Tuesday, September 9, 2014

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት 400 ሰዎች በተገደሉበት የጋምቤላ ጭፍጨፋ የሕወሓት ባለስልጣናት መሳተፋቸውን አጋለጡ

የቀድሞው የጋምቤላ መሪ በክልሉ ለደረሰው ጭፍጨፋ የህወሃት ባለስልጣናትን ተጠያቂ ማድረጋቸውን ኢሳት ዘገበ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞት ኦባንግ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ 400 ሰዎች የተገደሉበት የጋምቤላው ጭፍጨፋ እንዴት እንደተከናወነ በዝርዝር ሁሉን ነገር ተናግረዋል።

እንደ ኦሞት ገለጻ የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አባይ ፀሐዬ ግድያውን በተመለከተ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ያሉ ሲሆን በክልሉ ስለሚፈጸመው ሙስናና የመሬት ወረራ የቀድሞው ባለስልጣን በዝርዝር  ተናግረዋል።


የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞድ ወደ ውጭ ከወጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰጡት በተነገረው በዚህ ቃለምልልሳቸው ላይ 400 ሰዎች በግፍ በአባይ ፀሐዬ ከፍተኛ ሚና መገደላቸውን መዘርዘራቸው ወደፊት በነዚህ ባለስልጣናት ላይ ለሚከፈተው ክስ ጥሩ ምስክር ሊሆን ይችላል ተብሏል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/34458

No comments:

Post a Comment