ፍትሓዊ ምርጫ ከመጠበቅ ከዝንብ ማር መጠበቅ ይቀላል። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ሃፍተይ ገብረሩፋኤል ( መቀሌ )
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15298


Wednesday, July 23, 2014

በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴና አካባቢው የተነሳው ውጥረት ተባብሷል፤ ጫካ የገቡ መሪዎች የሕዝቡን አመጽ ተቀላቅለዋል

(በመርሃቤቴ አካባቢ በተነሳው ግጭት ተጎድተው ሆስፒታል ከገቡት መካከል)

ምኒልክ ሳልሳዊዝ እንደዘገበው፦

በሰሜን ሸዋ መርሃቢቴ እና አካባቢው ላይ የተነሳው የህዝብ እምቢተኝነት ከቀድሞው የበለጠ ተባብሶ ያለበት ሁኔታ መኖሩን ከአካባቢው የሚወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል። ሕዝቡ የመብራት ትራንስፎርመር መወሰዱን መሰረዙ ቢነገረውም ልታዘናጉን ነው። የከተሞቻችንን ንብረት የመጠበቅ ሃላፊነት አለብን የፌዴራል ፖሊሶች ከአካባቢያችን ይውጡልን የሚሉ ጥያቄዎችን በማንገብ መሳሪያውን ይዞ ወደ ከተማው በመውጣት አካባቢውን በውጥረት እንደሞላው ታውቋል።

የመርሃቢቴ ህዝብ አሁንም በያለበት እየተጠራራ የተደበቀውን የጦር መሳሪያ በማውጣትበመሰባሰብ መንገዶችን ተራሮችን ሸጦችን ተቆጣጥሮ ለውጊያ እየተዘጋጀ ነው። ጎረቤት ወረዳዎችም ይህንን የመሬን ህዝብ አመፅ በመደገፍ ወገናዊ ድጋፍና ትብብር ለማድረግ እየተዘጋጁና ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ከሚደርሱን መረጃዎች አረጋግጠናል። የየአካባቢው የወያኔ ታጣቂ ሚሊሻዎች፣ አስተዳደሮች፣ ካድሬዎች በሚያስደስት ሁኔታ ከህዝቡ ጎን ተሰልፈዋል።

እንደምኒልክ ዘገባ ከሆነ ወያኔ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል ወደ ማይችለው አዘቅትም ገብቷል። ህወኃትን ከነ ግሳንግስ አገዛዙ ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፣ በተለያየ መንገድ ሸፍተው በጫካ የነበሩ መሬዎች ሁሉ የህዝቡን አመፅ ተቀላቅለዋል ሲል ዘገባውን ቁጭቷል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32848

Saturday, July 19, 2014

Ethiopian Government Accused Zone 9 Bloggers Working with Ginbot 7

July 19, 2014
by William Davison
Bloomberg
Six Ethiopian bloggers and three journalists were charged with planning attacks in the East African country in partnership with a banned U.S.-based opposition group, a judge said.Zone 9 Bloggers in Ethiopia Jail
The members of the Zone 9 blogging group and reporters are accused under Ethiopia’s anti-terrorism law of working with Ginbot 7, which is classified as a terrorist group by the government, Judge Tarekegn Amare told the Federal High Court today in the capital, Addis Ababa. The defendants, who were arrested in April, received funding and training in explosives from abroad, he said.
“The prosecutors didn’t actually mention any specific act which it claimed that they planned to do,” defense lawyer Ameha Mekonnen told reporters after the hearing. “They simply said that they planned, organized themselves and conspired, things like that.”
Donors such as the U.S. and the United Nations have said that Ethiopia’s 2009 anti-terrorism law is used to criminalize legitimate dissent from journalists and opposition politicians.
Award-winning writer Eskinder Nega was sentenced to 18 years in prison in 2012, while two Swedish journalists who traveled with with a rebel group were accused of supporting the insurgents and convicted under the law in 2011.
Anyone prosecuted under the anti-terrorism law is part of a network that begins in Eritrea, Ethiopia’s regional enemy, and reaches Somalia, Kenya and South Sudan, Prime Minister Hailemariam Desalegn told reporters today.
Banned Organization
“When you put yourself into this network and you try to be a blogger, don’t think you are going to escape from the Ethiopian government,” he said in the capital. “I don’t think becoming a blogger makes anyone immune if somebody involves into this terrorist network that destabilizes my country.”
The Oromo Liberation Front, a banned organization fighting for more autonomy for Ethiopia’s Oromo people, was mentioned in the charges once, Ameha said.
The charges didn’t appear “professionally done” and the defendants, who are all in their 20s and 30s, accused the authorities of forcing them to sign confessions in previous hearings, he said. “They were forced to sign statements that they did not write,” Ameha said.
Similar allegations have been made in previous terrorism cases and are false, State Minister of Communications Shimeles Kemal said by phone from Addis Ababa. “There is nothing whatsoever to substantiate these allegations,” he said.
Next Hearing
A seventh member of the Zone 9 group, Soliana Shimelis, coordinated foreign relations and was charged in absentia, Addis Standard magazine said on its website. The defense will make an initial response to the charges, which were mainly under Article 4 of the law regarding planning acts of terrorism, at the next hearing on August 4, Ameha said.
Ginbot 7 was formed after a disputed 2005 election by former leaders of the opposition Coalition for Unity and Democracy. The group considers Ethiopia’s government a dictatorship and says “all means necessary” are justified to depose it.
http://ecadforum.com/2014/07/19/ethiopian-government-accused-zone-9-bloggers-working-with-ginbot-7/

Wednesday, July 16, 2014

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዬጵያ አንድነት ድምፅ ( የዕለቱ ዜና ዘገባ ) 16.07.2014

የእንግሊዝ መንግስት ለወያኔ የሚሰጠውን እርዳታ ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር ይያያዝ  ሲል የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አዘዘ ፣፣
የስኳር እጥረት በመላው አገሪቱ ተዳረሰ ፣፣
ጋዜጠኞችና ጦማርያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፋይላቸው ተዘጋ ፣፣
የወያኔ ከፍተኛ ካድሬዎችና የፓርላማ አባላት ጥያቄና አቤቱታ አቀረቡ ፣፣

ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ፣http://www.finote.org/Finot16_07_2014.mp3

Tuesday, July 15, 2014

በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል

በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። #Ethiopia  የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ከባድ መሳሪያዎች ተወልውለው በድንበሩ ዙሪያ ተኮልኩለዋል።


የአንዳርጋቸው ጽጌ መያዝ ፡ የግንቦት ሰባት ጥሪ እና የትሕዴን ሰራዊት መመረቅን ትከትሎ በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ሰሜን ምስራቅ ድንበር ላይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ለሰሜን እዝ ቅርብ የሆኑ የሰራዊቱ ምንጮቻችን በደረሱን መረጃ አስታውቀዋል።እንዲሁም በአፋር ክልል ውስጥ ክፍተኛ ደህንነቶች በማፍሰስ ሕዝቡን እየሰለሉት መሆኑ ሲታወቅ ከፍተኛ አመጽ በክልሉ እንዳይነሳ ወያኔ መስጋቱ ታውቋል።

ወያኔ ተጠባባቂ ጦሩ ላይ እምነት ስለሌለው የትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ብቻ በተለያዩ ወረዳዎች በመሰብሰብ አስፈላጊውን መመሪያ የሰጠ ሲሆን በሁምራ ክዚህ በፊት ሰልጥነው የሰፈሩ እና መኖሪያቸውን እዛው ያደረጉ የወያኔ ልዩ ተጠባባቂ ጦር አባላት በነፍስ ወከፍ አዳዲስ ላውንቸር ክላሽንኮቭ እና ከበርካታ ጥይቶች ጋር እንደትድላቸው ታውቋል። 

እንዲሁም በትግራይ ውስጥ የሰለጠኑ ሚሊሻዎች ከነትጥቃቸው ድንበር አከባቢ ከዚህ ቀደም መሬት ተሰቷቸው የሰፈሩትም ለዚሁ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ተደርገዋል።ታንኮች መድፎች እና ከባባድ መሳሪያዎች ወደ ድንበሩ በመጠጋት አስፈላጊውን አሰሳ እያደረጉ ሲሆን የ24 ሰአት ልዩ ጥንቃቄ የተሞላበት ወታደራዊ የቁጥጥር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ መልክ በጎንደር በጎጃም እና በሰሜን ሸዋ ነዋሪዎችን መሳሪያ ማስፈታት ሊጀመር መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህም የሚያምለክተው አማራው ከግንቦት ሰባት ጋር ይሸፍታል የሚል ስጋት ስላላቸው መሆኑ ታውቋል። በዚህ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ይቀርባሉ።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32554

Monday, July 14, 2014

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ




ቅዳሜ ጁለይ 12/2014 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን በሚል አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የደንነት ሀይሎች መታፈንና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ታላልፈው መሰጠታቸውን በተመለከተ ወደ ፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ በኖርዌ ኦስሎ ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል::
ሕዝባዊ ውይይቱ ከቀኑ 15: 00 ሰአት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያኖች የአቶ እንዳርጋቸው ምስል ያለበትና ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን የሚል ጹሁፍ የተጻፉበትን ቲሸርት በመልበስ ለስብሰባው ድምቀት የሰጡት ሲሆን ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውንም የትግል አጋርነት አስማስክራዋል እነዚህን ቲሸርቶች የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ በራሳቸው አነሳሽነት የሰሩ ሲሆን የድጋፍ ድርጅታችን ወጪውን በመሸፈን ለተሰብሳቢው በነጻ ኣድሏል።
ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አቢ አማራ በሃያ ሶስት አመታት በወያኔ ጨካኝ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉትና በግፍ ለሚሰቃይዩ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ አስጀምረውታል በመቀጠልም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር በስብሰባው ላይ የተገኛውን ሕዝብ እንኮን ደህና መጣችሁ በማለትና በማመስገን ፐሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ሲሆን አቶ ዮሀንስ በንግግራቸው የወያኔ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረሰው አፈና ግንቦት 7 የክተት አዋጅ ማስተላለፉን ጠቅሰው አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል እየታገሉ ባሉ ታጋዮች ላይ ሳይቀር እስር እያደረሰባቸው እንዳለ በማመልከት ሰሞንኑን እንኮን የሰመያዊ፣ የአንድነት፣ የአራና የፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ለስር ተዳርገዋል ብለዋል::
ስለሆነም ህዝባችንን ለእስር እያደረገ ያለውን አገዛዝ ለመቃወም ሁሉም በአንድነት መሰባሰብ እንዳለበት አጠንክረው በመናገር በአሁን ሰአት የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታፈንና መታሰር መላውን ኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር እያንቀሳቀሰውና ሕዝቡም እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቅሰው በአሁን ሰአት ትግሉ የግንቦት 7 ብቻ አይደለም ይህን ትግል በዚሁ አንድ ሆነን መቀጠል እለብን ብለዋል::
በመቀጠል አቶ ደባስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባል የአቶ አንዳርጋቸውን ከወጣት እድሜያቸው ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ አካሄድ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ማን ነው ? በሚል ርእስ የአቶ አንዳርጋቸውን የትግል ጉዞ የሚዳስስ ዘገባ ሰፋ ባለ ትንታኔ በጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢሀፓ ፣ የአርበኞች ግንባር፣ የሸንጎ ፣የስደተኛው ማህበር ተወካዮች እና ሌሎችም ሰዎች በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የየድርጅቷቹም ተወካዮች የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መታፈንና ለእስር መዳረግን በተመለከተ የድርጅታቸውን አቋም ለተሰብሳቤው ያስረዱ ሲሆን የሁሉም ፖርቲ ተወካይች በአቶ አንዳርጋቸው መታፈንና ለእስር መደረግ ማዘናቸውን ገልጸው ሁሉም በአንድነት በመተባበር በማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ የወያኔንን መንግስት ማስወገድ እንዳለባቸው አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል::
በየፕሮግራሞቹ መሀል ግጥሞችና ሌሏችም ፕሮግራሞች ቀርበው የመጀመሪያው ዞር ተጠናቋል::ከ30 ደቂቃ የእረፍት የሻይ እና የቡና ፕሮግራም በኋላ የሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ፕሮግራም በተያዘለት ጊዜ ተጀምሮ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ያሰተፈ ፕሮግራም በአቶ አብዱ የሱፍ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ ምክትል ሊቀመንበር ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪን ካብራሩ በኋላ ለተሰብሳቢው ለውይይት በማቅረብ በኖርዌ የምንኖር ኢትዮጵያኖች ይህን የትግል ጥሪ ለማስፈጸም ምን እናድርግ በማለት ለውይይት አቅርበው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአቶ ዮሀንስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር አወያይ አማካኝነት በስፋት ተወያይተውበታል ::
ተሰብሳቢውም በብዙ ነገሮች ከተወያዩ በኋላ ይሄ ግንቦት 7 ያወጣውን የመጀመሪያ እንከን የትግል ጥሪ ተግባራዊ በየቦታው አለም አቀፍ ታክስ ፎርሶች እየተቋቋሙ እንዳለና በኖርዌይም ይህንኑ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቷች ያካተተ ታክስ ፎርስ እንዲቋቋም ተወስኖል:: በመቀጠልም በተሰብሰቢዎች በተመረጡ ሰዎች የተጻፋ ባለ ስድስት አሃዝ የተሰብሳቢው የአቋም መግለጫ ለጉባሄው በጹሁፍ ቀረቦል:: ተሰብሳቢው ያወጣው የአቋም መግለጫ
1. ሁላችንም አንዳርጋቸው ወይም አንድ አርጊያቸው ነን ስንል ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሐገራችን ኢትዮጵያ ለማስፈን የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ማለታችን ነው።
2. የተለያዩ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት የሚያደርጉትን መጠላለፍ እንዲቀርና በጋራ ወይም አንድ በመሆን እንዲሰሩ ግፊት እናደርጋለን።
3. ለሚቀርብልን ሐገርን የማዳን ጥሪ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
4. የየመን መንግስት ከአለም አቀፍ ህግ ጋራ የሚፃረር ስራ በመስራት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት የሰራውን ወንጀል ለዓለም አቀፍ ህግ የማቅረብ ስራ በጋራ እንደምንሰራ።
5. የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ መታፈን ትግሉን የበለጠ እንደሚያጠናክረውና ወደ ውጤት እንዲያመራ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን።
6. ወያኔ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን እስርቤት ማስገባቱን እንዲቀርና የታሰሩትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንጠይቃለን በማለት የአቋም መግለጫ አውጥተዋል ።

በመጨረሻም አቶ ዳንሄል አበበ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሰብሳቢ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የአቋም መግለጫ ለተሰብሳቢው በጹሁፍ ያሰሙ ሲሆን በንግግራቸውም አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የቋሙ የነጻነት ታጋይ ናቸው እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ የምንል ሁሉ ለሃያ ሶስት አመታት ህዝብን በዘረኝነት የከፋፈለውን ወያኔን በቃ ልንለው ይገባል ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ አፈና፣ ግድያው፣ እስራቱ መጨመሩን በመናገር ይኼን ጨቋኝና አፋኝ ስርአት ለማስወገድ እንነሳ በማለት ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን በመጨረሻ እኔ እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ እናንተስ በማለት የፕሮግራሙን ተሳታፊ በመጠየቅ ፕሮግራሙ በተያዘለት ሰዓት ከምሽቱ 20:00 ተጠናቋል ::

እኛ ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32493

Saturday, July 12, 2014

ወያኔም ዳግማዊ ደርግ ዉነ እሱም በቅርብ ጊዜ የእጁን ያገኛል



ጥላቻ በዛ፣ ቂም አበበ፣ በቀል አፈራ!! ኢህአዴግም አልረካም ደርግም መወደቂያው ላይ ከዛሬ 23 ዓመት በፈት እንዲህ ነበር እንደ አበደ ዉሻ አንቀዠቅዦት ሲያስር ሲገድል ሲገርፍ መዉደቂያዉን ያፉጠነው አሁንም አገሪቷን በጉልበት ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠራት የወያኔ ቡድን ጋዜጠኞችን፣አክቲቪስቶችን፣ ብሎገሮችንና ፖለቲከኞችን በሽብርተኝነት በመወንጀል ያስራል ይገርፋል ይገድላል ወያኔም ዳግማዊ ደርግ ዉነ እሱም በቅርብ ጊዜ የእጁን ያገኛል ልክ እንደ ደርግ ።

Dawit Demelash

ጥላቻ በዛ፣ ቂም አበበ፣ በቀል አፈራ!! ኢህአዴግም አልረካም

prisoners1July 11, 2014 11:55 pm 

“እነሱ ሁለት አገር አላቸው። ኢትዮጵያን ይዘዋታል። በስደትም እንደፈለጋቸው እየኖሩ ነው። እኛ ግን አንድም አገር የለንም። በስደት እንኳን እንዳንኖር እየተደረግን ነው። ሸሽተን በተሰደድንበት ምድር እንኳን ዋስትና የለንም። ከዚህ በላይ ምን ይምጣ?” ይህንን የዛሬ ሶስት ወር ገደማ ለጎልጉል የተናገሩት በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሐፊ ወ/ት የሺሃረግ በቀለ ነበሩ። የወ/ት የሺሃረግን ሃሳብ በመንተራስ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንዳሉት “አገር ውስጥም እስር፣ በስድት ምድርም ስጋትና እስር ካለ፣ የይለይለት መንፈስ መነሳቱ አይቀርም። ሰዎች የመኖር ተስፋቸው ሲመናመን የፈለገው ይምጣ ይላሉ። አሁን ኢህአዴግ ከስጋቱ ብዛት እየፈጸመ ያለው ድርጊት ሰዉን ሁሉ ወደዚሁ የሚያመራ ነው።”
ሰሞኑን ኢህአዴግ የወሰደውን፣ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ ሲከናውን የቆየውን፣ ወደፊትም በቀጣይነት የሚገፋበትን እስርና አፈና አስመልክቶ የተፈጠረው ስሜት ከራር ነው። ኢህአዴግ ቋንቋው ሁሉ እስር መሆኑ እየፈጠረ ያለው ስሜት ኬላና ልጓሙ እንዳይፈርስ የሚሰጉ ጥቂት አይደሉም። የኢህአዴግ የአፈና መረብ ያልገባበት ቤትና መንድር እንዲሁም ክልል የለም። በሃይማኖት ቤትም ያለው እሳትና ችግር ቀን የሚጠብቅ ነው። ኢህአዴግ ግን ሁኔታዎችን ከመመርመር ይልቅ ቋንቋውና መፍትሄው እስርና አፈና ብቻ መሆኑ አስገራሚ እንደሆነ ስምምነት አለ።
የሰሞኑ አጀንዳ
“የጦር አውሮፕላን በመያዝ ኢህአዴግን ያመለጡ ወገኖች የመን አመቺ ብትሆንም እንደማይመርጧት ይናገራሉ። የመን ከቶውንም የማይታመን አገር እንደሆነ ሰፊ ግንዛቤ አለ። አቶ አንዳርጋቸው ታዲያ እንዴት ሰንአን ረገጡ? ምን ቀን ጣላቸው? እሳቸው በየመን ትራንዚት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ መረጃው እንዴት ደረሰ? ከሦስት ሳምንት በፊት ስለሚያደርጉት በረራ ማን? እንዴት? መረጃ አስተላለፈ? የሚሉት ጉዳዮች በዋናነት መመርመር ግድ ነው። ቀጣዩ የቤት ስራም ይህ ነው።” ይህ በኢሜል ከደረሰን በፖሊሲያችን መሰረት ከማናትመው ሰፊ ጽሁፍ የተቀነጨበ ነው። ጽሁፉ ሌሎች የበረራ አማራጮች ስለመኖራቸውም ያወሳል። አቶ አንዳርጋቸው በተያዙበት ቅጽበት ወደ አዲስ አበባ መላካቸውና በበነጋታው ሽያጩ በትዕዛዝ ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፖል የትራንስ ኢትዮጵያ ሸሪክ ድርጅት ስለመሆኑም ይጠቅሳል።
andargachew11ሠሞኑን እጅግ አነጋጋሪ የሆነው ይህንን ዜና ተከትሎ የተለያዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ቢከናወኑም የአንዳርጋቸው ጽጌ የጉዞ መርሃ ግብር አስቀድሞ ሊታወቅ የቻለበት አግባብ ሊመረመር እንደሚገባ የሚጠቁሙ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም። የየመን አቋም እየታወቀና ሌሎች አመራሮች ወደዚያ እንዳያመሩ ተከልክለው አቶ አንዳርጋቸው እንዴትና በምን የተለየ ምክንያት የመን ሊገቡ ቻሉ? የመንን ተደጋጋሚ የጉዞ በረራ መስመር አድርገው ለምን መጠቀም መረጡ? ለወደፊቱስ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል? የሚለው አሁን እየተከናወኑ ካሉት ተግባራት ጎን ለጎን ትግሉ ወደሌላ አቅጣጫ በመጓዙ በፊት ሊመረመር እንደሚገባው ጠንካራ ጥቆማዎች አሉ።
በኢህአዴግ እጅ ሆነው “እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ … እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው” ሲሉ የተደመጡት የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን “በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከታዩ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ብልህ ፖለቲከኞች አንዱ” ሲል ግንቦት 7 ይገልጻቸዋል። አንዳርጋቸው መያዛቸው ይፋ ከሆነ በኋላም ሆነ አስቀድሞ የሚመሩት ድርጅታቸውን ጨምሮ ከተለያዩ ድርጅቶችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ የየመንን መንግሥት የሚቃወሙ መግለጫዎች ተበትነዋል። ሁኔታው ያንገበገባቸው ወገኖች ተቃውሞ አሰምተዋል። እያሰሙ የሚገኙ አሉ። ዜግነት የሰጣቸው የእንግሊዝ መንግሥትም በየዓመቱ 300 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደጉመውን ኢህአዴግን ከዚህ ቀደም ሲል የተወሰነው የሞት ፍርድ ተግባራዊ እንዳይሆን እየተማጸነ መሆኑ ተሰምቷል።
ወ/ሮ የምስራች ሃ/ማርያም አስቀድመው ባለቤታቸው አቶ እንዳርጋቸውን በቴሌቪዥን መስኮት ለመመልከት ቢከብዳቸውም፣ ከተረጋጉ በኋላ ያዳመጡት የባለቤታቸው ንግግር የተለመደ መሆኑንን አመልክተዋል። የሶስት ልጆች እናት የሆኑትና አስራ አንድ ዓመት በትዳር አብረዋቸው የኖሩት ወ/ሮ የምስራች ባለቤታቸው ኢህአዴግ በሰየመው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል። ወ/ሮ የምስራች ለአሜሪካ ሬዲዮ በሰጡት አጭር መግለጫ አቶ አንዳርጋችው ወዲያው ወደ ኢትዮጵያ መወሰዳቸውን የእንግሊዝ መንግሥት ዘግይቶም ቢሆን እንዳረጋገጠላቸው አመልክተዋል።yemi
ወንድማቸው አቶ በዛብህ ጽጌ ከአሜሪካ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ ስለወንድማቸው የሚያወቁትን አብራርተዋል። በንግግራቸው ወንድማቸው ከራሳቸው ጋር ስለመታረቃቸው የተናገሩት “የቀረውን ራሳችሁ አድርጉ” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ገልጸዋል። በማያያዝም “ለፕሮፖጋንዳ የሚቀርብ” በማለት የወንድማቸው ንግግር ሁሌም እንደሚደረገው የተቆራረጠና ለተፈለገው ዓላማ እንዲመች የማድረግ ነገር ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ወንድማቸው አቶ አንዳርጋቸው በቅጽበት ወደ ኢትዮጵያ በመተላለፋቸው ሙሉ በሙሉ የእንግሊዝ መንግሥትን ነገሮችን የማጣራት ጊዜ እንኳን እንዲያገኝ አላስቻለውም ሲሉ ተደምጠዋል። የ1966 የተማሪዎች ንቅናቄ አባል የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ለራሳቸው ያልኖሩ ሰው እንደነበሩም አስታውቀዋል።
የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ሲናገሩ “እንደ አንዳርጋቸው ከራሱ ጋር የታረቀ ሰው አላየሁም … በእውነት በጣም እድለኛነት ነው እንዲህ ከውስጥ ከራስ ጋር መታረቅ” በማለት አስቀድመው የተናገሩትን አቶ አንዳርጋቸው በኢቲቪ ዜና እወጃ ላይ በተመሳሳይ “እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ … እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው” በማለት ተመሳሳይ ቃላትን/ሃሳብን በመጠቀም በኢቲቪ ላይ አስተያየት ሲሰጡ ተደምጠዋል።
ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ
ኢቲቪ ተለቅ ያሉ ጉዳዮች ሲገጥሙት በተደጋጋሚ ከፊት መስመር የሚሰለፈው ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ ነው። አቶ መለስ “በድንገት ቢያልፉም” በፖለቲካ ጉዳይ ታፍኖ የቆየውን ያረጀ ዜና እንደ አዲስ ይዞ የቀረበው ተመስገን ነበር። ተመስገን ጥቁር ልብስ አሰፍቶ፣ ጥቁር ስሜት ውስጥ ሆኖ፣ እምባ እምባ እያለው አቶ መለስ “ተሰዉ” ሲል የሃዘኑን ጥልቀት ከቶውንም ሊሸሸግtemesgen1የማይችል እንደነበር ወቅቱን የሚያስታውሱ የሚሰጡት ትዝብት ነው።
ሰሞኑን አቶ አንዳርጋቸው ተያዙ የሚለውን ዜና ለማቅረብ አሁንም ግንባር የሆነው ተመስገን፣ ዜናውን ሲያውጅ ልቡ በአፉ ሾልካ የምትወጣ እስክትመስል ደስታው ወደር አልነበረውም። ለፍረጃ የሚጠቀሙባቸውን ቃላቶች እየረገጠና እያጎላ፣ በኩራት መንፈስ አንዳርጋቸውን ጽጌ “እኔ አሁን ከራሴ ጋር ታርቄ ሰላም አግኝቻለሁ … እውነቴን ነው የምልህ ተረጋግቼ ያለሁበት ሁኔታ ነው” ሲሉ እንድንሰማ “ጋብዞናል”። ለሙያው ቀረብ ያሉ ለጎልጉል እንደገለጹት እንዲህ ያለው ወሬን ተከትሎ የሚፈራረቅ ስሜት ሙያውን የሚያረክስ ነው። ትንሽ ቆየት ቢልም ተመስገን መንገድ ላይ መደብደቡ የሚታወስ ነው።
ኢህአዴግ – የቂምና የበቀል “ገበሬ”
“ኢህአዴግ፣ በተለይም ዋናው የኢህአዴግ አስኳል ህወሃት ቂም በመዝራትና በቀል በመፈልፈል ቀዳሚ ነው” በሚል በተደጋጋሚ አስተያየትየሚሰጡ ክፍሎች በአገሪቱ እየተበራከተ የሄደው እስር፣ አፈና፣ ቶርቸር፣ ያልተመጣጠነ ኢኮኖሚያዊ “ወረራ”፣ የቅኝ ግዢ ይዘት ያለው አገዛዝና ከአገዛዙ ባህሪ በመነሳት እየተተገበሩ ያሉ “የወደፊት ዓላማን” ተገን ያደረጉ ክንዋኔዎች ህዝብን ሆድ ካስባሱ ዓመታት አልፈዋል።
በስደት አገራቸውን ለቀው ለመኖር የተገደዱ፣ በስደት አገር እንኳ ራሳቸውን መከላከል እየተሳናቸው ነው። በኬኒያ ኢህአዴግ ያሻውን እንዳያደርግ ከልካይ የለውም። ኬንያ ተጨማሪ የኢህአዴግ የስለላ መረብና የስለላ ሰራተኞች መፈንጫ ስለመሆኗ በርካቶች በምሬት የሚናገሩት ነው። አገር ጥለውና ሰሽተው ኬንያ የመሸጉ በህወሃት ታጣቂዎች ይያዛሉ፣ ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ፣ ስር ስር እየተከታተለ የሚያቀርበው የለም እንጂ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ታፍነው የሚወሰዱት ጥቂት አይደሉም።
ደቡብ ሱዳን ገድጋዳና እንብጭ መንግስት ከመሆኗ ጋር ተዳምሮ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንዳሻው የሚጋልብባትokello መናፈሻው እንደሆነች በርካታ ማስረጃ በመዘርዘር አስተያየት የሚሰጥበት ነው። በደቡብ ሱዳን የዓለም አቀፍ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ዘልቀው የፈለጉትን ማፈን ህወሃት ለሚመራው የአፈና መዋቅር እጅቅ ቀላል ጉዳይ ነው። የቀድሞውን የጋምቤላን ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎን በተመሳሳይ አፍኗል። በርካታ የጋምቤላ ወጣቶችም አሸባሪ በሚል ታፔላ ተለቅመዋል።
አገር ቤት እስር ላይ የሚማቅቁ ወገኖች ቁጥር ከቀን ወደቀን እያሻቀበ ኢህአዴግ የሚዘራው የጥላቻና የበቀል ስሜት እያጎነው ነው። በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ታሳሪዎች በምህረት ስም ቢለቀቁም በሚታወቁትና ሚስጥር በሆኑት ማጎሪያዎች የታፈኑ ወገኖች ቁጥር የሚቀንስ እንዳልሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የችግሩ ሰለባዎች ቢማጸኑም ሰሚ ጆሮ ባለማግኘታቸው በየቤቱ ቂም እየተወቀጠ ነው። በየዘመድ አዝማዱ ዘንድ ቂም እየተደለዘ ነው። በየቀዬው ቂም እየተላመጠ ነው። በየቦታው ቂም ያፈራው የበቀል ፍሬ ሊቀነጠስ እየተቃረበ ነው። በራሱ በኢህአዴግ ሟቹ መሪ አገላለጽ “ቂም ሊያተራምስ” ተቃርቧል በሚል ስጋታቸውን የሚገልጹ እያየሉ ነው።
እስካሁን የታሰሩትና ግፍ እየተፈጸመባቸው ያሉት ያነሱ ይመስል አሁንም እስር ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቅርቡ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ከሚሉት ክፍሎች ውስጥ መልካቸው ቀይረው ብረት ካነሱ ድርጅቶች ጋር የሚሰሩትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደሚሰራ ተናግረው ነበር። እንደተባለውም አቶ አንዳርጋቸው በየመን ታግተው ኢትዮጵያ ላይ ላለው አገዛዝ ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌውና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢና ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ እንዲሁም የዓረና ስራ አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይፋ ሆኗል። የታሰሩት የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮች እስካሁን ድረስ ክስ አልተመሰረተባቸውም። የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ በፖሊስ ከተያዙ በኋላ የት እንዳሉ እንኳ እንደማይታወቅ ድርጅታቸው አረናን በመጥቀስ አሜሪካ ራዲዮ ዘግቧል። ሚዲያ የማያውቃቸውን ቤታቸውና ወገናቸው ይቁጠራቸው።4 party officials 1
ምርጫ መጣ – የኢህአዴግ ምርጫም ቀደመ
ምርጫ በመጣ ቁጥር ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት 1997ን እያሰበ ብርክ ብርክ እንደሚለው የሚናገሩ በተለይ በወቅቱ አቶ መለስ ህመማቸው እንደጨመረ ይገልጻሉ። የስልት ችግርና ተራ የወንበር ጥማት አባዜ ድሉን እንደ ጉም አበነነው እንጂ ኢህአዴግ ዛሬ ላይ ሊኖር እንደማይችል የሚገልጹ ክፍሎች፣ ምርጫ ሲደርስ ኢህአዴግን የሚያጥወለውለው “ጠፍቼ ነበር” ከሚለው የሞት ያህል የሚከብድ ፍርሃት በመነሳት ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢህአዴግ እንደ ሸምዳጅ ተማሪ ምርጫን 99.6% በማምጣት እየነቀነቀ ማሸነፍ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም።
ለዚህም ውሳኔው አፈጻጸም እራሱ የፈለፈላቸው “ባለሃብቶች” ገንዘብ አሰባስበው ዘመቻ ያካሂዳሉ። ማታ ማታ የሚጠየፉትን የንብ አርማ ለብሰው ይተጋሉ። የተቀናቃኝ ፓርቲ ውስጥ ጎላ ያለ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ይለቀማሉ። ከዚህ ቀደም እንደታየው ሁሉ ህዝብን የሚገዛ ስብዕና ይኖራቸዋል ተብሎ የሚታሰቡትን መልቀም ይጀመራል። በተለመደው የፍርድ ሂደት “አሸባሪ” ተብለው እስር ቤት ይጣላሉ። ከምርጫ ጋር አብሮ የሚመጣው የኢህአዴግ ምርጫ እንዲህ አይነቱ ምርጫ እንደሆነ በርካቶች ይስማሙበታል።
በዘንድሮ ዓመት የተቀናቃኝ ፓርቲዎች የርስ በርስ ንትርክ በንጽጽር የቀነሰበት፣ ውህደት የታየበት፣ ከውጪ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባሉት አገሮችም ከወዲሁ ምርጫ ላይ ኮስተር የማለት እቅድ እንዳላቸው ምልክት የሰጡበትና ተቀናቃኞችን ወደ አንድ ህብረት እንዲመጡ ያሳሰቡበት በመሆኑ ኢህአዴግ የራሱን ምርጫ “እስር” አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፓርቲዎች ዘንድ ስጋት አለ።
“አገዛዝና” “መንግሥት” አልተለዩም
በአገር ውስጥም ሆነ ውጭ ባሉት ዘንድ ህወሃት/ኢህአዴግን እንደ ሕዝብ እንደሾመው አመራር “መንግሥት” እያሉ የሚጠሩት ጥቂቶች አይደሉም፡፡ አገር ውስጥ ያሉት ተቀናቃኝ ፓርቲዎች አማራጭ የላቸውም፣ ተገድደው ነው፣ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ላለመክተት ነው፣ … ቢባልም በውጭ የሚገኘው ተቃዋሚ ግን ይህንኑ አጠራር መከተሉ የሚያሳስባቸው ወገኖች ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከድርጅቶች በሚወጡ መግለጫዎችና ማሳሰቢያዎች ኢህአዴግን አብጠልጥለው እየወቀሱ “የህወሃት መንግሥት”፣ “የኢህአዴግ መንግሥት”፣ “የወያኔ መንግሥት”፣ የሚሉ ስያሜዎችን በንግግርም ሆነ በጽሁፍ መጠቀም እርስበርሱ የሚቃረን ሃሳብ ነው፡፡ ከዚያም ሲያልፍ በተለይ “መንግሥት” የሚለውን መሠረታዊ ሃሳብ ገደል የሚከትና ለህወሃት/ኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር ሥልጣን እንዳለው ዕውቅና የሚሰጥ ነው፡፡ በተለይ በውጭው ዓለም በሚገኙ ድርጅቶች ዘንድ የሚታየው ይህንን እንኳን ያላገናዘበ ተቃውሞ ፈጽሞ ሊስተካከል እንደሚገባው አስተያየታቸውን የሚሰጡ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ “ዱሮ ድልድይ ከማፍረስ ጀምሮ አሁን አገር የሚመራ ሽፍታ፣ ራሱ አሸባሪና ወንበዴ ነው፤ “መንግሥት” ሳይሆን በግድ በሕዝብ ላይ ራሱን የጫነ “አገዛዝ” ነው፤ ይህም አጠራር ሲበዛበት ነው” በማለት ተቃዋሚዎችም ሆኑ ሌላው ለህወሃት “መንግሥት” የሚለውን ቃል ከመጠቀም በመቆጠብ “አገዛዝ” በሚለው መተካት እንዳለባቸው ከአገር ውስጥ ለጎልጉል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
http://www.goolgule.com/how-andargachews-route-known/

Friday, July 11, 2014

በመጭው ምርጫ ከባድ ፈተና ሊገጥመን ስለሚችል ክወዲሁ መዘጋጀት አለብን ሲል ወያኔ አስታወቀ።

july 11th, 2014
” ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፈታተን መግጠም አለብን። ” የወያኔ ባለስልጣናት
” አላርፍ ካሉ ፍቃዳቸውን ሰበብ ፈጥረን እንነጥቃቸዋለን። ” የምርጫ ቦርድ ሃላፊ
በኢሕአዴግ ባለስልጣናት እና በምርጫ ቦርድ መካከል መጭውን ምርጫ በተመለከተ ሰፋ ያለ ዝግ ስብስባ ተካሂዶ ነበር ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አከባቢ የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። በአይቶ ጸጋዬ በርሄ የተንታለለ የመሃይማን ቢሮ ውስጥ የምርጫ ቦርድ ታዛዥ ሃላፊዎች እስከምሽት ድረስ ሲያደነቁሩ እና ሲደናቆሩ ያመሹት የወያኔ ባለስልጣናት በመጪው ምርጫ ሕዝቡ ፊቱ እንደሚያዞርባቸው ሳይሸሽጉ ለምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የወያኔ ባለስልጣናት ወደ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ ይዞ የሚመጣ ፓርቲ ካለ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሪፖርት ለኢሕአዴግ ቢሮ እንዲደረግ እና ፓርቲዎቹ የሚሰጣቸውን መልስ በተለያዩ ዘዴዎች በማዘግየት እንዲሰላቹ እንዲደረግ እንዲሁም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ እየገመግገ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ መድረክ እና ኢዴፓ ላይ ነገሮች እንዳይጠብቁ ሆኖም ግን በመድረክ የተሸሸገው ኢፌኮ የኦነግ ተቀጽላ ስለሆነ በኦሮሚያ ክልል ባሉ የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፎች በኩል ጥቃት መሰንዘር የሚሉ መመሪያዎች ይገኝባቸዋል።
የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሊቀመንብሩን ጨምሮ የተሰታቸውን መመሪያ የዋጡት ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በተመለከተ እንደከዚህ ቀደሙ ከኢሕ አዴግ የሚተላለፍላቸውን መመሪያ እንደሚተገብሩ እና ፓርቲዎቹ አላርፍ ብለው ከ እኩይ ተግባር ይማይቆጠቡ እና መንግስትን መዝለፋቸውን የሚቀጥሉ ከሆነ ሰበብ በመፍትር ምርጫ ቦርድ ፈቃዳቸውን እንደሚነጥቃቸው እና ከመንግስት የመጣውን መመሪያ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እንዲሁም ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን አቤቱታ ለኢሕ አዴግ ቢሮ ሪፖርት እንደሚይደርጉ ቃል ገብተዋል።

ወያኔ በመጭው ምርጫ ስጋት ስለገባው ጠንካራ ፖለቲክኞችን ከማሰር ጀምሮ እስከ ፓርቲዎች ፈቅድ ደከመንጠቅ እንደሚደርስ ይገመታል ፡ ለዚህም ተጠቂ የሚሆኑ አረና ኦፌኮ ሰማያዊ እና አንድነት ሲሆኑ ከመድረክ በወያኔ ደምወዝ የሚከፈላቸው በየነ ጴጥሮስ እና ቡድናቸው እንዲሁም ኢዴፓ እንደማይነኩ ሲታወቅ ኢሕ አዴግ ለምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ስም ዝርዝራቸውን በምስጢር የሚሰጣቸው ሰዎች ምርጫውን እንዳለፉ እንደሚደረግ ታውቋል። በምርጫ ቦርድ አከባቢ ያለውን ሁኔታ በተመለከት ዝርዝር መረጃዎች ስለሚኖሩ ይከታተሉ። 
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15204

ትግሉ የጥቂቶች ሳይሆን የሚሊዮኖች ነዉ።


http://www.youtube.com/watch?v=3vosVXUOMXM

Thursday, July 10, 2014

ሰላማዊ ዜጎችን ማሰር የሽንፈትና የደካማነት ምልክት ነው

july.10.2014

አገር ቤት ያሉ መሪዎች ቁርጠኝነት ያስደንቀኛል። ግርማ ሰይፉ «ለመታሰር እንዘጋጅ» አለ። ዳንኤል ተፈራ «ገዥዎች፣ እመኑኝ ባሮጌው መንገዳችሁ በርካቶችን ነፃነት ናፋቂዎች በሰፋፊ እስር ቤታችሁ ታጉሩ ይሆናል፡፡
ነገር ግን የዚህን ትውልድ የነፃነት መንፈስ ግን ልታስሩት አትችሉም» አለ። የፍኖት ዋና አዘጋጅ ነብዩ «ጨቋኞችን መታገል ፅድቅ እንጂ ኩነኔ እንደሌለው አምናለሁ፤ ጭቆናን እምቢ በማለቴ የምጠጣት እያንዳንዷ ፅዋ በፈጣሪ ዘንድ ወሮታ እንደምታከማችልኝም አምናለሁ፡፡ ፍርሀትን ብቻ እፈራለሁ» ሲለን፣ የአዲስ አበባ አንድነት ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ያሬድ አማረ ደግሞ «ወደኋላ አንመለስም። ዘመን ተሻጋሪ ወጣቶች በቅለናልና በምንም መልኩ ለሚደረግ ማዋከብ፤ እስራት እና ግድያ ከጀመርነው የሰላማዊ ትግል መስመር ስንዝር አያዘንፈንም፡፡ ደግሞም አምባገነኖች ባሉበት ሀገር የጀግና ቤቱ እስር ቤት አልያም መካነ መቃብር ውስጥ ሊሆንም እንደሚችል ስንጀምር ያለአስረጂ እናውቃለንና» በማለት የትግሉ ደረጃ ምን መስመር ላይ እንዳለ እቅጩን ይነግረናል።
አንድነት እና መኢአድ ሊዋሃዱ ዝግጅት ላይ ናቸው። በየክልሉ ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፎች ተቃዉሞዉን እያሰማ ነው። ሂዱ አዳማ፣ ሂዱ ወላይታ፣ ሂዱ ጎንደር፣ ሂዱ ደሴ ፣ ሂዱ ጂንካ፣ ሂዱ ጊዶሌ ….ሕዝቡ «በቃን፣ መረረን« እያለ ነው። ለ23 አመት የተዘራዉን የዘር መከፋፈል አረም እየነቀለ አንድ ነን እያለ ነው። «ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትምህክተኛ፣ ጠባብ….እያላችሁ አትከፋፍሉንም» እያለ ነው። የሚሊዮኖች ንቅናቄ ተጧጡፎ እንደሚጧጧፍ፣ የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት በስኬት እንደሚጠናቀቅ፣ የምርጫ ዘመቻና ዝግጅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ የአንድነት አመራሮች እየነገሩን ነው። አገዛዙ ዜጎችን በማሰር ትኩረት ለማስቀየር የሚያደርገውም ደባ አይሳካለትም።
ትላንት ብርቱካንን ሲያስሩ ያበቃ መሰሏቸው ነበር። ትላንት እስክንድርን ሲያስሩ ያበቃ መሰላቸው ነበር። ትላንት ርዮት አለሙን ሲያስሩ ያበቃ መሰላቸው ነበር…..ግን ተሳሳቱ። እነ ሃብታሙ አያሌው ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ዞን ዘጠኖች ….ብቅ አሉ። እነርሱን ደግሞ በጭካኔ እየደበደቡ ወደ ማእከላዊ ወሰዱ። ሚሊዮኖች ግን ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። «የነፃነት ታጋዮችን በማሰር የወጣችው የኢትዮጵያዊነት ፀሀይ ትደምቃለች እንጂ አትጠፋም» እንዳለ ዳዊት ሰለሞን ፣ ገዥው ፓርቲ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰሩ ደካማነቱን፣መክሰሩን፣ መሸነፉን ፣ መደንገጡን በአንድ በኩል እያመላከተ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ትንሳኤ መቅረቡን የሚያሳይ ነው።
አንድ በሳል መሪ፣ ችግሮች ሲፈጠሩ፣ ችግሮቹን በዉይይት፣ ሌሎችን በማሳመን፣ ኮምፕሮማይዝ በማድረግ ለመፍታት ይሞክራል። ያኮረፈዉን፣ የሚቃወመዉን፣ ሸፍቶ ነፍጥ ያነሳዉን ለማግባባትና ወደ እርሱ ለማምጣት ይሞክራል። ተቃዉሞ የሚያቀርቡትን፣ የተለያየ ስም እየሰጠ ለማጥፋት አይሞክርም። የኢሕአዴግ መሪዎች፣ እያደረጉ ያሉት ነገር ቢኖር ግን፣ አንድ በሳል መሪ ማድረግ ያለበትን ሳይሆን፣ የአንድነት ፓርቲ መግለጫ እንዳስቀመጠው፣ መንግስታዊ ዉንብድናን ነው። መንግስት እንደ አባት ነበር የሚታየው። ዜጎችን ማክበር፣ ማገልገል ይጠበቅበታል። የዜጎችን ጥቅም በአገር ዉስጥ ሆነ ከአገር ዉጭ ለማስከበር ይተጋል። የኛዎቹ የኢሕአዴግ መሪዎች ግን፣ ዜጎችን እያሸበሩ ነው። ኢትዮጵያዉያንን እያስፈራሩና እያዋረዱ ነው። ጨካኞች፣ ግትሮች፣ ለሰብእና ከበሬታ የሌላቸው፣ ሕግን እየጠመዘዙ፣ ፍርድ ቤቶችን በካድሬ ዳኞች እየሞሉ፣ የዉሸት ምስክር እያቀረቡ ዜጎችን የሚያንገላቱ፣ ያለነርሱ አዋቂ፣ ያለነርሱ ኢኮኖሚስት፣ ያለ እነርሱ ኢንጂነር፣ ያለ እነርሱ የሕግ አዋቂ ያለ አይመስላቸውም። እነርሱን የሚቃወም ሁሉ «አሸባሪ» ነው።
ኤሚ ሰለሞን የምትባል ብሎገር «ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ለምን ጻፋቹህ ? ለምን ያገባናል አላችሁ ? ተብለው በየእስር ቤቱ የታጎሩትና በየጊዜው እያንጠለጠሉ የሚወስዷቸው ስንት ናቸው ? ስንቱን ከሃገር አሰደዱ ? ማነው አሸባሪው ታዲያ ?» ብላ እንደጠየቀቸው፣ በአገራችን የሽብር ተግባር እየፈጸመ ያለው ኢሕአዴግ እራሱ ነው።
«እፎይ! ካሁን በኋላስ መቼም ቢሆን ከደርግ የከፋ መንግስት ሊመጣ አይችልም’ ብለን ነበር። ከ23 ዓመት በፊት . .» እንዳለው ኩሪ ሀገሬ የተባለ ብሎገር፣ ከ23 አመት በፊት፣ ብሶት የወለደው የኢሕአዴግ ሰራዊት ፣ አዲስ አበባ ሲገባ እና ለሰፊዉ ሕዝብ ጥቅም የኢትዮጵያን ራዲዮን እና ኢቲቪ ሲቆጣጠር ፣ ቢያስን የተሻለ ነገር ይመጣል ብለን ነበር። ዳሩ ግን ቅሉ፣ ከፈረንጆች በልመና በተገኘ ገንዘብ ግንብና ፎቅ እየሰሩ፣ ክብራችንን፣ ስብእናችንን፣ ነጻነታችን ገፈው በአገራችን ባሪያ ሊያደርጉን የሞት ሽረት እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።
ነገር ግን አሁን ከ10 አመት፣ ከ15 አመት በፊት እንደነበረው አይደለም። ሕዝቡ መሮታል። የግፍ ቀንበርን ለመታገስ አይችልም። ኢትዮጵያ እሳት የለበሱ፣ ወኔ የሞላባቸው፣ ነፍጥ ሳይጨብጡ ጀግንነት ለመስራት የተዘጋጁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዳግማዊ ጣይቱዎች አሏት። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዳግማዊ ባልቻ አባ ነፍሶዎች አሏት። የሚሊዮኖችን ኃይል ደግሞ ሊቋቋም የሚችል ምንም ኃይል አይኖርም።
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15164

Wednesday, July 9, 2014

ደሚት በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አስመርቆ ለትግል ማዘጋጀቱን አስታወቀ (ቪዲዮ ይዘናል)



https://www.youtube.com/watch?v=R9rYKScsdDM#t=73

አንበሳውን በጅቦች ተከቦ አየሁት (ነቢዩ ሲራክ)

july.9.2014
ኢቲቪ የአንዳርጋቸው ንግግር ነው ብሎ ያቀረበው ፊልም አስቂኝ ነው። እንደነ ቢቢሲ በኮርፖሬሽን ደረጃ ለመዋቀር በቃሁ የሚለው ድርጅት በሴኩርቲ ( በድብቅ )ካሜራ የተቀረጸ የደበዘዘና የተቆራረጠ ፊልም ሲያቀርብ ማፈር ነበረበት።
አንዳርጋቸው ከተያዘ 2 ሳምንታት አለፉ። ዛሬ በድብቅ ካሜራ ተቀርጾ የተላለፈው ፊልም በእለቱ ኢትዮጰያ ሲገባ የተቀረጸ ነው – አለማቀፍ ግፊት ቢበዛብን እናሳየዋለን ብለው ቀርጸው ያስቀመጡት ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግን አንዳርጋቸው እያንዳንዷን ቀን በድብደባ እያሳለፈ ነው። ኢቲቪ ልብ ካለው አንዳርጋቸውን ላይቭ(Live) ያሳየን።
አንበሳው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውል አንድም ነገር አልሰጣቸውም። “እኔ ስራየን ጨርሼ ደክሞኛል፣ እረፍት እፈለግ ነበር” ነው ያለው፤ ይህንን ደግሞ ዶ/ር ብርሃኑ ና ንቅናቄው አስቀድመው ተናግረውታል- አንዳርጋቸው ስራውን በጊዜ አጠናቆና ሃላፊነቱን ለወጣት አመራሮች ሰጥቶ እሱ መጠነኛ የዲፕሎማሲ ስራ እየሰራ ነበር።
ህወሃቶች በደንፎ “የትግራይን ህዝብ ትጠላለህ?” ብለው ጠየቁት። “ለማንም ህዝብ ጥላቻ የለኝም” ብሎ መለሰላቸው። አንዳርጋቸው የትግራይን ህዝብ ከጉጅሌው እንለየው የሚል ጽኑ አቋም ነበረው፣ያንን ነው የደገመው።
የታዩትን ፎቶግራፎች ድሮም አውቃቸዋለሁ፤ ከላፕቶፑ የተወሰዱ ናቸው። በእዚህ እድሜው የአውሮፓ ህይወቱን ትቶ በዛ አይነት ህይወት ለመኖር መፍቀዱ የሚደነቅ ነው። የእኔንም ኮምፒዩተር በቫየረስ በከሉት እንጅ እነዚህና ሌሎች ፎቶዎችም ነበሩኝ።
ፈገግታና ደግነት ደግሞ ባህሪው ነው። ጠላቶቹን ሳይቀር በፈገግታው ይገላቸዋል።
ከሁለት ሳምንት ድብደባ በሁዋላ ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ነገር አለማግኘታቸው ሃረር ውስጥ በጅቦች ተከቦ አልበላም ብሎ ሲታገል የነበረውን አንበሳ አስታወሰኝ።
ኮራሁብህ ወንድሜ አንዲ።
ትናንትን ያስታወሱኝ ትናንትና ዛሬ
ሜጀር ጄኔራል ፋንታ በላይ …

ግንቦት 8/1981 በደርግ የመጨረሻ አመታት መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ ከሸፈ። የመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሽ የተባሉት ሃገሪቱ በከፍተኛ ወጭ ያስተማረቻቸው ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች የተወሰኑት ሲሰው የቀሩት በቁጥጥር ስር ዋሉ። ዛሬ ላይ ሆኘ በጎልማሳ እድሜየ ከጋዜጠኛ ወንድሜ ጋር ስኖር እኔም እጋራቸው የነበሩ መረጃዊችን እና ያችን ቀን ሳስታውሳት ልዩ ስሜት ይሰማኛል ። ያ ስሜት ዛሬ አቶ አንዳርጋቸውን በኢቲቪ ጎስቁለው ሳያቸው በአይነ ህሊናየ የተከበሩት ሜጀር ጄኔራል ፋንታ በላይን አስታወስኩ: (
ሜጀር ጄኔራል ፋንታ አፈር መስለውና ገርጥተውና ፊታቸው ክችም ብሎ በቁጥጥር ስር ውለው ለመርማሪዎች በሰጡት ቃል ጦርነቱን ለማስቆም ብቸኛው አማራጭ አስተዳደሩን መቀየር ውጭ ሌላ መንገድ የለውም ብለው ኩዴታውን እንዳቀነባበሩ በድፍረት ተናገሩ ! ሜጀር ጀኔራል ፋንታ በላይ በሃገሪቱ ከፍተኛ የሚባሉትን ስልጣኖች የጨበጡ ፣ ኑሯቸው የተደላደለላቸው ቢሆንም ለኢትዮጵያ መጻኢ ሰላም ሲባል መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ መነሳሳታቸውን ሳይደብቁ ታሪካው ምላሽ ነበር !
ሐምሌ 13 ቀን 1981 ዓም ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በደርግ ሳንባ የሚተነፍሱት ራዲዮና ቴሌቪዥኑ “… የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያቀናበሩት ከሀዲው ጄኔራል ፋንታ በላይ ጠባቂያቸውን በካራቴ መትተው ለማምለጥ ሲሞክሩ በሌሎች ዘቦች ተገደሉ” ብሎ የታላቁን ጀኔራል ሞት አረዳን: (
የደከሙ የተጎሳቆሉ አቶ አንዳርጋቸውን ጸጋን ንግግር ማምሻውን ከኢቲቪ ብሰማ ሜጀር ጀኔራል ፋንታ በላይን አስታወሰኝ ! ትናንት ጀኔራል ፋንታ የሞቱላት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ዛሬው ልጆቿን እየበላ ነው: ( ይህ ሂደት የት ላይና መቸ እንደሚቆም ያሳስበኛል ኢትዮጵያን አምላክ ይታረቃት … ብየ ጎኔን አሳረፍኩ
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/32266