Friday, September 19, 2014

የወያኔን መንግስት ስርዓት ለመቃወም ዘር፣ ሀይማኖት ፣ ፆታ እና ጎሳ አይለየንም።


እኛ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተውጣጣን የተለያዩ ቋንቋዎች የምንናገር የተለያየ ሀይማኖት ያለን ለዘመናት የተነሱብን አምባገነን አገዛዞች ነጻነት አሳጥተውን ከሰው በታች አድርገው ያዋረዱን መሆናችን አንድ ያደረገን ለነጻነታችን፣ ለሰውነት ክብራችን የቆምን ኢትዮጵያውያን ነን።

እኛ
 ኦሮሞነታችን፣አማራነታችን፣ ሶማሌነታችን፤ ዳውሮነታችን፤ትግሬነታችን፣ ወዘተ ሳያግደን በኢትዮጵያዊነታችን አብረን ሌሎች በአገራቸው የተጎናጸፉትን ነጻነት እኛም በተራችን ልንጎናጸፍ የተነሳን ኩሩ ኢትዮጵያውያን ነን። 

እኛ ነጻነት የተራብን፣ኑሮ ያማረረን፣ ዘረኝነት ያንገፈገፈን፣ ዴሞክራሲ የተጠማን ኢትዮጵያውያን በግብጽና በቱኒዚያ የተደረገውን አይነት አብዮት በአገራችን ልናስነሳ፣ ልንመራውና በአገራችን ዴሞከራሲ ልናሰፍን ከነፍሳችን ተማምለን ተነስተናል። 

የተመኘነውን እውን እስክናደርግ ምንም ዓይነት ምድራዊ ሃይል አያቆመንም። እስካሁን በአገራችን በተነሱት አገዛዞች ማለትም በአጼው ፊውዳላዊ፣ በደርጉ ወታደራዊ፣ በወያኔ ዘረኛ፤ አፋኝና አረመኔ አገዛዝ የተማረርን ነጻነታችንን የምንወድ በሌሎች ነጻነት እየቀናን መኖር የማንሻ ኩሩ ኢትዮጵያውያን ነን። በአሁኑ ሰአት የአረመኔው እና የአፋኙን የወያኔን መንግስት ስርዓት በመቃወም ዘር፣ ሀይማኖት  ፆታ እና ጎሳ ሳይለያየን የአፋኙን የወያኔን ውድቀት ለማፋጠን ለነፃነታችን በወያኔ ላይ የተቃውሞ ድምጻችንን እናሰማለን:: 

ዳዊት ደመላሽ 


No comments:

Post a Comment