Friday, July 11, 2014

በመጭው ምርጫ ከባድ ፈተና ሊገጥመን ስለሚችል ክወዲሁ መዘጋጀት አለብን ሲል ወያኔ አስታወቀ።

july 11th, 2014
” ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፈታተን መግጠም አለብን። ” የወያኔ ባለስልጣናት
” አላርፍ ካሉ ፍቃዳቸውን ሰበብ ፈጥረን እንነጥቃቸዋለን። ” የምርጫ ቦርድ ሃላፊ
በኢሕአዴግ ባለስልጣናት እና በምርጫ ቦርድ መካከል መጭውን ምርጫ በተመለከተ ሰፋ ያለ ዝግ ስብስባ ተካሂዶ ነበር ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አከባቢ የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። በአይቶ ጸጋዬ በርሄ የተንታለለ የመሃይማን ቢሮ ውስጥ የምርጫ ቦርድ ታዛዥ ሃላፊዎች እስከምሽት ድረስ ሲያደነቁሩ እና ሲደናቆሩ ያመሹት የወያኔ ባለስልጣናት በመጪው ምርጫ ሕዝቡ ፊቱ እንደሚያዞርባቸው ሳይሸሽጉ ለምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የወያኔ ባለስልጣናት ወደ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ ይዞ የሚመጣ ፓርቲ ካለ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሪፖርት ለኢሕአዴግ ቢሮ እንዲደረግ እና ፓርቲዎቹ የሚሰጣቸውን መልስ በተለያዩ ዘዴዎች በማዘግየት እንዲሰላቹ እንዲደረግ እንዲሁም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ እየገመግገ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ መድረክ እና ኢዴፓ ላይ ነገሮች እንዳይጠብቁ ሆኖም ግን በመድረክ የተሸሸገው ኢፌኮ የኦነግ ተቀጽላ ስለሆነ በኦሮሚያ ክልል ባሉ የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፎች በኩል ጥቃት መሰንዘር የሚሉ መመሪያዎች ይገኝባቸዋል።
የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሊቀመንብሩን ጨምሮ የተሰታቸውን መመሪያ የዋጡት ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በተመለከተ እንደከዚህ ቀደሙ ከኢሕ አዴግ የሚተላለፍላቸውን መመሪያ እንደሚተገብሩ እና ፓርቲዎቹ አላርፍ ብለው ከ እኩይ ተግባር ይማይቆጠቡ እና መንግስትን መዝለፋቸውን የሚቀጥሉ ከሆነ ሰበብ በመፍትር ምርጫ ቦርድ ፈቃዳቸውን እንደሚነጥቃቸው እና ከመንግስት የመጣውን መመሪያ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እንዲሁም ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን አቤቱታ ለኢሕ አዴግ ቢሮ ሪፖርት እንደሚይደርጉ ቃል ገብተዋል።

ወያኔ በመጭው ምርጫ ስጋት ስለገባው ጠንካራ ፖለቲክኞችን ከማሰር ጀምሮ እስከ ፓርቲዎች ፈቅድ ደከመንጠቅ እንደሚደርስ ይገመታል ፡ ለዚህም ተጠቂ የሚሆኑ አረና ኦፌኮ ሰማያዊ እና አንድነት ሲሆኑ ከመድረክ በወያኔ ደምወዝ የሚከፈላቸው በየነ ጴጥሮስ እና ቡድናቸው እንዲሁም ኢዴፓ እንደማይነኩ ሲታወቅ ኢሕ አዴግ ለምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ስም ዝርዝራቸውን በምስጢር የሚሰጣቸው ሰዎች ምርጫውን እንዳለፉ እንደሚደረግ ታውቋል። በምርጫ ቦርድ አከባቢ ያለውን ሁኔታ በተመለከት ዝርዝር መረጃዎች ስለሚኖሩ ይከታተሉ። 
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15204

1 comment:

  1. በመጭው ምርጫ ከባድ ፈተና ሊገጥመን ስለሚችል ክወዲሁ መዘጋጀት አለብን ሲል ወያኔ አስታወቀ።
    #Ethiopia #Election2015 #EPRDF #UDJ #Blueparty #Medrek #Arena

    " ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፈታተን መግጠም አለብን። " የወያኔ ባለስልጣናት
    " አላርፍ ካሉ ፍቃዳቸውን ሰበብ ፈጥረን እንነጥቃቸዋለን። " የምርጫ ቦርድ ሃላፊ

    Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
    በኢሕአዴግ ባለስልጣናት እና በምርጫ ቦርድ መካከል መጭውን ምርጫ በተመለከተ ሰፋ ያለ ዝግ ስብስባ ተካሂዶ ነበር ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አከባቢ የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። በአይቶ ጸጋዬ በርሄ የተንታለለ የመሃይማን ቢሮ ውስጥ የምርጫ ቦርድ ታዛዥ ሃላፊዎች እስከምሽት ድረስ ሲያደነቁሩ እና ሲደናቆሩ ያመሹት የወያኔ ባለስልጣናት በመጪው ምርጫ ሕዝቡ ፊቱ እንደሚያዞርባቸው ሳይሸሽጉ ለምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

    የወያኔ ባለስልጣናት ወደ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ ይዞ የሚመጣ ፓርቲ ካለ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሪፖርት ለኢሕአዴግ ቢሮ እንዲደረግ እና ፓርቲዎቹ የሚሰጣቸውን መልስ በተለያዩ ዘዴዎች በማዘግየት እንዲሰላቹ እንዲደረግ እንዲሁም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ እየገመግገ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ መድረክ እና ኢዴፓ ላይ ነገሮች እንዳይጠብቁ ሆኖም ግን በመድረክ የተሸሸገው ኢፌኮ የኦነግ ተቀጽላ ስለሆነ በኦሮሚያ ክልል ባሉ የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፎች በኩል ጥቃት መሰንዘር የሚሉ መመሪያዎች ይገኝባቸዋል።

    የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሊቀመንብሩን ጨምሮ የተሰታቸውን መመሪያ የዋጡት ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በተመለከተ እንደከዚህ ቀደሙ ከኢሕ አዴግ የሚተላለፍላቸውን መመሪያ እንደሚተገብሩ እና ፓርቲዎቹ አላርፍ ብለው ከ እኩይ ተግባር ይማይቆጠቡ እና መንግስትን መዝለፋቸውን የሚቀጥሉ ከሆነ ሰበብ በመፍትር ምርጫ ቦርድ ፈቃዳቸውን እንደሚነጥቃቸው እና ከመንግስት የመጣውን መመሪያ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እንዲሁም ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን አቤቱታ ለኢሕ አዴግ ቢሮ ሪፖርት እንደሚይደርጉ ቃል ገብተዋል።

    ወያኔ በመጭው ምርጫ ስጋት ስለገባው ጠንካራ ፖለቲክኞችን ከማሰር ጀምሮ እስከ ፓርቲዎች ፈቅድ ደከመንጠቅ እንደሚደርስ ይገመታል ፡ ለዚህም ተጠቂ የሚሆኑ አረና ኦፌኮ ሰማያዊ እና አንድነት ሲሆኑ ከመድረክ በወያኔ ደምወዝ የሚከፈላቸው በየነ ጴጥሮስ እና ቡድናቸው እንዲሁም ኢዴፓ እንደማይነኩ ሲታወቅ ኢሕ አዴግ ለምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ስም ዝርዝራቸውን በምስጢር የሚሰጣቸው ሰዎች ምርጫውን እንዳለፉ እንደሚደረግ ታውቋል። በምርጫ ቦርድ አከባቢ ያለውን ሁኔታ በተመለከት ዝርዝር መረጃዎች ስለሚኖሩ ይከታተሉ።#ምንሊክሳልሳዊ

    ReplyDelete