የአዲስ
አበባ አንድነት ወጣቶች ኮሚቴ፣ በአዲስ አበባ ለመስከረም 11 ቀን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ እየተዘጋጀ እንደሆነ የደረሰን መረጃ
ይጠቁማል። እንቅስቃሴው በዋናነት ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ለታሰሩ የፖለቲካ መሪዎች፣ ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞች፣የሰባአዊ መብት ተሟጋቾች
…ሶሊዳሪቲዉን በማሳየትና ሻማ በማብራት እስረኞች በማሰብ ላይ ያተኮረ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ለአቡጊዳ ገልጸዋል።
የአንድነት
ፓርቲ ከዚህ በፊት የሚያደርጋቸው የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓቶች፣ በጽ/ቤት ብቻ እንደነበረ፣ የገለጽት አዘጋጆቹ፣ አሁን ግን ዝግጅቱ
ለማድረግ የታሰበው በሕዝባዊ አደባባዮች እንደሆነ ይናገራሉ። ጥሪዉም የሚቀርበው ለመላው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደሆነ የሚናገሩት
አዘጋጆች፣ በመኪና ቅስቀሳ እንደሚደረግም ለአቡጊዳ አሳዉቀዋል።
የአዲስ
አበባ አስተዳደር ሕዝባዊ እንቅስቃሴዉን በአራት ኪሎ ወይንም በስድስት ኪሎ ማድረግ ይቻል ዘንድ እውቅና እንዲሰጥ ቢጠየቅም፣ አስተዳደሩ
በሁለቱ አደባባዮች ማድረግ አይቻልም የሚል ምላሽ ሰጧል። አራት እና ስድስት ኪሎ ህዝብ እንዳይሰባሰብ የሚከለክል ምንም አይነት
ሕግ እንደሌለ ቢታወቅም፣ የአንድንነት ወጣቶች አላስፈላጊ ክርክር ዉስጥ ላለመግባት፣ ሌሎች አራት አማራጭ ቦታዎችንን እንዳቀረቡ
ለማወቅ ችለናል።
No comments:
Post a Comment