Thursday, September 25, 2014

“ኣብራሃ ደስታን ኣላሰርኩም” የመቐለ ህወሓት (አምዶም ገብረስላሴ – ከትግራይ)

Sep.25.2014
የትግራይዋ ህወሓት ማለቴ በሰማእታት ሓወልት ፅሕፈት ቤትዋ ያደረገችው ህወሓት( ኣዲስ ኣበባ የህወሓት ኣንጃ ሰላለች ነው) “ኣብራሃ ደስታ የታሰረበት ምክንያት ኣላውቅምኣለች።

ይህ ኑዛዜ የተሰማው በኣገር ደረጃ ለመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና የሚሉት(ተቃዋሚና ያለፉት ስርዓቶች የሚሰድቡበት መድረክ ስለመሰለ ነው) በትግራይ ክልል ፅህፈት ቤት(ደጀን ቢሮ) የሚሰሩ ሰራቶኞች በፕላኔት ሆቴል እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው።

በዚህ መድረክ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎችና ሃሳቦች እጅጉን ጠንካሮችና የህወሓት ተራ ኣባላትና ጥቂት ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ፍፁም ታላቅ ልዩነት መነሩ የሚያሳዩ ናቸው።

በዚህ መድረክ “…ኣብራሃ ደስታ ህገ መንግስት የስጠው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን በኣግባቡ በመጠቀሙ ለምን በሽብር ኣምካኝታቹ ኣሰራቹት?…” ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ነው የመቐለዋ ህወሓት ኣብራሃን እንዳላሰረችናየማሳሰርያው ምክንያትም ኣላውቅምብላ የካደችው።

ስብሰባው እየመሩት የነበሩት የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ “..ስለ ኣብራሃ ደስታ መታፈንና መታሰር በፌስቡክ ስሰማ በቀጥታ ወደ ህወሓት ቢሮ ሂጀ ኣነጋጋርኳቸው። ከህወሓት ፅህፈት ቤት ያገኘሁት መልስ ምንም የሚያውቁት እንደሌለና ህወሓት እንዳላሳሰረው ረግረውኛል..” ሲሉ በስብሰባው ገልፀዋል።

ኣብራሃ ደስታን የመቐለዋ ህወሓት ካላሳሰርችው ሌላዋ ተጠያቂ የኣዲስ ኣበባዋ የህወሓት ኣንጃ ናት ማለት ነው።
ከፍተኛ ቁጣ የተላበሰው የፕላኔት ሆቴል ተስብሳቢ ህዝብ ለህወሓት መሪዎች ኣስፈሪ ነበር።

ኣገሪትዋ እየበጠበጥዋት ያሉት መላ የህወሓት ኣባላት ሳይሆኑ የተወሰኑና ጥቂት ሰዎች መሆናቸው በግልፅ በመላ ትግራይ ያሉ ስብሰባዎች የተነሱ ሃሳቦች ቁልጭ ኣድረገው እያሳዩ ናቸው።


ሌላው ከፍተኛ የመወያያ ኣጀንዳ በዓረና ኣባላት እየደረሰ ያለው ዓፈና፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ኣማራጭ ሃሳብ ወደ ህዝቡ እንዳይቀርብ ማደናቀፍ የኣዲስ ኣበባዋ ኣንጃ ሳትሆን የመቐለዋ ኣንጃ ስራ መሆኑ በግልፅ ተነግራቸዋል።

http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15811

Wednesday, September 24, 2014

ስዊድን የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

ኢሳያስ አፈወርቂ ጉዳዩ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው አሉ

ስዊድንና ኤርትራ በዲፕሎማቲክ የእሰጣ እገባ ውስጥ ከገቡ በርከት ያሉ ጊዜያት የተቆጠሩ ሲሆን በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ባልተገባ ተግባር ተገኝተዋል በሚል የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ስዊድንን በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ የስዊድን መንግስት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ እጅ አለበት ብለዋል። 


በስዊድን የወጣውን አዲስ ሕግ ተከትሎ የስዊድን መንግስት በኤርትራ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ላይ በዚያው በስዊድን ክስ መመስረቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሻክሯል።

የኤርትራ መንግስት ዋነኛ የውጪ ምንዛሪ ገቢ በተለያዩ ሀገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ላይ የጣለው ሁለት በመቶ የገቢ ታክስ ሲሆን በድርጊት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኤርትራውያን በኢምባሲያቸው ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። በስዊድን የሚገኙ ኤርትራውያንም ኢምባሲያቸው የሚጠበቅባቸውን የታክስ መጠን ካልከፈሉ የተለያዩ የዜግነትና የጉዞ ዶክመንቶችን ከመከልከል ባለፈ በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በማያዣነት ተጠቅሞ እስከማስፈራራት ደርሷል በሚል ለስዊድን መንግስት ክስ ሲያሰሙ መቆየታቸው ታውቋል።

 የኤርትራ መንግስት በስዊድን በሚገኙ ኤርትራውያን እና የስዊድን ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኤርትራውያን የተደራጀ ተቃውሞ እየገጠመው ሲሆን የተቃውሞ አደራጅ ግለሰቦችን ለይቶ ለመከታተል በስዊድን የሚገኘውን ኤምባሲውን እና ዲፕሎማቶችን ይጠቀማል በሚልም ጭምር ነው የስዊድን ባለስልጣት የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ለማባረር በምክንያትነት ያስቀመጡት።


የኤርትራ መንግስት በየሀገሩ በሚገኙ ኤምባሲዎቹ አማካኝነት ከኤርትራ ዲያስፖራዎች በታክስ መልኩ በሚሰበሰበው ሁለት በመቶ ገቢ ሽብርተኞችና በፋይናንስ እያገዘ ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አማካኝነት ማዕቀብ ከተጣለበት ዓመታት ተቆጥረዋል።

 ሆኖም ከማዕቀቡ በኋላ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግስት በተለያየ ሀገራት ኤምባሲዎች በኩል ታክሱን ለመሰብሰብ የሚያደርገው ሙከራ በየሀገራቱ መንግስታት ተቃውሞ እያስነሳበት ነው። ከዚህ ቀድም በተመሳሳይ መልኩ ካናዳና ኤርትራ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የካናዳ መንግስት በቶሮንቶ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን በ48 ሰዓታት ውስጥ እስከማባረር ደርሷል።


የስዊድን እርምጃ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው ብለውታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የኤርትራ መንግስት ሁለት በመቶ ታክሱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በሽብርተኝነት ለማተራመስ ይጠቀምበታል በሚል ማዕቀቡ እንዲጣልበት ሰፊ የዲፕሎማሲ ሚናን መጫወታቸውን በምስራቅ አፍሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ጂስካ አፍሪካ ኦንላይን ዘግቧል።

 (ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34808

Tuesday, September 23, 2014

የህወሓት ትውልድ ገዳይ ስውር መርዝ

አሁን እጅግ በላቀ የዕድገት ደረጃ ሆኖው የሚናያቸው የአለም አገራት መሰረታቸው እውቀት ነው::ያለ እውቀት ፈጠራና ምርምር÷ጥበብና ክህሎት÷ዕድገትና ልማት ሊኖሩ አይችሉም::

ትምህርት የእውቀት ቤት ነው:: እውቀት ካለ ደግሞ ምክንያትነት አለ:: ምክንያትነት ካለ ደግሞ ምርምርና ጥናት አለ::ምርምር ካለ ደግሞ መጠየቅ አለ:: መጠየቅ ካለ ደግሞ መከራከርና መወያየት አለ:: መከራከር ካለ ደግሞ የለውጥ መንገድ አለ:: የለውጥ መንገድ ካለ ደግሞ ዕድገት አለ!!!!


ህወሓት ገና በረኻ ደደቢት እያለች 1973 “የወደፊት የኔ ጠላት ሙሁሩ ክፍል ነው” ማለቷም “የኔ ጠላት ዕውቀት ነው” ከሚል ሐሳብ ጥልቅ የሆነ ግንኙነት አለው::በአሁኑ ዘመን ትምህርት ምላሷ እንጂ ተክለ ሰውነቷ(ቁመናዋ) የለም ማለት ይቻላል:: ይህ ማለት ደግሞ የዕውቀት ግንብ ፈርሷል ማለት ነው::ይህ ማለት ደግሞ የጥበብና የምርምር ቤት ተንዷል ማለት ነው::ይህ ማለትም ምክንያታዊ አስተሳሰብና ግንዛቤ ቀብሮ አገርን ያለ ጠያቂና ተጠያቂ በማስቀረት የለውጥ ድልድይ እንዳይሰራ ያደርጋል::አሁን እያየነው ያለነውም ይህ ነው::


በህወሓት ዘመነ ስልጣን ብዙ ሙሁራን ደብዛቸውን ጠፍቷል::ወህኒ ቤት(ጓንታናሞ) ወርዷል::አገራቸውን ለቀው በባዕድ አገር ሰፍሯል::ይህ ማለት ደግሞ የህወሓት/ኢህአዴግ የዕቀት ጠላትነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታዎት ነው::

ህወሓት በእውነት ለኢትዮጵያ ዕድገት ከልብ የሚቆረቆር ቢሆን ኖሮ አሁን ያለው እጅግ የሞተ የትምህርት ጥራት አስተካክሎ ትውልድን የዕውቀት ባለቤት አድርጎ የምርምር ማዕበል በመክፈት ለውጣዊ የዕድገት መንገድ መስራት በቻለ ነበር:: ዳሩ ግን ይህ አይደለም::

የህወሓት ዋና አለማ ከጅምሩ የትምህርት ጥራትን በማበላሸት የትውልድ የእውቀት ጥይትን በመቅበር አገር ያለ ምንም ጠያቂና ተጠያቂ በማስቀረት ዘላለማዊ አምባገነናዊ ስልጣን መቆናጠጥ ነው::ይህ እባባዊ ጥቁር ሴራ “ለህዝብ ኑሮ ለህዝብ የሞተ አገራዊ÷አህጉራዊና አለማዊ ምጡቅ መሪ”እየተባሉ የተሞካሹ የአቶ መለስ ዜናዊ ነው:: አቶ መለስ ዜናዊ የትውልድ የእውቀት ጥይት ለመቅበር የእውቀት አባት የሆኖውን ‘መምህር’ ክብሩን ዝቅ አድርገው በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማያቅ አኳሃን አድቅቀውና አመንምነው አረከሱት::የእኝህ ሰው ታላቁ ጥቁር አስተሳሰብም መነሻው ይህ ነው::ትውልድ ገዳይ ስውር መርዝም ይህ የእውቀት ጠላትነት ነው!!


በአሁኑ ዘመን መምህርና ትውልድ ላይገናኙ አብረው እየተራመዱ ነው::እውቀትና ትውልድም በጣም ተራርቋል::የዕውቀት ድልድይ ተንዳለች::የትውልድ አስተሳሰብም በእጅጉ ወርዷል::የለውጥ ሻማም ጠፍታለች::


ኢትዮጵያ የትምህርት አብዮት ያስፈልጋታል::የዕውቀት አብዮት ያስፈልጋታል::የጥበብና የምርምር አብዮት ያስፈልጋታል::የባህል አብዮት ያስፈልጋታል::ይህን ሳታደርግ ዕድገት ልታመጣ አትችልም::ኢትዮጵያ በድንጋይ ሳይሆን በእውቀት መገንባት አለባት::በምላስ ሳይሆን በተግባር መገንባት አለባት::በዘፈቀደ ሳይሆን በምርምርና በጥበብ መገንባት አለባት::

ህወሓት በአሁኑ ጊዜ የት እንደነበረ÷አሁን የት እንዳለ÷ለወደፊት ወዴት እየሄደ እንዳለ በእውን ለይቶ የማያቅ የምክንያታዊ አስተሳሰብ መኸን ትውልድ እያፈራ ይገኛል:: ይህም ዛሬ ኢትዮጵያ በካድሬው÷ ነገ ደግሞ በካድሬው ልጆች መመራቷ የማይቀር ነው ማለት ነው::


ይህ የህወሓት ጥቁርና የማይረባ አጉል አስተሳሰብ(የእውቀት ጠላትነት) እስካልተወገደ ድረስ “ኢትዮጵያ መካክለኛ ዕድገት ካላቸው አገራት ትቀላቀላለች” ማለትም ከንቱ ምኞት(ቅዠት) ከመሆን የሚያልፍ አይደለም::………..


http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34765

Monday, September 22, 2014

ወያኔ ከነዋይ ደበበ ጋር በስዊድን ያዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት በኪሳራ ተመታ፤ በጀርመንም ይቀጥላል

በሃገረ ስዊድን በትናንትናው ዕለት ወያኔ ነዋይ ደበበን ተጋባዥ ድምፃዊ አድርጎ ያዘጋጀው የሙዚቃ ምሽት በታዳሚ እጦት ተመታ። ነዋይ ደበበ ከፍተኛ የሞራል ድቀት እንደደረሰበትም ጉዳዩን በቅርብ ይከታትሉ የነበሩ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል። ነዋይ በጀርመንም እንዲሁ ኦክቶበር 4 ከፍተኛ ቦይኮት እንደሚገጥመው በዛው ያሉ ኢትዮጵያውያን አስታውቀዋል።
በውጭ ሃገር የሕወሓት መንግስትን እየደገፉ በሙዚቃ ኮንሰርትና በሌሎች የትያትር ዝግጅቶች ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚመጡ አርቲስቶችን ሕዝቡ ቦይኮት እየጠራባቸው ሲህን ከዚህ ቀደም በጀርመን ማዲንጎ አፈወርቅ በተመልካች ድርቅ ተመቶ ወደ ሃገር ቤት ተመልሷል። ሃመልማል አባተም በዋሽንግተን ዲሲ ለሲዲ ምርቃት ያዘጋጀችው ኮንሰርትም እንዲሁ በተመልካች ድርቅ የተመታ ሲሆን፤ ሸዋፈራው ደሳለኝ በበኩሉ በደረሰበት ከፍተኛ ተቃውሞ የኮሚዲ ዝግጅቱን ሳያቀርብ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

“ነዋይን ነዋይ አሳሳተው” በሚል በተደጋጋሚ የሚተቸው ድምጻዊው በስዊድን የሕወሓት አስተዳደር በጠራው ኮንሰርት ላይ እንደሚገኝ ፍላየር ከተበተነ ጊዜ ጀምሮ በዚያው ሃገር የሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በመሰባሰብ የቦይኮት ፍላየሮችን በማዘጋጀት ሲቀስቀሱ ሰንብተዋል። በዚህም መሠረት ነዋይ ትናንት ምሽት የሕዝቡን ተቃውሞ በመፍራት ተደብቆ በመግባት ዝግጅቱን ያቀረበ ሲሆን መድረክ ላይ ሲወጣ የጠበቀው የሕዝብ ቁጥር ከ50 የማይበልጥ በመሆኑ እጅጉን ማፈሩን አብረውት የነበሩ የቅርብ ምንጮች ገልጸውልናል። በዚህ ኮንሰርት ላይ የተገኙት 50 የማይሞሉት ሰዎችም የኢምባሲ ሰራተኞች እና አንዳንድ ከኢትዮጵያ መንግስጥ ጥቅማትቅም የሚያገኙ ሶማሌዎች እንደሆኑ ምንጮቻችን ገልጸዋል። እንደነዚሁ የቅርብ ምንጮች ገለጻ ነዋይ በኮንሰርቱ ውስጥ የተጠበቀውን ያህል ሰው ባለመገኘቱ “ሕዝቡን ምን አድርገነው ነው፤ ስንጠራው የማይመጣው?” እስከማለት ደርሷል። ነዋይ በተደጋጋሚ በሆዱ ሳይሆን በሕሊናው እንዲያስብ ተመክሯል የሚሉት በስዊዲን የሚገኙት ኢትዮጵያውያን “ሕዝቡን ምን አድርገነው ነው ስንጠራው የማይመጣው?” ማለቱ በራሱ የአመለካከት ደረጃው የት ላይ እንዳለ ያሳያል ብለዋል።

በተመሳሳይ ዜና ነዋይ ደበበ በጀርመን ሃገር ኦክቶበር 4 የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚያቀርብ የሰሙት ኢትዮጵያውያን ቦይኮት ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ጨምሮ የደረሰን ዜና ያስረዳል።

ነዋይ ደበበ በቅርብ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የመጣ ጊዜ ለመለስ ዜናዊ የዘፈነውን “የሙሴ በትር” ዘፈን ‘ዝፈን ብለው ሰጥተውኝ እንጂ ትርጉሙ አልገባኝም ነበር፤ ከዘፈንኩት በኋላ ነው መሳሳቴን ያወቅኩት” ብሎ ለጓደኞቹ የነገራቸው ሲሆን ወዲያው ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ ደግሞ ተገልብጦ በተቃራኒው መገኘቱን የቅርብ ሙያ አጋሮቹ ይተቹታል።

ነዋይ የስዊድን ኮንሰርቱ ከመደረጉ በፊት በኢሳት ራድዮ ተቦርነ ያቀረበውን ዜና ለግንዛቤ እዚህ አምጥተነዋል፦



http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34700



Sunday, September 21, 2014

EthioSwedish Task Force Decorated woyane Ambassader with Rotten Fish &eggs

September 21,201
Ethio Swedish Task Force with cooperation with Ogden Association jointly embraced the Woyane Ambassador in Stockholm, decorated with rotten fish and eggs over their car !! Watch the Video



http://www.youtube.com/watch?v=egF7fs7S6uo


The Silent Genocide on the Amhara Documentary



https://www.youtube.com/watch?v=1K--5J6tmdg#t=336

Friday, September 19, 2014

የወያኔን መንግስት ስርዓት ለመቃወም ዘር፣ ሀይማኖት ፣ ፆታ እና ጎሳ አይለየንም።


እኛ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተውጣጣን የተለያዩ ቋንቋዎች የምንናገር የተለያየ ሀይማኖት ያለን ለዘመናት የተነሱብን አምባገነን አገዛዞች ነጻነት አሳጥተውን ከሰው በታች አድርገው ያዋረዱን መሆናችን አንድ ያደረገን ለነጻነታችን፣ ለሰውነት ክብራችን የቆምን ኢትዮጵያውያን ነን።

እኛ
 ኦሮሞነታችን፣አማራነታችን፣ ሶማሌነታችን፤ ዳውሮነታችን፤ትግሬነታችን፣ ወዘተ ሳያግደን በኢትዮጵያዊነታችን አብረን ሌሎች በአገራቸው የተጎናጸፉትን ነጻነት እኛም በተራችን ልንጎናጸፍ የተነሳን ኩሩ ኢትዮጵያውያን ነን። 

እኛ ነጻነት የተራብን፣ኑሮ ያማረረን፣ ዘረኝነት ያንገፈገፈን፣ ዴሞክራሲ የተጠማን ኢትዮጵያውያን በግብጽና በቱኒዚያ የተደረገውን አይነት አብዮት በአገራችን ልናስነሳ፣ ልንመራውና በአገራችን ዴሞከራሲ ልናሰፍን ከነፍሳችን ተማምለን ተነስተናል። 

የተመኘነውን እውን እስክናደርግ ምንም ዓይነት ምድራዊ ሃይል አያቆመንም። እስካሁን በአገራችን በተነሱት አገዛዞች ማለትም በአጼው ፊውዳላዊ፣ በደርጉ ወታደራዊ፣ በወያኔ ዘረኛ፤ አፋኝና አረመኔ አገዛዝ የተማረርን ነጻነታችንን የምንወድ በሌሎች ነጻነት እየቀናን መኖር የማንሻ ኩሩ ኢትዮጵያውያን ነን። በአሁኑ ሰአት የአረመኔው እና የአፋኙን የወያኔን መንግስት ስርዓት በመቃወም ዘር፣ ሀይማኖት  ፆታ እና ጎሳ ሳይለያየን የአፋኙን የወያኔን ውድቀት ለማፋጠን ለነፃነታችን በወያኔ ላይ የተቃውሞ ድምጻችንን እናሰማለን:: 

ዳዊት ደመላሽ 


Thursday, September 18, 2014

ነዋይ ደበበ በስዊድን ተቃውሞ እንደሚጠብቀው ተገለጸ

በስቶኮልም ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አና ተውልደ ኢትዮጵያውያን በጋራ “ልማታዊ አርቲሰት” ንዋይ ደበበ ኮንስርት ሊያቀርብ አይደለም ሊያስበው እንደማይገባ አሰታወቁ።

የኢትዮጵያውያን ስቃይ ላይ ጭቆና ላይ ከወያኔው ጋር በመሆን ጮቤ ዳንኪራ የሚረግጠው ንዋይ ደበበ ወደ ስቶክሆልም ሴፕቴምበር 20 ቀን 2014 ዓ.ም ለመዝፈን ስለሚመጣ ውርደቱን ማከናነብ ደግሞ ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይጠበቃል ያሉት በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከዓባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ! ከዓባይ በፊት በግፍ የታሰሩት ይፈቱ! ከዓባይ በፊት ሰብዓዊነት ይቅደም! የህዝብ መብት ይከበር! … ድምፃችን ይሰማ! መሪዎቻችን ይፈቱ! ንጹኀንን መግደልና ማሰር ይቁም! መንግሥት ከኃይማኖት ላይ እጁን ያንሳ እንድሁም የዞን ዘጠኝ እና የእስረኛ ጋዜጠኞች ስቃይ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰቆቃ የጋዜጠኞች ስደት የፖለቲክ መሪዎች እና አጠቃላይ የዜጎች ግድያ ቁስሉ የኛ የዲያስፕራውያንም ስለሆነ ቦይኮቱን በመቅላቀል ንዋይ ደበበን በመጣበት አሳፍረን መመለስ አለብን።” ብለዋል።

“አዲስ ዓመት የአምባገነንነት ዘመን ውጣ የነፃነት ዘመን ግባ ብለን ካለው የተሻለ ነገር የምንፈጥርበት እንዲሆንልን በመመኘት ካለፉት ብዙ አዲስ አመቶች የሚለይበትን እና በሕይወታችን ትርጉም ያለው ለውጥ የምናመጣበት እንዲሆን የህሊና ጥንካሬያችንን ማጎልበት ይጠበቅብናል::” ያሉት ኢትዮጵያውያኑ የነዋይን ዝግጅት ቦይኮት ለማድረግ የተለያዩ ወረቀቶችን እየበተኑ እንደሆነ አስታውቀዋል።


ኢትዮጵያውያኑ በዲያስፖራ ከገዳዩና አሳሪው መንግስት ጎን ቆመው የሚወጉትን አርቲስቶች ቦይኮት ማድረግ ከጀመረ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳ ሃመልማል አባተ እንዲሁም በቅርቡ ሸዋፈራው ደሳለኝ ዝግጅቶቻቸው ቦይኮት ተደረገው ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው አይዘነጋም።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34659

Wednesday, September 17, 2014

እኛ ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን ስንል ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ ለውጥ እንፈልጋለን ማለታችን ነው • •

ስብሃት አማረ

እንደሚታወቀው ላለፉት 23 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀምጠውን ዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታ በጀመርነውና በተያያዝነው አዲስ አመት ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶቻችንን በማቻቻል በጋራ ልንታገል የሚገባና ለህዝባችንና ለሃገራችን ስር ነቀል ለውጥ ልናመጣ የሚያስችለንን ምዕራፍ  የምንጀምርበት አመት መሆን አለበት። 

ባሳለፍናቸው በርካታ  የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በእርስ መፈራረጅና መወነጃጀል  የወያኔን እድሜ ከማራዘም ውጪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያተረፈው  አንዳችም ነገር የለም። የአንድነት የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተቻቻለ የሃሳብ መግባባት ተቻችሎ እና ተግባብቶ ሁለገብ የትግል ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅብናል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን ስንል እውነተኛና ዴሞክራስያዊ የሆነ ለውጥ እንፈልጋለን ማለታችን ነው ። ለለውጥ፣ ለፍትህና ለእኩልነት ነገ የምንጠብቀውንና የምንናፍቀውን የማይቀረውን ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለውጥ እስከምናገኝ ድረስ እንደትናንቱ ዛሬም አሁንም ድምጻችን እንዲሰማ እንጮሃለን።

በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ በትክክለኛው መንገድ የማያስቀምጡ የወያኔ ሚዲያዎች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ዘገባዎችን በመስራት እና እውነትን ለመሸፋፈን በመትጋት የሕዝቦችን የማወቅ መብት ያለርሕራሄ እየተጋፉት/እየገፈፉት ይገኛል። ይህ በወያኔ የፕሮፓጋንዳ አካላት የሚፈጸም ማጭበርበር እና ማደናገር የገዢውን ፓርቲ ውስጣዊ ዝርክርክነት በይፋ ያሳብቃል።

 የሌለውን እንዳለ፤ ያልተሰራውን እንደተሰራ፤ ሕዝቡ የማያገኘውን አገልግሎት እንደሚያገኝ፤ ወዘተ በማድረግ በተጋነነ ሁኔታ ባልሆነ ስሌት በማባዛት በመቶኛ በማስላት በመደመር በማባዛት የሌለ ምስልን በመፍጠር ሕዝቡንና እርዳታ ሰጪ መንግስታትን ለማደናገር  ይሞክራሉ።

ፍትሕ  አጣን፣ ፍትሕ ዘገየብን፣ ፍትሕ ተነፈግን የሚሉ በርካታ ዜጎች ባሉበት አገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓቱ ተደራሽነት ወደር እንደሌለው የሚደሰኩሩ  የመንግስት ሪፖርቶችና መግለጫዎች የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ሕዝቡ በየፍርድ ቤቱ በተጓደለ ወይም በተነፈገ ፍትሕ ምክንያት ከላይ ታች ሲባዝን/ሲንከራተት እየታየ የማይመስልና የሌለ ነገር  ይነገራል፡፡

 ከሰሞኑእንኳን ጋዜጠኞችና ጦማሪያኑ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁና በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ የአለም ህዝብ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ያወገዙት የወያኔ ተግባር ነው። በየእስር ቤቱ የሚማቅቁትንና የግፍ ግፍ እየተፈጸመባቸው ያሉት በነርዕዮት፣ ውብሸት፣ አንዷለም፣ እስክንድርና በሌሎችም ላይ እየተደረገ ያለው ስቃይና እንግልት ሳያንስ ሰሞኑን ደግሞ የሚወዱትን ህዝብ፣ የሚወዱትን ሃገርና የሚወዱትን ሞያቸውን በመተው የተሰደዱትን ጋዜጠኞች ማስታወስና እየከፈሉ ያሉትን መስዋእትነት መዘከር ያስፈልጋል። 

እኚህ የተሰደዱትና የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም፥ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ለህግም ተገዢ እንዲሆን ጠየቁ እንጂ ።

ሌላው በየአካባቢው ‘ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ አግባብነት የሌለው ጥያቄ ጠየቅህ፣ ባለስልጣን ተዳፈርክ፣ ከሁለት በላይ ተሰብስበህ አየንህ’ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው፣ እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ኢትዮጵያዊ የሰራው ወንጀል የለም። በፍጹም አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ ወይንም እያስቀመጠ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሲያበቃ ‘ሊያፈነዱ ሲሉ ተደረሰባቸው’፣ ወይንም ‘ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ’ ብሎ ውዥንብር የሚነዛው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ ኢትዮጵያዊ እንደአይደለ የታወቀ ነው።

ተደጋግሞ ከተለያዩ የህግ ባለሙያዎች እንደተገለጸው አለምዓቀፍ ህግን በተጻረረ መልኩ ኦኬሎ አኳይንና አንዳርጋቸው ጽጌን ከመንገድ ያውም ከሰው አገር በጉቦ አስጠልፈውና አፍነው በመውሰድ ያው የተለመደ  ግፋቸውን እየፈጸሙ ይገኛሉ፣ ይህ የሚያሳየው ወያኔ እጁ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ ነው። እነዚህ ሁለት የፍትህና የእኩልነት ታጋዮች ኦኬሎ አኳይንና አንዳርጋቸው ጽጌ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንደ ሌሎች የተቃዋሚ መሪዎች የበኩላቸውን ለማበርከት ደፋ ቀና ሲሉ በወያኔ መረብ ውስጥ ቢገቡም ለፍትህና ለእኩልነት እንዲሁም ለሃገር ነጻነት የከፈሉት አስተዋጽኦ መቼም የማይረሳ ታላቅ መስዋእትነት ያበረከቱ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።

በአጠቃላይ ሲታይ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ  የመሆኑን ያህል የወያኔ አባልና ደጋፊ  ‘ጤነኛ’ ለሃገር አንድነትና ለፍትህ የሚከራከረው ተቃዋሚው ወገን ደግሞ ‘አሸባሪ’  የሚል አጸያፊ ተቀጥላ በማበጀት ንጹሃኑን በየእስር ቤቱ በማጎር ህዝባዊውን ትግል ለማኮላሸት በመፍጨርጨ ላይ ይገኛል፡፡

ትግልን በጋራና በውህደት ማቀናጀት ወቅቱ የሚጠይቀው ሁኔታ እንደሆነ እየታዩ  ያሉት አንዳንድ ምልክቶች አሉ፣ በመሆኑም ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚል ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል በመፋለም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለባቸው ከሰሞኑ የተወሰዱት የ3 ድርጅቶች የውህደት ንግግርና ስምምነት ያሳያል።

ወቅቱ ለጠየቀው የሀገር አድን ጥሪ ምላሽ በመስጠት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የአርበኝነት ትግል ችቦውን በመለኮስ እንደ ሻማ በመቅለጥ ብርሃን እየሰጠ ያለ ግንባር እንደመሆኑ መጠን የተለኮሰውም የትግል ችቦ ሳይጠፋ የታለመለትንና ለታቀደለን አላማ እስከግብ ድረስ እንዲዘልቅ የወያኔን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር ትግሉን በማጠናከር በአሁኑ ሰዓት ግንባሩ ከግንቦት 7 የፍትሕ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ጋር ውህደት ለማድረግ መስማማታቸው የሚያስመሰግንና ለሌሎችም የአንድነት ሃይሎች ተባብሮ የመስራትን ነገር ማሳያ በመሆን አስፈላጊ የሆነ ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል/ከፍቷል። ውህደቱ ተጠናቆ የድሉን ፍሬ ተቋዳሽ የምንሆነበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን አምናለሁ።

ስለዚህ ኢትዮጵያውያን የአንድነት ሃይሎች በመተባበር፣ በመጣመርና በመዋሃድ ሃይልን፣ እውቀትን፣ ህብረትን እንዲሁም ገንዘብን በማቀናጀት የወያኔን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ምድር ወደ ከርሰ መቃብር ለአንዴና ለመጨረሻ አሸቀንጥሮ ወርውሮ ሃገርንና ህዝብን ለነጻነት ለማብቃት በጋራ መታገል ግዴታችን መሆኑን አውቀን በአንድነት ስርዓቱን ማስወገድ ማንኛውም ሃገሬንና ህዝቤን እወዳለሁ የሚል ዜጋ ሊነሳለት እና ሊተገብረው የሚገባ መሆኑን በመግለጽ የበኩሌን ሃሳብ ለማቅረብ እወዳለሁ::

አንድነት ኃይል ነው !!


ድል ለሰፊው ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34632

Tuesday, September 16, 2014

በአይሳኢታ፣ በዱብቲ፣ በአዋሽ፣ በአሚ ባራ፣ በገዋኔ፣ በአፍዴራ፣ በዶቢና ሚሌ የሚገኙ አፋሮች መሬታቸውን ተቀምተው በርሃብ እየተቆሉ ነው

የደርግ ስርዓት ወድቆ የኢህአዴግ መንግስት ሲመጣ ብዙ የአፋር መሬት ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለስ ተደርጓል። በሰሜናዊው የአፋር ክልል በዳሉል ወረዳ ይተዳደሩ የነበሩ ብዙ የአፋር ህዝቦች በግዴታ በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲተዳደሩ ተደርገዋል!
ለምሳሌ፦ ያህል፥ ታላክ፣ ጎደለ፣ ሰሄሎ እና ሰውነ ሲሆን ከዚህ በላይ ስማቸው በተጠቀሱት ቦታዎች ከኢህአዴግ ሰርዓት በፊት ከአጼዎች ዘመን ጀምሮ የአፋር መሬት እንደነበረ ይታወቃል። ታላክ እና ጎደለ እሰከ ሰሄሎ በደጅ አዝማች አህመድ ሲተዳደሩ ሰውነ ደግሞ በኦና ማሕሙድ ይተዳደር ነበር።


በዚህ አካባቢ የሚተዳደሩ የአፋር ህዝቦች እስካሁን ድረስ በቋንቋቸው የመማር ማስተማር እንዲሁም ባህላቸውን የማሳደግ የሰብዓዊ መብት ያላገኙ ሲሆን በሚኖሩበት የትግራይ ክልል እንኳን የአፋር ብሄረሰብ አይባሉም ኢህአዴግ ይኸው ቆምኩላችሁ መብታችሁን አስከበርኩላችሁ እያለ የአፋር ህዝብ ግን ገና ጭቆና ላይ መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ወገኖቻችንና ለዴሞክራሲም ሆነ ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ የመብት ታጋዬች ሊያውቁልን ይገባል! ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ደርግን ለመዋጋት ወደ ጫካ ሲገቡ ይሄ የአፋር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ የቅርብ ጎረቤት ስለነበር ምግባቸውን አብስለው ለተጋዬች ከማቅረብ ጀምሮ ከጎናቸው የቆመ ህዝብ ቢሆንም ዛሬም ከጭቆና ልወጡ አልቻሉም።

ወድ የተከበረችሁ ወገኖቼ ሆይ ይሄን ስናገር ግን የቀረው የአፋር ህዝብ መብት ተክሮለታል ማለት አይደለም! በክልላችን በወያኔ ያልተወረረ የአፋር መሬት የለም። በአይሳኢታ፣ በዱብቲ፣ በአዋሽ ፣በአሚ ባራ፣ በገዋኔ ፣በአፍዴራ ፣በዶቢና ሚሌ የሚገኙ አፋሮች በአሁኑ ጊዜ ከመሬታቸው ተፈናቅለው በረሀብ እየተሰቃዩም ይገኛሉ።

የተንዳሆ የስኳር ፋብሪካ የተጀመረው በ2001 ዓ.ም ቢሆንም እሰከ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ከስኳር ችግር አልወጣም። ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠሩት የህወሃት ባለ ስልጣናት ሲሆኑ አብዛኛቸው ከመከላኪያ ሰራዊት በጡረታ የወጡ መኮነኖች ናቸው! የአፋር ክልል መንግስትም ቢሆን ለስራቸው የሚሰጠውን ባጀት ወደ ውጭ ሀገር እየላኩ ማስቀመጥ ብቻ ነው!! ሌላው ቀርቶ በአፋር ክልል በሰላም ሲኖሩ የነበሩ የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን በግዳጅ ከአፋር ክልል እያስወጡ ይገኛሉ። በዚህ አመት ብቻ ከ400 ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች በሰፈራ ፕሮግራም ወደ አፋር ክልል ገብተዋል!!

በመጨረሻም:- የአፋር ህዝብ ከኢትዮጵያ ነፃነት ታጋዮች ጋር ለሚደረገው ትግል ከዳር እስከ ዳር ዝግጁ መሆኑን በአፋር ወጣቶች ስም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። የአፋር ህዝብ ይህ የአንባገነን ስርዓት አብቅቶ የነፃነት ፀሃይ የምትወጣበት ቀን በጉጉት የሚጠብቅ ጭቁን ህዝብ ነው!


ነፃነት ለኢትዮጵያ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34586

Monday, September 15, 2014

በህወሀት እና በአጋር ፓርቲዎቹ መካከል አለመተማመን እየተፈጠረ ነው


እስከ ጳጉሜ 4 2006 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በርካታ እንግዳ ክስተቶችን ይዞ የተገኘ እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል:: በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚሁ የድርጅቱ ስብሰባ ብአዴን እና ኦህዴድ ድርጅታዊ ተልእኮዎችን የማስፈጸም ውስንነት እንደታየባቸው አልፎ ተርፎም የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ኢሊባቡር እና አምቦ የኦነግ ምሽግ የሆኑ ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በአርበኞች ግንባር ቁጥጥር ስር ለመዋል እንደተቃረበ፣ በአመራሩ እንዝህላልነት ህዝቡ ከኢህአዴግ እየራቀ እና ለድርጅቱ ጀርባውን እንደሰጠ ከመድረክ ተገልጽዋል:: በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገሩት የብአዴን እና የኦህዴድ አመራሮች የተቀሰው አካባቢ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሚሆኑ አባላት እጥረት እንዳለ፣ ህዝቡ በተደጋጋሚ በአካባቢው አመራሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደሚያደርስ ገልጸው ይህም ሊሆን የቻለው በአካባቢው ያለው የሀይል እጥረት እንደሆነ ገልጸዋል::

በሌላ በኩል በብኣዴን እና በኦህዴድ ውስጥ የሚገኙ አባላት ድርጅታዊ ታማኝነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እየመጣ እንደሆነ በርካታ አባላት በየሄዱበት ሀገር ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን መጪው የ2007 ምርጫ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ሁሉም መሰረታዊ ድርጅቶች አባላታቸውን ጠንክረው እንዲያንቀሳቅሱ በተጨማሪም የሚዲያው ክፍል ልማታዊ አርቲስቶች ወደ ህዝቡ ልብ እንዲገቡ መሰራት እንዳለበት ለዚህም እቅድ ተነድፎ በቅርቡ ለሚዲያው ክፍል ገቢ እንደሚሆን እና ስራው ተግባራዊ እንደሚሆን ከመድረክ ተገልጹአል::

በሌላ በኩል ህወሀት በ2007 ቴዎድሮስ አድሀኖምን የድርጅቱ ኮከብ በማድረግ ላቅ ብሎ ለመታየት የሚያደርገው ሙከራ በአንዳንድ የኦህዴድ እና የብአዴን አባላት ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ነገር ጸድቶ ትክክለኛ የህወሀት ስራ አስፈጻሚ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው ደህዴን እንድሆነ ለማወቅ ተችሉአል::

በተያያዘ ዜና ህወሀት እና የተቃዋሚው ቡድን ለእርቀ ሰላም ይቀመጡ ዘንድ በአፍቃሪ ህወሀቶች ዘንድ ውስጥ ውሰጡን ስራ እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣ ይህንንም ስራ በበላይነት ይዘው እየሰሩ ያሉት አቶ መነገሻ ስዩም እንደሆኑ በተጨማሪም አሜሪካን ሀገር ሜሪላንድ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር ጥላሁን በየነ በቡድኑ ውስጥ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችልዋል::


የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከየትኛው ወገን እንደተነሳ ባይታወቅም የተለያዩ አስተያየት ሰጪ የኢህአዴግ አባላት ህዝቡ ከኢህአዴግ በተቃራኒ በመቆሙ በተለይም በሐገር ውስጥ በትግራይ ክልል የአረና ፓርቲ ተቀባይነት ማግኘት በመሀል ኢትዮጵያ ደግሞ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች መጠናከር በሚጠሩት ሰልፍ ላይ የሚገኘው የህዝብ ቁጥረ ከእለት ወደ እለት መጨመር በውጪ ሀገራት ደገሞ ግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ወደ አንድ መስመር መምጣት በህወሀት ነባር አመራሮች ለድርጅታቸው እንደ አደጋ በመታየቱ የእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከህወሀት አመራሮች ሊነሳ እንደሚችል ይገመታል፣ በተቃዋሚው በኩል በእርቀ ሰላሙ ዙሪያ ያለው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34574

Sunday, September 14, 2014

መስከረም 11 ቀን ፣ በአዲስ አበባ ባለ አደባባይ ሕዝባዊ የሻማ ማብራት እንቅስቃሴ እንደሚደረግ፣ የአዲስ አበባ አንድነት ወጣቶች ለአስተዳደሩ አሳወቁ

Sep.13.2014
የአዲስ አበባ አንድነት ወጣቶች ኮሚቴ፣ በአዲስ አበባ ለመስከረም 11 ቀን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ እየተዘጋጀ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። እንቅስቃሴው በዋናነት ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ለታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች፣ ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞች፣የሰባአዊ መብት ተሟጋቾች …ሶሊዳሪቲዉን በማሳየትና ሻማ በማብራት እስረኞች በማሰብ ላይ ያተኮረ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ለአቡጊዳ ገልጸዋል።
የአንድነት ፓርቲ ከዚህ በፊት የሚያደርጋቸው የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓቶች፣ በጽ/ቤት ብቻ እንደነበረ፣ የገለጽት አዘጋጆቹ፣ አሁን ግን ዝግጅቱ ለማድረግ የታሰበው በሕዝባዊ አደባባዮች እንደሆነ ይናገራሉ። ጥሪዉም የሚቀርበው ለመላው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደሆነ የሚናገሩት አዘጋጆች፣ በመኪና ቅስቀሳ እንደሚደረግም ለአቡጊዳ አሳዉቀዋል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕዝባዊ እንቅስቃሴዉን በአራት ኪሎ ወይንም በስድስት ኪሎ ማድረግ ይቻል ዘንድ እውቅና እንዲሰጥ ቢጠየቅም፣ አስተዳደሩ በሁለቱ አደባባዮች ማድረግ አይቻልም የሚል ምላሽ ሰጧል። አራት እና ስድስት ኪሎ ህዝብ እንዳይሰባሰብ የሚከለክል ምንም አይነት ሕግ እንደሌለ ቢታወቅም፣ የአንድንነት ወጣቶች አላስፈላጊ ክርክር ዉስጥ ላለመግባት፣ ሌሎች አራት አማራጭ ቦታዎችንን እንዳቀረቡ ለማወቅ ችለናል።

http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15727#more-15727

Saturday, September 13, 2014

ማን ነው በአሸባሪነት መጠየቅ ያለበት ?

በወያኔ መንደር ሽብርተኝነት ለየት ያለ መልክ ነው ያለው የወያኔ የሽብርተኝነት መስፈርትም ሆነ ትርጓሜ ብዙ ሃገሮች፤ አንባገነን የተባሉት ሳይቀሩ ስለሽብርተኝነት ካላቸው ግንዛቤም ሆነ ከአለም አቀፉ መመዘኛዎች የተለየ ነው። የሽብርተኝነት ተግባር እየተተረጎመ ያለው በወያኔ ባልሥልጣናት የመሸበር መንፈስና ሰለራሳቸው ሥልጣን ብቻ በማሰብ ከጭንቀት በመነጨ የፍርሃት ስሜት ላይ የተመሰረተ ነው:: ባለሥልጣናቱን ጭንቅት ወስጥ የሚጥል፣ የሚያስደነብር፣ የሚያስቀይም፣ የሚያስቆጣ ወይም የሚያሰፈራራና እንቅልፍ አጥተው እንዲያድሩ የሚያደርግ ተግባራትን የፈጸመ ሁሉ በሽብርተኛነት ይፈረጃል:: ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀይ መስመር አስምረውና አዋቅረውት የሄዱትን የወያኔን አጥር የሚነቀንቅ ብቻ ሳይሆን ጠጋ የሚልም ሁሉ በአሸባሪነተ ሊፈረጅ፣ ሊታሰርና ሊከሰስ እንዲሁም ሊፈረድበት እንደሚችል እየታየ ነው:: ለአገዛዝ ሥርዓቱ የሥልጣን ዘመን መራዘም ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉዋቸውን አካላትና ግልሰቦች ሁሉ አሸባሪ አያሉ መክሰስ የተለመደ ሆኗል። ብዕራቸውን አንስተው በመንግሥት ላይ የሰሉ ትችቶችን በመጻፍ ተቃውሟቸውን የገለጹ፣ የሃይማኖትና የተለያዩ ማህበራዊ ተቋማትን በመወከል የመብት ጥያቄዎችን አንስተው የተሟገቱ የሕዝብ ወኪሎች፣ በወያኔ በባለሥልጣናት የተፈጸሙ ወንጀሎችን፣ ሙስናዎችን፣ አገርና ሕዝብን ያዋረዱ ተግባራትን ያጋለጡና ባደባባይ ሥርዓቱን የሞገቱ ጋዜጠኞች፣ የማህብራዊ ድረ-ገጽ ገተሳታፊዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ጭምር የሽብርተኝነት ካባ እያከናነቡ ማጎርና መወንጀል የሥርዓቱ ዋና ስልት ሆኗል። ይህም ወያኔ አለም በሚሸበርበት ጉዳይ ሳይሆን ራሱ በፍርሃት በፈጠረው የሽብር ዓለም ወሰጥ መሆኑን ያሳያል::

   ዳዊት ደምመላሽ

Wednesday, September 10, 2014

በፕሬሱ ላይ የተመዘዘው ሰይፍ


መረጃ የማግኘት ነጻነት ከዋነኞቹ የዴሞክራሲ መገለጫዎች ወይም እሴቶች መካከል ይጠቀሳል፡፡ መረጃ የማግኘት ነጻነቱ የተከበረለት ህዝብ በሀገሩ የስልጣን መንበሩ ላይ የተቀመጠውን አስተዳደር (መንግስት) የመቆጣጠር ኃይሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ሙስና፣ ብልሹ አስተዳደርና ሌሎችን ንቅዘቶች በማጋለጥ የመንግስትን ተጠያቂነት በማስፈን ሂደት ውስጥ ህዝብ ንቁ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ መረጃ የማግኘት ነጻነቱን ሊጎናጸፍ ይገባዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ መረጃ የሚያደርሱት ሚዲያዎች በስፋት መኖር የግድ ነው፡፡ ለዚህም ነው በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ውስጥ የሚዲያ (ፕሬስ) ሚና እንዲጎላ የሚደረገው፡፡

በተቃራኒው በአምባገነን ስርዓት ውስጥ ገዥዎች የሚዲያ (ፕሬስ) ነጻነትን በማፈን ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ይስተዋላል፡፡ አምባገነኖች ስርዓቱን የሚተቹ የፕሬስ ውጤቶችን ይዘጋሉ፣ ጋዜጠኞችን ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ አለፍ ሲልም ይገድላሉ፤ ያስገድላሉ፡፡ አምባገነኖች ለይስሙላ የሚዲያ ነጻነት መረጋገጡን የሚያሳዩ ህጎችን በማውጣት በውጭ ሆኖ ለሚመለከታቸው አካል ዴሞክራት በመምሰል በውስጥ ተግባራቸው ግን ካወጧቸው ህጎች ፍጹም ተቃራኒ በመሆን የአፈና ስራ ያከናውናሉ፡፡ የግል ፕሬሶችን በቀጥታም ሆነ በእጃዙር ጨምድዶ በመያዝ፣ ፕሬሶች ህጉን ተከትለው በፈቃዳቸው ያሻቸውን እንዳይሰሩ ያደርጋሉ፡፡ እንዲህ አይነቶቹ የአምባገነኖች ተግባራት በበርካታ ሀገራት ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡

ለአብነትም ለረጂም አመታት ቻይናን እየገዛ ያለው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በሀገሩ የሚንቀሳቀሱ የሚዲያ ውጤቶች ላይ ባሻው ጊዜ ሁሉ ህገ-ወጥ እርምጃዎችን በመውሰድ ይታወቃል፡፡ ይኸው የቻይና ገዥ በ2012 ብቻ ከ16 በላይ ዌብሳይቶችንና ብሎጎችን ከርችሟል፡፡ ይህ አምባገነን ስርዓት በምድረ ቻይና የመረጃ መረብ እቀባ በማድረጉ ምክንያት፣ ሀገሪቱ በተለያየ ጊዜ ከታዋቂዎቹ ዓለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች ጎግልና ያሁ ድረ-ገጾች ጋር አተካራ ውስጥ ስትገባም ይታያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቻይና በሀገሯ የሚታተሙ ጋዜጦችንና መጽሔቶችንም በመክሰስና በመዝጋት ስሟ በአሉታ ይነሳል፡፡


ቻይና ዲንግ ዲያን የተሰኘውን ከፍተኛ ተነባቢ ሳምንታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ በ2006 መዝጋቷንም እዚህ ጋር እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ የቻይና ገዥዎች ጋዜጣውን የዘጉት በሀገሪቱ ያለውን የማህበራዊ ቀውስ፣ በሙስና የተጨማለቀውን አስተዳደር፣ በከተሞች ያለውን የከፋ የአየር ብክለት፣ ያልተመጣጠነ የዜጎች የደመወዝ ክፍያን፣ ልቅ የመሬት ይዞታን እና ሌሎች ችግሮቹን በተከታታይ ማጋለጡን ተከትሎ እንደነበር ይወሳል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የቻይና መሪዎች ትችትን ለመቀበል አለመፍቀድ እንዲህ አይነት እርምጃዎችን እንዲወስዱ አድርጓቸዋል፡፡ ቻይናውያን ጋዜጠኞች በቻይና መንግስት የሚወሰደው እርምጃ ፍጹም ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲሉ ቢከራከሩም ሰሚ አግኝተው የሚያውቁ አይመስሉም፡፡

በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ያለው እውነታም ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ በእነዚህ አምባገነን ስርዓቶች ገዥዎች ፕሬሱ በተቋም ደረጃ ጎልብቶ በሁለት እግሩ እንዲቆም የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ ስለሆነም የራሳቸውን የግል ስልጣን ጠብቆ ለመቆየት ነጻ ፕሬሶችን ሰለባ ያደርጓቸዋል፡፡ በእርግጥም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ፣ አምባገነኖች በነገሱባት ሀገር ፕሬሱና ሙያተኛው በነጻነት ተደራጅቶና ጎልብቶ ተቋም እንዲመሰርት አይፈቀድለትም፡፡ ለዚህም ይመስላል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በ2009 አፍሪካን ሲጎበኙ ጋና አክራ ላይ ‹‹አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን (መሪዎችን) ሳይሆን ጠንካራ ተቋማትን ነው የምትሻው›› ሲሉ ሀቁን የተናገሩት፡፡
በእርግጥም አፍሪካ ጠንካራ ተቋማት የላትም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የጠንካራ ተቋማት እጦት ችግር ደግሞ ከብዙ የአፍሪካ ሀገራትም የከፋ ነው፡፡ በተለይ ለሌሎች ተቋማት መጎልበት አይነተኛ ሚና የሚጫወተው የሚዲያ ተቋም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ምንም በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አምባገነኖቹ ገዥዎች ድክመቶቻቸውን በሚያጋልጥባቸው ሚዲያ ላይ የሚወስዱት ህገ-ወጥ እርምጃ አሉታዊ ሚና አለው፡፡

ፕሬሱ ላይ የተመዘዘው አዲሱ ሰይፍ

የኢህአዴግ ገዥዎች ፕሬሱን በማዳከም ሂደት ላይ ከቻይና ‹‹ምርጥ ተሞክሮ›› ሳይወስዱ አልቀሩም፡፡ ልክ እንደ ቻይና ሁሉ ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችን፣ ዌብሳይቶችን…ይዘጋሉ፤ ይከስሳሉ፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነጻነት ህገ-መንግስታዊ እውቅና አግኝቷል፤ ዋስትና ግን የለውም፡፡ ምክንያቱም ህገ-መንግስታዊ እውቅና ያገኘው የፕሬስ ነጻነት በተለያዩ አፋኝ አዋጆች ዋስትናውን አጥቷል፡፡ የፕሬስ ተቋማትም ሆነ ሙያተኞች (ጋዜጠኞች) ህገ-መንግስቱ ላይ በሰፈረው መሰረት ለመስራት ሲንቀሳቀሱ በተለያዩ ተልካሻ ምክንያቶች በህገ-ወጥ እርምጃ በተደጋጋሚ ተደናቅፈዋል፤ እየተደናቀፉም ይገኛሉ፡፡ በዘመቻ መልክ የግሉን ፕሬስና ጋዜጠኞችን የማሳደድ ስራ ከተከናወነበት ምርጫ 97 ጀምሮ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ይህን ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተቸረውን ነጻነት ሲገረስስ ታይቷል፡፡

አስገራሚው ጩኸት ደግሞ ኢህአዴግ እነዚህን የአፈና ስራዎች ሲሰራ ‹ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ› በሚልና በልማት ሽፋን መሆኑ ነው፡፡ ህግን እየጣሱ ህግን ለማስከበር ስል ነው የሚለው የኢህአዴግ መንግስት ከሰሞኑ ደግሞ ሌላ የአፈና መስመርን ዘርግቷል፡፡ ይኸውም ‹‹ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በአመፅ ለመናድ በማሴር የተጠረጠሩ የህትመት ውጤት አሳታሚዎችና ድርጅቶች›› ላይ በ‹ፍትህ ሚኒስቴር› አማካኝነት ክስ መመስረት ነው፡፡

ተጠርጣሪ ተከሳሽ አሳታሚዎችና ድርጅቶች የክስ ቻርጅ ሳይደርሳቸው እንደማነኛውም ሰው የስርዓቱ አፍ በሆነው በኢቴቪ መስማታቸውን የገለፁት የክስ ይዘት፣ ለብዙዎቻችን ግርምትን የሚያጭር ነው፡፡ የፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ስለጉዳዩ ሲያትት እንዲህ ይላል፤ ‹‹በየጊዜው ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም ተጠርጥረዋል፡፡››

ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ተነባቢነት እንዳላቸው የሚታወቁት አምስት መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ናቸው፡፡ እነዚህም ፋክት፣ ጃኖ፣ ሎሚ፣ አዲስ ጉዳይ እና እንቁ መፅሄቶችና አፍሮ ታይምስ የሚባል ጋዜጣ አሳታሚዎችና ድርጅቶች ናቸው። ምናልባትም ኢህአዴግ ክሱን ለመመስረት መስፈርቱ ፕሬሶቹ ከፍተኛ ተነባቢነት ማግኘታቸው ሳይሆን አይቀርም፤ አለበለዚያም በምንም አይነት መልኩ ምንም ባደርግ አትተቹኝ ባይነት መሆኑ ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ለመሆኑ ‹‹…ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ በማድረግ…›› ማለት ምን ማለት ነው? ሲጀመርስ ስርዓቱ በህዝብ ዘንድ አመኔታ አለው ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡

ይህን መሰሉ የመንግስት እርምጃ የግሉ ፕሬስና ጋዜጠኞቹ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ኢህአዴግ ጠንቅቆ የሚያውቀው ይመስላል፡፡ ከአሁን በፊት እንደታየው ከሆነ መንግስት እነዚህን መሰል አሳታሚዎች ክስ ሲመሰርትባቸው ጋዜጠኞቹና አሳታሚዎቹ ወዴት ሊያመሩ እንደሚችሉ የበፊት ተሞክሮው ማህደር የሚነግረው እውነታ አለ፡፡ የኸውም ጋዜጠኞቹና አሳታሚዎቹ ክሱ በሚያሳድርባቸው ጫና ሀገር ጥለው መኮብለል፣ አልያም ስራቸውን እርግፍ አድርገው መተው እንደሆነ አይቶታል፡፡ ይህን አይነት በፍትህ ሚኒስቴር በኩል የሚወጣ ‹መረጃ› እነ አዲስ ነገርና አውራምባ ታይምስን የመሳሰሉ ጋዜጦችን ከህትመት ውጭ አድርጓቸው እንደነበርና ጋዜጠኞችንም ለስደት እንደዳረጋቸው ኢህአዴግ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ የዚህኛው ክስ ጉዳይም ከዚህ ጋር የተመሳሰለ ምላሽን እንዲያስገኝለት በማሰብ የመሰረተው ክስ ሊሆን ይችላል፡፡

የራሷ ሲያርባት…

አንዳንዴ ከራስ ግዙፍ ጉድፍ ይልቅ የሌላን ጥቃቅን ችግር ማየት የተለመደ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ መንግስት በእነዚህ አምስት መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የመሰረተው ክስ ተገቢነት የሚኖረው ከሆነ ኢህአዴግም በተመሳሳይ የሚከሰስባቸው አግባቦች መኖራቸውን ልብ ያለው አይመስልም፡፡ ይኸውም መንግስት በራሱ ቁጥጥር ስር በሚገኙ ሚዲያዎች ዘወትር ህዝብን ባዶ ተስፋ እየመገበ ከማወናበዱ በተጨማሪ፣ በተቃውሞው ጎራ ያሉትን ኃይላት ከህዝብ ለማራቅ የሚያደርሰው የስም ማጥፋትና ማጥላላት አልታወሰውም፡፡ መቼም በዶክሜንተሪ ፊልም ስም በተለያዩ አካላት ላይ የሚሰራው ስራ ምን ያህል ጤነኛ እንዳልሆነ ከራሱ ከኢህአዴግ ሰዎች የተሰወረ ሊሆን አይችልም፡፡

ስለሆነም መንግስት አሳታሚዎችንና ድርጅቶችን ‹‹…የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በኃይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም…›› ከጠረጠረና ከከሰሰ፤ እሱ ህጋዊና ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ‹‹ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር›› እያለ ስማቸውን ሲያጎድፍ እንዴት አያፍርም ያስብላል፡፡

ያም ሆነ ይህ ግን መንግስት ምርጫ 2007 ዓ.ም ሳይደርስ ህዝብ መረጃ የሚያገኝባቸውን ፕሬሶች ከወዲሁ ከመስመር እንዲወጡ ማድረጉን ተያይዞታል፡፡ ቀደም ብሎ በተለያዩ ፕሬሶችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ጦማሪያን ላይ ሲወስደው የቆየውን እርምጃ አሁንም ገፍቶበታል፤ ገናም ይቀጥልበታል፡፡ ለዚህ ማሳያ ምልክቶች የሚሆኑት ደግሞ በአሳታሚዎችና ድርጅቶቹ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ቀጣይ መሆኑን ፍትህ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ በግልጽ መናገሩ ነው፡፡ ‹‹በህገ-መንግስቱ የተበጁትን ገደቦች በማን አለበኝነት በመጣስ ስራዬ ብለው ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ በሚጥል መልክ አመፅና ሁከትን የሚቀሰቅሱ፣ አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን የሚያወድሱ እንዲሁም የሚያበረታቱ፣ በህዝቡ መሃከል የዘርና የሃይማኖት ጥላቻን የሚቀሰቅሱ፣ የህዝብ መሪዎችንና የተቋማትን መልካም ስምና ዝና በሀሰት የሚያጠፉና የሚወነጅሉ አንዳንድ ህትመቶች እንዳሉም ሊታወቅ ይገባል›› ሲል ማስፈራሪያ አዘል መግለጫውን አሰምቷል፡፡

‹አያ ጅቦ…›

አሁን በአምስቱ የመጽሔት እና አንድ ጋዜጣ አሳታሚዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ብዙ የተንሸዋረሩ ምክንያቶችና ሰበቦችን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ ለምሳሌ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባስጠናው ‹የአዝማሚያ ጥናት›፣ መሰረት ‹‹አብዛኛዎቹ በህትመት ላይ ያሉ መጽሔቶች የጽንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልሳኖች ናቸው›› ሲል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህም የኢህአዴግ መንግስት በ‹ጥናት› አረጋግጠናል በሚል ‹‹አያ ጅቦ ሳታማሃኝ ብላኝ›› ማለቱ እንደሆነና በቀጣዩ እርምጃ ሊወሰድባቸው የተመረጡ ፕሬሶች መኖራቸውን ያሳየ ነበር፡፡ በዚህም አሁን ክስ የተመሰረተባቸው የፕሬስ አሳታሚዎች በዚያ ‹ጥናት› ስማቸው በክፉ ተነስቶ ጥርስ የተነከሰባቸው እንደነበሩ ማየቱ በቂ ነው፡፡

ሌላው ማመሃኛ ወይም ማደናገሪያ ደግሞ መንግስት ‹ይኽን ክስ እንድመሰርት የተገደድኩት በህዝብ ግፊት ነው› ለማለት የሞከረበት ድንግርግሮሽ ነው፡፡ ‹‹የጥቃታቸው ሰለባ የሆነው ህዝብ በእነዚህ የህትመት ውጤቶች የህግ ከለላ በተሰጣቸው ጥቅሞቹ ላይ ያለማቋረጥ የሚደርሰውን ጥሰት ለማስቆም መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ በተለያዩ መንገዶች ሲጠይቅ ቆይቷል›› ይላል መንግስት በፍትህ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫው፡፡

በእርግጥ የኢህአዴግ መንግስት ከረጂም ጊዜ ተሞክሮው እንደታየው አካሄዳቸው ያላማረውን (የሚተቹትን፣ ድክመቶቹን የሚያጋልጡትን) ማናቸውንም የግል ህትመት ውጤቶች በተለያዩ ዘዴዎች ከመስመር ማስወጣቱን ልብ ማለት ይቻላል፡፡ መንግስት አዲስ ዘመንን፣ ኢቴቪንና አይጋ ፎረም የመሳሰሉ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰፊ ማጥላላት ሲከፍትባቸው የነበሩትንና ያሉትን ፕሬሶችና ጋዜጠኞች ስንመለከት ኢህአዴግ ህግ የማይገዛው፣ በአንጻሩ ግን ህግን በማስከበር ስም ሌሎች ላይ ጥቃት እያደረሰ የሚገኝ መሆኑን እናያለን፡፡

ተቋም እንዳይኖር ማድረግ

ኢህአዴግ ፕሬሱ በተቋም ደረጃ እንዲጎለብት አይፈቅድም፡፡ ስለሆነም የግል ፕሬሱ እንደ ፕሬስም ሆነ ጋዜጠኞቹ በነጻነት ተደራጅተው ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ አይደረግም፡፡ በዚህ አመት ላይ ራሳቸውን በማህበር ለማደራጀት የሞከሩ ጋዜጠኞች እንኳ እጣፈንታቸው ከመበታተን ያለፈ አልሆነም፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንግስት ጫና አሉታዊ ሚና አለው፡፡ ለምሳሌ ሁለቱ አመራሮች (የማህበሩ ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ እና የህዝብ ግንኙነት የነበረው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ) ስርዓቱ ባደረሰባቸው ጫና ሀገር ጥለው ተሰድደዋል፡፡

ኢህአዴግ መደራጀት መብት ነው ሲል፣ በራሱ ማዕቀፍ ጥገኛ እስከተሆነ ድረስ ማለቱ እንደሆነ በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ላይ ነጻና ገለልተኛ ማህበራትን ማየት ብርቅ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም በየማህበራቱ የኢህአዴግ እጅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አለ፡፡ ስለሆነም የፕሬሱን ጉልበት ማዳከሚያ ዋና መሳሪያው ያገባኛል የሚሉ አካላት በነጻነት እንዳይደራጁ ማድረግ ነው፡፡
እስካሁን ድረስ የግል ፕሬሱ አንድ የጋራ ጠንካራ ማተሚያ ቤት እንኳ ሊኖረው አልቻለም፡፡ ፕሬሱ የአንጋፋ የመንግስት ማተሚያ ድርጅት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጥገኛ ነው፡፡ ሌሎች የንግድ ማተሚያ ቤቶችም ቢሆን አንድም አቅማቸው የሚያወላዳ አይደለም፤ ሁለትም በተዘዋዋሪ መንገድ በስርዓቱ ተጽዕኖ ስር የወደቁ ናቸው፡፡

የተመዘዘውን ሰይፍ ለማጠፍ…


በአጠቃላይ አሁን ያለው የሀገራችን የፕሬስ ነጻነት እጅግ አሳሳቢና አደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑ ግልጽ ሆኗል፡፡ እስካሁን ከተለመደው የጋዜጠኞቹ እስርና ድብደባ እንዲሁም ስደት በከፋ ሁኔታ አሁን ደግሞ አሳታሚዎች ላይ ክስ መመስረት መቻሉ መንግስት ምን ያህል የግል ፕሬሱን ማሽመድመድ እንደፈለገ ጉልህ ማሳያ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ይህን በፕሬሱ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለማቃለል የተደራጀ ርብርብ በሚመለከታቸው ተቆርቋሪ አካላት ዘንድ መደረግ ይኖርበታል፡፡ መንግስት ህገ-መንግስቱን አክብሮ ፕሬሱ በነጻነት እንዲቀሳቀስ መፍቀድ ግዴታው መሆኑን በተለያዩ ስልቶች (ለምሳሌ የፕሬሱ አባላት የሚያስተባብሩት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ፣ የተዘጉ ፕሬሶችን የቀደሙ ኮፒዎች ይዞ በአደባባዮች በህብረት መታየት፣ አፍን በጥቁር ፕላስተር አሽጎ ተቃውሞን መግለጽ…) በመሳሰሉት ማስገደድም የተገባ ይሆናል፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34447

አዲሱን ዓመት በማስመልከት ከነጻነት ታጋዮች ጋር በቂሊንጦ እስር ቤት

ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል፡፡

ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ

‹‹ሀገሬ ላይ እርግጠኛ የሆንሁበት ጉዳይ ቢኖር እኔን እንደ ዜጋ የሚጠብቀኝ መንግስት የሌለኝ መሆኑን ነው፡፡ ህገ-መንግስቱ አልጠበቀኝም፡፡ ህገ-መንግስቱ ጥሩ ቢሆንም አልተከበረም፡፡ ይህ ሁሌም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ነው፡፡


ታስሬ ባለሁባቸው ቀናት ሁሉ የታዘብኩት ነገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት በሁሉም ዘርፍ መኖሩን ነው፡፡ አቅም ያላቸው ዜጎች ከስርዓቱ በመገፋታቸው ክፍተቱ እንዲሰፋ ሆኗል፡፡ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ የሚሰሩ ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ አለመኖራቸውን አይቻለሁ፡፡ የሚያሰራ ስርዓት ስለሌለ ብዙዎች ህሊናቸውን መርጠው በመራቃቸው ይመስለኛል አቅም ያላቸው ሰዎች የራቁት፡፡ ይህ ለሀገር አሳሳቢ ነው፡፡

የሚቆጨኝ ነገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ተቋማት በእንግሊዝኛ የተሰሩ የጥናት ስራዎችን በመምረጥ አሰባስበን በአማርኛ ቋንቋ በጆርናል መልክ ለመስራት አስበን ያን ሳንሰራ በመታሰራችን ነው፡፡

አሁን በተለያዩ ሁኔታዎችና ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያው በኩል የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እኛን አስረው ሌላው ዝም እንዲል ፈልገው ኖሮ ከሆነ እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ለሀገር የሚያስቡ ብዙ ወጣቶች በየጊዜው ማበባቸው አይቀሬ ነው፡፡ እየታየ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ምንግዜም የሚበረቱ ሰዎች ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አምናለሁ፡፡››

አይመዲን ጀበል፣ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

ልትጠይቁን ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ በተለይ ወጣቶቹ እያደረጋችሁ ያለው እንቅስቃሴ እንሰማለን፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡ እስካሁን በአገር ጉዳይ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የቆዩት የ1960ው ትውልድ አባላት ናቸው፡፡ አሁን ወጣቶች እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

ያሲን ኑሩ፣ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል

‹‹እስር፣ እንግልትና ሌሎችም በደሎች የአምባገነኖች እርምጃ መለያ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖችን አንድ የሚያደርጓቸው እነዚህ ባህሪያት ናቸው፡፡ አምባገነኖች ከታሪክ አይማሩም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ሆነ 50 አመት ወደ ስልጣን የሚወጣ አምባገነን ይህን ነው የሚደግመው፡፡

መንግስት በኃይማኖቶች መካከል ልዩነት መፍጠር ይፈልጋል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች የኃይማኖት ድንበር ጥሳችሁ ከእኛ ከሙስሊም ወንድሞቻችሁ ጋር መቆማችሁን እናደንቃለን፡፡ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ መብት በመቆም የሚያደርገውን ጥረት እናደንቃለን፡፡ እኛን ለመጠየቅ እስር ቤት ድረስ ስለመጣችሁ በጣም እናመሰግናለን፡፡ ትግሉ ከዚህም በላይ መስዋዕትነት ያስከፍላልና በርቱ፡፡››

ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ

‹‹ማዕከላዊ የገባነውን የመጀመሪያ ሰሞን ለእኛ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በማንኛውም ጊዜ እስር ሊኖር ይችላል በሚል ማዕከላዊ የሚደረጉትን ነገሮች ለማሳወቅ እንጥራለን፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የጻፍናቸው ጽሁፎች ለዚህ ያግዛሉ ብየ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም በእኛ ላይ ከደረሱብን ነገሮች ሌሎች ይማሩባቸዋለን ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ሲሆን የሚታሰሩ ሰዎች የሚደርስበት ችግር አዲስ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ የተሻለ ነገር ቢኖርም አሁንም ድረስ መጽሃፍና ጋዜጣ አይባልንም፡፡

በጥቁሩ ሳምንት ዘመቻ ያደረጋችሁትን ነገር ሰምተናል፡፡ በጣም ደስ የሚል ስራ ሰርታችኋል፡፡ መጥታችሁ ስለጠየቃችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እስሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ቢታወቅም፣ በየትኛውም ሁኔታ በርታትችሁ እንድትቀጥሉ እፈልጋለሁ፡፡
በየቀኑ ጋዜጠኞች በሚደርስባቸው ጫና አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንሰማለን፡፡ ይህ በጣም ያሳዝናል፡፡››

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ

‹‹ከመታሰሬ በፊት ማዕከላዊ ውስጥ ስለሚፈጸሙ በደሎች በተለያዩ ሪፖርቶች ላይ ማንበብ ችዬ ነበር፡፡ ማዕከላዊ ከገባሁ በኋላ ያየሁት ግን ሰፊና ከጠበኩት በላይ ነው፡፡ በተለይ ትጥቅ ትግልን የመረጡ ተቃዋሚዎች አባላት ናቸው የተባሉ አሊያም በሚዲያው የማይታወቁና ጠያቂ የሌላቸው አካላት ላይ የሚደርሰው በደል ዘግናኝ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ተመሳሳይ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ድሮ ማዕከላዊ ውስጥ ይደረጉ እንደነበር ሰምቼ ነገር ግን ይሆናሉ ብዬ የማላምናቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡

የማዕከላዊ መርማሪዎች አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን ጥፋተኛ መሆናችንን እንድናምንላቸው ነው ሁሌም ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያነሱልን፡፡ አንዳንዶቹ ጥያቄዎች በጣም የሚገርሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በምርመራ ወቅት ‹‹እከሌ ጋር ሻይ እየጠጣን›› ብለን የተናገርነውን ነገር እነሱ ‹‹ስብሰባ አድርገን›› ብለው ይጽፉታል፡፡ ሻይ መጠጣት በእነሱ ስብሰባ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ አንድ ጋዜጠኛ የሚሰራው ህጋዊ ስራ ህገወጥ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለአብነት ያህል ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25/2004 ዓ.ም ባደረገው ሰልፍ ተገኝቼ ፎቶ አንስቼ ነበር፡፡ ይህ ፎቶ ግራፍ በክስ ቀርቦብኛል፡፡ አስቡት በዚህ ሰልፍ ኢቲቪና ሌሎች የመንግስት ሚዲያዎችም ፎቶ አንስተዋል፣ ቪዲዮ ቀርጸዋል፡፡ መርማሪዎቹን ‹‹ይህ ስራዬ ነው፡፡ አያስወነጅለኝም›› ብትል አያምኑልህም፡፡ ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስም ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ ተገኝተሃል የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡

በተመሳሳይ ዩጋንዳ እያለሁ ባቋቋምኩት ጋዜጣ ላይ ሙሃመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ ሙሃመድ ጋ ጠብቂኝ›› በሚል ከጻፈው መጽሃፍ ላይ ያሉ ጽሁፎችን ጋዜጣው ላይ አውጥቻቸው ነበር፡፡ ሆኖም ይህም በክስ ቀርቦብኛል፡፡ ‹‹መጽሃፍ ላይ ነው የወሰድኩት፡፡ መጽሃፉ ህጋዊ ሆኖ አገር ውስጥ ይሸጣል›› ብትል ማንም አይሰማህም፡፡ ፖሊስ ህዝብን ለመጠበቅ የቆመ አካል ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ነገር ግን ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ገና ሳይፈረድብን ‹‹እናንተስ ለምን ሽብር ትፈጥራላችሁ?›› ያሉን ፖሊሶች አጋጥመውናል፡፡ ቀድመው ፈረዱብን ማለት ነው፡፡

በምርመራ ወቅት በጣም የሚያስገርሙ ነገሮች ተነስተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጆን ኬሪ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ወቅት መርማሪዎቹ የሚገርም ጥያቄ አንስተውልን ነበር፡፡ ‹‹ጆን ኬሪ ጓደኛችሁ ነው?›› ብለው ጠይቀውናል፡፡ በጣም የሚገርም ነው፡፡ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን የእኛ ጓደኛ እንደሆነ አድርገው አቅርበውታል፡፡ ደግሞም ይህንንም ህገወጥ አድርገው ነው የሚያቀርቡት፡፡ በሌላ በኩል አንዴ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ከግንቦት ሰባት ሌላ ጊዜ ደግሞ ከኦነግ ጋር ግንኙነት እንዳለን ይገልጹልናል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በምንም መልኩ የሚገናኙ አይደሉም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ጋዜጠኛ የሚከሰሰው በመጻፉ አይደለም፡፡ በጋዜጠኝነት ብትከሰስ አንድ ነገር ነው፡፡ እነሱ ግን የሚያነሱብህ ክስ ሌላ ነው፡፡

ፌስቡክና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበርን ሰዎች ያለመረጃ ስንቀመጥ ከባድ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያዎቹ 75 ቀናት ነገሮች አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ቢያንስ ኢቲቪን መመልከት ችለናል፡፡ ኢቲቪ በሚያቀርባቸው ጉዳዮች ላይ የየራሳችን ትርጉም እየሰጠን አገራችን ውስጥ በጥቂቱም ቢሆን ምን እየተካሄደ እንዳለ መረዳት እንችላለን፡፡ ወደ ቂሊንጦ ከመጣን በኋላ ነገሮች የተሻሉ ናቸው፡፡ ከጠያቂዎቻችን መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡››


ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34486