Sunday, December 1, 2013

የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ከሰራዊቱ ሊቀነሱ መሆኑ ታወቀ

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል፤ የሕወሃት ጄኔራሎች ፈርተዋል

ምንሊክሳልሳዊ-

በሰራዊቱ ውስጥ የተነሳውን ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ተከትሎ የቀድሞ የኢሕዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ እንደሚቀነሱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:: በየቀኑ ለስብሰባ የሚቀመጠው ሕወሓት መራሹ የጄኔራል መኮንኖች የአንድ ብሄር ቡድን ተጠንቷል ባለው እና የተወያየበት ሰነድ እንደሚያመለክተው በሰራዊቱ ውስጥ የሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች የሚፈጠሩት ከአማራው እና ከኦሮሞው ወገን ከሆኑት መኮንኖች ሲሆን ይህንንም የሚመሩት የውስጥ መዥገር የሆኑት የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ስለሆኑ ከሰራዊት ውስጥ በመቀነስ በተለያዩ መንገዶች በወንጀል ለማጥመድ እና ከነማን ጋር እንደሚገናኙ አስፈላጊውን የደህንነት ክትትል ማድረግ ይገባል ሲል ተነጋግሮበታል::
እነዚሁ የለውጥ ጥያቄ ያነሱት የሰራዊቱ መኮንኖች ከተለያዩ የታጠቁ የጠላት ሃይሎች እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በመገናኘት የመንግስትን ህልውና እየተፈታተኑት ከመሆኑም ባሻገር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከቀድሞ ስርኣት የተወረሱ እና ለዲሞክራሲው እና ለልማቱ እንቅፋት ስለሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ተብሏል::ከግንቦት ሰባት እና ከተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘት በሰራዊቱ ውስጥ ያለነበሩ እና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በመፍጠር ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ሰዎችን በማስኮብለል መረጃ በማቀበል እንዲሁም አለመተማመን እንዲኖር በመስራት ከፍተኛ ደንቃራ ሆነዋል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ እንደገለጹት የቀረበው ሰነድ ለጄኔራል መኮንኖቹ ያልተበተነ ሲሆን የስብሰባው መሪ የሆኑት ኢታማጆር ሹሙ እጅ በመሆን ሰነዱ እየተነበበ የተወያዩበት እና ይህም የሚያመለክተ በሕወሓት ጀኔራሎች መካከልም መተማመን አለመኖሩን ያሳያል ብለዋል::በሙስና ከአስተዳደርዊ ባለስልጣናት በበለጠ የተዘፈቁት የሕወሓት ጄኔራሎች በስብሰባ እና አብዛኛው ንብረቶቻቸን በተዘዋዋሪ በመሸጥ ስራ ላይ እየተንቀሳቀሱ ሲገኝ በሱዳን በኢምሬት እና በአውሮፓ አገሮች እንዲሁም በአሜሪካ በቤተሰቦቻቸው ስም የተለያዩ ንብረቶችን በመግዛት ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮሽ ጨምረው ገልጼዋል::

  Posted By.Dawit Demelash

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10271

No comments:

Post a Comment